Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የማያቧራው የመንግስት ግፍ በቤተ ክርስትያን ሊቁን ከሀገር አሰደዳቸው ።

@ortodoxtewahedo
ሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት
አመራሮች ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር በወቅታዊ
የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙሪያ ተወያዩ፤
****

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ማደራጃ መምሪያ ሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አመራሮች በቤተክርስቲያናችን መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር ውይይት አደረጉ።

በውይይቱ ወቅት የሰንበት ትምህርት ቤት አንድነቱ አመራሮች የቤተክርስቲያናችንን መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ጥቅል ጥናታዊ ሰነድ ከመፍትሔ አቅጣጫ ጭምር ያቀረቡ ሲሆን ያቀረቡት ሰነድ በዝርዝር ተዘጋጅቶ፣
በማስረጃና በመረጃ ዳብሮ ችግሮቹን ደረጃ በደረጃ መፍታት በሚያስችል አግባብ እንዲቀርብ ቋሚ ሲኖዶስ አቅጣጫ ሰጥቷል።

ሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት አመራሮቹም ለቋሚ ሲኖዶስ ያቀረቡት ሰነድ ሁኔታዎችን ለማመላከት እንጂ ያለቀለት ሰነድ እንዳልሆነ ገልጸው ዝርዝር ጥናቱን፣የጥፋቱን መጠን፣ባለቤቱንና የመፍትሔ አቅጣጫዎቹን የሚያመለክት ዝርዝር ሰነድ በማዘጋጀት እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል።

በውይይቱ ወቅትም ከቋሚ ሲኖዶስ አባላት ጥያቄና አስተያየት ተሰጥቶ ከሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት አመራሮቹ ምላሽ ተሰጥቶበታል።

ምንጭ: የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

@ortodoxtewahedo
#ሰንበተ ክርስትያን

እሑድ ማለት"አሐደ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙ የመጀመሪያ እንደማለት ነው። ይኽች ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ "ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን " በመባል ትታወቃለች።

ዮሐንስም በራዕዩ "የጌታ ቀን" ያላት ናት
(ራዕይ 1፥10)

ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ "ዕለተ እግዚአብሔር" የሚላት ዕለተ እሑድ ናት።

መልካም ዕለተ ሰንበት ይኹንልን

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
#ሰላም_ለኪ [ መልክአ ኪዳነ ምህረት ]

እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት ሆይ፤ እንደ ቃል ኪዳንሽ ምስጋናሽ የሚነገርበትን ቤተ ክርስቲያን በስምሽ ያሳነፀውን መታሰቢያሽን ያደረገውን በስምሽ የጸለየውን ከበረከትሽ ታሳትፊውና ይቅር ባይ ከሚሆን ልጅሽ ይቅርታን ታሰጭው ዘንድ ሰላም እያልኩ ከፊትሽ ወድቄ በቃል ኪዳንሽ እማፀንሻለሁ፡፡

#እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፤ በክፉ ሰዎች እጅ ከመውደቅ በቃል ኪዳንሽ ጠብቂኝ፡፡ በልዩ ጠላት በዲያብሎስ ወይም በሰይጣን ኃይል ተይዞ ከመቀጥቀጥ በእግረ አጋንንት ከመረገጥና ከመጠቅጠቅ አድኚኝ ለዘላለሙ አሜን🤲

@ortodoxtewahedo
Audio
እኔ ካንተ ጋር ነኝና አትፍራ
                         
Size 23.8MB
Length 1:08:15

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
Audio
👉 ፀሎት ድንቅ ትምህርት

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
አድምጡት ብዙ ታተርፊበታላቹ ።

"ትግሁ ወ ፀልዩ ከመ ኢትባሁ ውስተ መንሱት"
     "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ"
             
           ማትዮስ  26:41

       @ortodoxtewahedo
#ከምኵራብ_የወጡት

ክርስቶስ ከመቅደሱ ያስወጣቸው 4 ነገሮች ዛሬም አማናዊቷን መቅደስ እየገቡ ያውኳታል። እነርሱም

1⃣ኛ ፍቅረ ሲመት ነው። “ወገፍትዐ ማእዳቲሆሙ ወመናብርቲሆሙ ለእለ ይሠይጡ ርግበ ገንጰለ” እንዲል ሥልጣን መውደድን፥ ፍቅረ ሲመትን ከመቅደስ አርቋል።

2⃣ኛ ርግብ ሻጮችንና ርግብ መሸጥን ነው። ይህም እንደ ሲሞን መሰርይ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በገንዘብ መሸጥና መግዛትን ነው። ይህም ዛሬ በመቅደስ ሰልጥኖ ሁሉ ነገር መለኪያው ገንዘብ ሆኗል።

3⃣ኛ “ወሰደደ ኩሎ እምኵራብ አባግዐኒ ወአልሕምተኒ” እንዲል እንስሳዊ ጠባይን፥ ሥርዓት የለሽነትን ከመቅደስና ከሰው ልጆች ውስጥ ሊያርቅ ቢመጣም እስካሁን ድረስ በእንስሳዊ ጠባይ የምንመላለስ ብዙዎች ነን።

4⃣ኛ ፍቅረ ንዋይን አርቋል። “ወዘረወ ወርቆሙ ለመወልጣን” እንዲል የገንዘብ ለዋጮችን ወርቅና ገንዘብ ከእነ ሐሳባቸው ቢያስወጣም ዛሬም የአማናዊቷ መቅደስ ትልቁ ፈተናዋ ገንዘብን መውደድ ሆኖ ሲያውካት ይኖራል።

ይደንቃል ክርስቶስ ወደ መቅደሱ ሲገባ መዝገበ ጸሎት የያዘ ጸሎተኛ፥ መጽሐፍ የያዘ መምህር፥ የሚባርክ ካህን ሳይሆን ገንዘብ የያዘ፥ ርግብ የታቀፈ፥ በግ በሬ የሚጎትት አማኝ ነበር ያገኘው። ዛሬስ በእኛ መቅደስ በሆነው ማንነታችን ውስጥ የሚሰማው ድምፅ ምን ይሆን? ድንገት ወደ ኅሊናችን መቅደስ ጌታችን ሲመጣ ሳንነጻና ሳንፀዳ የገበያ ማዕከል ሆነን እንዳንገኝ ማስተዋሉን ያድለን።

#ተጻፈ_በመምህር_ዲያቆን_ሳዶር_ሲሳይ

@ortodoxtewahedo
ግድያው እንደቀጠለ ነው የቤተ ክርስትያንን መከራ ቀጥላል

#እስከ ማዕዜኑ እግዚኦ ትረስዓኒ ለግሙራ

ለቤተክርስቲያን ምቹ ጊዜ ነው 🤬🤬🤬

የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
ሁለት አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው ተገደሉ

ይሄ ግፍ የተፈጸመው በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በዶዶላ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው።ለጊዜው ማንንነታቸው ባልታወቁ በተባሉ አካላት ተገደሉ::

ግድያው የተፈፀመው ትናንት መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ገደማ ነበረ፥ ሟቾቹ አንድ መሪጌታና ዲያቆንን ጨምሮ አምስት የቤተሰብ አባሎቻቸው በጥይት ተደብድበው መገደላቸው ታውቋል።

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በዶዶላ ከተማ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም በርካታ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ይታወሳል ሲል የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ዘግቧል።

ምንጭ ፦ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት
ገብርኤል ሆይ፤ ከሰው ወገን ጠዋትና ማታ ከቶ እንደ እኔ ኀዘንና ትካዜ የሚበዛበት የለም፣
ከመላእክትም ወገን እንደ አንተ ያዘኑትን የሚያረጋጋ የለም፣
ገብርኤል ሆይ፤ ስለዚህ እኔም አውቄና አንተን አምኜ ያቀረብኩትን ይህን ጸሎት እንደ ትልቅ ዋጋ ቆጥረህ የሚያረጋጋ ቃልህን አሰማኝ።

መልክአ ገብርኤል

እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓል በሰላም አደረሰን።

@ortodoxtewahedo
# መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል

❖ ከ7ቱ ሊቀነ መላእክት አንዱ ነው።

❖ ገብርኤል ማለት የስሙ ትርጉም የእግዚአብሔር ልጅ የሚመስል የእግዚአብሔር ሰው ማለት ሲሆን
ት.ዳን 3+25ሕዝ 9፥2 በተጨማሪም መጋቤ ሐዲስ( የሐዲስ ኪዳን አስተማሪ) እግዚእ ወገብረ (እግዚአብሔር አደረገ ) ማለት ነው።

❖ ብስራታዊ (አብሳሪው) መልአክ ነው። እመቤታችንንና ዘመዷ ኤልሳቤትና አብስሮአልና።

❖ ቅዱስ ገብርኤል አርባብ የተበለው ነገደ መላእክት አለቃ ነው።

❖ በመጀመሪያው የመላእክት ጦርነት ጊዜ አምላካችንን እስክናውቅ ባለንበት ፀንተን እንቁም በማለት መላእክት ያፀናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው።
❖ ተራዳዩ መልአክ ነው።

ዳን ፫፥፲፱-፳፯፣ዳን ፰፥፲፭ ዳን፱፥፳፩-፳፯
❖ ቅዱስ ገብርኤል ከ፯ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ነው።

❖ በጎ በጎውን የምንሰማበት መልካም መልካሙን የምናደርግበት መልካም ቀን ይሁንልን።

ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን "አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው:: አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው::

(መልክዐ ገብርኤል)

"በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም ." †

(ዳን. ፱፥፳)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

ለመቀላቀል👉@weludebirhane

#አቤቱ የሆነብንን አስብ

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

@ortodoxtewahedo
ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን "አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው:: አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው::

(መልክዐ ገብርኤል)

"በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም ." †

(ዳን. ፱፥፳)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

#አቤቱ የሆነብንን አስብ

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው ከፍ ከፍ አድርጋቸው።

@ortodoxtewahedo
2024/09/29 15:33:52
Back to Top
HTML Embed Code: