Telegram Web Link
"ሰማዕትነት ስር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚኽ ስር የሚያቆጠቁጡ ምርጥ ዘሮች ናቸው፡፡ ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፡፡ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፡፡ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፡፡ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፡፡

ሰማዕታት አክብሩን ብለው አይናገሩም፡፡ ነገር ግን በክርስቲያኖች ልብ የሚዘሩት ፍሬ ምእመናንን በፍቅር ያስገድዳል፡፡ እነርሱን እንዲመስሉ ያሳስባል፡፡

ሰማዕታት እንደ ፍቅረኛ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የፍቅረኛውን ስም በየአጋጣሚው ያነሣል፡፡ በዓይነ ሕሊናው ያስባል፡፡ በተለያየ መልኩ ያያል፡፡ ሰማዕታትም ለክርስቲያኖች እንደዚያ ናቸው፡፡ እጅግ የተወደዱና በፍጹም ከሕሊና የማይጠፉ ተወዳጆች ናቸው፡፡ የልጆቻችንን ስም በነርሱ ስም የምንሰይመው፣ ሥዕላቸውን ሥለን የምንተሻሸው የምንስመው ለሰማዕታቱ ያለንን ጥልቅ ፍቅር የምንገልጽበት መንገድ ስለኾነ ነው፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

                የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በረከት አይለየን!
አሳቀኝ
"በጎ ነገር አግኝተህ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ነገር ከአንተ ጋር ጸንቶ ይኖራል፡፡ በጎ ያልሆነ ነገር ደርሶብህ እንደሆነም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ያልሆነ ነገር ወደ በጎ ነገር ይቀየራል፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
መልካም ጁምዓ 😜 ብለናል ሃቢባውያን
#ልጅሽ_ደጅ_ላይ_ቆሟል

ከመስከረም 26 እስከ ሕዳር 6 ባሉ አንድ ቅዳሜ ማታ ከ3 ሰዓት በኋላ ማሕሌተ ጽጌን ለመቆም ወደ የካ ደብረ ሳሕል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እየሄድኩ ነው...መንገዱ ጭር ብሏል፤ አንድ ሱቅ ላይ ግን ደምበኛ (ገዢ) ቆሟል፤ እኔ መንገዴን እየቀጠልኩ ነው፡፡ ደንበኛው ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣ እና ‹‹አባ ይበርኩኝ?›› አለኝ። ‹‹ካህን አይደለሁም›› አልኩት፣ በለበስኩት ነጠላ ጋቢና በእጄ የያዝኩት የጸሎት መጽሐፍ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደምሄድ አውቆ ነው፡፡ ‹‹አውቃለሁ›› አለኝ እና ‹‹ወደየትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው የምትሄደው?›› ጠየቀ መለስኩለት፤ ‹‹እባክህን ልሸኝህ?›› አለኝ አዲስ ቪ 8 መኪና እያሳየኝ፣ ‹‹ብዙም ሩቅ ስላልሆነ በእግሬ ነው የምሄደው›› አልኩት....

ግለሰቡ የጠጣ ይመስላል፣ በእርግጥም የመጠጥ ሽታ ሸትቶኛል፤ በእጁ ፓኬት ሲጋራ ይዟል፣ ከሱቁ ሲመጣ ከፓኬቱ ውስጥ አንዱን አውጥቶ ከንፈሩ ላይ አድርጎ ነበር ሲቀርበኝ በጣቶቹ መሃል ያዘው፣ ምልከታዬን አስተውሎ ነው መሰለኝ የያዘውን ሲጋራ በሙሉ ጣለና በእግሩ ረጋገጠው፡፡ ‹‹አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ ልትል ነው አይደል?›› አለኝ

ከዚህ ንግግር በኋላ ስካሩ ሙሉ ለሙሉ ሲጠፋ በግልጽ ይታያል፡፡ ሁሉንም የመኪናውን በሮች ከፈተና ‹‹እንዲናፈስ ፈልጌ ነው...በሲጋራና በመጠጥ ሽታ  የታጠነ መኪና ውስጥ እንዳትገባ›› አለኝ፤ በግርምት ቆምሁ፤

‹‹እባክህ አሁን እንሂድ?›› የጋቢናውን በር ብቻ ትቶ ሌሎቹን ዘጋጋና መኪናውን ለመንዳት ተዘጋጀ፤ በእምነት ገባሁና ተቀመጥኩ። መንገድ ስንጀምር በጣም ባዘነ ድምጸት

‹‹ሽሮ ሜዳ ነው ያደግሁት...ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን...ጽጌን በፍቅር ቆሜ ነው ያደግኩት...ለረጅም ዓመታት...አክሊለ ጽጌ ብዬ...ክበበ ጌራ ወርቅ ብዬ›› ዓይኖቼን ከመንገዱ ነቅዬ ወደርሱ ሳዞር መንታ መንታ ሆነው የሚወርዱ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም መስማት ብቻ

‹‹ዲግሪዬን ከያዝኩ በኋላ አንድ ዓለም አቀፍ ኤን ጂ ኦ ገባሁ...በከፍተኛ ደመወዝ በቃ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ተለያየሁ...አልሳለም፣ ኪዳን አላደርስ፣ አላስቀድስ፣ አላድር፣ አላነግስ ከሀገር ሀገር መዞር ከጓደኞቼ ጋር መጠጣት፣  ሲጋራ ማጨስ...ይኸውልህ ሚስትና ልጆች እያሉኝ ነው እዚህ ያገኘኸኝ፣ የመጠጥና የሲጋራ ጓደኞቼ በልጠውብኝ ነው ያገኘሁህ...ውስኪአቸውን ይዘው እየጠበቁኝ ነው ›› ያለቅሳል፣ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ግን በሥርዓት ረጋ ብሎ ይነዳል፤ መናገሩን ይቀጥላል

‹‹ተረጋግቼ ማሰብ አልፈልግም...ምክንያቱም ከተረጋጋሁ ልጅነቴን ማሰብ እጀምራለሁ...ልጅነቴን ማሰብ ከጀመርሁ ቤተ ክርስቲያንን ማሰብ እጀምራለሁ...ደጀ ሰላሟን ማሰብ እጀምራለሁ...መቅደሷን ማሰብ እጀምራለሁ፣...የዕጣኑን ሽታ ማሰብ እጀምራለሁ...ማልቀስ እጀምራለሁ...ፍቅሯን አስባለሁ....የጸናጽሉ፣ የከበሮው ድምጽ ይሰማኛል፣ በመሃል ሰይጣኔ ይመጣና እውነቴን ነው ስጠራው ነዋ የሚመጣው....ለጓደኞችህ ደውል ይለኛል....በመጠጥ ራስህን ደብቅ ይለኛል እታዘዘዋለሁ ልጆቼንና ሚስቴን ጥዬ እወጣለሁ›› 

አሁን ወደ ቤተክርስቲያን ታጥፈናል፤ ወደ ግቢው የሚያስገባ በር ጋር ስንደርስ ቆመ፣ ወደውስጥ ለመግባት በሮቹ የተከፈቱ ቢሆንም አልገባም፤
‹‹ወደ ውስጥ ገብተህ ትንሽ ቆይተህ አትሄድም?›› አልኩ ሀዘኑ ተጋብቶብኝ ‹‹አልገባም ግን ድሮ የሚወድሽ ልጅሽ ደጅ ቆሟል በላት›› አለና ሳግ ተናንቆት መሪውን ተደግፎ ድምጽ አሰምቶ አለቀሰ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ለምን እንዳለቀሰ፣ እንዴት እንዳለቀሰ በዓይኔ ያየሁ መሰለኝ፤
‹‹እባክህን ግባና አልቅስ›› አልኩ፣ የቻለውን ያህል አልቅሶ እንዲወጣለት ፈለግሁ፣

‹‹ማን....እኔ? አልገባም ግን ንገርልኝ አሁንም ይወድሻል በልልኝ....እዚህ በር ላይ ቆሟል በልልኝ›› አለኝ፣ እያለቀሰ ወረድሁ

ቅዱስ ዳዊት ‹‹በኃጥአን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ›› መዝ 84፣10 ያለው ለምን እንደሆነ ይበልጥ ገባኝ። ሳላውቀው የእኔም እንባ መንገዱን ጀምሯል፤ ‹‹ማን ስለሆንኩ ነው እንዲህ በፍቅርህ የተሸከምከኝ›› አልኩ አምላኬን፣ በላዔ ሰብዕ ትዝ አለኝ በልጅነቱ የሚያስታውሳትን የድንግልን ድንቅ ስሟን ሲሰማ ከክህደት እንደተመለሰና ለመዳን ምክንያት እንደሆነችው፡፡ እናም ‹‹በልጅነቱ ይወድሽ የነበረውን ልጅሽን አስቢው ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢለት›› አልኳት

(#ዲያቆን_አብርሃም_ይኄይስ እንደጻፈው)
The commencement of the Divine Inspiration to Allah's Messenger (ﷺ) was in the form of good dreams which came true like bright daylight, and then the love of seclusion was bestowed upon him. He used to go in seclusion in the cave of Hira where he used to worship (Allah alone) continuously for many days before his desire to see his family. He used to take with him the journey food for the stay and then come back to (his wife) Khadija to take his food likewise again till suddenly the Truth descended upon him while he was in the cave of Hira. The angel came to him and asked him to read. The Prophet (ﷺ) replied, "I do not know how to read." The Prophet (ﷺ) added, "The angel caught me (forcefully) and pressed me so hard that I could not bear it any more. He then released me and again asked me to read and I replied, 'I do not know how to read.' Thereupon he caught me again and pressed me a second time till I could not bear it any more. He then released me and again asked me to read but again I replied, 'I do not know how to read (or what shall I read)?' Thereupon he caught me for the third time and pressed me, and then released me and said, 'Read in the name of your Lord, who has created (all that exists), created man from a clot. Read! And your Lord is the Most Generous." (96:1, 96:2, 96:3) Then Allah's Messenger (ﷺ) returned with the Inspiration and with his heart beating severely. Then he went to Khadija bint Khuwailid and said, "Cover me! Cover me!" They covered him till his fear was over and after that he told her everything that had happened and said, "I fear that something may happen to me." Khadija replied, "Never! By Allah, Allah will never disgrace you. You keep good relations with your kith and kin, help the poor and the destitute, serve your guests generously and assist the deserving calamity-afflicted ones." Khadija then accompanied him to her cousin Waraqa bin Naufal bin Asad bin 'Abdul 'Uzza, who, during the pre-Islamic Period became a Christian and used to write the writing with Hebrew letters. He would write from the Gospel in Hebrew as much as Allah wished him to write. He was an old man and had lost his eyesight. Khadija said to Waraqa, "Listen to the story of your nephew, O my cousin!" Waraqa asked, "O my nephew! What have you seen?" Allah's Messenger (ﷺ) described whatever he had seen. Waraqa said, "This is the same one who keeps the secrets (angel Gabriel) whom Allah had sent to Moses. I wish I were young and could live up to the time when your people would turn you out." Allah's Messenger (ﷺ) asked, "Will they drive me out?" Waraqa replied in the affirmative and said, "Anyone (man) who came with something similar to what you have brought was treated with hostility; and if I should remain alive till the day when you will be turned out then I would support you strongly." But after a few days Waraqa died and the Divine Inspiration was also paused for a while.


👉 ካፊሮች በእዚህ ሐዱስ ላይ ያላችሁን ጥያቄ እስኪ በትህትና አቅርቡ

ውድ ሙስሊሞች ደግሞ በኢማን መልስ አስቀምጡ 🥰 🥰
የመምህራችን ፍሬ ነው😍
"ክርስትና የሚጀምረው ከተግባር እንጂ ከወሬ አይደለም፡፡ ሕይወታችን በጥቅስ ተገንዞ በጥቅስ የተቀበረ ከሕይወትና ከሥራ የተለየ እንዲሆን አንፍቀድለት፡፡"
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
"ሰዎች #እንዲያደንቁህ ብለህ በጎ ምግባር አትሥራ፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
አበባይቱ ማርያም
ልባም ሴት 😍
አጭር ነው መሠል 😔🥰 ቢሆንም በቂ ነው።

ለምትወዶቸው ሁሉ እነሆ አዳርሷቸው 🥰

https://www.tg-me.com/lebam_set
#ንስሓ_የማያድነው_ኀጢአት

ከእግዚአብሔር ምህረት ቸርነት። ከእመቤታችን በስተቀር ከሰው ኀጢአት አይታጣም።

የዘመናችን የአጥማቅያን ቡድን አድናቂዎች እና ተከታዮች ሳያውቁት እና ሳይመስላቸው አምልኮተ ሰብእ እየፈጸሙ ይገኛሉ። ይህ ደግሞ ንስሓ የሌለው ኀጢአት ነው። ንስሓ የማያስተሰርየው በደል ኑሮ አይደለም፦ የጻድቅ ተከታይ ስለሆነ ጻድቃንን ይዘነጋል የእሱ ጻድቅ ከፊቱ ያለው አያ እንተና ብቻ ነው።

የፈዋሽ ተከታይ ስለሆነ ፈውሰ ነፍስ አያስፈልገውምና። ለፈውስ ደጅ የሚጠናው አቶ እንተናን ነው። የቅዱስ አጥማቂ ቸከታይ ስለሆነ ቅድስና አያስፈልውምና። የካህን ፊት እንዳያይ መተተኞች ጠንቋዮች እያሉ የልብ ጆሮውን ይዘጉበታል። ንስሓቸውን የጨረሱ ፈዋሾች ተከታይ ስለሆነ እነሱን በማገልገል ጊዜውን ያባክናል።

በፍርሀት ልቡናው እንዲርድ ጋኔን ወረረህ አሠረህ ተበተበህ እያሉ መውጫ ቀዳዳ ያሳጡታል። ሳያውቀው ያመልካቸዋል። ምክንያቱም እነሱ ከሌሉ በሕይወት የማይኖር ይመስለዋል። የዛር አድናቂ የልብ ተመጻዳቂ ያደርጉታል። ጻድቅ ሲባል አቶ እንተና ነው ትዝ የሚለው።
የማያድን ለንስሓ የማያበቃ ተከታይነት ይሄ አይደለምን??

አሁን አሁን ክፍት የሥራ ፈጠራ መንገዶች አራት ናቸው፦
#ባህታዊነት#አጥማቂነት#ሰባኪነት#ዘማሪነት ናቸው።

#ማንም ተነሥቶ ስማ ወገን ዓለም ሊናድ ነው ከበረሃ የመጣ መልእክት ነው... ካለ ባህታዊ እንተና ይሆናል። እውነተኛ ነው? ከየትኛው በረሀ? ከየትኛው ገዳም ማለት የለም መከተል ነው እንጂ ማን ያጣራዋል።

#ማንም ተነሥቶ ውጣ ልቀቅ ምናምን ቅብጥርጥር ካለ አጥማቂ እንተና ይሆናል። በዛር ነው? በእግዚአብሔር? መከተል ነው እንጂ ማን ያጣራዋል።

#ማንም ተነሥቶ ጎርነን ባለ ድምጽ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ...ካለ ሰባኪ እንተና ይሆናል። ተምሯል?አልተማረም? መከተል ነው እንጂ ማን ያጣራዋል።

#ማንም ተነሥቶ ያላንተ ለኔ፣ ካመድ ያነሣኸኝ...ካለ ዘማሪ እንተና ይሆናል። ሦስቱን የዜማ ልኮች ጠብቋል?አልጠበቀም? መከተል ነው እንጂ ማን ያጣራዋል።

አያችሁ? በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ ሆነና ይነዱን ጀመር። ሰውን የእውር አፍጣጭ የጨለማ ገልማጭ አደረጉት።
ለንስሓ የማያበቃ በደል ይሄ አይደለ?

(
#መምህር ገብረ መድኅን እንየው)
ሰው ሆይ! ጻድቅ መሆንን ትወዳለህን? አዎን ትለኝ እንደሆነ፥ እንግዲያውስ ለራስህ ንፉግ ለሌላው ግን ቸር ሁን፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
አንድ ልጅ ተወለደ። ልጁ ቁርጥ ጎረቤቱን ቢመስል፦ አባትየው ደስ ይለዋል? ወይስ ይከፋዋል? ተናገሩ እንጂ።
ይከፋዋል አይደል። ምን ብሎ ነው የሚከፋው? አቤት! የሌላ ልጅ ነው ብሎ ነዋ።
እኛስ ቁርጥ ዲያብሎስን ብንመስል እግዚአብሔር አይከፋውም?! የማን ልጆች ነን እኛ? የእግዚአብሔር። ከማን ነው የወለደን? ከቤተ-ክርስቲያን። ማንን ነው መምሰል ያለብን? አባታችን እግዚአብሔርን ነው መምሰል ያለብን።


ርዕሰ ሊቃውንት መምህር አባ ገብረ ኪዳን ካስተማሩት የተቀነጨበ
ነገ ፆም ይጀመራል  ። 

እንኳን አደረሳችሁ
2024/09/27 15:28:03
Back to Top
HTML Embed Code: