አልወጣም ከቤቴ!
ክፍል 4
ሳሙኤል፡- እሺ አሁን ውይይታችንን እንጀምር ስለምንድን ማወቅ ትፈልጋለህ?
መሀመድ፡- መልካም እንግዲህ ስለ ነብያችን ኢሳ የአላህ ሰላም ይውረድበትና ስለእሱ ነው መነጋገር ያለብን
ሳሙኤል፡- ኢሳ እንግዲህ ቁርአን ውስጥ የምናገኘው የአላህ መልእክተኛ ነው ስለ እርሱ እንድንወያይ ነው የምትፈልገው?
መሀመድ፡- አዎን ልጄ
ሳሙኤል፡- እሺ ግን ስለ ኢሳ የምንወያይ ከሆነ መፅሀፍ ቅዱሱን ለምን አምጣ እንዳልከኝ አልገባኝም
መሀመድ፡- ምክንያቱም ኢሳን መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ስለምናገኘው ነው!
ሳሙኤልም በመገረም፡- ኢሳን መፅሀፍ ቅዱሱስጥ የት አገኘኸው?
መሀመድ፡- አንተ ኢየሱስ ብለህ የምታመልከው ነብያችን ኢሳን ነው።
ሳሙኤል፡- ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ አምላክ እንደሆነ እኔ ብቻ ሳይሆን ማምነው አለም ሁሉ ሊያውቀው የሚገባ እውነታ ነው! ግን አንተ ኢሳንና ኢየሱስን አንድ ልታደርጋቸው እየሞከርክ ነው እንዴት
መሀመድ፡- ከውልደት እስከሞት የሰሩትን ስራ መመልከት እንችላለን ኢሳና ኢየሱስ አንድ ናቸው አታለያያቸው
ሳሙኤል፡- ከውልደት እስከሞት?? እሺ እንዳልከው ከውልደት እንጀምር ኢየሱስ የት ተወለደ? ኢሳስ የት ተወለደ? ስለ አንድነታቸውና ስለልዩነታቸው በእዚህ ወሳኝ ጥያቄ መመለስ እንችላለን።
መሀመድም ጥያቄው አስደነገጠው ቀዝቀዝ ብሎ እንዲህም አለ "እሺ ግን ውልደት ብቻ ሳይሆን በስራቸውም የምንወያይ ይሆናል ኢሳ የተወለደው ዛፍ ስር ነው"
ሳሙኤል፡- አየህ ለእዚህ ነው አይገናኙም የምልህ ኢየሱስ ደግሞ የተወለደው በበረት ነው ውልደታቸው እንኳ አይገናኝም ግን አንተ ልታጣምራቸው እየሞከርክ ነው ይህ ደግሞ አይሆንም!
መሀመድ፡- እሺ ግራ ቀኝ ከምንል ስለ ቁርአኑ እንተወውና ኢየሱስ አምላክ እንደሆነና "እኔ አምላክ ነኝ አምልኩኝ" ያለበትን ቦታ ከመፅሀፍ ቅዱስህ አምጣልኝ
ሳሙኤል፡- በመጀመሪያ ጥያቄውን አስተካክል አንድ አካል አምላክ ነኝ አምልኩኝ ስላለ ብቻ አይመለክም ምክንያቱም እንደዛ ከሆነ እኛ እስካሁን ሳጥናኤልን እያመለክነው በነበረ ግን አምላክን አምላክ የሚያሰኘው አምላክ የሚያደርገውን ነገር ብቻ ሲያደርግ ነው።
መሀመድ፡- እሺ መልካም መልሱን ስጠኝ አምላክነቱን የሚገልፅ ጥቅስ?
ሳሙኤል፡- እንደ መነሻ ዮሀ 10፥30 ላይ እኔና አብ አንድ ነን ብሎ ራሱን ከአብ ጋር አተካክሎ አምላክ ነኝ ብሏል
መሀመድም ሳቀ መልሶም እንዲህ አለው "አንድነታቸው አንተ እንደምትለው ተተካክለው ሳይሆን በሀሳብ ነው በሀሳብ"
ሳሙኤል፡- ይገርማል! አንተ ተወው ግን እርሱን የሚያሳድዱት አይሁዶች እንኳ የእርሱ ንግግር ምን እንደሆነ ተረድተውት ነበር! ቆይ ምን እንዳሉ እናንብብ እስኪ
ዮሐንስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
❝³⁰ እኔና አብ አንድ ነን።
³¹ አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ።
³² ኢየሱስ፦ ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ ማናቸው ሥራ ትወግሩኛላችሁ? ብሎ መለሰላቸው።
³³ አይሁድም፦ ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን #አምላክ_ስለ_ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት።❞
እንግዲህ እኔ የክርስቶስ ባሪያ ብቻ ሳልሆን አይሁን ቃሉ ንግግሩ ምን እያለ እንዳለ እየመሰከሩ ነው ስለ እዚህ ምን ትላለህ??
መሀመድ፡- አይሁድ ተሳስተዋል!
ሳሙኤል፡- ድንጋይ በማንሳታቸው አዎን ተሳስተዋል ግን ቃሉን ማብራራታቸው ላይ አልተሳሳቱም ክርስቶስ እዛ ላይ አምላክ ነኝ ብሏል ትንሽ ከፍ ስትል ደግሞ ህይወት እሰጣለሁ ይላል እስኪ ንገረኝ ህይወትን ከመስጠት የበለጠ አምላክነት አለ?
❝እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።❞
—ዮሐንስ 10: 28
መሀመድ፡- ለነማ ነው የዘላለም ህይወት የሚሰጠው?
ሳሙኤል፡- ለኛ ነዋ እርሱን ላመንን ❝በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤❞
—ዮሐንስ 10: 27
መሀመድ፡- እየውልህ ልጄ ቃሉን አንብበው አንተ እንደፈለከው ሳይሆን ቃሉ እንደሚመራህ ምንም እንኳ እኔና አብ አንድ ነን ቢልም ዮሀ 14፥28 ላይ አብ ከእኔ ይበልጣል ብሏል አንተ አንተ እንደምትለው መሲሑ ከአብ ጋር እኩል አይደለም።
ግ
ሳሙኤል፡- የመፅሀፍ ቅዱሱን ቃል ከአንተ ይበልጥ እኔ እከተለዋለሁ ስለዚህ ይህ ምን ማለት ነው ማብራሪያ ስጠኝ ማለት እንጂ መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ገብተህ ማብራራት አትችልም አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አብ ከእኔ ይበልጣል ማለቱ አይግረምህ ስጋ በመልበሱ ከመላእክት እንኳ ጥቂት አንሷል የባሪያ መልክ ይዟል ስለዚህ አብ ስጋ አልለበሰም ወልድ ኢየሱስ ግን ስጋ ለብሷል ስለእዚህም አብ ከእኔ ይበልጣል አለ።
መሀመድ፡- ልጅ ሳሙኤል ምንድን ነው የምታወራው ቃሉ ኮ ግልፅ ነው አብ ከእርሱ ይበልጣል
ሳሙኤል፡- እሺ አባ አንተ ባልከው መንገድ እንሂድና ይህ ቃል ዮሀ 10፥30 ካለው ቃል ጋር ይጋጫል ማለት ነው?? አይደለም ክርስቶስ በስጋውና በመለኮቱ ብዙ ጊዜ የተናገራቸው ቃላቶች አሉ ይህን ለመረዳት ደግሞ የግድ ከአብ መሳብን ይጠይቃል የሁለቱንም ቃላት ትርጉማት አብራርቼልሀለው የቱ ጋር ነው ያልገባህ?
መሀመድ፡- አብ ከኔ ይበልጣል ብሏል ስለዚህ እናንተ እንደምትሉት አይደለም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ባሪያ ነው እንጂ ልጅ አይደለም
ሳሙኤል፡- የግል አስተያየት ሳይሆን መፅሀፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ ጠይቀኝ ካስረዳውህ ላይ የቱ ነው ያልገባህ?
መሀመድ፡- አንተ እንደምትለው ኢየሱስ አምላክ ሳይሆን የአምላክ ፍጡር ነው በወንጌል ላይ አብን አምላኬ እያለ ሲጠራው ነበር እና ከየት አምጥታችሁ ነው ኢየሱስን አምላክ የምትሉት እርሱ እራሱ አምላኬ እያለ የበላይ እንዳለው እያሳያችሁ?
ሳሙኤል፡- መልካም ስለ ክርስቶስ ኢየሱስና አብ አንድነት የሰጠውህ ማብራሪያ ግልፅ ነው። እርሱን ትተን በእዚህ ነጥብ እንወያይ ማለት ነው?
መሀመድ፡- መቼ ጨረስን? ስለ ክርስቶስ አምላክነት ነው አይደል የምንወያየው ከመፅሀፍህ አምላክ እንዳልሆነ እያሳየውህ ነው ያለሁት።
ሳሙኤል፡- አውቃለሁ አይደለም ብለህ የምታመጣውን ጥቅስ ደግሞ እኔ እያብራራውልህ ነው ያለሁት በእርግጥ ክርስቶስ ኢየሱስ ዘላለማዊ አምላክ ነው ግን ውይይታችን ላይ ለምታነሳቸው ጥቅሶች ማብራሪያ እየሰጠውህ ነው ስለዚህ አሁን አብ ከእኔ ይበልጣል የሚለውን ጥቅስ ማብራሪያ ሰጥቼሀለው እርሱን ተረድተኸዋል? ከእዛን ክርስቶስ ለምን አምላኬ እንዳለ የምንመጣበት ይሆናል!
መሀመድ፡- ትቼው ነው እንጂ ምንም የሚዋጥ መልስ አልሰጠኸኝም በሌላው መንገድ ከተገለጠልህ ብዬ እንጂ የተናገርከው ነገር ምንም ከቃሉ ጋር አይሄድም።
ሳሙኤል፡- እኮ የቱ ጋር ነው አብሮ ያልሄደው የቱ ጋር ነው ያልገባህ ብዬ እየጠየቅኩህ ኮ ነው?
መሀመድም የሚጠይቀው ጥያቄ አጣ ስለዚህ ቅድም ባነሳው መንገድ ቢወያይ ሳሙኤል በምንም መንገድ ሊያሸንፈው እንደማይችል አሰበ።
ይቀጥላል.......

“አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ። በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ? እርስዋ እንደ መሃናይም ዘፈን ናት።”
— መኃልየ. 7፥1
— መኃልየ. 7፥1
✥ . ✥ . ይመስገን "ፈጣሪ" . ✥ . ✥
. ¯\_(ツ)_/¯
. [)(]
. _| \_
ዛሬ ከአንዲት ትዝብት ጋር ነው ብቅ ያልኩት። መቼም አዲስ ነገር ከመናገርና ከመስማት በቀር ሌላ ጉዳይ እንደሌላቸው የአቴና ነዋሪዎች " ምንተ ይፈቅድ ዝዘራዔ ነቢብ … ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይወዳል? " እንደማትሉኝ ተስፋ አለኝ! 【ሐዋ ፲፯፥፲፰】 እነርሱስ ‘የማይታወቅ አምላክ’ ተከታዮች ናቸው፤ እኛ ግን በከበረ ሥልጣን በተለየ ስም የምናውቀውና የምናመልከው ታላቅ ፈጣሪ የከበረ አምላክ "ሥሉስ ቅዱስ" ያለን ነን።
በሰዎች ዘንድ አንገት ከሚያስደፉን ፣ "በማንነታችን" እንዳንኮራ ከሚያሸማቅቁን ተግባራት መኻል ፦
🍂 ስመ እግዚአብሔርን በክብርና በልዩነት ደፍሮ ለመጥራት መጨነቅ፣
🍂 ከመቅደሱ ደጃፍ ቆመን አልያም በአንጻረ ቤተክርስቲያን ስናልፍ ፣ ማዕድ ፊት ስንቀርብ ፣ ስንደነግጥ … ለማማተብ መሳቀቅ
🍂 በአንገታችን ያሠርነውን ማዕተብ መደበቅ አልያም ማውለቅ…
ዛሬ (ጥቅምት ፫) ቤተክርስቲያን ጽንሰቱን የምታከብርለት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በረከቱ ይደርብንና በመጽሐፈ ምሥጢር ይህን " ሥርወ መሪረ ዘኀደገ ለነ ክርስቶስ ☞ ክርስቶስ የተወልን መራራ ሥር" ይለዋል።
"ኀደገ ለነ ሥርወ መሪረ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ምንት ውእቱ ሥርው መሪር ዘእንበለ ጽዋዔ ስሙ ቅዱስ ወዑታቤ መስቀሉ በኀበ ሰይጣን እምዝክረ ስሙ ይርዕድ ወእምዑታቤ መስቀሉ ይነፍጽ [ዝ ውእቱ መሪር ብሂል]"
"ኢየሱስ ክርስቶስ የሚመር ሥርን ተወልን፤ ቅዱስ ስሙን ከመጥራት በሰይጣን ላይ በመስቀል ከማማተብ ሌላ የሚመር ሥር ምንድር ነው። ከስሙ መጠራት የተነሣ ይንቀጠቀጣል በመስቀሉ ከማማተብም የተነሣ ይሸሻልና [መሪር ማለት ይህ ነው! ]" 【መጽሐፈ ምሥጢር ፳፪፥፱】
ታድያ ለሰይጣን የሚመረው "ጽዋዔ ስሙ ቅዱስ ወዑታቤ መስቀሉ ☞ ቅዱስ ስሙን መጥራትና በቅዱስ መስቀሉ ማማተብ" ለእኛም እንዴት መረረን? የዛሬው መነሻዬ የስሙ ጉዳይ ብቻ ነው (ሌላው ሌላ ጊዜ እናሰንብተው) ፤
አምላክ / ፈጣሪ ማነው? የእኛ አምላካችን ፣ ፈጣሪያች ፣ ጌታችን የከበረ ስም የለውም ይሆን? ስሙን መጥራትስ ለምን እያሳፈረን መጣ?
ለእኔ አስማተ መለኮትን (የመለኮትን ስሞች) እንዳንጠራ የቃናዎቹ ቱርክ ፊልም ተርጓሚዎች ያለማመዱን ከፖለቲከኞች (በተለይም "ከአበልጻጊዎቻችን") ና ከ "ሁሉን እናስደስታለን" ባዮች የወረስነው ክብር የማንሰጥበት ስሁት መንገድ መስሎ ታይቶኛል።
☆ ፈጣሪ/ አምላክ / ጌታ ይመስገን ፣
☆ ፈጣሪ/ አምላክ / ጌታ ኢትዮጵያን ይባርክ ፣
☆ እንደ ፈጣሪ / እንደ አምላክ / እንደ ጌታ ፈቃድ ፣
☆ አምልኮተ ፈጣሪ / ፈሪሃ አምላክ … የሚሉቱ መገለጫዎቻችንን በመደበቅ ፣ ስለሌሎች በመጨነቅ ፣ አብሮነትን በማድነቅ ፣ ለምስክርነት በመሳቀቅ ዋጋ እያሳጡን ያሉ አካኼዶች መሆናቸውን አጢነነው ይሆን? እንጃ!
« ምንችግር አለው? አታካብዱ…¡ » ለምትሉ ፤ ሳትቸገሩ ከብዳችሁ እንድትኖሩ ሳታፍሩ የከበረ ስሙን ጥሩ!
"ስምህ ይቀደስ" 【ማቴ. ፮፥ ፲】የምንለው! የአምላካችን እናቱ ለትውልደ ትውልድ የሆነ ምሕረቱን ስትመሰክር "ስሙም ቅዱስ ነው! " 【ሉቃ. ፩፥፵፱】ያለችው … የወል ስም ሳይሆን "ወላዲ ተወላዲ ሠራፂ" በሚባልበት ግብር የሚታወቅ አባት (አብ) ልጅ (ወልድ) እና መንፈስ ቅዱስ የሚባል የተለየ ስም አምላካችን ስላለው ነው።
☞አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ፣ እግዚአብሔር ፣ ሥሉስ ቅዱስ!
“ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ፥ በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ።” 【መዝ. ፳፪፥፳፪】
በጉባኤ መኃል ያልጠራነውን ስም ቢያንስ በተናጥል ስንገናኝ ፣ በግል የስልክ ጥሪዎችቻችንና በውሥጥ የጽሑፍ መልእክት እስክንሸማቀቅበት አልያም በቸልታና በልምድ ስንተወው መታየታችን ያሳዝናል።
የሚያሳፍረው ስሙን አለመጥራት እንጂ ለመክበር የከበረ ስሙን መጥራትስ አልነበረም!
"ስሙን አግኑት በምግባር በሃይማኖት ጸንታችሁ ለጌትነቱም ተገዙ … አሁንም በፍጹም ልቡናችሁ በፍጹም አንደበታችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑት ስሙንም ሁልጊዜ አመስግኑት"【ሲራ። ፴፱፥፲፭/፴፭】
ስለዚህ የተዋህዶ ልጆች ሁል ጊዜ ስሙን እንዲህ እያልን ማመስገን ይገባናል ፦
"ይክበር ይመስገን ሥሉስ ቅዱስ፣ እግዚአብሔር ይመስገን ፣ ክብር ምስጋና ለቅድስት ሥላሴ ፣ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የተመሰገነ ይሁን! "
እናስተውል የጣኦታትና የአጋንንትን ስም መጥራት እንደሚያረክሰው ሁሉ የአምላክን ስም መጥራትም ይቀድሳል።
"ዳግመኛም የአማልክትን የጣዖታትን ስም በአፋቸው አይጥሩ ፣ ፡ሰይጣንንና መላእክቱንም አይጥሯቸው ፣ ስሙንም በጠሩ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከእነርሱ ይለያልና ፣ በእርሱ ፈንታም መንፈስ ርኩስ በላያቸው ያድራል ።"
【መጽሐፈ ዲድስቅልያ ፳፯፥፬】

ክፍል 5
መሀመድ፡- ይገርማል አልሞት ባይ ተጋዳይ አትሁን ለእውነት ከመጣ ስለ እውነት መስክር ክርስቶስ በወንጌሉ አምላኬ ብሎ የጠራው ማንን ነው?? ፈጣሪውን?
ሳሙኤል፡- እሺ ጥሩ በመጀመሪያ አምላክ ማለት ምን ማለት ነው በሚለው እንወያይና ከእዛ ክርስቶስ አምላኬ ያለው በምን መንገድ እንደሆነ እንወያያለን
መሀመድ፡- አምላክ ማለት ፈጣሪ ነው ሌላ ምንም ትርጉም የለውም!
ሳሙኤል፡- መፅሀፍ ቅዱስ ግን ይህንን አይነግረንም አምላክ ማለት ፈጣሪ ብቻ አይደለም ፈጣሪያችንን "ጌታ" ስንል በባህሪ ሰዎችንም ደግሞ "ጌታ" ስንል በፀጋ እንደሆነው ሁሉ ፈጣሪያችንን አምላክ ስንልና ሰውን አምላክ ስንል ትርጉማቱ ይለያያል ለምሳሌ እግዚአብሔር ሙሴን በፈርኦን ላይ እንደ አምላክ አደርግሀለው ሲል በፀጋ የተሰጠው አምላክነት ነው!
መሀመድ፡- አምላክ በፀጋም አለ??? እሺ ቀጥል
ሳሙኤል፡- ስለዚህ ክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌሉ አምላኬ እያለ ሲጠራው የነበረው የባህርይ አባቱን ነው ይህም እያመለከው ሳይሆን በፀጋ ነው ክርስቶስ በስጋ ሲመላለስ ስጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ ስላለውም ይህንን ቃል ተናገረ
መሀመድ፡- ከምትለው አንዳችም አልገባኝም
ሳሙኤል፡- ምኑ ነው ያልገባህ እንዲህ አብራርቼው?
መሀመድ፡- ምን ተብራራ ልጅ ሳሙኤል የማይገናኝ ነገር ነው የምታወራው
ሳሙኤልም ተገረመ "ይህ ሰው አውቆ ነው እስካሁን እንዳልገባው እየመሰለ ያለው ወይንስ እውነት አልገባውም?" ብሎ በውስጡ እያሰበ እንዳለ የቅዱስ ጳውሎስ መልክት ወደ ልቦናው መጣለት «ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው» የሚለው ቃል ትዝ አለው።
ሳሙኤል መሀመድን ተረዳው የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት የማይወደው ከእግዚአብሔር ስላልሆነ መሆኑን አስተዋለ "በምን መንገድ እንዲገባው ላድርግ ግን የተናገርኩት ቃል የግድ በመንፈስ ሊተነተን የሚገባው ነገር አይደለም።
ቃሉ ግልፅ ነው መቀበል አለመቀበል የእርሱ ፋንታ ነው።" አለ
መሀመድ፡- ምነው ዝም አልክ መልስ የለም?
ሳሙኤል፡- መልሱንማ አብራርቼልሀለው መቀበል አለመቀበል የአንተው ፋንታ ነው
መሀመድ፡- እሺ መልሱን ለህሊና
መሀመድ ሁሌም በውይይት መሀል ይህችን ቃል ጣል ያደርጋታል ምክንያቱም ምንም እንኳ የሚወያዩት ሰዎች ልክ ቢሆኑም ይህንን ቃል ሲናገር እራሳቸውን እንዲጠራጠሩና እንዲፈሩ ስለሚያደርግ ነው። ግን ሳሙኤል የተናገረውን ጥርት አድርጎ ያቃልና መሀመድ ይህንን ቃል በተናገረ ሰአት ፈገግ አለ አስከትሎም
ሳሙኤል፡- አዎን መልሱን ለህሊና ህሊና ስለ እውነት ስለምትፈርድ እውነት በማን ዘንድ እንዳለች ትጠቁማለች።
መሀመድም ደነገጠ ምክንያቱም ከተወያያቸው ሰዎች በሙሉ ሳሙኤል ተለየበት መልስ እንደተመለሰለት እያወቀ ይህንን ሲናገር ሳሙኤል እንደሌሎች ሰዎች ግራ እንዳልተጋባና ራሱን እንዳልተጠራጠረ ሲመለከት ቀላል ሰው እንዳልሆነም ተረዳ።
መሀመድ፡- እሺ መልካም ልጅ ሳሙኤል የዛሬው ይበቃናል መሰለኝ በተመቸህ ሰአት እዚው ተገናኝተን እንወያያለን!
ሳሙኤል፡- ይብቃ? እሺ እንዳልከው ይሁን ከነገ ወዲያ እሁድ ስለሆነ በእዛን ቀን ተገናኝተን እንወያያለን
መሀመድ፡- እሺ ጥሩ ውይይት ነበረን አሁን ብንሄድ መልካም ይመስለኛል
ሳሙኤል፡- እሺ
አለና ከመቀመጫው ተነሳ ከመሀመድ ጋርም ወደ ቤቱ ሄዱ። እንደደረሱም
ፈዲላ፡- እንኳን ደህና መጣችሁ!
ሳሙኤል፡- እንኳን ደህና ቆየሽ
መሀመድ፡- እንኳን ደህና ቆየሽን ልጄ
ፈዲላ፡- ቁጭ በሉ ሻይ ላፍላላችሁ አለችና ወደ እቃ ቤት አመራች
መሀመድ፡- መልካም ልጄ አለና ቁጭ አለ
ሳሙኤል ግን ፈዲላን ሊቀርባት አልፈለገም ለሁለቱም ያለው አመለካከት ስለተቀየረ ፈጠን ብሎ ወደ ቢሮው ሄደና እዛ ቁጭ አለ
ፈዲላም ስትመለስ ሳሙኤል የለም ነበር ከእዚያም ለመሀመድ
ፈዲላ፡- ሳሙኤልስ?
መሀመድ፡- ወደ ቢሮው ገብቷል መሰለኝ
ፈዱላ፡- አስቀይመኸዋል አይደል አባ?
መሀመድ፡- ወይ ልጄ ምንድን ነው የምትይው? ስለ ሀይማኖት እንደምናወራ ታውቂያለሽ በቃ! ከእርሱ አልፌ የተናገርኩት ነገር የለም።
ፈዲላም፡- ይኸው አለቀልኝ ከአሁኑ ሳሙኤል እየሸሸኝ ነው ነግሬህ ነበር ስለ ሀይማኖት ማንሳት እንደሌለብህ ግን ብታስብልኝ ኖሮ ይህንን አታደርግም! ብላ ፍጥን ፍጥን እያለች ወደ ሳሙኤል ቢሮ ገባች እርሱም መፅሀፍ ቅዱስ እያነበበ ነበር።
ፈዲላ፡- ሳሚ ሻይ ፈልቷል ኮ
ሳሙኤል፡- .........
ፈዲላ፡- ሳሚ እያናገርኩህ ኮ ነው ሻዩ ፈልቷል!
ሳሙኤል፡- መፅሐፍ ቅዱስ ሲነበብ ዝም ብሎ ማቋረጥ ጥሩ አይደለም ስሜቴን አትረብሺው አሁን እያነበብኩኝ ነው
ፈዲላ፡- እሺ እዚህ ላምጣልህ?
ሳሙኤል፡- እሺ
ፈዲላም ልቧ ተሰበረ ዛሬ አትረብሺኝ ካለ ነገ ደግሞ ከቤት ያባርረኛል እያለች እያጉረመረመች ወደ ሳሎን ተመለሰች
ይቀጥላል........
@nubeberhanuenmelales

የክርስቶስ ሰላም ከእናንተ ጋር ይኹን የኦርቶዶክሳዊ ዓይን ቤተሰቦች🙏🏾
በቃላችን መሰረት ለጥያቄዎቻችሁ መልስ የተሰኘው መርሐ ግብራችን ከፊታችን እሑድ፣ ኅዳር ፰ ከምሽቱ ፲፪ ሰዓት ጀምሮ በነገረ ማርያም ዙርያ ለሚነሱ ወቅታዊ ጥያቄዎች @Orthodoxy_lense16 በሚለው የ Tiktok ድኅረ ገጻችን ላይ መመምህራነ ቤ/ክ በተገኙበት መልስ በመስጠት ይጀመራል።
በየትኛውም ርዕስ ላይ ያላችሁን ጥያቄ በእዚህ የ Telegram ገጽ @Orthodoxy_lense16 ላይ ያስቀምጡልን። ርዕሱን ጠብቆ ዘወትር እሑድ በሚኖረን መርኅ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ብሂል ፣ ምስጢር፣ ዘይቤ በጠነቀቀ መልክ የሚመለስ ይሆናል።
እንዲሁም የ YouTube ገጻችንን፣ youtube.com/@orthodox_lense16 Subscribe በማድረግ የሚተላለፉ ትምህርቶችን ይከታተሉ።
ለሌሎችም ማጋራት እንዳይረሱ።

ህግጋት
ኑ በብርሃኑ እንመላለስ
ዘጸአት 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔርም ይህን ቃል ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦
² ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ።
³ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።
⁴ በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።
⁵ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
⁶ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።
⁷ የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።
⁸ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።
⁹ ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፤
¹⁰ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፤
¹¹ እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም።
¹² አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።
¹³ አትግደል።
¹⁴ አታመንዝር።
¹⁵ አትስረቅ።
¹⁶ በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
¹⁷ የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።

#ማሜ_አያልቅበትም #ክፍል_5
ኑ የማሜን የጀነት ጉብኝት እንከታተለው 😂 ማሜ ጀነት ገብቶ አዳም ከነልጅ ልጆቹ በቀኝ በግራ የሲኦል ሰዎችን ጭሞር አይቷል 😂
እስኪ ኑ ማሜ እና ጅብሪል ጋር ወደ ጀነት እንግባ
Hadith
"حَدَّثَنَا يَحْيَى بْنُ بُكَيْرٍ، قَالَ حَدَّثَنَا اللَّيْثُ، عَنْ يُونُسَ، عَنِ ابْنِ شِهَابٍ، عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ كَانَ أَبُو ذَرٍّ يُحَدِّثُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ " فُرِجَ عَنْ سَقْفِ بَيْتِي وَأَنَا بِمَكَّةَ، فَنَزَلَ جِبْرِيلُ فَفَرَجَ صَدْرِي، ثُمَّ غَسَلَهُ بِمَاءِ زَمْزَمَ، ثُمَّ جَاءَ بِطَسْتٍ مِنْ ذَهَبٍ مُمْتَلِئٍ حِكْمَةً وَإِيمَانًا، فَأَفْرَغَهُ فِي صَدْرِي ثُمَّ أَطْبَقَهُ، ثُمَّ أَخَذَ بِيَدِي فَعَرَجَ بِي إِلَى السَّمَاءِ الدُّنْيَا، فَلَمَّا جِئْتُ إِلَى السَّمَاءِ الدُّنْيَا قَالَ جِبْرِيلُ لِخَازِنِ السَّمَاءِ افْتَحْ. قَالَ مَنْ هَذَا قَالَ هَذَا جِبْرِيلُ. قَالَ هَلْ مَعَكَ أَحَدٌ قَالَ نَعَمْ مَعِي مُحَمَّدٌ صلى الله عليه وسلم. فَقَالَ أُرْسِلَ إِلَيْهِ قَالَ نَعَمْ. فَلَمَّا فَتَحَ عَلَوْنَا السَّمَاءَ الدُّنْيَا، فَإِذَا رَجُلٌ قَاعِدٌ عَلَى يَمِينِهِ أَسْوِدَةٌ وَعَلَى يَسَارِهِ أَسْوِدَةٌ، إِذَا نَظَرَ قِبَلَ يَمِينِهِ ضَحِكَ، وَإِذَا نَظَرَ قِبَلَ يَسَارِهِ بَكَى، فَقَالَ مَرْحَبًا بِالنَّبِيِّ الصَّالِحِ وَالاِبْنِ الصَّالِحِ. قُلْتُ لِجِبْرِيلَ مَنْ هَذَا قَالَ هَذَا آدَمُ. وَهَذِهِ الأَسْوِدَةُ عَنْ يَمِينِهِ وَشِمَالِهِ نَسَمُ بَنِيهِ، فَأَهْلُ الْيَمِينِ مِنْهُمْ أَهْلُ الْجَنَّةِ، وَالأَسْوِدَةُ الَّتِي عَنْ شِمَالِهِ أَهْلُ النَّارِ، فَإِذَا نَظَرَ عَنْ يَمِينِهِ ضَحِكَ، وَإِذَا نَظَرَ قِبَلَ شِمَالِهِ بَكَى، حَتَّى عَرَجَ بِي إِلَى السَّمَاءِ الثَّانِيَةِ فَقَالَ لِخَازِنِهَا افْتَحْ. فَقَالَ لَهُ خَازِنُهَا مِثْلَ مَا قَالَ الأَوَّلُ فَفَتَحَ ". قَالَ أَنَسٌ فَذَكَرَ أَنَّهُ وَجَدَ فِي السَّمَوَاتِ آدَمَ وَإِدْرِيسَ وَمُوسَى وَعِيسَى وَإِبْرَاهِيمَ ـ صَلَوَاتُ اللَّهِ عَلَيْهِمْ ـ وَلَمْ يُثْبِتْ كَيْفَ مَنَازِلُهُمْ، غَيْرَ أَنَّهُ ذَكَرَ أَنَّهُ وَجَدَ آدَمَ فِي السَّمَاءِ الدُّنْيَا، وَإِبْرَاهِيمَ فِي السَّمَاءِ السَّادِسَةِ. قَالَ أَنَسٌ فَلَمَّا مَرَّ جِبْرِيلُ بِالنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم بِإِدْرِيسَ قَالَ مَرْحَبًا بِالنَّبِيِّ الصَّالِحِ وَالأَخِ الصَّالِحِ. فَقُلْتُ مَنْ هَذَا قَالَ هَذَا إِدْرِيسُ. ثُمَّ مَرَرْتُ بِمُوسَى فَقَالَ مَرْحَبًا بِالنَّبِيِّ الصَّالِحِ وَالأَخِ الصَّالِحِ. قُلْتُ مَنْ هَذَا قَالَ هَذَا مُوسَى. ثُمَّ مَرَرْتُ بِعِيسَى فَقَالَ مَرْحَبًا بِالأَخِ الصَّالِحِ وَالنَّبِيِّ الصَّالِحِ. قُلْتُ مَنْ هَذَا قَالَ هَذَا عِيسَى. ثُمَّ مَرَرْتُ بِإِبْرَاهِيمَ فَقَالَ مَرْحَبًا بِالنَّبِيِّ الصَّالِحِ وَالاِبْنِ الصَّالِحِ. قُلْتُ مَنْ هَذَا قَالَ هَذَا إِبْرَاهِيمُ صلى الله عليه وسلم ". قَالَ ابْنُ شِهَابٍ فَأَخْبَرَنِي ابْنُ حَزْمٍ أَنَّ ابْنَ عَبَّاسٍ وَأَبَا حَبَّةَ الأَنْصَارِيَّ كَانَا يَقُولاَنِ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم " ثُمَّ عُرِجَ بِي حَتَّى ظَهَرْتُ لِمُسْتَوًى أَسْمَعُ فِيهِ صَرِيفَ الأَقْلاَمِ ". قَالَ ابْنُ حَزْمٍ وَأَنَسُ بْنُ مَالِكٍ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم " فَفَرَضَ اللَّهُ عَلَى أُمَّتِي خَمْسِينَ صَلاَةً، فَرَجَعْتُ بِذَلِكَ حَتَّى مَرَرْتُ عَلَى مُوسَى فَقَالَ مَا فَرَضَ اللَّهُ لَكَ عَلَى أُمَّتِكَ قُلْتُ فَرَضَ خَمْسِينَ صَلاَةً. قَالَ فَارْجِعْ إِلَى رَبِّكَ، فَإِنَّ أُمَّتَكَ لاَ تُطِيقُ ذَلِكَ. فَرَاجَعْتُ فَوَضَعَ شَطْرَهَا، فَرَجَعْتُ إِلَى مُوسَى قُلْتُ وَضَعَ شَطْرَهَا. فَقَالَ رَاجِعْ رَبَّكَ، فَإِنَّ أُمَّتَكَ لاَ تُطِيقُ، فَرَاجَعْتُ فَوَضَعَ شَطْرَهَا، فَرَجَعْتُ إِلَيْهِ فَقَالَ ارْجِعْ إِلَى رَبِّكَ، فَإِنَّ أُمَّتَكَ لاَ تُطِيقُ ذَلِكَ، فَرَاجَعْتُهُ. فَقَالَ هِيَ خَمْسٌ وَهْىَ خَمْسُونَ، لاَ يُبَدَّلُ الْقَوْلُ لَدَىَّ. فَرَجَعْتُ إِلَى مُوسَى فَقَالَ رَاجِعْ رَبَّكَ. فَقُلْتُ اسْتَحْيَيْتُ مِنْ رَبِّي. ثُمَّ انْطَلَقَ بِي حَتَّى انْتَهَى بِي إِلَى سِدْرَةِ الْمُنْتَهَى، وَغَشِيَهَا أَلْوَانٌ لاَ أَدْرِي مَا هِيَ، ثُمَّ أُدْخِلْتُ الْجَنَّةَ، فَإِذَا فِيهَا حَبَايِلُ اللُّؤْلُؤِ، وَإِذَا تُرَابُهَا الْمِسْكُ "."
Narrated Abu Dhar:
Allah's Messenger (ﷺ) said, "While I was at Mecca the roof of my house was opened and Gabriel descended, opened my chest, and washed it with Zamzam water. Then he brought a golden tray full of wisdom and faith and having poured its contents into my chest, he closed it.

Then he took my hand and ascended with me to the nearest heaven, when I reached the nearest heaven, Gabriel said to the gatekeeper of the heaven, 'Open (the gate).' The gatekeeper asked, 'Who is it?' Gabriel answered: 'Gabriel.' He asked, 'Is there anyone with you?' Gabriel replied, 'Yes, Muhammad I is with me.' He asked, 'Has he been called?' Gabriel said, 'Yes.' So the gate was opened and we went over the nearest heaven and there we saw a man sitting with some people on his right and some on his left. When he looked towards his right, he laughed and when he looked toward his left he wept. Then he said, 'Welcome! O pious Prophet (ﷺ) and pious son.' I asked Gabriel, 'Who is he?' He replied, 'He is Adam and the people on his right and left are the souls of his offspring. Those on his right are the people of Paradise and those on his left are the people of Hell and when he looks towards his right he laughs and when he looks towards his left he weeps.' Then he ascended with me till he reached the second heaven and he (Gabriel) said to its gatekeeper, 'Open (the gate).' The gatekeeper said to him the same as the gatekeeper of the first heaven had said and he opened the gate. Anas said: "Abu Dhar added that the Prophet (ﷺ) met Adam, Idris, Moses, Jesus and Abraham, he (Abu Dhar) did not mention on which heaven they were but he mentioned that he (the Prophet (ﷺ) ) met Adam on the nearest heaven and Abraham on the sixth heaven. Anas said, "When Gabriel along with the Prophet (ﷺ) passed by Idris, the latter said, 'Welcome! O pious Prophet (ﷺ) and pious brother.' The Prophet (ﷺ) asked, 'Who is he?' Gabriel replied, 'He is Idris." The Prophet (ﷺ) added, "I passed by Moses and he said, 'Welcome! O pious Prophet (ﷺ) and pious brother.' I asked Gabriel, 'Who is he?' Gabriel replied, 'He is Moses.' Then I passed by Jesus and he said, 'Welcome! O pious brother and pious Prophet.' I asked, 'Who is he?' Gabriel replied, 'He is Jesus. Then I passed by Abraham and he said, 'Welcome! O pious Prophet (ﷺ) and pious son.' I asked Gabriel, 'Who is he?' Gabriel replied, 'He is Abraham. The Prophet (ﷺ) added, 'Then Gabriel ascended with me to a place where I heard the creaking of the pens." Ibn Hazm and Anas bin Malik said: The Prophet (ﷺ) said, "Then Allah enjoined fifty prayers on my followers when I returned with this order of Allah, I passed by Moses who asked me, 'What has Allah enjoined on your followers?' I replied, 'He has enjoined fifty prayers on them.' Moses said, 'Go back to your Lord (and appeal for reduction) for your followers will not be able to bear it.' (So I went back to Allah and requested for reduction) and He reduced it to half. When I passed by Moses again and informed him about it, he said, 'Go back to your Lord as your followers will not be able to bear it.' So I returned to Allah and requested for further reduction and half of it was reduced. I again passed by Moses and he said to me: 'Return to your Lord, for your followers will not be able to bear it. So I returned to Allah and He said, 'These are five prayers and they are all (equal to) fifty (in reward) for My Word does not change.' I returned to Moses and he told me to go back once again. I replied, 'Now I feel shy of asking my Lord again.' Then Gabriel took me till we '' reached Sidrat-il-Muntaha (Lote tree of; the utmost boundary) which was shrouded in colors, indescribable. Then I was admitted into Paradise where I found small (tents or) walls (made) of pearls and its earth was of musk."
Sahih
Sahih al-Bukhari, 349
In-Book Reference: Book 8, Hadith 1
USC-MSA web (English) reference: Vol. 1, Book 8, Hadith 345 (deprecated numbering scheme)

ክፍል 6
መሀመድም ሁኔታዋን ተመልክቶ
መሀመድ፡- ምነው ልጄ ምን ብሎሽ ነው
ፈዲላ፡- አየህ ነግሬህ ነበርኮ
መሀመድ፡- ምን አለሽ
ፈዲላ፡- አትረብሺኝ የኔ ድምፅና ንግግሬ ረበሸው።
መሀመድ፡- ከሚሰራው ስራ ጋር ንግግር አይመቸው ይሆናላ በሌላ መንገድ አትውሰጂበት
ፈዲላ፡- ነው ብለህ ነው
መሀመድ፡- አዎን ልጄ!
ፈዲላ፡- እሺ እንዳልከው ይሁን
መሀመድ፡- አሁን ወደ ቤት መሄድ አለብኝ የሶላቱም ሰአት እየደረሰ ነው
ፈዲላ፡- እሺ ጥሩ አባ በቃ ተጣጠብና ቀለልም ይበልህ
መሀመድ፡- እሺ ልጄ
አላትና ከመቀመጫው ተነስቶ ሻወር ቤት ገባ እርሷም ሻይ የጠጡበትን ስኒ አነሳሳችና ጠረቤዛው ወልውላ ቁጭ ብላ ቲቪ መመልከት ጀመረች። ቲቪውን እያየች ሀሳብ ጭልጥ አድርጎ ወሰዳት።
የምታስበው ስለ ሳሙኤል ነበር "ሳሙኤል አሁን ስለኛ ምን እያሰበ ነው? መቼስ ጥሎን ለመሄድ እያሰበ እንዳልሆነ አስባለሁ! ግን ጥሎን ከሄደ ምን ላደርግ ነው?"
ይህንን ሁሉ እያሰበች በዛው ጋደም እንዳለችው እንቅልፍ ወሰዳት። ሳሙኤልም መፅሀፉን በእግዚአብሔር መንፈስ በመታገስ ማንበቡን ቀጠለ። መሐመድም አብረው እንዲሰግዱ ሊጠራት ሲሄድ ተኝታ ነበር።
መሀመድ፡- ልጄ ተነሺ ወደ ቤት ልሄድ ነው ቻው በይኝ
ፈዲላ፡- ..............
መሀመድ፡- ስሚኝ እንጂ ልጄ በቃ ሄድኩ
አላትና ከእንቅልፏ ሳትነቃ ጥሏት ሄደ። ሳሙኤልም ብዙ ካነበበ ብርኋላ ወደ ሳሎን ቡና ልመጠጣት መጣ ፈዲላም ተኝታ ተመለከታት አሳዘነችውና ትራስና ብርድ ልብስ ከመኝታ ቤት አምጥቶ አለበሳት። ቡናውንም አፍልቶ ጠጣና ወደ ቢሮው ዳግመኛ ተመለሰ
ፈዲላም ከ2፡00 ብኋላ ከተኛችበት ነቃች ቤቱ ጭር ብሏል ትራስ ላይ ተደግፋም ብርድ ልብስ ለብሳለች። "ማን ነው ያለበሰኝ ሳሚ ታረቀኝ ማለት ነው።" አለችና ከሶፋው ላይ ዘላ ወደ ሳሚ ቢሮ ሄደች
ስትገባም መፅሀፍ ቅዱስን አሁንም እያነበበ ነበር። አየችውና "በድጋሚ እንዳልረብሸው" ብላ ተመልሳ ወጣች ሳሙኤልም ሁኔታዋን ሲመለከት በድጋሚ አሳዘነችውና ፀልዮ መፅሀፍ ቅዱሱን ዘጋውና
ሳሙኤል፡- ውዴ?
ፈዲላ፡- አቤት ውዴ ጠራኸኝ
እያለች ወደ ቢሮው በድንጋጤ ተመለሰች ። ሳሙኤልም በሁኔታዋ ተገረመ ምንም እንኳ በሀይማኖቷ ሊቀርባት ባይወድም ያነበበው መፅሀፍ ቅዱስ ባይፈቅድለትም ከሷ ፍቅር ግን መደበቅ አልቻለም ነበር።
ሳሙኤል፡- እራት አዘጋጂና በልተን እንተኛ?
ፈዲላ፡- እሺ አሁን አቀርባለሁ
አለችና ወዲያው ወደ እቃ ቤት ሄዳ ሽንኩርት መክተፍ ጀመረች ሳሙኤልም ቢሮውን አስተካከለና ሻወር ቤት ገባ። በጨረሰችም ሰአት ሳሙኤልን ጠርታው እራታቸውን በሉና ትንሽ ፊልም አይተው ወዲያው ተኙ።
ሶስተኛ ቀን
ፈዲላም ከሳሙኤል ቀድማ ተነሳችና ይወደዋል ብላ የምታስበውን ቁርስ በያይነት ሰራችለት። እንደጨረሰችም ወደ መኝታ ቤት ሄዳ
ፈዲላ፡- ሳሚ ሳሚ ተነሳ
ሳሙኤል፡- እሺ እሺ እነሳለሁ አለና ወዲያው ከእንቅልፉ ተነስቶ መነቃቃት ጀመረ
ከፈዲላ ጋርም ቁርሱን ከበላ በኋላ ወደ ስራ ሄደ ፈዲላም በአኳሗኑ ደስ ተሰኝታ ነበር። ሳሙኤል ግን ውስጡ እየከለከለው ቢሆንም ግን ልቡ አሸነፈው እሷን መራቅ እንዳለበት እያወቀ ግን እሷ ላይ መጨከን አልቻለም ነበር።
በስራም ተጠምዶ ከኑን ሙሉ ዋለ ፈዲላም ቀኑን መፅሀፍ ቅዱስን ስታነብ ነበር ያሳለፈችው። የክርስቶስን ትምህርቶች እጅጉን ከመውደዷ የተነሳ ሁሌ የሉቃስን ወንጌል ደጋግማ ታነብ ነበር ።
ከስራ እንደተመለሰም ፈዲላ በፍቅር ተቀበለችው የሚወደውን እራት ሰጠችውና አብረው በልተው ተኙ
አራተኛ ቀን
ሳሙኤል በጠዋቱ ማልዶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደ ቀኑ ሰንበት ነውና በመንፈስም የዝማሬ ስግደት መእዋት አቅርቦ ጉባኤው እስኪያልቅ ድረስ ቁጭ ብሎ ተማረ።
እንዳለቀም አንዱን የቤተ ክርስቲያን ካህን ሊያንውጋግር ወዶ ነበርና ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ቀረበ። ካህኑም አሳልሞ እስኪጨርስ ድረስ ጠበቀ ሲጨርስ ሳሙኤልም ተሳለመ የካህኑም ስም “መንግስተ አብ” ነበር
ሳሙኤል፡- አባ ስለ አንድ ጉዳይ ላነጋግሮት ነበር
መንግስተ አብ፡- መልካም ልጄ ስለምንድን ነበር ልታናግረኝ የፈለግኸው?
ሳሙኤል፡- ንሰሀ መግባት እፈልጋለሁ
መንግስተ አብ፡- እሺ ጥሩ ልጄ ወደ ማታ 11 ሰአት ላት ናና የሰራኸውን ሁሉ ትነግረኛለህ ተባረክ
ብለውት መስቀሉን ጭንቅላቱን አስነክተው ሄዱ። ሳሙኤልም ደስ አለው ግን በደስታ ውስጥ የፈዲላ ነገር ትዝ አለውና መልሶ አዘነ። በሁለት ስሜት ሆኖ ወደ ቤቱ ሄደ በመንገድ ላይም ሳለ የሴት ልጅ ጩኸት ሰማ። ምንድን ነው ብሎ ለማጣራትም ሲሞክር ፊት ለፊት ካለው ቤት ይህ ድምፅ እንደሚመጣ አወቀ።
በጣም ደነገጠና ዘሎ ግቢውስጥ ገባ። ወደ ቤቱም ዘለቅ እንዳለ አንዲት ሴት በሰው ስትደበደብ ተመለከተ ልጅቷም(መቅደስ) "አድነኝ አድነኝ አባት ሊገለኝ ነው እባክህ አድነኝ" ትላለች ይህንንም ባለች ቁጥር ልጁ(አቤል) "ዝም በይ እያለ መምታቱን እጥፍ ይጨምራል።
ሳሙኤል፡- ተዉ እንጂ እባካችሁ ችግራችሁን በውይይት ፍቱት
አቤል፡- ይህች ሁሉም በዱላ ካልሆነ አይገባትም..... ዝም በይ
ሳሙኤል፡- እባክህን ወንድም ስለ ወንድ ልጅ አምላክ አቁም
ሲል አቤል ንዴቱን ሳይጨርስ መቅደስን መምታት አቆመ
ሳሙኤል፡- እሺ አሁን ምን ሆናችሁ እንደሆነ ንገሩኝ
መቅደስ፡- አቤል ባለቤቴ ነው ሁልጊዜ የምንጣላበት ምክንያት አንድ ነው ሁሌም ይጠጣል ለሚጣ ራሱ እስራስ መግዣ ብር የለንም ይህንን አቁም ስለው ለምን ተናገርሽኝ ብሎ ሁሌም ይቀጠቅጠኛል።
አቤል፡- አንቺ ውሸታም ዝም አትይም??
አለና ሊመታት ከመቀመጫው ተነሳ
ሳሙኤል፡- ተው ወንድሜ ተቀመጥ ለምንድን እንደምትመታት ከአንተ እንስማ
አቤል፡- እየውልህ ወንድሜ የኔ ስራ በጣም ከባድ ነው የቀን ሰራተኛ ነኝ በጣም ይደክመኛል ደክሞኝ ስመጣ ምግብ ነው ወይስ ጭቅጭቅ ሊቀርብልኝ የሚገባው??
ሳሙኤል፡- ሁለታችሁንም እንዲህ ናችሁ ብዬ እኔ አይደለሁም ላስማማችሁም ላጣላችሁም የምችለው ስሜታችሁን አረጋግታችሁ በጠረቤዛ ዙሪያ ቁጭ ብላችሁ የሚያጣላችሁን ነገር ተነጋገሩ
መቅደስ፡- በአንተ ሀሳብ በጣም እስማማለሁ ግን እሱ ትእግስት የለውም እንደወጣህ ድብደባውን ይጀምረዋል
አቤል፡- ባልከው ነገር ብስማማ እንኳ እግርህ እንደወጣ ነው ጭቅጭቁ የሚጀምረኝ ታዲያ በእዚህ ሁኔታ እንዴት ልንግባባ ነው
ሳሙኤል፡- ሁለታችሁም ተረጋጉ እንጂ በመልካም መንፈስ ሁኑ ሁለታችሁም ችግራችሁን ተወያዩና ለመፍታት ሞክሩ እንዲህ ሲሆን እዚህ ቤት እጅጉን ሰላም ይበዛል
አቤል፡- እሺ እሱ ጥሩ ይመስለኛል
መቅደስ፡- ጥሩ ብለሀል አባት አናመሰግናለን ገመናችን ወደ ውጪ እንዳይወጣ
ሳሙኤል፡- ይህ ሁሉም ቤት ያለ ነገር ነው በሉ ደህና ዋሉ
አቤል፡- ስምህ ማነው?
ሳሙኤልም፡- ሳሙኤል እባላለሁ
አቤል፡- እኔ ደግሞ አቤል እባላለሁ እንተዋወቅ መልካም ሰው ነህ።
አለውና እጁን ዘረጋለት መቅደስም እንዲሁ መተዋወቅ ፈልጋ ነበርና እሷም ዘረጋችለት።
ሳሙኤል፡- ስለተዋወቅኳችሁ ደስ ብሎኛል በሉ ደህና ዋሉ
አቤል፡- እሺ ወንድም ደህና ዋል
መቅደስ፡- እሺ አባት ደህና ዋል
ካሉት በኋላ እንዳላቸው ሁለቱም ቁጭ አሉ። እየተፋጠጡም ጀምር ምንድነው ችግሩ ጀምሪ ምንድነው ችግሩ ይባባሉ ነበር።
ይቀጥላል.........
https://www.tg-me.com/nubeberhanuenmelales

Telegram
ኑ በብርሃኑ እንመላለስ
እንኳን በሰላም መጣችሁ
በዚህ
☞የእምዬ የተዋህዶን አስተምህሮ(ነገረ ክርስቶስ ፣ ክብረ ድንግል ማርያም ፣ ምክረ ቅዱሣን አበው ወእመው ታሪክ እና ተግሣፅ፣ መዝሙር
☞የመሀመዳውያንን ቁርዓን እና ሐዲስ ጉዶች
☞የሉተራውያን እና መሰል ድርጅቶች ጥያቄ መልስ
☞ የእናንተ ጥያቄ መልሶችም ይቀርባሉ