Telegram Web Link
አባታችን ብፁእ አቡነ መቃሪዮስ በሰንበት ትምህርት ቤታችን በመገኘት ለህፃናትን ባርከዋል
ላይቭ ነን
ዛሬ ማታ 3:00 በቲክቶክ አርሻችን እንዘልቃለን

ርዕሳችን :- መሐመድ ነቢይ ነው ወይ ? የሚል ነው ።
ጥልዙ ፖሰሰተር ትዝታው ገና ከመግባቱ ክስ ተከሰሰ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሕግ አገልግሎት መምሪያ በአቶ ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ መሰረተ።

የቤተክርስቲያናችን ሕግ አገልግሎት መምሪያ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባቀረበው ክስ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ የምርመራ መዝገቡ መብቱ ለሚፈቅድለት የዐ/ሕግ ዘርፍ እንዲተላለፍለፍ ጠይቋል።

በወንጀል ተጠርጣሪ /ተከሳሽ - አቶ ትዝታው ሳሙኤል
ተጠርጣሪ /ተከሳሹ ነዋሪነቱን በውጪ ሃገር በማድረግ የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ ውሳኔ ሰጪ አካልን ለማዋረድ፣
ለመስደብ እና የምዕመኑን ስሜት ለመንካት ብሎም በሀገሪቱ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በማሰብ በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶች እና ከ5000 በላይ ተከታዮች ባሉት የራሱ የዪቲዩብ ቻናል በመጠቀም ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

በማያያዝም ግለሰቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶችን፣ በየገዳማቱ ውስጥ የሚገኙ ገዳማውያን መነኮሳትና አገልጋዮችን <<ግብረ ሰዶማውያን ናቸው>> በማለት፣እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን <<የመተት እና ጠንቋይ ቤት ናት >>በማለት፣ሲቀሰቅስ የቆየ መሆኑን የገለጸው መምሪያው ግለሰቡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምትገለገልባቸውን ሃይማኖታዊ የፀሎት፣የታሪክ ፣የገድላትና ድርሳናት መጻሕፍትን <<ድውያን መጽሐፍት ናቸው መጥፋት አለባቸው>>ማለቱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቅድስናየምታ
ከብራቸውንና የምትዘክራቸውን ቅዱሳን አባቶች እና እናቶችን << ጣኦታትና ጣኦት አምላኪ>> ናቸው በማለት ግለሰቡ የፈጸመውን የወንጀል አድራጎት በመጥቀስም ክስ መስርቶበታል።

መምሪያው በአጠቃላይ ሰባት ነጥቦችን ያካተቱ የወንጀል ዝርዘርሮችን በመግለጽም ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል ቀርቦ ግለሰቡ በሕግ ተጠያቂ እንዲደረግ ባቀረበው አቤቱታ ገልጿል።
2025/07/05 09:49:30
Back to Top
HTML Embed Code: