Forwarded from አርማ "Airdops" (አሸብርㅤㅤㅤㅤ ㅤ ㅤ ㅤㅤㅤㅤ)
. ARMAGEDON

#መተባበር

እንዴት የአክሱም ሃውልትንና የላሊበላ ቤተ ክርስቲያናትን በነበረን
ቴክኖሎጂ መስራት ቻልን? ምናልባት ሌሎች ስልጡን ሕዝቦች
ሰርተውልን ወይም በሌላና ሰው ባልሆኑ አካላት እርዳታ ተሰርተው
ይሆን? የሚሉ ጥያቄዎች ሲጠየቁ እንሰማለን፤ ምክንያት ሆነው
ሲቀርቡም ይታያል። ትክክለኛው ምክንያት ግን የሕዝብ ሕብረት የትልቅ
ፈጠራና ተግባር ውጤት ምክንያት መሆኑን ነው። አባቶቻችን ይህን ትልቅ
ውጤት ያስገኘ ሕብረት መፍጠር ችለው የነበሩ መሆኑንም ያሳያል።
ይህን ሕብረት እንዴት እንመልሰው ይሆን?

@wedefkr
@wedefkr
ዉድ የቻናል አባላቶቼ እንዴት ናችዉ።ለተወሰነ ግዜ ያህል የአገልግሎት መስጠት አቁመን ነበር ነገር ግን አሁን ለገና በዓል ታላቅ ዝግጅት አደርገናል ለዚህም ያላችሁን ግጥሞች፣ መነባንቦች አዲስ መዝሙሮችን በ @Ttwh4 በላክ ከዋዜማዉ ጀምሮ ዝግጅቱን አጠናቀን ወደ እናንተ እንደርሳላን እንዳያመልጦ።



አሁን ጀምሮ መላክ ይቻላል ከስማችዉ ጋር።




ይጠብቁን !!!!!!
Wifi ያላችዉ ሰዎች እዩት
Forwarded from Dagi Yo
"ርዕይክዋ ለቤተ ክርስቲያን አፍቀርክዋ ለቤተክርስቲያን" ብሎ ቅዱስ ያሬድ ይናገራል! "ቤተ ክርስቲያንን አየዃት ፣ ቤተ ክርስቲያንን ወደድኳት" ማለት ነው። ይህም ማለት ቤተ ክርስቲያንን ለማፍቀርና ለመውደድ ቤተ ክርስቲያንን ማየት ያስፈልጋል። ሥርዓቷን ማየት፣ ዜማዋን መስማት፣ መፃሕፍቶቿን መመርመር ያስፈልጋል። በትኩረት ካየናት በፍቅር መከተላችን የግድ ነው።
ከምናይበት መንገዶች ደግሞ ታሪኳን ማወቅ ነው። የሙሉ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም የተለያዩ አድባራትን ታሪክ እና ቃልኪዳን ማወቅ ድኅነት ያስገኛል።
በዚህም መሰረት አንድ ወንድማችን በትጋት የኢትዮጵያን አድባራት ታሪኮች ከምስል ጋር እያስደገፈ እያቀረበልን ይገኛል።
ቻናሉም 👇👇👇👇👇👇👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
⛪️ @orthodoxchurchhistory ⛪️
⛪️ @orthodoxchurchhistory ⛪️
⛪️ @orthodoxchurchhistory ⛪️
⛪️ @orthodoxchurchhistory ⛪️
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
አሁኑኑ ሊንኩን በመጫን ቤተ ክርስቲያናችንን እንመልከታት!!!!
Channel photo removed
Channel name was changed to «የኢትኤል ብዕሮች»
#ስንክሳር_ዘሰኔ_2


⭐️አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሁለት በዚህች ቀን የመጥምቁ #ዮሐንስ ሥጋ የቀናተኛው ኤልያስ ደቀ መዝሙር ከሆነው ከነቢዩ #ኤልሳዕ ሥጋ ጋር በአንድነት ተገኘ፡፡

ከሀዲው ንጉሥ ዑልያኖስ የጥጦስ ልጅ አስባስያኖስ ከአፈረሰው በኋላ በዘመኑ በኢየሩሳሌም የአይሁድ ምኵራባቸውን ሊሠራ በወደደ ጊዜ እርሱ በቅዱስ ወንጌል ደንጊያ በደንጊያ ላይ ተቀምጦ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም የተባለውን የእግዚአብሔርን ቃል ሊሽር ፈልጎ መሥራት በጀመረ ጊዜ ሦስት ጊዜ ፈረሰበት፡፡

አይሁድም እንዲህ አሉት የደጋግ ክርስቲያኖች ዐፅሞቻቸው በዚህ ቦታ ስለሚኖሩ ከዚህ ካላወጣሃቸውና ካላቃጠልኻቸው በዚህ ቦታ ምኵራብ አይሠራም፡፡

በዚያንም ጊዜ የቅዱሳንን ዐፅሞቻቸውን አውጥተው በእሳት እንዲአቃጥሉት አዘዘ በአፈለሱም ጊዜ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስንና የነቢዩ ኤልሳዕን ሥጋቸውን አግኝተው በእሳት ሊአቃጥሉ ፈለጉ ምእመናንም መጥተው ለወታደሮች ብዙ ገንዘብ ሰጡ ንጉሡም ሰምቶ እንዳያጠፋቸው በዚያች ሀገር እንዳያስቀሩ ከአማሏቸው በኋላ የቅዱሳንን ሥጋ ወሰዱ፡፡

የዑልያኖስም ዜናው እንዲህ ሆነ የጳጳሳት አለቆች ባስልዮስንና ጎርጎርዮስን በአሠራቸው ጊዜ እነርሱ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ዘንድ እያለቀሱ ጸለዩ፡፡ የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችንን የከበረ ስሙን ሰድቧልና ያን ጊዜ እግዚአብሔር ቅዱስ መርቆሬዎስን በአካለ ነፍስ ላከው ዑልያኖስንም በጦር ወጋው ከደሙም ዘግኖ ኢየሱስ የሰጠኸኝን ነፍስ ተቀበል እያለ ወደ አየር ረጨ ወዲያውኑም በክፉ አሟሟት ሞተ፡፡

የከበሩ የዮሐንስንና የኤልሳዕን ሥጋ ግን እሊያ ሰዎች በእስክንድርያ ከተማ ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ አባ አትናቴዎስ አደረሱ፡፡ እርሱም በእርሳቸው ታላቅ ደስታ ደስ አለው ቤተ ክርስቲያንም እስኪሠራላቸው ድረስ በርሱ ዘንድ አኖራቸው፡፡

በአንዲት ዕለትም አባ አትናቴዎስ በአባቶቹ ቦታዎች ላይ ስለ ጸሐፊው ቴዎፍሎስም አብሮት ሳለ እግዚአብሔር መልካም ዘመን ቢሰጠኝ ሥጋቸውን በውስጧ አኖር ዘንድ ለቅዱሳን መጥምቁ ዮሐንስና ለነቢዩ ኤልሳዕ በስማቸው በዚህ ቦታ ቤተ ክርስቲያን እሠራለሁ አለ ቴዎፍሎስም ሰማው፡፡

አባ ቴዎፍሎስም በተሾመ ጊዜ አባ አትናቴዎስ የተናገረውን ያንን ቃል አስቦ ቤተ ክርስቲያን ሠራ፡፡ ከርሱ ጋራም ብዙዎች ካህናትንና የክርስቲያን ወገኖችን ይዞ የቅዱሳን የመጥምቁ ዮሐንስና የነቢዩ ኤልሳዕ ሥጋቸው ወዳለበት ሔደ በታላቅ ክብርም ተሸክመው አምጥተው ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገቡ፡፡

ሥጋቸውንም ይዘው በሚጓዙበት ጊዜ በጎዳናቸው አቅራቢያ ቤት ካለበት ቦታ ደረሱ በውስጡም በምጥ ተይዛ አራት ቀናት እየጮኸች ለሞት የተቃረበች ሴት ነበረች፡፡ እርሷም አረማዊት ነበረች በቅዱሳኑም ሥጋ ዘንድ ካህናቱ የሚያመሰግኑትን ሰምታ በቤቷ መስኮት ተመለከተች ይህ ምንድን ነው ብላ ጠየቀች፡፡ የቅዱሳን የመጥምቁ ዮሐንስና የነቢዩ ኤልሳዕ ሥጋቸው ነው አሏት እርሷም ከዚህ ሥቃይ ከዳንኩ ክርስቲያን እሆናለሁ አለች ገና ቃሏ ከአፉዋ ሳይፈጸም ያን ጊዜ መልካም ሕፃን ወለደች ስሙንም ዮሐንስ ብላ ጠራችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከቤተሰቦቿ ሁሉ ጋራ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀች፡፡

የቅዱሳኑንም ሥጋቸውን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩት ከእርሳቸውም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ፡፡

በቅዳሴ ቤተ ክርስቲያኑም ጊዜ ከሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ ጋራ ብዙዎች ሰዎች ቅዱሳን መጥምቁ ዮሐንስንና ነቢዩ ኤልሳዕን ሲዞሩ አዩአቸው በቀድሞ መልካቸው ያውቋቸዋልና የመጥምቁ ዮሐንስ መልክ ሁለመናው ፀጉር ሲሆን ጽሕሙ በደረቱ ላይ የወረደ ነበር ኤልሳዕም ቁመቱ ረጅም ራሱ በራ ነበር፡፡

ከዚህም በኋላ ኤጲስ ቆጶሱ #አባ መቃርስ በሰማዕትነት በሞተ ጊዜ ሥጋውን ከቅዱሳን ዮሐንስና ኤልሳዕ ሥጋ ጋራ አደረጉ፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን ለዘላለሙ አሜን፡፡

⭐️በዚህችም ዕለት የቄርሎስ የአክሌጥስና የኢትዮጵያ መነኮስ #የቀውስጦስ መታሰቢያቸው ነው፡፡ እግዚአብሔር በጸሎታቸው ይማረን ለዘላለሙ አሜን፡፡

ሰማዕቱ ዮስጢኖስ (100-165 ዓ.እ.) እንዲህ አለ፦

“በምክረ ከይሲ የመጣው አለመታዘዝ በዚያ መንገድ ይወገድ ዘንድ [የእግዚአብሔር ልጅ] ከድንግል ማርያም ሰው ኾነ፤ ድንግል እና ንጽሕት የነበረችው ቀዳማዊት ሔዋን የእባቡን ቃል ሰምታ አለመታዘዝንና ሞትን ወልዳለችና፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም ግን እምነትንና ደስታን ፀነሰች፡፡ ከእርስዋ የሚወለደው አንዱ ቅዱስ [በተዋሕዶ ከብሮ] የእግዚአብሔር ልጅ ይኾን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ወደ እርስዋ እንደሚመጣ፣ ኃይለ ልዑልም እንደሚጸልላት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ብስራቱን በነገራት ጊዜ፡- 'ይኵነኒ በከመ ትቤለኒ' ብላ መለሰች (ሉቃ.1፡38)፡፡ ስለዚህም እንደ ተናገርነው ቅዱሳት መጻሕፍት አስቀድመው የተናገሩለት [ወልድ በሥጋ] ከእርስዋ ተወለደ፡፡ በእርሱም እግዚአብሔር እባቡን ቀጠቀጠው፤ ከእርሱም ጋር እንደ እባብ የኾኑትን መላእክትንና ሰዎችን [ቀጠቀጣቸው]፡፡”

መልካም ቀን🙏
በጥንት ዘመን አንድ ንጉሥ በሁለት ሰዎች ላይ ሞት ፈርዶ ሲያበቃ ለመጨረሻ ጊዜ የምትናገሩት ሐሳብ ካለ ይዛችሁት ከምትሞቱ ሐሳባችሁን ግለጹ አላቸው። አንደኛው የሞት ፍርዱ ላይነሳልኝ ምን አደከመኝ ብሎ ያስብና ምንም የምናገረው ነገር የለኝም የለኝም ይላል።

ሌላኛው ግን ዝም ብዬ ከምሞት ብሎ ያስብና አንድ መላ ያመጣል። ንጉሱ አንድ በጣም የሚወዳት ምርጥ ፈረስ እንዳላቸው ስለሚያውቅ "ንጉስ ሆይ ሺ ዓመት ይንገሡ! እኔ የሚወዱትን ፈረስዎ ለአንድ ዓመት መብረር ላለማምውደ እችላለሁ" ይህ የሚሆነው ግን የአንድ ዓመት ዕድሜ ከተሰጠኝ ብቻ ነው ይላል።

ንጉሡም አባባሉ ቢያስገርመውም "የሚበር ፈረስ ያለው በዓለም ላይ ብቸኛ ንጉሥ" መባሉን ውስጡ ስለወደደው በነገሩ ተስማምቶ የአንድ ዓመት ዕድሜ እንዲሰጠው ፈቀደ ።

ከችሎቱ መልስ ያ ዝም ያለው ባልንጀራው በዚህኛው ላይ ስላቅ ተናገረበት "ወፈፍ ያረግሃል ልበል? አሁን በየት ሀገር ነው ፈረስ የሚበረው? አንድ ዓመት ረዥም መስሎህ ነው ይህን የማይሆን ነገር የምትናገረው? ምናለ ጣርህን ባታበዛው" አለው።

ብልሁ ሰው ግን ተኩራርቶ እኔ እንዳንተ ዝም ብዬ አልሞትም ይህን ሃሳብ ሳቀርብ ነጻ ለመውጣት አራት አማራጮች አሉኝ እነርሱም፡-
፩ኛ. #በዚህ #አንድ #ዓመት #ንጉስ #ሊሞቱ #ይችላሉ

፪ኛ. #እኔ #እራሴ #ልሞት #እችላለሁ

፫ኛ. #ፈረሱ #ሊሞት #ይችላል

፬ኛ. #ማን #ያውቃል #ምንአልባት #ፈረሱን #መብረር #አስተምረው #ይሆናል። አለው ይባላል።

እኛም ዝም ብለን ከነኃጥያታችን ልንሞት አይገባም ንስሐ ገብተን ሥጋ ወደሙን ተቀብለን ነጻ ወጥተን ብንሞት ይሻለናል።
Channel photo updated
Forwarded from አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ  (አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ)
🌻
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቀም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።
🌻
ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው።

ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።

በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ - መንፈሳዊው መንገድ መጽሐፍ አያሌው ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)
🌻
የሕይወት ፡ እናቱ ፡ ሆይ፤ ተቀዳሚ ፡ ተከታይ ፡ በሌለው ፡ በአንድ ፡ ልጅሽና ፡ በእኛ ፡ መካከል ፡ አስታርቂን።
🌻
The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 19 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 8 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
2025/04/07 09:53:06
Back to Top
HTML Embed Code: