Telegram Web Link
"እኛ መና አለን ይህ መና እስራኤላውያን በምድረ በዳ የተመገቡት መና አይደለም። እኛ መንፈሳዊ መጠጥ አለን፤ ይህ መጠጥ እስራኤላውያን ከዐለት ውስጥ ፈልቆ የጠጡት መጠጥ አይደለም።አሁን እኛ የአንድነትን (ገዳማዊ) አኗኗር እየኖርን ነው።አሁንም ያለነው በገዳም ውስጥ ነው። በምድረ በዳ ያለቅድስና መኖር ማለት በአካል ከሰው ከመነጠል በቀር ምንም ትርጉም የለውም። ያ በረሃ እንዲህ አስፈሪ የሆነበት ምክንያት ምንድነው? ጊንጡ ወይስ ሐሩሩ ነው? ወይስ ነቢዩ ሙሴ፦ "እባብና ጊንጥ ጥማትም ባለባት ውኃም በሌለባት በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራህን"(ዘዳ.8፡15) እንዲል እንዲሁም ነቢዩ ኤርሚያስ "ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር" (ኤር.2፡6) ያላትን ነውን? ይህ ገዳም ነውን የሚያስፈራው? አይደለም። ከእርሱ ይልቅ የጽድቅ ፍሬን ከመስጠት የመከነ የሰው ገዳም አያስፈራምን? በዚህ ምሳሌ ምን ያህል ጊንጦችና መርዛም እባቦች በዚህ ገዳም (ዓለም) ውስጥ አሉ? ምን ያህል እባቦችና የእፉኝት ልጆች በዚህ ገዳማችን (ዓለም) ውስጥ ይኖራሉ? (ማቴ.3፡7) እኛ በእነዚህ መካከል የምንኖር አይደለንምን? እንዲህ ቢሆንም ግን እንፈራቸው ዘንድ አይገባንም ምክንያቱም እኛን ከእነዚህ እባቦች የሚያድነን ሙሴ ሳይሆን ከእርሱ የበረታው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ነው"


St. John Chrysostom, Homilies on Ephesians.Homily XXlll.P.165
በእንተ_ሥጋዌ_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
147.8 KB
በእንተ ሥጋዌ

ለተማሪዎቹ የሚያስብ ርኀሩህ አስተማሪ አንዳንዶቹ ተማሪዎቹ ረቀቅና መጠቅ ያለው ትምህርት እንዳልገባቸው ሲያይ ወደ እነርሱ ደረጃ ዝቅ ብሎ እነርሱ በሚገባቸው በማንኛውም ሁኔታ እንደሚያስተምራቸው ሁሉ የእግዚአብሔር ቃልም እንዲሁ አደረገ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም እንዲህ እንዳለ፡- በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኗልና፡፡»"

#ቅዱስ_አትናቴዎስ_ሐዋርያዊ_ህይወቱና_ትምህርቱ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
#እግዚአብሔርን_ጠብቅ

እግዚአብሔርን የሚጠብቅ ሰው እርሱን በተስፋ፤ በእምነት፤ በተሞላ ሙሉ ልብና ያለምንም ድካም ይጠብቀዋል። ይህ በመሆኑም እንደዚህ ዓይነቱ ሰው እግዚአብሔር በመካከል ገብቶ እንደሚሰራና ሁሉም ነገር ለበጎ እንደሚሆን ያምናል። "እግዚአብሔር ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።" [ሮሜ 8፥28] "እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ አይታክቱም ይሄዳሉ አይደክሙም።" [ኢሳ 40፥31] ኃይላቸው በመከራ የተናወጠባቸው ሁሉ እግዚአብሔርን በተስፋ በመጠባበቅ ኃይላቸውን ያድሳሉ ማለት ነው። "ጎልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል" የሚል ቃል ተጽፏል [መዝ 102፥5] ስለሆነም ማንም ቢሆን እግዚአብሔር እምነት በተሞላ ብርቱ ልብና በእርሱ ላይ በመተማመን ይጠብቀዋል።

ነገር ግን አንድ ሰው እግዚአብሔር እርምጃ እንደሚወስድና እርምጃውም ግልጽና ኃያል እንደሆነ መተማመን አለበት። ከዚሁ ጋር እርምጃው በተመቻቸ ሰዓት ፍሬያማ በሆነ መንገድ የሚከናወን ነው። እግዚአብሔር አንድ የሆነ እርምጃ ለመውሰድ ከወደደ ምንም የሚጠባበቀው ሰዓት አይኖርም። ኢየሱስ ክርስቶስ " ... አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም አላለምን ? [ሐዋ 1፥7] አንተ ችግርህን እግዚአብሔር እንደሚያቃልልህ በማመን መቼ ለችግርህ መፍትሔ እንደሚሰጥህ ሳታስብ በእርሱ እጅ ላይ ብቻ ጣለው።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል

“ይህንም ብሎ፡ በታላቅ ድምፅ፦ አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና፡ ብሎ ጮኸ።”
[ዮሐንስ 11:43]

ከሞተ አራት ቀን ወደ ሆነው “ይሸታል” ወደተባለው ሙት ጌታችን መጥቶ አስነሳው.. መግነዙን ፍቱት አለ.. እና አባ ሲያስተምሩ ምን አሉን በኃጢአት ብትተሳሰሩ እንኳ ጌታን ተስፋ አድርጉት እርሱ ከታሠራችሁበት ማሰሪያ ፈትቶ ነጻ ያደርጋችኋል.. እርሱን ብቻ ተስፋ አድርጉ.. የሞተውን አበቃለት የተባለውን እንኳ አስነስቷልና..

እርሱ የትኛውንም ልብ ሳይጸየፍ በልዩ ፍቅሩ በዛ ሊኖር ይመጣልና እናንተ ደግሞ ጌታን የሚቀበል ልብ ይኑራችሁ.. ጌታችሁ የልባችሁን በር ዘወትር ያንኳኳልና ክፈቱለት እርሱ ይግባ..

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers
ሱባዔ

ሱባዔ ምንድን ነው ?
ሱባኤ በሰዋሰው ትርጉሙ "ሰባት"ማለት ሲሆን በመንፈስ አተረጋጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከ ዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪየ ጋር እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው ፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ ፦ ፈጣሪ አለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፋጥረትን ከመፋጠር ማረፋ ፥ለጸሎት የሚተጉ ምዕመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥር ፋጹምነት ያመለክታል ፡፡ (ዘፍ 2፥2 , መዝ 118፥164) አንድ ሰው 7 ቀናት ቢጾም "አንድ ሱባኤ ጾመ" ይባላል ፡፡

ሱባኤ መቼ ተጀመረ?
የተጀመረው ከውድቀት በሓላ በመጀመርያው ሰው በአዳም ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት እንዳስተማሩት የቤተ ክርስቲያናችን መዛግብት ያስረዳሉ በምላሹም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ስጋን ለብሼ ከ 5 ቀን ተኩል በኋላ አድንሃለሁ የሚለውን ቃል ኪዳን የሰማው ሱባኤ በመግባቱ ነው፡፡

ሱባዔ ለምን ይጠቅማል?
የሰው ልጅ ሓጢአት በሚስማማው የሥጋ ሰውነቱ ዘወትር ፈጣሪውን ይበድላል፡፡ በፈፀመው በደል ህሊናው ይወቅሰዋል ይጸጸታል፡፡ በመጀመርያ ደፋሮ በሰራው ሀጥያት በኋላ ይደነግጣል ይህ በማንኛውም ሰብአዊ ፋጥረት ኀሊና ውስጥ የሚፈራረቅ ክስተት ነው ፡፡ በዚህ ግዜ የፈጣሪውን ይቅርታ ለማግኝት ያስባል ይተክዛል፡፡ ሰው በደፋርነቱ የኃያሉን አምላክ ትእዛዝ ተላልፎ አለም ሲያስጨንቀው  ሸክሙን የሚያቃልልበትና የሚያስወግድበት  መንፈሳዊ ጥበብ ከቸሩ ፈጣሪ ተሰጥቶታል፡፡ ይህውም በጥቂት ድካም ሥጋ ያልተወሰነ ጸጋ እግዚአብሔር የሚያገኝበት ሥርዓት ሱባዔ ነው፡፡

1- እግዚአብሔርን ለመማጸን፦
ማንኛውም ሰው ሱባኤ ሲገባ በቁርጥ ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማፅኖ ሊኖረው ይገባል፡፡ ምንም የምንጠይቀው ( የምንማፀነው) ነገር ሳይኖር ሱባዔ ብንገባ የምናገኝው መልስ አይኖርም፡፡ ስለዚህ ሱባኤ ከመግባታችን በፊት፦ ሱባዔ የምንገባው ለምንድን ነው ?  በማለት እራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል ፡፡

2- የቅዱሳንን በረከት ለመሳተፍ
ቅዱሳን አባቶችና እናቶች የተጋደሉትን ተጋድሎ በማዘከር ቃል ኪዳን በተሰጣቸው ገዳማትና አድባራት የሚገባ ሱባኤ የቅዱሳን በረከት ተካፋይ ያደርጋል፡፡ በጾመ ነብያት የነብያትን፣ በጾመ ሀዋርያት የሀዋርያትን፣ በጾመ ፋልሰታ የእመቤታችንን በረከት ለመሳተፋ ሱባኤ መግባት የነበረ ነው፡፡

የሱባዔ አይነቶች፦
1- የግል ሱባኤ ( ዝግ ሱባዔ)፦
አንድ ሰው ብቻውን አመች ቦታ ማንም ሳያየው በግሉ የጸሎት በአቱን ዘግቶ በሰቂለ ኀሊና ሆኖ ፈጣሪው ብቻ እንዲያየው በኀቡዕ የሚፈፅመው ሱባኤ ነው ፡፡

2- የማህበር ሱባዔ፦
ካህናት ምዕመናን ወንዶች ሴቶች ሽማግሌወች ፤ወጣቶች ፤በአንድ ሆነው በቤተ ክርስትያንና አመች በሆኑ ቦታወች ሁሉ ተሰብስበው የሚገብት ሱባዔ ነው፡፡

3- የአዋጅ ሱባዔ፦
በሀገር  ላይ ድንገተኛ አደጋ ፤ አባር ቸነፈር ጦርነት ሲነሳ እንዲሁም በማህበረ ምዕመናን ላይ አስጊ የሆነ መቅሰፋት ሲከሰት እግዚአብሔር መዓቱን በምህረት ቁጣውን በትዕግስት እንዲመልስ የሚያዝ የሱባዔ አይነት ነው፡፡

ለሱባዔ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅት፦
ሱባኤ ከመግባታችንም ሆነ ከገባን ግዜ እንዲሁም ከጨረስን በኋላ ምእመናን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይገባናል፡፡

➢ ሱባኤ ከመግባት አስቀድሞ
በመጀመርያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል ፡፡
፪ ሱባኤ ለመግባት የወሰንበትን ምክንያት ከለየን በኋላ ምክንያታችንን ይዘን የንስሃ አባታችንን ማማከር ያስፈልጋል፡፡
፫ ለምን ያህል ቀናት መቆየት እንዳለብን መወሰን ያስፈልጋል ፡፡ሱባኤ ከዚህ እስከዚህ እቆያለሁ ብለን ዕቅድ የምንይዝበት ነው፡፡
፬ ወቅትና ቦታ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችን በአብዛሀኛው ግዜ ሱባዔ የሚገባው በአጽዋማት ወቅት በመሆኑ ይህንን መለየት ነው፡፡ ምክንያቱም በጾም ወቅት ብዙ አባቶች ጸሎት የሚይዙበት ስለሆነ ፀሎታችን ከእነርሱ ጋር አብሮ ያርግልናልና ነው፡፡ እዚህ ላይ በማንኛውም ግዜ ሱባኤ አይያዝም ለማለት አይደለም በማንኛውም ግዜ ፈተና ያጋጠመው ሰው ሱባዔ ሊይዝ ይችላል፡፡

➢ በሱባዔ ግዜ 
ሀ. በጸሎት ሰአት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ምስራቅ መልሶ መቆም ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰቂለ ህሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል፡፡
ለ . በቅደም ተከተል መፀለይ ይገባል በመጀመርያ አአተብ ከሚለው ተጀምሮ አቡነ ዘበሰማያትን ጠቅሶ ጸሎተ ሀይማኖትን መጨረስ ፡፡ሰግዱ እና ስለ መስቀል በሚያነሳው ላይ እየሰገዱና እያማተቡ መጸለይ ፡፡ በማስቀጠል አቡነ ዘበሰማያት ፤መዝሙረ ዳዊት ውዳሴ ማርያም ሌሎችንም ማስከተል ከዚያ 41 ግዜ ኪራላይሶ ይባላል ፡፡
ሐ.  በሱባዔ ግዜ ከተሐራሚው የሚጠበቀው ነገር ሐጢአቱን እያሰበ ማዘን ማልቀስ ለእያንዳንዱ በደል ማልቀስ ማዘን ይገባዋል ፡፡
መ.  በመጨረሻም ሱባዔ የገባው ሰው ሱበዔውን ሳይጨርስ ወይም አቋርጦ ከማንኛውም ሰው ጋር ፈፅሞ መገናኝት የለበትም ፡፡

3- ከሱባዔ በኋላ
ላቀረብነው ተማፅኖ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን ነገር  መጠበቅ ይኖርብናል። ሱባዔ የገባ ሰው ሁሉ ራዕይ ላያይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልስ አሰጣጥ ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡ ከሱባዔ በኋላ መጀመሪያ የምናገኝው የህሊና ሰላም ነው፡፡ ይህ ትልቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱባኤ ገብተን ያሰብነውን  ካላገኝን ዳግመኛ ተዘጋጅተን እስከ መጨረሻው ሰዓት በመማፀን መጽናት ይኖርብናል፡፡፡

መጭው ጾመ ፋልሰታ (የመቤታችን ጾም ) በመባል የሚታወቀው እና ቤተ ክርስቲያናችን አበይት አጽዋማት ብላ ከደነገገቻቸው ወስጥ አንዱ ነው ፡፡ በዚህ ወራት ብዙዎቹ አባቶቻችንና እናቶቻችን በረከተ ስጋ ወነፍስ ያገኙበት የበረከት ጾም ነው እኛም ቢቻለን በሱባኤ ባይቻለን አቅማችን የፈቀደውን እየጾምን በጸሎት አምላካችንን መጠየቅ እንዲሁም እመቤታችን በምልጃዋ  ታስበን ዘንድ መማፅን ያስፈልገናል ፡፡


(ቃለ ተዋሥኦ ቁጥር 2 )
🕊

† እንኳን ለቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም  በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !  †

†  🕊 ቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም  🕊

† ቸር እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ ጾም ነው:: የሰው ልጅ ከፈጣሪው ክብር እንዲደረግለት ክፋትን መስራት የለበትም:: መልካም መሆንም ይጠበቅበታል:: ለዚህ ምንጮቹ ደግሞ ጾም: ጸሎትና ስግደት ናቸው:: ያለ እነዚህ ምግባራት መቼም ወደ ጽድቅ መድረስ አይቻልም::

ይቅርና እኛ ክፉዎቹ የሰማይና የምድር ፈጣሪ: የክብር ሁሉ ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደ ጊዜ የመጀመሪያ ሥራው ያደረገው ጾምን ነው:: ስለዚህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፯ [ 7 ] አጽዋማትን በጉባዔ ሠርታ: በአዋጅ እንዲጾሙ ታደርጋለች:: ከእነዚህም አንዱ ጾመ ፍልሠታ ነው::

"ፈለሠ" - ሔደ: ተጉዋዘ እንደ ማለት ሲሆን "ፍልሠታ" ማለት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የዕርገት ጉዞ የሚያዘክር ቃል ነው:: እመ ብርሃን በዚህ ዓለም ለ ፷፬ [64] ዓመታት ኑራ ካረፈች በሁዋላ ሥጋዋ እንደ እኛ አልፈረሰም::

ለጊዜው በዕጸ ሕይወት ሥር ቆይታ እንደ ልጇ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: እርሷ በሁሉ ነገሯ ቀዳሚና መሪ ናትና:: ጾመ ፍልሠታን የጀመሩት አበው ሐዋርያት ሲሆኑ እንድትጾምም ሥርዓት የሠሩ ራሳቸው ናቸው:: ከ፯ [7] ቱ አጽዋማትም እጅግ ተወዳጅና እየተናፈቀች የምትፈጸም ናት::

ካህናትና ምዕመናንም ጾሟን እንደየአቅማቸው ክብር በሚያሰጥ መንገድ ይፈጽሟታል::
- የቻሉ ወደ ገዳማት ሔደው ጥሬ እየቆረጠሙ: ውሃ እየተጐነጩ ክብርን ያገኛሉ::
- ሌሎቹ ደግሞ ባሉበት ደብር አካባቢ እያደሩ ሌሊት ሰዓታቱን: በነግህ ኪዳኑንና ውዳሴ ማርያም ትርጉዋሜውን: በሰርክ ደግሞ ቅዳሴውን ይሳተፋሉ::
- የኔ ብጤ ደካማ ደግሞ ጠዋት ማታ ወደ ደጇ እየተመላለሰ "አደራሽን ድንግል" ይላታል::

† በእርሷ አምነን አፍረን አናውቅምና ነጋ መሸ ሳንል እንማጸናታለን::

🕊

† ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ልበለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::
- ጾሙን የፍሬ: የትሩፋትና የበረከት ያድርግልን::


🕊                        💖                     🕊
Audio
ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘረቡዕ
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 1
Audio
ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘሐሙስ
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 2
Audio
ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘአርብ
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 3
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የሌሎች መልእክታት ክፍል

“የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።”
[1ኛ ጴጥሮስ 4: 3]

የክርስትና አንዱ አዋጅ ይህ ነው.. በክርስቶስ የሆነ አዲስ ሕይወት ይኑራችሁ.. ክርስቶስ ስለ ኃጢአት ለእናንተ የሞተው ኃጢአታችሁ ይቅር እንዲባል ብቻ ሳይሆን ይልቁን እናንተም ደግሞ ለኃጢአት ሞታችሁ ለጽድቅ እንድትኖሩ ነው ነው.. ይህም ከአሕዛብ ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወጥተን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድናደርግ ነው..

ራስን መግዛት ላይ በጣም መስራት አለብን.. በአንዴ ላናድግ እንችላለን ግን የጠራን ጌታ የታመነ ነውና በትንሹ እንታመንለት.. በድርጊት ከሚሰሩ ኃጢአቶች እየተቆጠብን ስንመጣ እርሱ ደግሞ ጥቃቅን የሚባሉትንም እያስተወን ይመጣል.. ቀስ በቀስ እርሱን እስክንመስል ያሳድገናል.. ለዚህም ነውና እርሱ እኛን መስሎ በሥጋ የተገለጠው..

በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንም.. ዛሬ የወደቅን የሰነፍን ተስፋ እንደሌላቸው የምንረሳ አይደለንም.. መደገፊያችንን ልኡል እግዚአብሔርን ተደግፈን እንነሳለን.. ጌታችን እስከ ሞት ድረስ ወዶን ፍቅሩ እዛ ላይ ያበቃም አይደለም ደግሞ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦም በነገር ሁሉ እያገዘን ይቅርም እያለን ያሳድገናል..

ጌታችን አሳዳጊያችን ነው.. በጸጋው ሁላችንን ያሳድገን..

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers
2024/09/27 09:24:13
Back to Top
HTML Embed Code: