Telegram Web Link
"ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።"
ዕንባቆም 3 ፥17- 19
🎈"አምላከ ሰማይ ይረድአነ ወንሕነ አግብርቲሁ ንትነሣእ ወነሐንጽ ሎቱ የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን" መጽሐፈ ነህምያ ፪÷፳

ለቅዱስ አማኑኤል ልጆች
በመጠናቀቅ ላይ ላለው ለደሴ ደብረ ሣህል ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ግንባታ የጣራ ከንች ብረት ያስፈልጋልና በቅዱስ አማኑኤል ስም የተቻላችሁን ድጋፍ አድርጉ።

1000267053239
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዐራት ኪሎ ቅርንጫፍ
BEDESSIE D/S/K/AMANUEL & K/RAG CHURCH
#ዘመቻ_ደሴ_አማኑኤል
ኑ በጅማሮ ላይ ያለውን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን እንሥራ
#የፍቅር_ሥራ_ይህች_ናት

ባልንጀራውን የሚረዳውን ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ይረዳዋል፡፡ ለወንድሙ የሚነቀፍበትን ስም የሚያወጣውን ፈታሒ በርትዕ እግዚአብሔር እንዲሰደብ ያደርገዋል፡፡ ክፉ ስለ ሠራ ወንድሙን በቤቱ ለብቻው ሆኖ የሚመክረው ሰው ግን በምክሩ ዐዋቂ ይሆናል፡፡ ወንድሙን በዐደባባይ የነቀፈ ግን ኀዘን ያጸናበታል፡፡ ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ብዛት ያስረዳል፤ በባልንጀሮቹ ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል፣ የምቀኝነቱን ጽናት አስረዳ፡፡ 

ወዳጁን ተሠውሮ የሚመክር ሰው ብልህ ባለመድኃኒት ነው:: ያ እንዳዳነው መክሮ አስተምሮ ያድነዋልና፡፡ ወንድሙን በብዙ ሰው ፊት የሚያመሰግነው ሰው እሱ እውነተኛ ጠላቱ ነው፣ በውዳሴ ከንቱ ይጎዳ ብሎ ነውና።

ኀዘን ያለበት የርሕራሄ ምልክቱ የበደሉትን ሁሉ ይቅር ማለት ነው። የጠማማ ምልክቱ ጸብ ክርክር ነው፡፡ ወደ ክብር የሚያደርስ ረብህ ጥቅም ያግኝ ብሎ የሚመክር፣ የሚያስተምር በፍቅር ይመክረዋል፣ ያስተምረዋል፡፡ ቂም በቀል የሚሻ ሰው ፍቅር የለውም፡፡ አንድም እበቀለዋለሁ ብሎ የሚመክር ከፍቅር የተለየ ነው፡፡

ስሙ ይክበርና እግዚአብሔር በፍቅር ይመክራል፣ ያስተምራል፣ እበቀላለሁ ብሎ ያይደል፡፡ እሱስ በምሳሌው የተፈጠረው ሰውን ለማዳን ይገሥጻል፡፡ አንድ ጊዜስ እንኳን ቂም አይዝም፣ መዓትን አያዘጋጅም፡፡ የፍቅር ሥራ ይህች ናት፣ በቅንነት ትገኛለች፡፡ ቂም ለመያዝ እበቀላለሁ አትልም፣ በፍቅር ሰውን መናገር ነው።

ብልህ የሚሆን ቅን ሰው ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ይመስለዋል፡፡ ሰውን ክፉ ስላደረገ እበቀለዋለሁ ብሎ አይገሥጸውም፣ ሊመክረው ወዶ ነው እንጂ ሌሎችንም ለማስፈራት ነው እንጂ። ተግሣጽስ በፍቅር ካልሆነ ተግሣጽ አይባልም፡፡ በጎ ነገር ያደርግልኛል ብሎ በጎ የሚሠራ ኋላ ፈጥኖ ይተዋል፡፡

(
#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ - በዲ/ን ሞገስ)
"ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ....."

(አባ ሕርያቆስ - ቅዳሴ ማርያም)
"የማርን ጥፍጥና ማርን ቀምሶ ለማያውቅ ሰው በመቅመስ እንጂ በቃላት ማስተማር እንደማይቻል ሁሉ የእግዚአብሔርን መልካምነት በቃላት በጠራ መልኩ ማስተማር አይቻልም። ራሣችን ወደ እግዚአብሔር መልካምነት ዘልቀን መግባት ይኖርብናል እንጂ።"

ቅዱስ ባስልዮስ ታላቁ
#የትሩፋት_ሥራ_ጀምር

ጨክነህ ቆርጠህ የትሩፋትን ሥራ ጀምር፡፡ በትሩፋት አጠገብ እየተጠራጠርህ አትኑር፡፡ ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ከማመን ተስፋ ወጥተህ በልብህ እንኳ አትጠራጠር፡፡ ትሩፋትህ ረብህ ጥቅም የሌለው እንዳይሆን የትሩፋት ሥራ ክቡድ አይምሰልህ፡፡ መሐሪ እግዚአብሔር ለለመኑት ሰዎች ጸጋውን ፈጽሞ እንዲሰጣቸው እመን እንጂ ስጦታው እንደየሥራችን አይደለም፡፡ በትጋታችን፣ በማመናችንና በመሻታችን መጠን ነው እንጂ እንደ ሃይማኖትህ ይደረግልህ ብሏልና፡፡

የትሩፋት ሥራም ይህች ናት፣ አንዱ መተምተሚያ አዘጋጅቶ መሐል ራሱን ይተመትመዋል፡፡ በየጊዜው በሚጸልየው ጸሎት እንዳያፍር ትቀርበኛለች ብሎ ያዝናል፡፡ አንዱ አብዝቶ ይሰግዳል፣ ልጸልይ ያለውን ይጸልያል፣ ስለ ጸሎቱ ፈንታ ብዙ ያለቅሳል፣ በልቅሶው ረብህ ጥቅም ያገኝበታል፡፡ አንዱ የልቡና ሥራ የምትሆን ትሩፋትን በመዘከር ይጋደላል፣ ወደ ተወሰነለት ጸጋ ይደርሳል፣ አንዱ ምግብ ነስቶ ሰውነቱን በረኃብ ያስጨንቃታል ጸሎቱን መፈጸም የማይቻለው እስኪሆን ድረስ፣ አንዱ ተናዶ እየመላለሰ ዳዊት ይጸልያል። በመድገም ዘወትር ጸሎትን ገንዘብ ያደርጋታል፣ አንዱ መጽሐፍ ለመመልከት፣ ለመድገም ጽሙድ ሆኖ ይኖራል፣ አንዱ ከአምላክ በተገኙ መጻሕፍት ያለውን ትርጓሜ ምሥጢር ያስበዋል፣ ያስተውለዋል፣ ይመረምረዋል። ወደ ሥራው ይሳባል፤ አንዱ የዐቢይ ምዕራፉን መለያ አይቶ ምሥጢሩን ያደንቃል፣ ዝምታ ይሰለጥንበታል፡፡ በልማድ መጽሐፍ ከመመልከት በልማድ ከመድገም ይከለከላል፡፡

አንዱ ደግሞ ሁሉንም አንድ አድርጎ ይሠራቸዋል፡፡ በዚህም ይሰለቻል፡፡ ዓለማዊ ሥራ ይሠራል፣ ለሐኬት ጽሙድ ሆኖ ይኖራል። አንዱ መጽሐፍ ከመመልከት ጥቂት ምሥጢር ያገኛል፡፡ በዚህም ትዕቢት ያድርበታል፡፡ በሰው መዘበት ያድርበታል፤ ይበድላል፡፡ አንዱ የልማድ ምክንያት ይሰለጥንበታል፣ አንዱም ይህን ሁሉ ድል ይነሣል፤ ከዚህ ሁሉ ይጠበቃል፡፡ ዕንቁ ክርስቶስን ገንዘብ እስኪያደርገው ወደኋላ አይመለስም፡፡ ደስ ብሎህ እግዚአብሔር ያዘዘውን የትሩፋት ሥራ ጀምር፡፡

#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ
"ኃጢአት ሲሠራ ባየኸው ወንድም ላይ አትፍረድ፥ አንተ ግልጽ የወጣ ኃጢአቱን እንጅ በስውር ለካህን የሚነግረውን ንስሐ አታውቅምና። ስለዚህ የራስህን ድካም ተመልከት።"

#ታላቁ_ቅዱስ_ባስልዮስ
"ብርሃን ወደ አንድ ቤት ውስጥ ሲገባ ጨለማን እንደሚያስወግድ ሁሉ፤ እግዚአብሔርን መፍራት ወደ አንድ ሰው ልብ ሲገባም አለማወቅን (በኃጢአት የሚወድቅባትን) ያስወግዳል።"

#አባ_እንጦንስ
እጅግ የተወደደና የተከበረው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ

“ወዳጄ ሆይ ወንድምህ ከአንተ ይልቅ አስተዋይና አዋቂ ብርቱም ቢሆን በዚህ ቅር አይበልህ ከዚህ ይልቅ እግዚአብሔርን አመስግን

ከወንድምህ አስተዋይነትና ብርታት ትጠቀማለህና በዚህ ሳታቆም ራስህን ስጦታየ ምንድነው?ወንድሜን እህቴን በምን ልጥቀም ?ብለህ ጠይቅ

ይህን ጥያቄ በትክክል ስትመልስ እንደመለስከው ምላሽም ስትተገብር በአንድ መልኩ በሚበልጥህ ሰው ቅር መሰኘትህን በሌላ መልኩ ደግሞ የምትበልጠውን ወንድምህን መናቅህን ታቆማለህ”
🌼እንኳን በሰላም መጣችሁ እህት ወንድሞችን 🌼
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዙሪያ ላላችሁ ጥያቄ መልስ የምታገኙበት እናንተም የምትጠየቁበት ማህበር ነው ።
👉በተጨማሪም ተከታታይ ትምህርቶች
👉ውይይቶች ይኖራሉ
በሚደረጉ ሐይማኖታዊ ውይይቶች ላይ
👉አንዱ የሌላውን እምነት ማናናቅ
👉የሌሎችን ፅሁፍ ቀድቶ መገልበጥ
👉...በጥብቅ የከለከለ ነው ።
🍀መልካም የውይይት ጊዜ🍀
Forwarded from ልባም ሴት 😍 (አላትዮን)
አንቺ ፀሐይ ሆይ የዛሬው ፈተና ልክ እንደደመና ተናፋቂ እንዲያደርግሽ እንጂ ፈፅማ የሚትጠፋ እንደማያደርግሽ አውቀሽ በተስፋ ኑሪ ።
አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሰዋል፤ ያበሰብሰዋልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ትምህርት በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ የተተረጎመ
ሰው ሁን!
1ኛ ነገ. ፪፥፫
አበባ አቤ
2025/07/06 09:18:54
Back to Top
HTML Embed Code: