Telegram Web Link
አዲሱን ዓመት ለመጀመር ቀናት ቀርተዋል ! ምን አቅደዋል?

በአዲሱ ዓመት እነዚህን ለማድረግና በእግዚአብሔር ሐሳብ እና ፈቃድ ለመመላለስ ብናቅድስ?
እንደምን አመሻችሁ ወዳጆች? አመታችንን የቃኘንበት ቪዲዮ ትናንት ማታ upload ከተደረገ በኋላ በቪድዮው ላይ በተስተዋሉ ችግሮች ምክንያት መልሰን አንስተነው ነበር። ዛሬ እነዚያን ችግሮች ለመቅረፍ ሞክረናል። በጣም ብዙ ወዳጆቻችንም ቪዲዮው private ይላል ብላችሁ ስትነግሩን ነበር። ለተፈጠረው ቴክኒካዊ ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን። ጥቂት ቦታዎች ላይ የተወሰኑ ግድፈቶች ላይጠፉ ይችላሉ። በቀጣይ አመት የምንሰራቸው ጥንቅሮች እንዲህ ካሉ ቴክኒካዊ ችግሮች የፀዱ እንዲሆኑ የቻልነውን እንደምናደርግ ቃል በመግባት ይህንን መሰናዶ ትከታተሉት ዘንድ እንጋብዛለን። ቸር ቆይታ።

https://youtu.be/FCAzJQVD_5k?si=wCuyhywS_w3S2bYy
ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመት ሲመጣ መደሰት፣ ብዙ መብልና መጠጥ ማዘጋጀት፣ አዲስ ልብስም መልበስ ጥቅም የለውም፡፡ ነፍሳችን በኀጢአት እየተጨነቀች፣ ነፍሳችን ተርባና ተጠምታ ሳለ፣ የተዳደፈ የኀጢአት ልብስም ተጆቡና ሳለ አዲስ ዓመት ማክበር ለእኛ ምን ጥቅም ይሰጠናል? እንዲህ ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመትን ማክበር ማለት ለእኔ እንደ ልጆች የዕቃ ዕቃ ጨዋታ ነው፡፡

ክርስቶስ ከዚሁ ሥራ አውጥቶናል፡፡ ከሕፃንነት አዕምሮ ወደ ማወቅ አሸጋግሮናል፡፡ ከምድራውያን ለይቶ ከሰማያውያን ጋር ደባልቆናል፡፡ ስለዚህ “መልካሙን ሥራችሁን ዐይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ” እንደ ተባለ አፍአዊ ሳይኾን መንፈሳዊውን ብርሃን ልናበራ ይገባናል (ማቴ.5፡16)፤ በአዲሱ ዓመት፡፡ ይህም ብርሃን ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን የሚያስገኝ ነው፡፡

ወዳጄ ሆይ! ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ? ነፍስህ በኀጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ? አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከኾነ ከሰው እጅ ሳይኾን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ ኹል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትኹን ብዬ እመክርኻለሁ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትኾኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ኹሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ያለንም ስለዚሁ ነውና በአዲሱ ዓመት በድርጊቶቻችን ኹሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንዘጋጅ (1ኛ ቆሮ.10፡31)፤ አዲስ ዓመት ማክበር ማለት ይኼ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ - #ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ላልተለወጠ ሰው አዲስ ዓመት ምንም ትርጉም የለውም !"
ወደ ላይ አያዳልጣችሁ!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን አንድ ጨዋነት የራቀው ሰው ሰደባቸው አሉ። በኋላ ግን ጸጽቶት እግራቸው ላይ ወድቆ “ይማሩኝ፣ አጥፍቻለሁ፣ አድጦኝ ነው” ሲላቸው፣ እርሳቸውም “ታዲያ ወደ ታች ያድጣል እንጂ ወደ ላይ ያድጣል እንዴ?” አሉት ይባላል።

ወደ ላይ የሚያድጣቸውን ብዙ ሰዎች እያየን ነው። ሰሞኑን ዘነበ ወላ የተባለ ግለሰብ፣ ሊነቅፈው ቀርቶ ሊረዳውና ሊያደንቀው እንኳ እጅግ የሚበዛበትን የምናኔ ሕይወት ለመንቀፍ ሲሞክር ሰምተናል (የተነገረው በሕንድኛ ወይም በታይ ቋንቋ አይደለም!)። ይህን የመሰሉ እናውቃለን ከሚሉ አላዋቂዎች ወይም ጭፍን ጥላቻ ካሳወራቸው ሰዎች በኦርቶዶክሳዊነት ላይ በተለያየ መንገድ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እየበዙ መምጣታቸው ጉዳዩን እንደ ቀላል ለማለፍ የማይቻል ያደርገዋል። ዛሬ ካለው የተከማቸ ኦርቶዶክስ-ጠልነት ያደረሱን ከ20ኛው መ/ዓ መጀመሪያ ጀምሮ ኦርቶዶክስ ጠል በነበሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ይሰነዘሩ የነበሩ የጥላቻ ንግግሮችና ጽሑፎች መሆናቸውን ልብ ይሏል።

ምናኔያዊ ሕይወት፣ ከትንሣኤ በኋላ የምናገኘውን እንደ መላእክት የመሆንን ሕይወት፣ በዚህ ዐለም ገንዘብ የማድረግ ሕይወት ነው። “በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም” እንዳለ ጌታችን። ማቴ. 22፡30 መላእክት በተፈጥሯቸው እንደማያገቡና እንደማይጋቡ ሁሉ፣ ከትንሣኤ በኋላ ደግሞ ለሰዎችም ማግባትና መጋባት እንደማይኖር ሁሉ፣ መላእክት ዛሬ የሚኖሩትን፣ የሰው ልጆች ደግሞ ከሞት በኋላ የሚያገኙትን ሕይወት መናንያን ገዳማውያን በአሁኑ ሕይወት ይኖሩታል። እንደዚሁም ምናኔያዊ ሕይወት አዳም ከመበደሉ በፊት የነበረው ሕይወት ምን ይመስል እንደ ነበረ በመስታወት የሚያሳይ ነው፣ ጌታችን የሰጠውን ሕይወት በምልዓት የሚያሳይ ነው።

ምናኔያዊ ሕይወት በክርስትና ውስጥ ያለውን እጅግ የገዘፈና ዘርፈ-ብዙ የሆነ ነገረ-ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ፋይዳ ለጊዜው ብናቆየው እንኳ፣ ክርስቲያናዊ ገዳማት ለሰው ልጆች ያበረከቷቸው ኢኮኖሚያዊ፣ እውቀታዊና ታሪካዊ ጠቀሜታዎች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው። ጥቂቶቹን እንኳ ብናስታውስ፤ ዩኒቨርሲቲዎችና አዳሪ ት/ቤቶች በዋናነት የተቀዱት ከገዳማት ነው። የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ሲመረቁ የሚለብሱት ጋዋንና የሚደፉት ቆብ የገዳማትን ቀሚስና ሞጣህት እንዲሁም ቆብ የሚመስለው በአጋጣሚ አይደለም።

በአውሮፓ የውኃ ኃይልን ለወፍጮና ለቆዳ ሥራ መጠቀምንና ማዕድናትን ማውጣትንና መጠቀምን በስፋት ያስተዋወቁት ገዳማውያን ናቸው። የአውሮፓን የእርሻ መሬት፣ ሥነ ጥበብና እውቀት ከጥፋት በመጠበቅና በማበልጸግ ረገድ ገዳማት የተጫወቱት ሚና ምትክ አልባ ነው። አንዳንድ ገዳማት በየዓመቱ የአበምኔቶች መደበኛ ስብሰባ ስለነበራቸው፣ የደረሱባቸውን አዳዲስ የቴክኖሎጂ እውቀቶችና ልምዶች ይለዋወጡ ስለነበር በዚህ መንገድ ሥልጣኔ በመላው አውሮፓ እንዲስፋፋ የራሳቸውን ታላቅ ሚና ተጫውተዋል።

ከክርስትና በፊት የጉልበት ሥራ መልካም ክብርና ስም አልነበረውም። በግሪኮች ትምህርት መሠረት የጉልበት ሥራ የዝቅተኞቹ ኅብረተሰብ ክፍል (የድሀውና የባሪያዎች) ሥራ ተደርጎ ይወሰድ ነበር። በሮማውያን ዘንድም ለሥራ የነበረው መንፈስ ተመሳሳይ ነበር። ለጉልበት ሥራ በተለይም ለግብርና ከፍ ያለ ቦታና ከበሬታ የሰጡት ገዳማት ናቸው።

ከዚህም ጋር ገዳማት ለድሆች፣ ለስደተኞች፣ ለወላጅ አልባ ልጆች፣ ለሕሙማንና ለችግረኞች መጠጊያዎች በመሆን አገለግልዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በ4ኛው መ/ዓ የነበረው ቅዱስ ባስልዮስ የመሠረታቸው ገዳማት ሐኪም ቤቶች፣ የድሆች መመገቢያዎችና የችግረኞች መርጃ ማዕከሎችም ነበሩ። የዘመናዊ ሆስፒታል ጽንሰ-ሐሳብ መሠረቱ ክርስቲያናዊ ገዳማት ናቸው።

እንደዚሁም ገዳማት የሥነ ጽሑፍና የትምህርት ማዕከላት ነበሩ። ታላላቅ ቤተ መጻሕፍት የነበራቸው ብዙ ገዳማት ነበሩ። ብዙ መጻሕፍት ከእኛ እንዲደርሱ ያደረጉት መጻሕፍትን የሚሰበስቡና ባለሙያዎችን መድበው በእጅ የሚያስገለብጡ ገዳማት ናቸው። ብዙዎቹ መጻሕፍትና የታሪክ መዛግብት ከጥፋት ተርፈው ከዛሬ የደረሱት በገዳማት ተደብቀውና ተጠብቀው ስለኖሩ ነው።

ግሪኮች በኦቶማን ቱርክ በተገዙባቸው ወደ 300 የሚደርሱ ዘመናት ውስጥ እምነታቸውን ብቻ ሳይሆን ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውንና ሥነ ጽሑፋቸውን ሕያው አድርገው የጠበቁት በገዳማት ዋና ማዕከልነት ነበር። ገዳማቱ ለካህናት ብቻ ሳይሆን በቱርኮች ግዛት ሥር ለነበሩ መላው ግሪካውያን ስውር ት/ቤቶች ነበሩ። በአገራችንና በሌሎች አገራትም ብዙ ተመሳሳይ ታሪኮች አሉ። ነጻነትን ለሚወዱና ባርነትን ለሚጸየፉ ሰዎች ሁሉ እነዚህ ትርጉማቸው ጥልቅ ነው። የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ገዳማትን ትቁር ጥምድ የሚያደርጓቸውም ለዚህ ነው።

መናንያን አባቶችና እናቶች ለሰው ልጅ ሁሉ ምሕረትን ከእግዚአብሔር የሚለምኑ ናቸው። በአስቄጥስ ገዳም ስለ ነበረ አባ ኢሳይያስ ስለ ተባለ አባት በመጽሐፈ ገነት እንዲህ ተብሎ እናገኛለን፡- “በዋዕየ ፀሐይ ላይ ራቁቱን ቁሞ ስለ መላው ዐለም ሲጸልይ ሳለ ከመነኰሳት አንዱ እንዲህ የሚል ድምጽ ሰማ፡- ‘ከእርሱ ጸሎት የተነሣ ለዐለሙ ሁሉ ምሕረት አድርጌያለሁና ሂድና ለአባ ኢሳይያስ ሰውነቱን የሚሸፍንበት ልብስ ስጠው።’”

ገዳማውያን መናንያን ሌላውን የሚዘርፉና የሚያጠፉ ሳይሆኑ ለሰው ልጆች ሁሉ ምሕረትን የሚለምኑ ናቸው፣ ሰውን የሚያሳድዱ ሳይሆኑ የተሰደዱትን የሚቀበሉ ናቸው። እንኳንስ የሰው ልጅ እንስሳትና አራዊት እንኳ አዳኞች ሲያሳድዷቸው ሸሽተው የሚጠጉባቸው ናቸው። የፍርሃትና የአጎብዳጅነት መንፈስ ያይደለ የእውነትና የጥብዓት መንፈስ ያለው ሁሉ ይህን ይረዳል።

ምንም እንኳ ምናኔያዊ ሕይወት ዓላማው በዚህ ዐለም ሀብት መበልጸግ ባይሆንም፣ በኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ ረገድም ቢሆን ገዳማት በየዘመናቱ የነበራቸው ሚና ቀላል አልነበረም። ለአብነት ያህል በዘመናችን የግብፅን የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች በከፍተኛ ድርሻ የሚሸፍኑት ኦርቶዶክሳውያን ገዳማት ናቸው። የአስቄጥስ ገዳም ለግብፅ የአየርና የዐፈር ጠባይ ተስማሚ የእህልና የአትክልት ዝርያዎችን በማምረት የአገሪቱን የምግብ አቅርቦት ችግር በመፍታት ረገድ የተጫወተው ሚና ታላቅ ነው።

በተለይም ደግሞ የአስቄጥስ ገዳም መነኰሳት በሳይንሳዊ ምርምር በግብፅ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ ያመረቱት “ፎደር ቢት” (fodder beet) የተሰኘ የስኳር ድንች ዓይነት አዲስ ምርት በእጅጉ ተመስግነውበታል። የአሰቄጥስ ገዳም መነኰሳት በዚህ ረገድ ላበረከቱት አስተዋጽዖ ሙስሊሙ መሪ አንዋር ሳዳት ከታላቅ ምስጋና ጋር ብዙ ሽልማት አበርክቶላቸዋል። ሌሎቹ የግብፅ ገዳማትም ለበረሃው ተስማሚ የሆኑ የዕፅዋትና አዝዕርት ዓይነቶችን በሳይንሳዊ ምርምር በመፈለግ ረገድ ከፍተኛ ሥራ እየሠሩ ናቸው።

ወደ ግብጽ አባ ቢሾይ ገዳም ተጉዞ የነበረ አህመድ ኤል-ጋማል የተባለ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ ጋዜጠኛ November 21, 1988 ላይ በወጣ “Khaleeg” በተባለ ጋዜጣ ላይ “A visit to the Depth of the Desert” በሚል ርዕስ እንዲህ ጽፎ ነበር፡-
....“በአባ ቢሾይ ገዳም ከአባቶች መነኰሳት ጋር ተገናኘሁ። በዚያም የቦታውን መንፈሳዊነትም ሆነ የእንግዳ ተቀባይነታቸውን ነገር፣ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ የሆነውን ተግባራቸውንና ትምህርታቸውን ተመለከትሁ፤ ሆኖም ግን ካየሁት ሁሉ አንዱንም እንኳ እንደሚገባ አድርጌ አሟልቼ ልገልጸው አልችልም። ሆኖም የክርስትና ገዳማዊ ሕይወት በታሪካችን ውስጥ የነበረውን ሚና መዘንጋት ለእያንዳንዱ ዐረብ ታላቅ ኪሳራ የመሆኑ ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ማስተዋል ተገቢ መሆኑን ለራሴ ተረድቻለሁ። በእ*ስልምና ሃይማኖት ውስጥ ምንኲስናና ገዳማዊ ሕይወት የሚባል ነገር አለመኖሩን ማሰብ ውስጥን የሚረብሽና የሚያሳዝን ነገር ነው።”

መናንያን በሥራ የሻከሩ እጆች ያሏቸው ብቻ ሳይሆኑ ከርኩሰትና ከነውር ንጹሕ የሆነች ነፍስ ትኖራቸው ዘንድ የሚጋደሉ እውነተኛ ጀግናዎችና ትክክለኛ ፈላስፋዎች ናቸው። ከመብላትና መጠጣት፣ ከማግባትና ከመጋባት ባሻገር ወዳለው ሰማያዊ ሕይወት የሚያመለክቱ አቅጣጫ ጠቋሚዎችና ዐዋጅ ነጋሪዎች ናቸው።

ስለሆነም ሰው ያልደረሰበትን ነገር በመሰላል ወጥቼ ልንቀፍ ማለት ተገቢ አይደለም! ሊታገሡት የሚገባም አይደለም! በዕድሜያቸውም ሆነ በእውቀታቸው ታዳጊ የነበሩት የ1950ዎቹና 60ዎቹ ትውልዶች በኦርቶዶክስ-ጠል መምህራን የተሞሉት ጥላቻ ዛሬ ያፈራውን መራራ ፍሬ እያየን፣ የእነዚያ የመንፈስ ልጆች የሆኑ በዕድሜ እንኳ ባይሆን በአእምሮ ሕፃናት የሆኑ ኦርቶዶክስ-ጠሎች ተገቢ ያልሆኑ ነገሮችን ሲናገሩና ሲጽፉ እያዩ ኦርቶዶክሳውያን ዝም ማለት አይችሉም።

ኦርቶዶክሳውያን፣ ገና ለገና ያሻንን ብንላቸው ለክፉ አይሰጡንም የሚሉ የፈሪዎችና የአጎብዳጆች የብዕር መፈተኛና የአፍ ማሟሻ መሆንን መቀበል ከማይችሉበት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ስለዚህ ወደ ላይ አያዳልጣችሁ! የሚታየውን ብቻ ሳይሆን የማይታየውን መፍራትም ብልህነት ነው!
ቅዱስ አትናቴዎስ -795.pdf
19.9 MB
ቅዱስ አትናቴዎስ ሕይወቱ እና ትምህርቱ በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
ፍኖተ ቅዱሳን (1).pdf
152.9 MB
ፍኖተ ቅዱሳን

በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
"ዳዊት በቀንም በማዕልትም ሕጉን የሚያነብ ብጹዕ ነው ብሏልና ፡፡ በጎዳናም ቢሆን ፤ በቤትም ቢሆን ፤ ስትተኛም ቢሆን ፤ ከእርሱ ይቅርታንና ቸርነትን ታገኝ ዘንድ ፤ ፈጣርህ እግዚአብሔርን በፍፅም ህሊናህ ፤ በፍፅም አእምሮህ ፤ በፍጹም ልቦናህ ፤ ውደደው" !! ።

       መፅሐፈ ዲዲስቅልያ
+ ስለቅዱሳንና ቅድስና ጥቂት +

በዘመነ ሐዲስ ቅዱሳን ሲባል፡- ሐዋርያት፣ ነቢያት፣ ሰማዕታት፣ ሊቃውንት፣ መናንያን /ገዳማውያን/፣ ደጋግ ሰብአ ዓለም ይጠቀሳሉ፡፡ ቅዱሳን ዜግነትና ተቋማዊ አጥር ባይኖርባቸውም በልማድ እንደየሚከበሩበት ቦታ ስፋትና ጥበት አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ እየተባሉ ይለያሉ፡፡ የቅድስና አሰጣጡ አስቀድሞ በጉባኤ ደረጃ አልነበረም፡፡ ሰማዕታት የሆኑ እንደሆነ ምስክርነቱ የአደባባይ ነውና በቶሎ ቅድስና ያገኛሉ፡፡ አንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅና ቅዱስ ባስልዮስ ያሉ በአፍም በመጻፍም የገነኑ አበው ግብርና ቅድስናቸው ከመጉላቱ የተነሣ ከቤተ ክህነቱ ቀድሞ ምዕመኑ በቅድስና ጠርቷቸዋል፡፡ ቅድስናው በገቢረ ተአምርና በራእይ የሚገለጥም አለ፡፡

በዚህ ዘመን ግን ከሞላ ጎደል በሁሉም ሐዋርያዊ ትውፊትን በሚከተሉ አብያተ ክርስቲያናት ቅድስና በቃለ ሲኖዶስ ይሰጣል፡፡ የእኛም አካሄድ ተመሳሳይ ነው፡፡ አንድ አባት ቅዱስ ከተባለ በኋላ ስለሚደረገው ልዩ ልዩ ተግባር በ #ወልታ_ጽድቅ ወይም በዲያቆን ሰሎሞን #የኢትዮጵያ_ቤተ_ክርስቲያን_ወርቃማ_ዘመናት ወይም ደግሞ በዶ/ር ሐዲስ የሻነው የትምህርተ ሃይማኖት መጻሕፍት ማንበብ ይቻላል፡፡ ቅድስና በየጊዜው የሚጨመር ነው፤ አይቆምም፡፡ በሌላ በኩል በበጎ የሚነሣው አባት ላይ ከጊዜ በኋላ የሃይማኖት ህፀፅ የተገኘ እንደሆነ የሚታረምበት ዕድል ስለመኖሩ የአርጌንስ ታሪክና የእኛ ሲኖዶስ የግብፆችን የስንክሳር ስርዋጽ ያረመበት ድርጊት ይጠቁመናል፡፡

በ1960ዎቹ ተጀምሮ ሲካሄድ ቆይቶ እንደ መቀዛቀዝ ባለው የኦሪየንታል-ምሥራቃውያን ኢመደበኛ ንግግር የቅድስና አሰጣጥን፣ ማንና እንዴት ቅዱስ ይባል ማለትን ለነገረ መለኮትና ለታሪክ ምሁራን በመተው በግራ ቀኝ ወገኖች የተላለፈው ግዝት እንዲነሣ ሐሳብ ቀርቦ ነበረ፡፡ ሐሳቡ እስካሁን ዳር አልደረሰም ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያናችን በ1988 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ በተቋቋመ የጳጳሳትና የሊቃውንት ኮሚቴ የተዘጋቸው የእምነት፣ ሥርዓትና የውጭ ግንኙነት መጽሐፍ በኬልቄዶናውያን ላይ የተላለፈው ግዝት እንደማይነሣ፣ በእነርሱ ስር ያሉ አበውንም በቅድስና መቀበል እንደማይችል በአጽንዖት ገልጧል፡፡ ቀድመው በስንክሳራችን በገቡት የሃይማኖት ጀርባቸው ከወደ ኬልቄዶን በሚመዘዝ አበው ላይ ግን ያሳረፈው ውሳኔ የለም፡፡
---

( ደብተራ በአማን ነጸረ )

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
“ንስሐ ሰውን ከፍ የደርጋል”

“ለቅሶ የሰማይ በር ያንኳኳል”

“ቅዱስ ትህትና ይከፍታል”

ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋሰው (St. John Climacus)

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
2024/09/27 07:28:36
Back to Top
HTML Embed Code: