Telegram Web Link
ዘንድሮ ኡኡኡ ነው አቦ
• ኢስመላብ አል ቅዱስ አላዋሒድ። አሜን

"…ኢዩ ጩፋን ተዉት ከምር እኔ እንደዚህ የምዕራብ ሸዋ ኦሮሞ ልጅ ያሳዘነኝ የለም። ምንአለ እንደው ያንን ቪድዮ ባላወጣሁበት ኖሮ። ምን ነክቶኝ ነው ግን በናታቹ። ከምር ያገኘውን ዲቪ ሎተሪ የሆነ ምርጥ እድል የቀደድኩበት ያህል እየተሰማኝ ነው። ማንም መንገደኛ የሚሾመውን ሹመት፣ ማንም መንገደኛ የሚበላውን የኦርቶዶክስ እንጀራ አመድ ደፍቼበት ምቀኛ ነው የሆንኩበት። ፀፀተኝ።😭😭

"…ይቴ ጭሷ ከድር ሁሴን በናትሽ አፉ በዪኝ ነፍሴ። አለ አይደል ነገሩ ሁሉ እንዲህ መላቅጡ የሚጠፋ ሳይመስለኝ እኮ ነው የገገምኩብህ። ሁለት ዓመት ሙሉ በእጄ ያስቀመጥኩትን የአንተን ቪድዮ እና ፎቶ ስትሾም ጠብቄ አውጥቼ ጉድ አደረግኩህ። አሁን 3 የወለደ ሲሾም እያየሁ አንተ ገና ለገና ሰልመሃል፣ ስትደንስ ታይተሃል፣ ከኤርትራዊት ሴተኛ አዳሪ አንድ ልጅ ወልደሃል ብዬ ሄጵ ማለቴ ዛሬ ላይ ሳስበው ከምር ትክክል እንዳልነበርኩ ተሰምቶኛል። 😂 አንዳንዴ ያው አለአይደል ስትበሰጭ የምታደርገውን አታውቅም አይደል? ኢንዴዣ ኡኖቢኝ ኖ ይቴ። በጣም ኢንቂርታ፣ ኢንቂርታ በጣም ማይ ብሩደር…ብራዘር።

• ጵጵስና ግን እንዴት አባቱ ነው የሚያምርበት በጌታቸው…!
"መላው ዓለምን ያስደነገጡ ታላላቅ መከራዎች ኹሉ መነሻቸው ትዕቢት ነው፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
በመጨረሻ ዳታ ተለቀቀ😍
አንድን በክፉ ምግባር የተያዘን ሰው ወደ መልካም ነገር ልትመልሰው ብትወድድ መጀመርያ ሰላሙን እንዲያገኝ አድርገው፡፡ በፍቅር ቃል ከፍ ከፍ አድርገው። እንዲህ ያለን ሰው ከክፉ ስራው እንዲመለስ ለማድረግ ከዚህ የተሻለ ዘዴ የለምና። ሰው በተግባር የሚያደርገው ፍቅር ሰዎችን የመለወጥ ፍጹም ሀይል አለውና።

ቀጥለህ በፍቅር አንድ ሁለት ቃልን ንገረው፣ በቁጣ አትንገረው። በእርሱ ላይ አንዳች የጠላትነት ስሜት አታሳይ። ፍቅር ሰዎችን ለመለወጥ መንገዱን እርሱ ያውቅበታል። ብቻ እንተ እድሉን ስጠው። የፍቅር ሰውም ሁን።

(መክስምያኖስ ባህታዊ ዘሶርያ - የበረሃ ፈርጦች)
«ወዳጄ ሆይ! እግዚአብሔር ነዳያንን የሚልክልህ መስጠትን እንድትለማመድ ነው፡፡ ዛሬ በነዳያኑ አድሮ የሚለምንህ ለኋለኛይቱ ቀን ስንቅ እንዲያስቀምጥልህ ወድዶ ነው፡፡ ታድያ ንጉሥ ወደ ቤቱ መጥቶ የሚያባርር ሰው እንደምን ያለ ጎስቋላ ሰው ነው? እንግዲያውስ ነዳያንን ስታይ ወደ አንተ የመጣው ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስ እንጂ ሰው አይደለምና አትግፋው፡፡ በረከትህንም ከቤትህ አውጥተህ አትሸኘው፡፡»

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ወነፍሖ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት ለዝንቱ መፅሐፍ ወበጊዜሃ ተደምሰሰ ...።
“እኔ ክርስቲያን ነኝ፡፡ ለሚጠይቁት እንደዚህ ብሎ የሚመልስ ሰው በአንድ ጊዜ በኹሉም ነገሮቹ ላይ ማወጁ ነው፡፡ ሀገሩ የት እንደ ኾነ፣ ሥራው ምን እንደ ኾነ፣ ቤተሰቡ እነማን እንደ ኾኑ መመስከሩ ነው፡፡ ክርስቲያን የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ነዋሪ እንጂ በምድር ላይ ካሉት ከተሞች የአንዲቱም አይደለምና፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
#እስልምና_ይህን_ምን_ይላል?
ጅብ ሰውን ይበላል ወይስ ሰው ነው ጅብን የሚበላ?
**
እስክ ዛሬ ድረስ ጅብ ህፃናትን እንደሚበላ ስትሰሙ ኖራችዋል።እንሆ በእስልምና ጅብን መብላት እንደሚፈቀድ በሐዲስ ላይ ተዘግቧል።

ነብዩ ሙሐመድም ጅብን መብላት ሐላል እንደሆነ መናገራቸው ተዘግቧል።ሐዲሱ Sahih ሲሆን ታማኝ መረጃ ነው። እርግጠኛ ነኝ ሙስሊሞችን ጅብ ትበላላችሁ ወይ ብትሏቸው አንበላም እንደሚሉ። ምክንያቱም ሙስሊሞች በየ ሀገሩ ያለውን ባህልና ስርአት ይከተላሉ እንጂ የሐዲሳቸውንና የነብያቸውን ሱና ሙሉ ለሙሉ ኡይተገብሩም። እኔ እተገብራለሁ የሚል ሙስሊም ካለ ግን የጅብ ሥጋ እየበላ ሊያሳየን ይገባል።
ማስረጃ👇
Ibn Abi Ammar said:
"I asked Jabir bin Abdullah: 'Is the hyena game?' He said: 'Yes'" He said: "I said: 'Can it be eaten?' He said: 'Yes.'" He said: "I said: 'Did the Messenger of Allah say that?' He said: 'Yes.'"
حَدَّثَنَا أَحْمَدُ بْنُ مَنِيعٍ، حَدَّثَنَا إِسْمَاعِيلُ بْنُ إِبْرَاهِيمَ، أَخْبَرَنَا ابْنُ جُرَيْجٍ، عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُبَيْدِ بْنِ عُمَيْرٍ، عَنِ ابْنِ أَبِي عَمَّارٍ، قَالَ قُلْتُ لِجَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ الضَّبُعُ أَصَيْدٌ هِيَ قَالَ نَعَمْ ‏.‏ قَالَ قُلْتُ آكُلُهَا قَالَ نَعَمْ ‏.‏ قَالَ قُلْتُ أَقَالَهُ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ نَعَمْ ‏.‏ قَالَ أَبُو عِيسَى هَذَا حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ ‏.‏ قَالَ عَلِيُّ بْنُ الْمَدِينِيِّ قَالَ يَحْيَى بْنُ سَعِيدٍ وَرَوَى جَرِيرُ بْنُ حَازِمٍ هَذَا الْحَدِيثَ فَقَالَ عَنْ جَابِرٍ عَنْ عُمَرَ ‏.‏ وَحَدِيثُ ابْنِ جُرَيْجٍ أَصَحُّ ‏.‏ وَهُوَ قَوْلُ أَحْمَدَ وَإِسْحَاقَ وَالْعَمَلُ عَلَى هَذَا الْحَدِيثِ عِنْدَ بَعْضِ أَهْلِ الْعِلْمِ فِي الْمُحْرِمِ إِذَا أَصَابَ ضَبُعًا أَنَّ عَلَيْهِ الْجَزَاءَ ‏.‏
Grade: Sahih (Darussalam)
Reference : Jami` at-Tirmidhi 851In-book reference : Book 9, Hadith 44English translation : Vol. 2, Book 4, Hadith 851
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ እንዲህ አሉ፦ ማንም ቢሰድብህ ስለ መሰደብህ ሳይሆን ስለ ሰደበህ ሰው አስብ። ያ ሰው ወንድምህ ነው። በፍቅር የተሞላህ መንፈሳዊ ሰው እንደመሆንህ መጠን አንተን በመስደብ ኃጢአት ላደረገው ወንድምህ ምን ልታደርግለት እንደምትችል ታስብ ዘንድ ይገባሃል። በእርግጥ አንተን የተሳደበበት ስድብ በድኅነቱ መግቢያ ላይ ቆሞ ይከለክለውና በዚሁ ሳቢያ ውድ ነፍሱ ወደ ሲዖል ትወርድ ዘንድ አትሻም። በመሆኑም ያንን ኃጢአት ቆጥሮ እንዳይቀጣው ይልቁንም ይቅር እንዲለው እግዚአብሔርን ትጠይቅለታለህ ከዚህ በተጨማሪም እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ካለው ኃጢአት እንዲያወጣውና ዳግመኛ አንተን ሆነ ሌሎችን በመስደብ እንዳይበድል ልትጸልይለት ይገባል።
+ ድንገት የተበጠሰ ገመድ +

የደብረ ዳሞ ገዳም በገመድ ብቻ የሚወጣ እጅግ ጥንታዊ ገዳም ነው:: ይህንን አቡነ አረጋዊ በዘንዶ የወጡትን ታላቅ ገዳም ለመውጣት በግንባታው ወቅት በአፄ ገብረ መስቀል የተሠራ ደረጃ ነበረው:: ሆኖም አቡነ አረጋዊ ደረጃውን ዳህምሞ (አፍርሰው) ብለው በማዘዛቸው እስከ አሁን ድረስ በገመድ የሚወጣበት ገዳም ሆኖአል::

የደብረ ዳሞ መውጫ ገመድ እጅግ ወፍራም ሲሆን እስከ አሁን ድረስ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተንጠላጥለው ወጥተው ወርደውበታል:: ይህ እጅግ ወፍራም ገመድ ለዘመናት ሲያገለግል ተበጥሶ ሰው ጥሎ አያውቅም:: በታሪክ የማይዘነጋና መሃል ላይ የተበጠሰበትና ሰው የጣለበት ቀን አለ:: (የዲያቢሎስ መተናኮል ነው የሚል አለ)

በዚያ ቀን በተበጠሰው ገመድ ላይ የወረደው መንገደኛ ጻድቁ አባ ተክለ ሃይማኖት ነበሩ:: መነኮሳቱን ተሰናብተው በዚያ ገመድ ሲወርዱ ተበጥሶ የማያውቀው ገመድ ድንገት ተበጠሰ:: ከላይ የሚያዩት አባቶች ቁልቁል እያዩ በድንጋጤ ጮኹ:: ሆኖም እግዚአብሔር ለጻድቁ የብርሃን ክንፍ ሠጥቶአቸው ከተበጠሰው ገመድ ተለይተው እንደ መልአክ በርረው ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ወርደው መሬት ላይ አረፉ:: ባረፉባት ሥፍራም ቤተ ክርስቲያን ተሠራባት::

ወዳጄ በሕይወትህ ድንገት የተበጠሰ ገመድ የለም? ሳትጠብቀው የተበጠሰ ገመድ ማንም ላይ ሳይበጠስ አንተ ላይ የጨከነ ገመድ የለም? ምን ዓይነት ገመድ አትበለኝ:: የእንጀራ ገመድ የኑሮ ገመድ የትምህርት ገመድ የፈለግኸው ገመድ በለው:: እሱን ተጠምጥመህ ይዘህ ወደ አንዳች ቦታ ለመድረስ የተማመንክበት ተስፋህን ሙሉ በሙሉ የጣልክበት ገመድ የለም? ድንገት ተበጥሶ ዙሪያው ገደል አልሆነብህም? ሰዎች ማንም ላይ ያልተበጠሰ ገመድ አንተ ላይ ሲበጠስ አይተው "ምኑ ዕድለ ቢስ ነው?" ብለው የተደነቁብህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "ከባሕር አደጋ ተርፎ ዕባብ የነደፈው እንዴት ኃጢአተኛ ቢሆን ነው?" ብለው በትዝብት ዓይን እንዲያዩህ ያደረገ በሕይወትህ ሳታስበው ተበጥሶ ዙሪያው ገደል የሆነ ሥፍራ ላይ የጣለህ የሕይወት ገመድ ይኖር ይሆናል::

በዕድልህ አትማረር በሕይወትህ ድንገት የሚበጠስብህ ገመድ የምትወድቅበት ሳይሆን ክንፍ አውጥተህ የምትበርበት ነው:: ፈጣሪ የተማመንክበትን የምታየውን ገመድ እንዲበጠስብህ ከፈቀደ ያላየኸውን ክንፍ ሊሠጥህ እንጂ ሊጥልህ አይደለም:: የሕይወትህን ገመድ የተበጠሰበትን ቀን "እግዚአብሔር ለመልካም አሰበው" ብለህ እንደ ዮሴፍ ታመሰግንበታለህ::
ገመድህን የሚበጥሰው ከገደል ሊጥልህ ሳይሆን በክንፍ አብቅሎ ሊተክልህ ነው:: የሚተክልህ በበረሃ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ነው:: ተራ ተክል የምትሆን እንዳይመስልህ:: የሃይማኖት ተክል (ተክለ ሃይማኖት) ትሆናለህ:: ተክለ መንፈስ ቅዱስ ተክለ ወልድ ተክለ አብ ትሆናለህ:: አብ የተከለው ደግሞ አይነቀልም!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 24 2013 ዓ ም
አሁን ደግሞ ለአባ ግርማ ልጅ ሰይጣን ለሚያጮኸው ሞባይል የሚባርከው ሰው የህሊና ፀሎት እናደርጋለን።

ክብረ ክህነት ወዴት ሔደች ጃል 🤔
ሰበር ዜና
በትግራይ የሚገኙ "ጳጳሳት" ሕገ ቤተ ክርስቲያንን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ገዳም የሕገ ወጥ ሢመት "የአስኬማ ጸሎት" እያደረጉ መሆኑ ተዘገበ !

ሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ ፣ በብፁዕ አቡነ መርሐክርስቶስ ፣ በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ እና በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የሚመራው እና በቅዱስ ፍሬምናጦስ ስም የሚነግደው ሕገ ወጥ ቡድን በዛሬው ዕለት በድፍረት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ መረጥኳቸው ላላቸው መነኮሳት "የአስኬማ ጸሎት እያካሄደ እንደሚገኝ የትግራይ ቲቪ ካሰራጨው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

የ"አስኬማ ጸሎት" በሚል እያከናወኑት በሚገኘው ሥርዓት ላይ መንግስታዊው የትግራይ ቲቪ የቀጥታ ሥርጭት ሽፋን እየሰጠው የሚገኝ ሲሆን በቡድኑ መሪ በብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ አማካይነት እና በሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት ተባባሪነት ሕገ ወጥ ሢመቱ እየተከናወነ መሆኑ ታይቷል።

በትግራይ የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት ፖለቲከኞች እንኳ ምርጫቸው ያደረጉት የሰላም እና የይቅርታ መንገድ በመርገጥ ፍቅረ ሢመት ያደረባቸው መነኮሳትን በመሰብሰብ የጨረቃ ሢመት ለማድረግ እያደረጉት ያለው ጥድፍያ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መከፋፈል ምን አልባትም ከቀድሞ ጀምሮ ሲያልሙት የነበረውን "የሀገረ ትግራይ" ምሥረታ ለማካሄድ በቅድሚያ የያዙት የፖለቲከኞች ሀሳብ መሆኑን ምሁራን ይናገራሉ።
#እስመ_አንተ_ትፈድዮ_ለኩሉ_በከመ_ምግባሩ

ነገ አፈር ለሚሆን ስጋዊ ፍትወታችሁ አድልታች ቅድስት ቤተክርስቲያኔን የምትከፋፍሉ ረበናተ ክህደት ሆይ ይብላኝ ለእናንተ አካለ ክርስቶስ የሆነችው እምየ ተዋህዶ ግን እንደ እንቁ እየበራች ያለ አንዳች ተፈልጦት ወተከፍሎት ፀንታ ትኖራለች ።

ቤተክርስቲያን ማለት ህንፃ ብቻ አይደለም ምን አልባት ስጋዊ በሆነ አይናችሁ ተመልክታችሁ ፤ በበቀል ጥማት እና በማይረካው የስልጣን ፍቅር የታወረው ህሊናችሁ #ቤተክርስቲያን ማለት ግንቡ እና ዋሻ ገደሉ እንደሆነ ነግሮችሁ አመላክቶችሁ ይሆናል ። ግን ቤተክርስቲያን ማለት ይች ብቻ አይደለችም ...

ቤተክርስቲያን በንፁሁ እና ቅዱሱ አምላኳ ደም ተዋጅታ እና ታትማ ዘወትር ያለመለያየት የለመነጣጠል የአንዱ አምላኳ አካል ሆና ዘወትር ትኖራለች ። ቤተክርስቲያን ማለት ወልድ ዋህድ ብለው በአንድ ልብ ያመኑ በአምላካቸው ቅዱስ ስጋ ክቡር ደም የታተሙ ምዕመናን ህብረት ናትና ።

ዛሬ ጊዜ ስልጣን ሰጥቶችሁ ነገሮች ተሳክተውላችሁ ከፍልን ብላችሁ ቀኖናዋን እንደ ትቢያ በትዕቢት እግሮቻችሁ ረጥሮጣችሁት ሊሆን ይችላል ። ግን ነገ ዛሬ የረጠረጣችሁ ቀኖና አልሰማም ብላችሁ ጆሮችሁን የደፈናችሁበት የየዋህ ክርስቲያኖች እንባ ይፈርድባችኋል ።

የቤተክርስቲያን አምላኳ እራስ የሆነላት ጌታዋ ይፈርድባችኋል ... ። ለእያንዳንዱ የትዕቢት ግብራችሁ ዋጋው እጥብ ድርብ ሆኖ ይከፈላልና ።

#እስመ_አንተ_ትፈድዮ_ለኩሉ_በከመ_ምግባሩ
2024/09/29 17:43:45
Back to Top
HTML Embed Code: