This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይሄንን መንዙማ ሰምቶ አይቶ ለአመሳቅ ሐራም ነው 😂
ማሜ ወለላው 😂😂
ማሜ ወለላው 😂😂
🤣5
የቅቤ እምነት ነው ያሉት 🤔
ኧረ ወገን ግራ አታጋቡን
ከመቼ ጀምሮ በቅቤ 🤔
ከስድብ በፊት ግን ቆይ አንዴ ሙሉ ሐሳቤ ላስረዳ 🤝
እግዚአብሔር ከሃሊ ኩሉ ገባሬ ኩሉ እንደሆነው ሁሉ ቅዱሳኑን ከእርሱ ባገኙት ፀጋና ክብር ሁሉን ይችሉ ዘንድ አስችሏቸዋል ። በቅድስት ወንጌሉም “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ #ከዚህም_የሚበልጥ_ያደርጋል፥”— ዮሐንስ 14፥12 ይሄ ቃሉ የታመነ ነው ሁሉን ስለሱ ሲሉ ስለተው ፈንታ እርሱ ሁሉን ማድረግ እንዲችሉ በሁሉ ላይ ሹሞቸዋል ።
ይህም ብቻ አይደለም በእርሱ ለምናምን ለእኛ ለሁላችንም ሁሉን ማድረግ እንችል ዘንድ በሁሉም ነገር ላይ ስልጣንን ሰጥቷናል ። በእምነታችን መሠረት እግዚአብሔር ያድነን ዘንድ የታመነነ ነው ።
እነ ዘእውሩን በዮሐ 9 ላይ በምራቁ ጭቃን ለውሶ ሲፈውስ አይተናል ። ሐዋርቱም በጥላቸው እና በጨርቃቸው ፈውሰዋል ። ከዚህ የሚያስገርመው ደግሞ ቅዱሳኑ የተማፀኑበት ቃልኪዳንን ያገኙበት ቦታ እንኳን ሳይቀር ድንቅ ነገሮችን ሲፈፅም ምስክር ነን ሊቃውንቱ "ሰብእ ይቀድስ ለመካን መካን ይቀድስ ለሰብእ " እንደሚሉት ። ቅዱሱ አባታችን አቡነ ሐብተማርያም በሎሚያቸው ከጨጎራ ጀምሮ እስከ ካንሰር ከዚያም በላይ ሲፈውሱም ሰምተናል ። ከማዕጠንቱ በሚወጣው የእጣኑ ጢስም የሚፈፀመው ድንቅ ነው
አዎ እግዚአብሔር በእፅዋቱ ፣በአፈሩ ፣ በጠጠሩ ፣በእጣኑ ፣በሎሚው ....ብቻ ቅዱስ ስሙን እምነት ከቅድስቲቱ ቤተመቅደሱ #በሚወጡ ነገሮች ዶንቅ ያደርጋል ። ያው ተዓምራት በእራሳቸው #እንደዋና_እና_ብቸኛ የእምነት ማረጋገጫ ባይቆጠሩም ።
ግን ሁሉም ነገር ልክ ሊኖረው ይገባል ። መመዘን አለበት ገና ለገና በአባቶች ተባርኮል ተፀልዮበታል በሚል ጭፍን ሃሳብ የተገኘው ሁሉ #እምንት ወይም #ጠበል አይባል። ገና ለገና ይፈውሳል በሚል ያንንም ያንንም መጋፈፉ መልካም አይደለም ።
ለምሳሌ በቅርቤ የሰማሁት የቅቤ እምነት እጅጉን ያስገርማል ።
ስለ ቅቤ እምነት
👉በቅዱሳን መፃህፍት ተጠቅሷም ተነግሮም አያውቅም (በመፅሐፍ ቅዱስ በገድላት በድርሳናት ...)
👉የመጠቀሚያ ጊዜው የተገደበ ነው (በፍትሐ ነገስት በተቀነኑት በሰባቱ አፅዋማት ጊዜ ጥቅም አይውልም) ልበ አምላክ ዳዊት “ጕልበቶቼ በጾም ደከሙ፤ ሥጋዬም #ቅቤ በማጣት ከሳ።”መዝሙር 109፥24 ባለው ላይ መሰረት አድርገን የእንስሳት ተዋፅዖን በአፅዋማት ጊዜ አንጠቀምምና ።
👉በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ የፈውስ እና የፀሎት ተግባራት ውስጥ በአገልግሎት የለውም ። እንደ ቅዳሴ ጠበል ፣እንደ ማይጠንት እምነት ወይም እንደሌሎቹ በቤተክርስቲያን እና በአካባቢዋ እንደሚገኙ ነገሮች አይደለም ። #ባእድ_ነው ።
ከላይ ባቀረብኮቸው ሶስት ምክኒያቶች ቅቤ የሚባል ነገር ለመብለ ስጋ እንጂ ለፈውሰ ስጋ ውሎ አያውቅም ። እንደ ቤተክርስቲያን ልጅነቴ የሆነ ነጋዴ እንዲከብር ብዬ እንዲህ ያለውን ነገር ለመጠቀመምም ሰዎች እንዲጠቀሙ አላበረታታም ።
ሐሳባችሁ ለመስማት ዝግጁ ነኝ ....
@አላትዮን

ሙሴ በሞተ ጊዜ እስራኤል ለሰላሣ ቀን ያህል መታሰቢያ አደረጉ፤ አለቀሱ፡፡ ለድንግል ማርያምስ?
እስራኤል ዘሥጋ እጅግ የሚወዱት ነቢዩ ሙሴ 'ድንገት' ሞተባቸው፡፡ ወዳጆቹ ገንዘው አልቀበሩትም፡፡ መቃብሩንም አላወቁትም፡፡በዚህ ምክንያት ልባቸው በሐዘን የተሰበረባቸው እስራኤላውያንም ለሙሴ ሰላሣ ቀን/አንድ ወር ሙሉ መታሰቢያ አድርገው አለቀሱ፤ዘዳግም 34:8።
ቅድስት ድንግል ማርያም በሞተች ጊዜስ?
ቅዱሳን ሐዋርያትም ተመሳሳይ ነገር ነው ገጠማቸው፡፡
በሰማያዊ ሥልጣን ያከበራቸውን ጌታ የወለደችላቸው እመ አምላክን በዕለተ ሞቷ አልቀበሯትም፡፡ በዚህ ሲያዝኑ ሰነበቱ፡፡
ተለያይተ ከኖሩ በኋላ፥ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ፥በአንድ ስፍራ እኔ ሥጋዋን እያጠንኩ ሰነበትኩ ብሎ ነገራቸው፡፡
"እናትህን ያገለግል ዘንድ ዮሐንስን የመረጥክ ጌታችን ሆይ፥ እናትህን እንቀብር ዘንድ ፈቃድህ ይሁን" ብለው ሱባኤ ገቡ፡፡
ከሁለት ሱባኤ በኋላ ሥጋዋ ተሠጥቷቸው ቀበሯት፡፡በልጇ ክርስቶስ ሥልጣን ተነሣች፡፡
የቀበሯት ሐዋርያት ትንሣኤዋን ሳያዩ ያልቀበራት ቶማስ ትንሣኤዋን አየ፡፡ በዐመቱ ሌላ ሱባኤ ያዙ፡፡ ሁለተኛው ሱባኤ ሲያልቅ ትንሳኤዋን አዩ፡፡
እንግዲህ ምን እንላለን?
ነቢዩ ሙሴ፥ በሲና ተራራ እሳት ሲነድ ከሩቅ አይቶ ወደ እሳቱ ቀረበ፡፡ የቀረበው እሳት ዐይኑን ሲበዘብዘው ፊቱን በጨርቅ ሸፈነ፤ ዘፀአት 3:6፡፡
ይኽ ሰው በሞተ ጊዜ አንድ ወር ሙሉ መታሰቢያ ከተደረገለት፥
ሙሴ በዐይኑ ያየው ዘንድ ያልቻለውን እሳት በማሕፀኗ የተሸከመች፣ በጀርባዋ ያዘለች፣ጡቶቿን ያጠባች 'የጌታየ እናት'
ሁለት ሱባኤ የመታሰቢያ ቀን ያንሳል እንጂ ይበዛልን?
ደምርነ እሙ ምስለ ፍልሰትኪ!
/ በሊቀ ሊቃውንት ሥሙር አላምረው /

👍2🥰2❤1
Forwarded from ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ነፍሴ ሆይ ፦ የምትድኝበትን እኔ እነግርሻሁ ከዚህ ሁሉ ይልቅ ወደ ቅድስት ድንግል አንዲህ በይ የብርሃን እናት ሆይ ፤ በልጅሸ ፊት በደልሁ ኃጢአቴን አስተሰርይልኝ፡፡
መጽሐፈ አርጋኖን
መጽሐፈ አርጋኖን
“ከልቦቻችን በማይነቀሉ የፍቅሩ ችንካሮች ተቸነከርን:: ያዝነው አንለቀውም እርሱም አቀፈን አልተወንም:: ወደ እርሱ በሃይማኖት አቀረበን:: ከእርሱም ወደ ቀኝ ወደ ግራ አንሸሽም:: እንደ ቀለበት በልባችን እንደ ማኅተም በክንዳችን አኖርነው:: እንደ ዕንቁ በልባችን ሳጥን አስቀመጥነው:: እንደ ወርቅ በሕሊናችን መዝገብ አኖርነው::
እንደ ግምጃ ለበስነው:: እንደ ሐር ግምጃ ተጎናጸፍነው:: እንደ ወታደር ሰይፍ ታጠቅነው:: ለጦር ዕቃ እንደተዘጋጀ የድል ጋሻ ተደገፍነው:: ተከዜና ግዮን በኢሎል ወር እንደሚሞሉ ፍቅሩ በልባችን መልቶአል:: እንደ መከር ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ እንደ ክረምት ጊዜም የጤግሮስ ወንዝ ስንዴ ሲያሹት እንደሚሆን እንደ ኤፍራጥስ ወንዝ ልባችንን በወንጌል ፈሳሽነት አረሰረሰው:: መርከባችንንም በሃይማኖት ወንዝ አስዋኘው"
ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
መጽሐፈ ምሥጢር 24:20
መልካም ዕለተ ሰንበት 🙏

❤5👍1