Telegram Web Link
በትናንቱ እንግዳ የሕዋ ክስተት ዙሪያ ከተለያዩ የሕዋ አካላት መከታተያ እና የመረጃ ቋቶች ያገኘናቸውን መረጃዎች በማጠናቀር ባደረግነው ጥልቅ የሆነ ትንተና መሰረት የሚከተለው ሳይንሳዊ መላምት ላይ ደርሰናል።
በመረጃው መሰረት የሕዋ አካሉ ባለቤትነቱ የቻይና የሆነ ሺ ጂያን-19 (ShiJian-19) የተባለ ሳተላይት ቀሪ አካል ሊሆን እንደሚችል ያመላክታል።

ከዚህም በተጨማሪ የሳተላይቱን ቀሪ አካል የምህዋር እና የይዘት መረጃ ጨምረን ጠቅላላ ትንታኔውን ከዚህ ልጥፍ ጋር አጋርተናል። ሳተላይቱ በ መስከረም 17 2017 ዓ.ም ወደ ምህዋር የተወነጨፈ ሲሆን ተልዕኮውን ጨርሶ በ ጥቅምት 1 2017 ዓ.ም ወደ መሬት ተመልሷል።

ነገር ግን ሳተላይቱ በተልዕኮው ላይ ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ክፍሎቹ ከዋናው ሳተላይት ተነጥለው በምህዋር ላይ ሲዞሩ ቆይተዋል።

ለተጨማሪ መረጃ ከላይ የተያያዘውን ግራፊክ ይመልከቱ

ለትንተናው የተጠቀምናቸው መረጃዎች ከሶስተኛ ወገን የመረጃ ቋቶች የተገኙ በመሆኑ የተረጋገጠ መረጃውን የሳተላይቱ ባለቤት ሃገር ቻይና እስክታረጋግጥ መጠበቅ ይኖርብናል።


ዋቢ ምንጮች፡

https://www.satcat.com/sats/61506
http://www.satflare.com/track.asp?q=61506&sid=2#TOP

@officialesss
New Social Media Unlocked !🦋

በአዲሱ የማኅበራዊ ትሥሥር መድረክ ብሉስካይ ላይ መጥተናል።

ይሄንን በመጫን https://bsky.app/profile/officialesss.bsky.social ይቀላቀሉን

We're on the new social media platform - Bluesky

Join us via https://bsky.app/profile/officialesss.bsky.social

#ESSS #JoinBluesky
Application for the Ethiopian Space Science Society's Youth Space Ambassador Award is out now!

🚀Become the next ESSS Youth Space Ambassador

Click here to apply!

Learn More about the application Process 🔗here

#ESSS #YSA #YSA25

🚀Follow Us
FACEBOOK | YOUTUBE | INSTAGRAM | X | LinkedIn | TELEGRAM | BlueSky
በቅጥር ላይ ነን

የሥራ መደብ: ጸሐፊ እና ገንዘብ ያዥ
የሥራ ቦታ: የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ዋና ጽ/ቤት
ቀነ ገደብ: ጥር 20 ፤ 2017 ዓ.ም

🔗ለማመልከት ይሄንን ይጫኑ
ℹ️ስለ ሥራ መደቡ ይበልጥ ለማወቅ እዚህ ይጫኑ

#ESSS #Vacancy #Opportunity
የፕላኔቶቹን ሰልፍ ከኛ ጋር በጋራ ይመልከቱ!🪐

ኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ እና የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በጋራ አዘጋጅነት በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ እና ምርምር ማዕከል የፕላኔቶች ምልከታ መረሃግብር ላይ ተጋብዘዋል!

በመርሃግብሩ በቴለስኮፖች በመታገዝ የህዋ አካላትን ለመመልከት ዕድል የሚያገኙ ሲሆን ይህ ምሽት "የፕላኔቶች ሰልፍ" የምንለው ሁሉም ፕላኔቶች በምሽቱ ሰማይ ላይ የሚታዩበት ቀን መሆኑ ለየት ያደርገዋል።

📅ቀን፡ ቅዳሜ፣ 17 2017 ዓ.ም
🕕ሰዓት፡ 12፡00 ከምሽቱ ጀምሮ
📍ቦታ፡ በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ እና ምርምር ማዕከል

ማሳሰቢያ፦
ℹ️መረሃግብሩን ለመሳተፍ መመዝገብ ይኖርብዎታል!
🚌ምንም ዓይነት የትራንስፖርት አገልግሎት የማንሰጥ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
❄️የአየር ሁኔታው ቀዝቃዛ ስለሆነ ወደ ዝግጅቱ ሲመጡ ጃኬትና ሙቀት ያለው ልብስ መልበስዎን አይርሱ!

ለመመዝገብ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ!

🔗https://forms.gle/ZQeoD28K4x4M394e9

#ESSS #SSGI #Stargazing
2025/04/10 01:42:46
Back to Top
HTML Embed Code: