Telegram Web Link
Forwarded from yordi ዘዮሐኒ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሀጅዋ ሌላ ታሪክ ውስጥ ናቸው 😁😂😂

ሾይጣንን ቀጠቀጡት እኮ😂
ሰሞኑን እስኪ አመቻችቼ የማቴዎስ ወንጌልን አብረን እናጠናለን ።

መምህር አጥሮናል ከቻላችሁ መምህራንን ብትጋብዙልን
ታላቁ ጅብሪል ሰላም ብሎችኋል
አልወጣም ከቤቴ !

ክፍል 3

ቁርሱንም መስራት ጀመረች። እንደተለመደውም አባቷ ለሳሙኤል ደወለ

ሳሙኤል፡- ሄሎ አባ ሰላም አደርክ

መሀመድ፡- እንዴት አደርክ ትላንት በሰላም ወደ ቤትህ ገባህ?

ሳሙኤል፡- አዎ እግዚአብሔር ይመስገን

መሀመድ፡- ጥሩ በቃ ዛሬ እንደትላንትናው ከስራ ስትወጣ እንገናኛለን

ሳሙኤል፡- ዛሬ ስራ አልሄድም አባ

መሀመድ፡- ምነው በሰላም ነው የቀረኸው ?

ሳሙኤል፡- አዎን በሰላም ትንሽ ደክሞኝ ነው

መሀመድ፡- እንደሱ ከሆነማ ወደ አራት ሰአት ላይ ለምን አንገናኝም

ሳሙኤል፡- እሺ ይቻላል የት እንገናኝ

መሀመድ፡- የምናዘወትረው ካፌ ቢቻልህ መፅሀፍ ቅዱስህን ይዘህ ና!

ሳሙኤል፡- መፅሀፍ ቅዱስ ደግሞ ለምንድን ነው ይዤ የምመጣው?

መሀመድ፡- ስትመጣ እነግርሀለው

ሳሙኤል፡- እንደሱ ነው ነገሩ መልካም ገብቶኛል

መሀመድ፡- እሺ እስከዛው ሰላም ዋል

ሳሙኤል፡- ሰላም ዋል!

ሳሙኤልም በጣም በመገረም "እስኪ እናያለን" አለና ከአልጋው ተነስቶ ወደ ሻውር ቤት ገባ ። በመስታውት እራሱን እየተመለከተም "ዛሬ አምላክ ሊጠራህ እያሰበ ነው ትመሰክርለትም ዘንድ ጠርቶሀል ራስህን እንዳታሳፍር ለሚጠይቅህ ጥያቄ በሙሉ ለመመለስ የተዘጋጀህ ሁን!" አለና ሻውር ወስዶ ወጣ።

ፈዲላም ሰርታ ጨርሳ ነበርና በፍቅር መንፈስ እየተወያዩና እየተጫወቱ ቁርሳቸውን አብረው በሉ። በመጨረሻም

ሳሙኤል፡- ውዴ ወደ አራት ሰአት ላይ እወጣለሁ

ፈዲላ፡- የት?

ሳሙኤል፡- ከአባትሽ ጋር ቀጠሮ አለኝ ስለትላንትናው ጉዳይ ዛሬ ነው የምንወያየው።

ፈዲላም በድንጋጤ፡- ምን ማለት ነው የትላንትናው ጉዳይ ምንድን ነበር?

ሳሙኤልም፡- እኔንጃ ዛሬ ነው የምሰማው ' በማለት ዋሻት

ፈዲላ፡- እሺ ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆንክ አብሬህ ልምጣ

ሳሙኤል፡- ለምንድን ነው ግን ሁሌ አባትሽን ለብቻዬ እንዳላገኘው የምታደርጊው? የምትፈሪው ነገር አለ እንዴ?

ፈዲላ፡- ኧረ እንደሱ አይደለም ስላመመህ ብዬ ነው

ሳሙኤል፡- ዛሬ ስላመመኝ ነው ሌላውን ቀንስ?

ፈዲላ፡- መስሎህ ነው ሳሚ እኔ እናተን ለመለያየት ያደረግኩት ነገር የለም።

ሳሙኤልም በመገረም፡- እሺ እንደሱ ከሆነ ጥሩ አሁን ልብሴን ልቀይር 'ብሎ ተነሳ

ፈዲላም ሁኔታውን በቆራጣ ትከታተል ነበር በልቧም "አሁን ምንም አማራጭ የለኝም ሳሙኤልን ላስቀረው አልችልም ነገሩ በከፊሉ ገብቶታል መሰለኝ ከአሁኑ እኔን መጠራጠር ጀምሯል ጉዴ ፈላ የፈራሁት ከደረሰ እኔ ያለሱ መኖር አልችልም" አለች

ሰአቱም በደረሰ ጊዜ ሳሙኤል ቻው ሳይላት ከቤቱ ወጣ ምክንያቱም የሆነ ነገር ፈጥራ ልታስቀረው እንደምትችል ልቦናው አውቆት ነበርና ቻው አላላትም።

ካፌም እንደደረሰ መሀመድ ምልክት ሰጠው አይቶትም ወደ ተቀመጠበት ቦታ አመራ

መሀመድ፡- እንኳን ደህና መጣህ ሳሙኤል

ሳሙኤል፡- እንኳን ደህና ቆየኸኝ አባ

መሀመድ፡- ሻይ ቡና?

ሳሙኤል፡- ሻይ

መሀመድ፡- እንግዲህ ውይይታችንን ስንጀምር ለምንድም እንደጠራሁህ በስልክ ከነገርኩህ ነገር ላይ ትንሽ ሹክ ብዬሀለው

ሳሙኤል፡- አዎን ስለ ሀይማኖት ልትናገረኝ እንደሆነ ግልፅ ነው

መሀመድ፡- ጥሩ እውነት የሆነውን ነገር መከተል መልካም ስለሆነ ብዬ ነው።

ይቀጥላል........

@nubeberhanuenmelales
ቀጣዩ እንዲለቀቅ የግሩፓችን አባላት ቁጥር 12,500 መሆን አለበት ። 😎😂
አሁን ሊለቀቅ ይችላል 12,500 ከገባን 💪👍👏👏
ጓዶች እየደረሳችሁ ነው እኔ ክፍል አራት ለመልቀቅ ተዘጋጅቻለሁ
ክፍል አራትን ለለቀው ነበር ግን ....12,500 አልገባም 😳
አልወጣም ከቤቴ!

ክፍል 4

ሳሙኤል፡- እሺ አሁን ውይይታችንን እንጀምር ስለምንድን ማወቅ ትፈልጋለህ?

መሀመድ፡- መልካም እንግዲህ ስለ ነብያችን ኢሳ የአላህ ሰላም ይውረድበትና ስለእሱ ነው መነጋገር ያለብን

ሳሙኤል፡- ኢሳ እንግዲህ ቁርአን ውስጥ የምናገኘው የአላህ መልእክተኛ ነው ስለ እርሱ እንድንወያይ ነው የምትፈልገው?

መሀመድ፡- አዎን ልጄ

ሳሙኤል፡- እሺ ግን ስለ ኢሳ የምንወያይ ከሆነ መፅሀፍ ቅዱሱን ለምን አምጣ እንዳልከኝ አልገባኝም

መሀመድ፡- ምክንያቱም ኢሳን መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ስለምናገኘው ነው!

ሳሙኤልም በመገረም፡- ኢሳን መፅሀፍ ቅዱሱስጥ የት አገኘኸው?

መሀመድ፡- አንተ ኢየሱስ ብለህ የምታመልከው ነብያችን ኢሳን ነው።

ሳሙኤል፡- ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ አምላክ እንደሆነ እኔ ብቻ ሳይሆን ማምነው አለም ሁሉ ሊያውቀው የሚገባ እውነታ ነው! ግን አንተ ኢሳንና ኢየሱስን አንድ ልታደርጋቸው እየሞከርክ ነው እንዴት

መሀመድ፡- ከውልደት እስከሞት የሰሩትን ስራ መመልከት እንችላለን ኢሳና ኢየሱስ አንድ ናቸው አታለያያቸው

ሳሙኤል፡- ከውልደት እስከሞት?? እሺ እንዳልከው ከውልደት እንጀምር ኢየሱስ የት ተወለደ? ኢሳስ የት ተወለደ? ስለ አንድነታቸውና ስለልዩነታቸው በእዚህ ወሳኝ ጥያቄ መመለስ እንችላለን።

መሀመድም ጥያቄው አስደነገጠው ቀዝቀዝ ብሎ እንዲህም አለ "እሺ ግን ውልደት ብቻ ሳይሆን በስራቸውም የምንወያይ ይሆናል ኢሳ የተወለደው ዛፍ ስር ነው"

ሳሙኤል፡- አየህ ለእዚህ ነው አይገናኙም የምልህ ኢየሱስ ደግሞ የተወለደው በበረት ነው ውልደታቸው እንኳ አይገናኝም ግን አንተ ልታጣምራቸው እየሞከርክ ነው ይህ ደግሞ አይሆንም!

መሀመድ፡- እሺ ግራ ቀኝ ከምንል ስለ ቁርአኑ እንተወውና ኢየሱስ አምላክ እንደሆነና "እኔ አምላክ ነኝ አምልኩኝ" ያለበትን ቦታ ከመፅሀፍ ቅዱስህ አምጣልኝ

ሳሙኤል፡- በመጀመሪያ ጥያቄውን አስተካክል አንድ አካል አምላክ ነኝ አምልኩኝ ስላለ ብቻ አይመለክም ምክንያቱም እንደዛ ከሆነ እኛ እስካሁን ሳጥናኤልን እያመለክነው በነበረ ግን አምላክን አምላክ የሚያሰኘው አምላክ የሚያደርገውን ነገር ብቻ ሲያደርግ ነው።

መሀመድ፡- እሺ መልካም መልሱን ስጠኝ አምላክነቱን የሚገልፅ ጥቅስ?

ሳሙኤል፡- እንደ መነሻ ዮሀ 10፥30 ላይ እኔና አብ አንድ ነን ብሎ ራሱን ከአብ ጋር አተካክሎ አምላክ ነኝ ብሏል

መሀመድም ሳቀ መልሶም እንዲህ አለው "አንድነታቸው አንተ እንደምትለው ተተካክለው ሳይሆን በሀሳብ ነው በሀሳብ"

ሳሙኤል፡- ይገርማል! አንተ ተወው ግን እርሱን የሚያሳድዱት አይሁዶች እንኳ የእርሱ ንግግር ምን እንደሆነ ተረድተውት ነበር! ቆይ ምን እንዳሉ እናንብብ እስኪ

ዮሐንስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
❝³⁰ እኔና አብ አንድ ነን።
³¹ አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ።
³² ኢየሱስ፦ ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ ማናቸው ሥራ ትወግሩኛላችሁ? ብሎ መለሰላቸው።
³³ አይሁድም፦ ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን
#አምላክ_ስለ_ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት።❞

እንግዲህ እኔ የክርስቶስ ባሪያ ብቻ ሳልሆን አይሁን ቃሉ ንግግሩ ምን እያለ እንዳለ እየመሰከሩ ነው ስለ እዚህ ምን ትላለህ??

መሀመድ፡- አይሁድ ተሳስተዋል!

ሳሙኤል፡- ድንጋይ በማንሳታቸው አዎን ተሳስተዋል ግን ቃሉን ማብራራታቸው ላይ አልተሳሳቱም ክርስቶስ እዛ ላይ አምላክ ነኝ ብሏል ትንሽ ከፍ ስትል ደግሞ ህይወት እሰጣለሁ ይላል እስኪ ንገረኝ ህይወትን ከመስጠት የበለጠ አምላክነት አለ?

❝እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።❞
  —ዮሐንስ 10: 28

መሀመድ፡- ለነማ ነው የዘላለም ህይወት የሚሰጠው?

ሳሙኤል፡- ለኛ ነዋ እርሱን ላመንን ❝በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤❞
  —ዮሐንስ 10: 27

መሀመድ፡- እየውልህ ልጄ ቃሉን አንብበው አንተ እንደፈለከው ሳይሆን ቃሉ እንደሚመራህ ምንም እንኳ እኔና አብ አንድ ነን ቢልም ዮሀ 14፥28 ላይ አብ ከእኔ ይበልጣል ብሏል አንተ አንተ እንደምትለው መሲሑ ከአብ ጋር እኩል አይደለም።

ሳሙኤል፡- የመፅሀፍ ቅዱሱን ቃል ከአንተ ይበልጥ እኔ እከተለዋለሁ ስለዚህ ይህ ምን ማለት ነው ማብራሪያ ስጠኝ ማለት እንጂ መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ገብተህ ማብራራት አትችልም አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አብ ከእኔ ይበልጣል ማለቱ አይግረምህ ስጋ በመልበሱ ከመላእክት እንኳ ጥቂት አንሷል የባሪያ መልክ ይዟል ስለዚህ አብ ስጋ አልለበሰም ወልድ ኢየሱስ ግን ስጋ ለብሷል ስለእዚህም አብ ከእኔ ይበልጣል አለ።

መሀመድ፡- ልጅ ሳሙኤል ምንድን ነው የምታወራው ቃሉ ኮ ግልፅ ነው አብ ከእርሱ ይበልጣል

ሳሙኤል፡- እሺ አባ አንተ ባልከው መንገድ እንሂድና ይህ ቃል ዮሀ 10፥30 ካለው ቃል ጋር ይጋጫል ማለት ነው?? አይደለም ክርስቶስ በስጋውና በመለኮቱ ብዙ ጊዜ የተናገራቸው ቃላቶች አሉ ይህን ለመረዳት ደግሞ የግድ ከአብ መሳብን ይጠይቃል የሁለቱንም ቃላት ትርጉማት አብራርቼልሀለው የቱ ጋር ነው ያልገባህ?

መሀመድ፡- አብ ከኔ ይበልጣል ብሏል ስለዚህ እናንተ እንደምትሉት አይደለም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ባሪያ ነው እንጂ ልጅ አይደለም

ሳሙኤል፡- የግል አስተያየት ሳይሆን መፅሀፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ ጠይቀኝ ካስረዳውህ ላይ የቱ ነው ያልገባህ?

መሀመድ፡- አንተ እንደምትለው ኢየሱስ አምላክ ሳይሆን የአምላክ ፍጡር ነው በወንጌል ላይ አብን አምላኬ እያለ ሲጠራው ነበር እና ከየት አምጥታችሁ ነው ኢየሱስን አምላክ የምትሉት እርሱ እራሱ አምላኬ እያለ የበላይ እንዳለው እያሳያችሁ?

ሳሙኤል፡- መልካም ስለ ክርስቶስ ኢየሱስና አብ አንድነት የሰጠውህ ማብራሪያ ግልፅ ነው። እርሱን ትተን በእዚህ ነጥብ እንወያይ ማለት ነው?

መሀመድ፡- መቼ ጨረስን? ስለ ክርስቶስ አምላክነት ነው አይደል የምንወያየው ከመፅሀፍህ አምላክ እንዳልሆነ እያሳየውህ ነው ያለሁት።

ሳሙኤል፡- አውቃለሁ አይደለም ብለህ የምታመጣውን ጥቅስ ደግሞ እኔ እያብራራውልህ ነው ያለሁት በእርግጥ ክርስቶስ ኢየሱስ ዘላለማዊ አምላክ ነው ግን ውይይታችን ላይ ለምታነሳቸው ጥቅሶች ማብራሪያ እየሰጠውህ ነው ስለዚህ አሁን አብ ከእኔ ይበልጣል የሚለውን ጥቅስ ማብራሪያ ሰጥቼሀለው እርሱን ተረድተኸዋል? ከእዛን ክርስቶስ ለምን አምላኬ እንዳለ የምንመጣበት ይሆናል!

መሀመድ፡- ትቼው ነው እንጂ ምንም የሚዋጥ መልስ አልሰጠኸኝም በሌላው መንገድ ከተገለጠልህ ብዬ እንጂ የተናገርከው ነገር ምንም ከቃሉ ጋር አይሄድም።

ሳሙኤል፡- እኮ የቱ ጋር ነው አብሮ ያልሄደው የቱ ጋር ነው ያልገባህ ብዬ እየጠየቅኩህ ኮ ነው?

መሀመድም የሚጠይቀው ጥያቄ አጣ ስለዚህ ቅድም ባነሳው መንገድ ቢወያይ ሳሙኤል በምንም መንገድ ሊያሸንፈው እንደማይችል አሰበ።


ይቀጥላል.......
“አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ። በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ? እርስዋ እንደ መሃናይም ዘፈን ናት።”
  — መኃልየ. 7፥1
ርግቧ እናቴ 🥰
ስደተኛዋ ሙሽራ 🥺
ንፅህይቷ እመቤት
ከርታታዋ ኮከብ
የውሃ ማሰሮዋ

.... 🥰🥰🥰

ሰላማዊውን ልጅሽን ተጠምተነዋል ። ጠጥተነው ተመግበነው ከረሐበ ሰላም እንፈወስ ዘንድ ይዘሽልን ነይ ።

አዛኟ እባክሽ ሰላምቻንን ክርሰሰቶስን ይዘሸቸልን ነይ 🥰🥺🥺
“አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ። በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ? እርስዋ እንደ መሃናይም ዘፈን ናት።”
— መኃልየ. 7፥1
የእስላም ስጋ አማትቦ መብላት ይገባልን
✥ . ✥ . ይመስገን "ፈጣሪ" . ✥ . ✥
. ¯\_(ツ)_/¯
. [)(]
. _| \_

ዛሬ ከአንዲት ትዝብት ጋር ነው ብቅ ያልኩት። መቼም አዲስ ነገር ከመናገርና ከመስማት በቀር ሌላ ጉዳይ እንደሌላቸው የአቴና ነዋሪዎች " ምንተ ይፈቅድ ዝዘራዔ ነቢብ … ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይወዳል? " እንደማትሉኝ ተስፋ አለኝ! 【ሐዋ ፲፯፥፲፰】 እነርሱስ ‘የማይታወቅ አምላክ’ ተከታዮች ናቸው፤ እኛ ግን በከበረ ሥልጣን በተለየ ስም የምናውቀውና የምናመልከው ታላቅ ፈጣሪ የከበረ አምላክ "ሥሉስ ቅዱስ" ያለን ነን።

በሰዎች ዘንድ አንገት ከሚያስደፉን ፣ "በማንነታችን" እንዳንኮራ ከሚያሸማቅቁን ተግባራት መኻል ፦
🍂 ስመ እግዚአብሔርን በክብርና በልዩነት ደፍሮ ለመጥራት መጨነቅ፣
🍂 ከመቅደሱ ደጃፍ ቆመን አልያም በአንጻረ ቤተክርስቲያን ስናልፍ ፣ ማዕድ ፊት ስንቀርብ ፣ ስንደነግጥ … ለማማተብ መሳቀቅ
🍂 በአንገታችን ያሠርነውን ማዕተብ መደበቅ አልያም ማውለቅ…

ዛሬ (ጥቅምት ፫) ቤተክርስቲያን ጽንሰቱን የምታከብርለት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በረከቱ ይደርብንና በመጽሐፈ ምሥጢር ይህን " ሥርወ መሪረ ዘኀደገ ለነ ክርስቶስ ☞ ክርስቶስ የተወልን መራራ ሥር" ይለዋል።

"ኀደገ ለነ ሥርወ መሪረ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ምንት ውእቱ ሥርው መሪር ዘእንበለ ጽዋዔ ስሙ ቅዱስ ወዑታቤ መስቀሉ በኀበ ሰይጣን እምዝክረ ስሙ ይርዕድ ወእምዑታቤ መስቀሉ ይነፍጽ [ዝ ውእቱ መሪር ብሂል]"

"ኢየሱስ ክርስቶስ የሚመር ሥርን ተወልን፤ ቅዱስ ስሙን ከመጥራት በሰይጣን ላይ በመስቀል ከማማተብ ሌላ የሚመር ሥር ምንድር ነው። ከስሙ መጠራት የተነሣ ይንቀጠቀጣል በመስቀሉ ከማማተብም የተነሣ ይሸሻልና [መሪር ማለት ይህ ነው! ]" 【መጽሐፈ ምሥጢር ፳፪፥፱】

ታድያ ለሰይጣን የሚመረው "ጽዋዔ ስሙ ቅዱስ ወዑታቤ መስቀሉ ☞ ቅዱስ ስሙን መጥራትና በቅዱስ መስቀሉ ማማተብ" ለእኛም እንዴት መረረን? የዛሬው መነሻዬ የስሙ ጉዳይ ብቻ ነው (ሌላው ሌላ ጊዜ እናሰንብተው) ፤

አምላክ / ፈጣሪ ማነው? የእኛ አምላካችን ፣ ፈጣሪያች ፣ ጌታችን የከበረ ስም የለውም ይሆን? ስሙን መጥራትስ ለምን እያሳፈረን መጣ?

ለእኔ አስማተ መለኮትን (የመለኮትን ስሞች) እንዳንጠራ የቃናዎቹ ቱርክ ፊልም ተርጓሚዎች ያለማመዱን ከፖለቲከኞች (በተለይም "ከአበልጻጊዎቻችን") ና ከ "ሁሉን እናስደስታለን" ባዮች የወረስነው ክብር የማንሰጥበት ስሁት መንገድ መስሎ ታይቶኛል።

☆ ፈጣሪ/ አምላክ / ጌታ ይመስገን ፣
☆ ፈጣሪ/ አምላክ / ጌታ ኢትዮጵያን ይባርክ ፣
☆ እንደ ፈጣሪ / እንደ አምላክ / እንደ ጌታ ፈቃድ ፣
☆ አምልኮተ ፈጣሪ / ፈሪሃ አምላክ … የሚሉቱ መገለጫዎቻችንን በመደበቅ ፣ ስለሌሎች በመጨነቅ ፣ አብሮነትን በማድነቅ ፣ ለምስክርነት በመሳቀቅ ዋጋ እያሳጡን ያሉ አካኼዶች መሆናቸውን አጢነነው ይሆን? እንጃ!

« ምንችግር አለው? አታካብዱ…¡ » ለምትሉ ፤ ሳትቸገሩ ከብዳችሁ እንድትኖሩ ሳታፍሩ የከበረ ስሙን ጥሩ!

"ስምህ ይቀደስ" 【ማቴ. ፮፥ ፲】የምንለው! የአምላካችን እናቱ ለትውልደ ትውልድ የሆነ ምሕረቱን ስትመሰክር "ስሙም ቅዱስ ነው! " 【ሉቃ. ፩፥፵፱】ያለችው … የወል ስም ሳይሆን "ወላዲ ተወላዲ ሠራፂ" በሚባልበት ግብር የሚታወቅ አባት (አብ) ልጅ (ወልድ) እና መንፈስ ቅዱስ የሚባል የተለየ ስም አምላካችን ስላለው ነው።

☞አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ፣ እግዚአብሔር ፣ ሥሉስ ቅዱስ!

“ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ፥ በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ።” 【መዝ. ፳፪፥፳፪】

በጉባኤ መኃል ያልጠራነውን ስም ቢያንስ በተናጥል ስንገናኝ ፣ በግል የስልክ ጥሪዎችቻችንና በውሥጥ የጽሑፍ መልእክት እስክንሸማቀቅበት አልያም በቸልታና በልምድ ስንተወው መታየታችን ያሳዝናል።

የሚያሳፍረው ስሙን አለመጥራት እንጂ ለመክበር የከበረ ስሙን መጥራትስ አልነበረም!

"ስሙን አግኑት በምግባር በሃይማኖት ጸንታችሁ ለጌትነቱም ተገዙ … አሁንም በፍጹም ልቡናችሁ በፍጹም አንደበታችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑት ስሙንም ሁልጊዜ አመስግኑት"【ሲራ። ፴፱፥፲፭/፴፭】

ስለዚህ የተዋህዶ ልጆች ሁል ጊዜ ስሙን እንዲህ እያልን ማመስገን ይገባናል ፦

"ይክበር ይመስገን ሥሉስ ቅዱስ፣ እግዚአብሔር ይመስገን ፣ ክብር ምስጋና ለቅድስት ሥላሴ ፣ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የተመሰገነ ይሁን! "

እናስተውል የጣኦታትና የአጋንንትን ስም መጥራት እንደሚያረክሰው ሁሉ የአምላክን ስም መጥራትም ይቀድሳል።

"ዳግመኛም የአማልክትን የጣዖታትን ስም በአፋቸው አይጥሩ ፣ ፡ሰይጣንንና መላእክቱንም አይጥሯቸው ፣ ስሙንም በጠሩ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከእነርሱ ይለያልና ፣ በእርሱ ፈንታም መንፈስ ርኩስ በላያቸው ያድራል ።"
【መጽሐፈ ዲድስቅልያ ፳፯፥፬】
ዛሬ አዳሜ አምላጦችኋል አብርሽ እየፈሰረ ነው 😎
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ክርስቲያን የሙስሊም ስጋ አይበላም
አልወጣም ከቤቴ ይለቀቅ ወይ

ስንቶቻችሁ እየተከታተላችሁት ነው ግን ?
ሀገረኪ ገሊላ እትዊ እስከ መቼ ድረስ እመቤቴ በሰው ሀገር ትኖሪያለሽ ? ሀገርሽ ገሊላ ግቢ። እናቴ ሆይ ወደ ልቤ ግቢ የእኔም ልብ ወደ ልጅሽ ወደ ወዳጅሽ ሚጠት መመለስን ይፈልጋልና ።
አልወጣም ከቤቴ!

ክፍል 5

መሀመድ፡- ይገርማል አልሞት ባይ ተጋዳይ አትሁን ለእውነት ከመጣ ስለ እውነት መስክር ክርስቶስ በወንጌሉ አምላኬ ብሎ የጠራው ማንን ነው?? ፈጣሪውን?

ሳሙኤል፡- እሺ ጥሩ በመጀመሪያ አምላክ ማለት ምን ማለት ነው በሚለው እንወያይና ከእዛ ክርስቶስ አምላኬ ያለው በምን መንገድ እንደሆነ እንወያያለን

መሀመድ፡- አምላክ ማለት ፈጣሪ ነው ሌላ ምንም ትርጉም የለውም!

ሳሙኤል፡- መፅሀፍ ቅዱስ ግን ይህንን አይነግረንም አምላክ ማለት ፈጣሪ ብቻ አይደለም ፈጣሪያችንን "ጌታ" ስንል በባህሪ ሰዎችንም ደግሞ "ጌታ" ስንል በፀጋ እንደሆነው ሁሉ ፈጣሪያችንን አምላክ ስንልና ሰውን አምላክ ስንል ትርጉማቱ ይለያያል ለምሳሌ እግዚአብሔር ሙሴን በፈርኦን ላይ እንደ አምላክ አደርግሀለው ሲል በፀጋ የተሰጠው አምላክነት ነው!

መሀመድ፡- አምላክ በፀጋም አለ??? እሺ ቀጥል

ሳሙኤል፡- ስለዚህ ክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌሉ አምላኬ እያለ ሲጠራው የነበረው የባህርይ አባቱን ነው ይህም እያመለከው ሳይሆን በፀጋ ነው ክርስቶስ በስጋ ሲመላለስ ስጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ ስላለውም ይህንን ቃል ተናገረ

መሀመድ፡- ከምትለው አንዳችም አልገባኝም

ሳሙኤል፡- ምኑ ነው ያልገባህ እንዲህ አብራርቼው?

መሀመድ፡- ምን ተብራራ ልጅ ሳሙኤል የማይገናኝ ነገር ነው የምታወራው

ሳሙኤልም ተገረመ "ይህ ሰው አውቆ ነው እስካሁን እንዳልገባው እየመሰለ ያለው ወይንስ እውነት አልገባውም?" ብሎ በውስጡ እያሰበ እንዳለ የቅዱስ ጳውሎስ መልክት ወደ ልቦናው መጣለት «ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው» የሚለው ቃል ትዝ አለው።

ሳሙኤል መሀመድን ተረዳው የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት የማይወደው ከእግዚአብሔር ስላልሆነ መሆኑን አስተዋለ "በምን መንገድ እንዲገባው ላድርግ ግን የተናገርኩት ቃል የግድ በመንፈስ ሊተነተን የሚገባው ነገር አይደለም።

ቃሉ ግልፅ ነው መቀበል አለመቀበል የእርሱ ፋንታ ነው።" አለ

መሀመድ፡- ምነው ዝም አልክ መልስ የለም?

ሳሙኤል፡- መልሱንማ አብራርቼልሀለው መቀበል አለመቀበል የአንተው ፋንታ ነው

መሀመድ፡- እሺ መልሱን ለህሊና

መሀመድ ሁሌም በውይይት መሀል ይህችን ቃል ጣል ያደርጋታል ምክንያቱም ምንም እንኳ የሚወያዩት ሰዎች ልክ ቢሆኑም ይህንን ቃል ሲናገር እራሳቸውን እንዲጠራጠሩና እንዲፈሩ ስለሚያደርግ ነው። ግን ሳሙኤል የተናገረውን ጥርት አድርጎ ያቃልና መሀመድ ይህንን ቃል በተናገረ ሰአት ፈገግ አለ አስከትሎም

ሳሙኤል፡- አዎን መልሱን ለህሊና ህሊና ስለ እውነት ስለምትፈርድ እውነት በማን ዘንድ እንዳለች ትጠቁማለች።

መሀመድም ደነገጠ ምክንያቱም ከተወያያቸው ሰዎች በሙሉ ሳሙኤል ተለየበት መልስ እንደተመለሰለት እያወቀ ይህንን ሲናገር ሳሙኤል እንደሌሎች ሰዎች ግራ እንዳልተጋባና ራሱን እንዳልተጠራጠረ ሲመለከት ቀላል ሰው እንዳልሆነም ተረዳ።

መሀመድ፡- እሺ መልካም ልጅ ሳሙኤል የዛሬው ይበቃናል መሰለኝ በተመቸህ ሰአት እዚው ተገናኝተን እንወያያለን!

ሳሙኤል፡- ይብቃ? እሺ እንዳልከው ይሁን ከነገ ወዲያ እሁድ ስለሆነ በእዛን ቀን ተገናኝተን እንወያያለን

መሀመድ፡- እሺ ጥሩ ውይይት ነበረን አሁን ብንሄድ መልካም ይመስለኛል

ሳሙኤል፡- እሺ

አለና ከመቀመጫው ተነሳ ከመሀመድ ጋርም ወደ ቤቱ ሄዱ። እንደደረሱም

ፈዲላ፡- እንኳን ደህና መጣችሁ!

ሳሙኤል፡- እንኳን ደህና ቆየሽ

መሀመድ፡- እንኳን ደህና ቆየሽን ልጄ

ፈዲላ፡- ቁጭ በሉ ሻይ ላፍላላችሁ አለችና ወደ እቃ ቤት አመራች

መሀመድ፡- መልካም ልጄ አለና ቁጭ አለ

ሳሙኤል ግን ፈዲላን ሊቀርባት አልፈለገም ለሁለቱም ያለው አመለካከት ስለተቀየረ ፈጠን ብሎ ወደ ቢሮው ሄደና እዛ ቁጭ አለ

ፈዲላም ስትመለስ ሳሙኤል የለም ነበር ከእዚያም ለመሀመድ

ፈዲላ፡- ሳሙኤልስ?

መሀመድ፡- ወደ ቢሮው ገብቷል መሰለኝ

ፈዱላ፡- አስቀይመኸዋል አይደል አባ?

መሀመድ፡- ወይ ልጄ ምንድን ነው የምትይው?  ስለ ሀይማኖት እንደምናወራ ታውቂያለሽ በቃ! ከእርሱ አልፌ የተናገርኩት ነገር የለም።

ፈዲላም፡- ይኸው አለቀልኝ ከአሁኑ ሳሙኤል እየሸሸኝ ነው ነግሬህ ነበር ስለ ሀይማኖት ማንሳት እንደሌለብህ ግን ብታስብልኝ ኖሮ ይህንን አታደርግም!  ብላ ፍጥን ፍጥን እያለች ወደ ሳሙኤል ቢሮ ገባች እርሱም መፅሀፍ ቅዱስ እያነበበ ነበር።

ፈዲላ፡- ሳሚ ሻይ ፈልቷል ኮ

ሳሙኤል፡- .........

ፈዲላ፡- ሳሚ እያናገርኩህ ኮ ነው ሻዩ ፈልቷል!

ሳሙኤል፡- መፅሐፍ ቅዱስ ሲነበብ ዝም ብሎ ማቋረጥ ጥሩ አይደለም ስሜቴን አትረብሺው አሁን እያነበብኩኝ ነው

ፈዲላ፡- እሺ እዚህ ላምጣልህ?

ሳሙኤል፡- እሺ

ፈዲላም ልቧ ተሰበረ ዛሬ አትረብሺኝ ካለ ነገ ደግሞ ከቤት ያባርረኛል እያለች እያጉረመረመች ወደ ሳሎን ተመለሰች

ይቀጥላል........

@nubeberhanuenmelales
2024/11/15 14:21:04
Back to Top
HTML Embed Code: