Telegram Web Link
"መሞታቸው ብቻ ሳይሆን አሟሟታቸውም ዘግናኝ ነበረ አስከሬናቸው እንኳ ተለቃቅሞ እንዲቀበር ነው የሆነው።"
መጋቤ ካህናት ቆሞስ አባ ሃብተ ጊዮርጊስ አስራት

የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ አዲስ አበባ)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ በግፍ በተገደሉት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች ዙሪያ ከተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ጋር ቆይታ አድርገዋል።

የመምሪያው ዋና ኃላፊ የሆኑት መጋቤ ካህናት ቆሞስ አባ ሃብተ ጊዮርጊስ ዓሥራት እንደተናገሩት ከጥቃቱ በፊትም በተደጋጋሚ የማስፈራሪያ ዛቻና ገዳሙን ለቃችሁ ውጡ የሚባሉ መልእክቶች ይደርሱ እንደነበር ገልጸዋል።

ከዚህ ክስተት ቀደም ብሎ የገዳሙ መጠበቂያ መሣሪያና የመናንያኑ እህል በኃይል ተወስዷል ያሉ ሲሆን የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ ትኩረት ካልሰጠ ወደ ፊትም ከዚህ ያልተናነሰ ወንጀል በገዳሙ ሊፈጸም የማይችልበት ምክንያት አይኖርም ብለዋል።

ምንም እንኳ ለቤተክርስቲያን አባቶች መደብደብ መሰደድና መገደል የነበረ ቢሆንም የአሁኑ ግን መሞታቸው ብቻ ሳይሆን አሟሟታቸውም ዘግናኝ ነበረ አስከሬናቸው እንኳ ተለቃቅሞ እንዲቀበር ነው የሆነው ሲሉ ተናግረዋል።

ገዳማትን መጠበቅ የቤተክርስቲያኗ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የመንግሥትም ኃላፊነት ነው መንግሥት ከፌደራል እስከ ክልል ባሉት የጸጥታ መዋቅሮቹ ገዳማትን እንደማንኛውም ተቋም ሊጠብቅ ይገባል በማለት አክለዋል።

በመጨረሻም በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያሉ ምእመናን በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መናንያን በገዳሙ ሕጋዊ አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000011282222 (የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም) ድጋፍ እናድርግ በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።

@ortodoxtewahedo
ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ህልውና በላይ የሚያስቀድመው አንዳች ነገር የሌለ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ፈተና ለማለፍ የሚጠበቅበትን መንፈሳዊ ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ዛሬ የካቲት 19/2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ማኅበሩ በመግለጫው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን መንፈሳዊ አንድነት የጠየቀ ሲሆን "ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅማት ጉዳይ የግል ፍላጎትንና ምድራዊ ዓላማን መሠረት አድርገው ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ውጭ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ለመተካት፣ ፓትርያርክ ለመሾምና የመሳሰሉትን ለመፈጸም" የሚንቀሳቀሱ ያላቸውን "አንዳንድ አባቶች" ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በማሳሰብ ጉዳዩንም በመከታተል መረጃውን ለምእመናን አደርሳለሁ ብሏል።፡፡

ይመለከታቸዋል ላላቸው ሌሎች የቤተ ክርስቲያን አካለትም ጥሪውን አስተላልፏል።

1. የተከበራችሁ አበው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፡፡ እንዳለ በዚህ ታላቅ የፈተና ወቅት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማስጠበቅ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጣችሁን ኃላፊነት ለመወጣት ምእመናንን አቅጣጫ በመስጠት የቀደሙ አባቶቻችሁን ፈለግ በመከተል ዛሬም በጽናት እንድትተጉ፤ ያከበረቻችሁን ቤተ ክርስቲያን በአንድነት ሆናችሁ እንድትጠብቁ በልጅነት መንፈስ በትሕትና እንጠይቃለን፡፡ በተጨማሪም የአባትነት የዋህ ልቦናችሁን በመጠቀም ያዘኑ፣ የጠቀሙ፣የተቆረቆሩ መስለው ቀርበው የግል ፍላጎታቸውን ለመፈጸም የሚጥሩ ስለሚኖሩ ሁሉንም በጥንቃቄ እንድትመረምሩ፤ቀኖች ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን በመዋጀት አንድነታችሁን እንድታጠነክሩና በቤተክርስቲያን ዙሪያ ስለሚፈጠሩ ችግሮች በጥልቀት እንድትወያዩና እንድትመካከሩ እናሳሰስባለን።

2. ከዚህ ውጭ ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅማት ጉዳይ የግል ፍላጎትንና ምድራዊ ዓላማን መሠረት አድርጋችሁ ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ውጭ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ለመተካት፣ ፓትርያርክ ለመሾምና የመሳሰሉትን ለመፈጸም የምትንቀሳቀሱ አንዳንድ አባቶች ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ማኅበራችን ይህንን ጉዳይ እየተከታተለ መረጃውን ለምእመናን የሚያደርስ መሆኑንም በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን፡፡

3. ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ መምህራነ ወንጌል፣ ካህናት ሆይ በጸሎትና በትምህርት ምእመናንን በማጽናናት፤ ከእውነት ጋር በመቆም እውነታውን በማሳየት ምእመናን ለቤተ ክርስቲያን ዘብ እንዲቆሙ በማድረግ ድርሻችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን።

4. ውድ ምእመናንና የማኅበራችን አባላት የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያንን ከአሳዳጆቿ የመጠበቁ ዋነኛ ኃላፊነት በዘመኑ ባለን ብፁዓን አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርሰቲያን፣ ካህናትና ምእመናን ሁላችን እጅ ላይ ወድቆአል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ለአባቶችና ለካህናት ትተን “እኔ አያገባኝም፤ አይመለከተኝም” ልንል አይገባም፡፡ ሁሉም በየድርሻው ቤተክርስቲያኑን ለመጠበቅ መትጋት አለበት፡፡ በቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን ጥፋትና ሊመጣ ያለውን ፈተና አስቀድሞ በመረዳት ቅዱስ ሲኖዶስ ቀደም ሲል በወሰነው መሠረት በየአጥቢያችን፤ በተለያየ መልኩ በመደራጀት፤ በቤተክርስቲያን ላይ ጥፋት ለማድረስ የሚመጡትን በመከላከል የቤተ ክርስቲያንን ስደት ለማስቆም መንፈሳዊ ግዴታችንን እንድንወጣ እንጠይቃለን፡፡

5. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በልዩ ልዩ አገልግሎት እየተሳተፋችሁ ያላችሁ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ማኅበራትና ሌሎችም ሁላችንም አንድነታችንን በመጠበቅ በጋራ አገልግሎቶችን በመፈጸም ድርሻችንን እንድንወጣ ለተግባራዊነቱ ጥሪ እናቀርባላን፡፡

6. ገዳም ድረስ ገብቶ መሣሪያ ያልያዙና: ራሳቸውን እንደሞቱ ቆጥረው እየኖሩ ያሉ መነኮሳት ላይ ግድያ የፈጸመ ማንኛውም የታጠቀ ኃይል (መደበኛም ይሁን ኢመደበኛ: በግልም ይሁን በቡድን: አማኝም ይሁን ኢአማኝ) ድርጊቱ ከሰውነት ተፈጥሮ የወጣ ነው፡፡ ምናኔንና የክህነት ክብርን በተቃረነ መልኩ ሰብእና የጎደለው ጥቃት ማድረስ ኢትዮጵያዊ ባህልም አይደለም፡፡ ጥቅም የሌለው ከንቱ ተግባር ነው፡፡ በዚህ የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ ይኖራል ብለን አናምንም፡፡ ጤነኛ በሆነ አእምሮ ታስቦ የተፈጸመ ነው ማለትም አይቻልም፡፡ ማስተዋል ተወስዶባቸው እውቀት ተሰውሮባቸው እንጂ ይህንን ማድረግ ቀርቶ ማሰቡም የሙት ሐሳብ ነው፡፡ ቀድሞ የሞተው ሟቹ ሳይሆን ገዳዩ ነው፡፡ በዚህ መንገድ የቤተ ክርስቲያን አማኞች ሲበዙ እንጂ ሲያንሱ በታሪክ አልታየም:: ይህ ድርጊት ክርስቲያኖችን ሲያጠነክር እንጂ ሲያዳክም ታይቶ አይታወቅም፡፡ መጽሐፍ “ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንን ቤት ገፋው በዓለት ላይ ስለተመሠረተ አልወደቀም ” ባለው መሠረት ቤተክርስቲያን በጽኑ ዐለት ላይ የተመሠረተች ስለሆነ አታሽነፏትም። ዲዮቅልጥያኖስም አላጠፋትም:: ዲያብሎስም ዝናሩን እንዲሁ ጨረሰ:: ስለዚህ አትድከሙ: አትሳቱም እናንተ ሳትወለዱ የነበረች ቤተ ክርስቲያን እናንተ አልፋችሁም እንደ እናንተ ላሉት በስሑት መንገድ ለሚጓዙት ሁሉ እየጸለች ትቀጥላለች:: ሐሳቧም፣ ሥራዋም፣ ዓላማዋም፣ ግቧም ሰማያዊ ነውና።

በመጨረሻም ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ህልውና በላይ የሚያስቀድመው አንዳች ነገር የሌለ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ፈተና ለማለፍ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት ጋር በመናበብ የሚጠበቅበትን መንፈሳዊ ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን በዚሁ አጋጣማ እያሳወቅን፥ የሁላችንም የመሰባሰብና የአገልግሎት ማእከል ቤተ ክርስቲያን በመሆኗ ከሁሉም ነገር በፊት ቅድሚያ ሰጥተን ሊመጣ ካለው አደጋ ቤተ ክርስቲያናችንን የመጠበቅ ኀላፊነት በትጋት እንወጣ ሲል ማኅበረ ቅዱሳን በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል፡፡

@ortodoxtewahedo
የማህበረ ቅዱሳ መግለጫ
በአጭሩ ሀሰተኞች አዲስ ፓትርያልክ
አዲስ የሲኖዶስ ጸሐፊ ለመሾም ጫፍ ደርሰዋል
ለመንፈሳዊ ተጋድሎ እንዘጋጅ 🙏

@ortodoxtewahedo
አምላክ ሰው እንዲሆንና ፍጡርና ፈጣሪ እንዲገናኙባት ምክንያት የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። "የአምላክ እናት" የሚለው ስም እግዚአብሔር በዓለም ውስጥ ያደረገውን የማዳን ሥራ ታሪክ ሁለ የያዘ ነው።

ክርስቶስ ከባርነት አውጥቶ ነፃነትን ይሰጠን ዘንድ ከእርሷ ተለወለደ። የነፃነታችን ደብዳቤ የተፃፈባት ማኀፀን እንደምን ያለ ነው! የፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ ባንቺ የታደሰ እመቤቴ ማርያም ሆይ እናመሰግንሻለን ከፍ ከፍም እናደርሻለን።

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በክርስትናው ሕይወት እየተጓዝን በቃልኪዳንሽ የምንጠቀም ልጆችሽ አድርጊን።

"ይኽቺን ቤተክርስቲያን አብ ቀድሞ ሠራት፤ ይኽቺን ቤት ወልድ አነጻት፤ መንፈስ ቅዱስም ፈጸማት! ወደርሷ (ቤተ ክርስቲያን) ገስግሱ የእግዚአብሔር ኃይል በርሷ ላይ አለና፡፡"

ቅዱስ ያሬድ

@ortodoxtewahedo
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 11ኛ ዓመት በዓለ ሲመታቸው የካቲት 24/2016 ዓ.ም ይከበራል።

@ortodoxtewahedo
Lalibela, Ethiopia 🇪🇹
ምድራዊ ገነት

📸Dimitar Karanikolov

@ortodoxtewahedo
“እስከ ትበጽህ ለሞት ተበዓስ በእንተ ጽድቅ እስመ እግዚአብሔር አምላክከ ይትበአስ
በእንቲአከ”

“እስክትሞት ለእውነት ታገል። እግዚአብሔር ላንተ ይታገልለሀልና”

           ሲራክ 4 ፡ 2
2024/09/30 13:24:24
Back to Top
HTML Embed Code: