Telegram Web Link
የእሁድ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ
ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን
👉 የእሁድ (ሰንበተ ክርስትያን)ውዳሴ ማርያም አንድምታ
ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ድምጸ
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 5
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"በቁም ላለመቀበር መንቂያው ጊዜ አሁን ነው"
#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
Audio
ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘሰኑይ
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 6
Audio
ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘሠሉስ
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 7
Audio
ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘረቡዕ
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 8
#ወንጌል

ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ.ም በቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ ምንባባት እና ቅድመ ወንጌል የሚባል ምስባክ
Audio
ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘሐሙስ
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 9
#ወንጌል

ነሐሴ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ ምንባባት እና ቅድመ ወንጌል የሚባል ምስባክ
Audio
ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘአርብ
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 10
#ወንጌል

ነሐሴ 10 ቀን 2016 ዓ.ም በቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ ምንባባት እና ቅድመ ወንጌል የሚባል ምስባክ
Audio
ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘቀዳሚት ሰንበት
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 11
አንዳንድ ሰዎች ልበ ቢሶች ሆነው "እግዚአብሄር ዘወትር ሳቅንና ጨዋታን ይስጠኝ እንጂ ሁልጊዜ ማዘንንስ ከእኔ ያርቅልኝ" ይላሉ። ከዚህ በላይ ምን አላዋቂነት አለ?  ዘውትራዊ ሳቅንና ጨዋታን የሚሰጥ ዲያቢሎስ እንጂ እግዚአብሔር አይደለምና። ቢያንስ እስኪ ሳቅንና ጨዋታን ያበዙት ዕጣ ፈንታቸው ምን እንደሆነ አድምጡ። "ሕዝቡም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ ሊዘፍኑም ተነሱ" ይላልና (1ኛ ቆሮ 10:7 ፣ ዘጸ 32:6)። የሰዶም ሰዎችና የኖኅ ዘመን ሰዎች እንደዚህ ነበሩ። የሰዶም ሰዎችን አስመልክቶ ግብራቸውን ሲናገር "ትዕቢት እንጀራን መጥገብ መዝለልና ስራ መፍታት" ይላልና (ሕዝ 16:49)። በኖኀ ዘመን የነበሩ ሰዎችም ለብዙ ዓመታት መርከቢቱ ስትዘጋጅ እንኳ  እያዩ ሊመጣ ያለውን መዓት ምንም ሳያስቡ ሲበሉ፣ ሲጠጡና ሲዘፍኑ ነበር(ማቴ 24:38)

ስለዚህ ይህ ከዲያቢሎስ የምትቀበሉትን ነገር እግዚአብሄር ይሰጣችሁ ዘንድ አትለምኑት። እግዚአብሔር የሚሰጠው የተሰበረና ትሑት ልብን፣ በመጠን መኖርንና ራስን መግዛትን፣ ፈሪሐ እግዚአብሔርን፣ ንሰሐን ኹሉና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የኾነ ኃዘንን ነውና።

ኢየሱስ ክርስቶስ ለአልዓዛርና ለከተማይቱ ዕንባውን አፍስሶአልና፣ በይሁዳ ምክንያትም ውስጡ ታውኮአልና።  አንድ ሰው ጌታችን ብዙ ቦታ ላይ እንደዚህ ሲያደርግ በርግጥ ያገኘዋል። አንድም ቦታ ላይ ግን ሳቀ፣ በጥቂቱም ወይም በትንሹም ቢኾን ፈገግ አለ የሚል አያገኝም። ንዑድ ክቡር የሚሆን  ጳውሎስም ሶስት አመት ሙሉ ሌሊትና ቀን በዕንባ እነደነበረ እርሱ ራሱ ተናግሯል ሌሎችም ይህንን መስክረውለታል (ሐዋ 20:31)። እንደ ሳቀ ግን እርሱ ራሱም የትም ቦታ አልተናገረም ሌሎችም ቅዱሳንም ስለእርሱም ኾነ እርሱን ስለሚመስሉ ሌሎች ቅዱሳን እንደሳቁ ምንም አልነገሩንም። ሣራ ብቻ እንደ ሳቀች በዚህም አንደተወቀሰች(ዘፍ 18: 12-15) ፣ ነፃ የነበረው የኖኅ ልጅም በመሳቁ ምክንያት የወንድሞቹ ባርያ እንደ ኾነ ግን ይነግሩናል (ዘፍ 9:25)።

እንደዚህ ብዬ ስናገር ግን የልብ አለል ዘሊልነትን ከእናንተ ማራቅ ስለምሻ እንጂ ሳቅን ኹሉ ስነቅፍ አይደለም። ጠቢቡ "ለመሳቅ ጊዜ አለው" እንዲል (መክ 3:4)።  ነገር ግን እስኪ ንገሩኝ ብዙ ወቀሳ ሊጠብቀን እንደሚችል፣ በሚያስፈራው የፍርድ ዙፋን ፊት እንደምንቆም፣ በዚኽ ዓለም ለሰራነውም ኹሉ አንድ በአንድ መልስ እንደምንሰጥ እያወቅን ተድላ ደስታን እንዴት እናደርጋለን?? ስለዚህ ዘወትር መሳቅ ፣ ስረአት የለሽና ቅምጥል መሆን ከዲያቢሎስ ጎን ለተሰለፉ ሰዎች ነው እንጂ ለእኛ ለክርስቲያኖች አይደለም።

አሁን የነገርኃችሁን ነገር ሰምታችሁ ካዘናችሁ አመሰግናችኋለው፣ " በእኔ ምክንያት ከሚያዝን በቀር ደስ የሚያሰኘኝ ማን ነው?" ይላልና (2ኛ ቆሮ 2:2) እንዲህ ማዘናችሁንና መፀፀታችሁንም መቼም ቢኾን መች አታቋርጡ። ይህ ሀዘን በበጎ ለመለወጥ መነሻ ይኾናልና። ንግግሬንም ያበረታሁትም በውስጣችሁ ያለው መርዝ ከምንጩ እንዲወጣ አድረጌ እናንተን ከዚያ ለማውጣትና ፅኑ መድኃኒት ጨምሬ ነፍሳችሁን ጤናማ ለማድረግ ነውና። እነደዚህ ብዬ የተናገርኩት ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ  ክብርና ጌትነት የባህርይ ገንዘቡ በሚኾን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ኹላችንም እግዚአብሔር የሚሰጠንን ርስቱና ክብሩን እንድንወረስ ነውና አሜን!

ቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ
የማቴዎስ ወንጌልን እንዳስተማረው
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል

“የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?”
[ሉቃስ 1:43]

5 ነጥቦች😊😊

1. “የጌታዬ እናት” ብላለችና ኢየሱስ ጌታ ነው.. ይህም ጌትነት በሌሎች ክፍሎች ላይ እንደተነገረው “የጌቶች ጌታ፣ አንድ(ብቸኛ) ጌታ” እንደመሆኑ ስለሆነ አምላክነቱን ያሳያል..

2. እመቤታችን የጌታ እናት መባሏ የአምላክ እናት መባሏ ነው.. ያው ከላይ እንዳልነው ለኢየሱስ ጌታ ሲባል አምላክነቱን ስለሚያሳይ.. ስለዚህም እመቤታችን የአምላካችን እናት ናት ቃልን በሥጋ ጸንሳዋለችና

3. የአምላክ እናት እንደመሆኗ እመቤታችን ያላት ታላቅ ክብር:— ቅድስት ኤልሳቤጥ ምንም እንኳ “በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ” እንደነበረች ይኸው ወንጌል ቢናገርም.. እግዚአብሔርም ታላቅ ተአምርን ቢያደርግላትም.. እመቤታችን ወደሷ ስትመጣ ግን “የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?” አለች.. የእመቤታችን ክብር ከእርሷ በጣም በእጅጉ ይበልጣልና..

4. ይህ ጌታ የኤልሳቤጥ ጌታ ብቻ ሳይሆን የፍጥረት ሁሉ ጌታ ነውና ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን “የጌታችን እናት” ይላል.. ስለዚህም በክብር እመቤታችን ከኤልሳቤጥ ብቻ ሳይሆን ከፍጥረት ሁሉ ትበልጣለች..

5. በቅድስት ኤልሳቤጥ ላይ የወረደው መንፈስ በትህትናዋ ተገልጧል.. መንፈስ ቅዱስ የትሕትና መንፈስ ነው.. “ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ አይገባኝም” አስባላት..

ስለዚህ እኛም ይህ ትህትና በሕይወታችን ውስጥ ይታይብን ዘንድ ይገባል.. ጌታችንም “ከእኔ ተማሩ እኔ የዋሕ በልቤም ትሑት ነኝና” ብሏል.. ትሑት ሰው የእግዚአብሔርን ድንቆች በሕይወቱ ውስጥ ያያል.. በነገር ሁሉ የእግዚአብሔርንም እርዳታ አያጣም..

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers
2024/09/27 07:26:15
Back to Top
HTML Embed Code: