Telegram Web Link
ሾይጧን ታስሯል ተብሎ የለ እንዴ 😂😳
😁3
የመግሪብ አዛን ውስጥ ነው 😂😍🫠😋
😁1🫡1
ማሜይዝም ይለምልም 💪😂😂
😁9
የጎሠቆለ ባሕርይ (Fallen Nature)

ይህን ጉዳይ ትንሽ ዘርዘር አድርጎ ለመረዳት አዲሱን "ዐይነ ልቡና" የሚለውን መጽሐፌን ይመልከቱ። አምስት ኪሎ "ሰርዲኖስ የመጻሕፍት መደብር" ዋና አከፋፋይ ኾኖ በሌሎችም የመጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁና። ዛሬ በአጭሪ ላቀርብ ወዳሰብኹት ጉዳይ ልግባ።

የጎሠቆለ ባሕርይ የሚባለው በዋነኛነት አዳም ከበደለ በኋላ የኾነው ነው። አዳም ከውድቀቱ በኋላ የሰውነት ባሕርዩ አልተለወጠም። ከውድቀት በፊት ኾነ ከውድቀት በኋላ በሰውነት ለውጥ የለምና። ነገር ግን ከውድቀት በፊት በንጹሕ ባሕርይ መልክአ እግዚአብሔሩ ሳይደክም፤ የጸጋ ልብስን ለብሶ በፍጥረት ላይ የገዥነትን ሥልጣን ተጎናጽፎ በክብር ይኖር ነበረ። ሕገ እግዚአብሔርን ተላልፎ በወደቀ ጊዜ ግን የባሕርይ ውድቀት (ሕማም) ወይም ንዴተ ህላዌ (የባሕርይ ድህነት) ገጠመው።

- Fallen Nature በዋነኛነት የመልክአ እግዚአብሔር መድከምን፦ አዳም የተፈጠረው በእግዚአብሔር መልክ ነው። ያን በተፈጥሮ የተሰጠውን መልክአ እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ባያጣውም በሕግ መተላለፉ ምክንያት አደከመው። አንዱና ዋነኛው የጎሠቆለ ባሕርይ ምልክት ይህ ነው። ኹለተኛው የጎሠቆለ ባሕርይ የሚባለው ከጸጋ እግዚአብሔር የተራቆተ፦ ማለትም እግዚአብሔር አልብሶት የነበረውን የብርሃን ልብስ ያወለቀ፥ የእግዚአብሔር ልጅነትን ያጣ ባሕርይ ነው። ሦስተኛ ከባሕርዩ መጎሥቆል የተነሣ ለኃጢአት የሚያዘነብል መኾን ነው። አራተኛ ጉሥቁል ባሕርይ ያለው ሰውነት ርግማንን ተሸክሟል። ይኸውም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ነው። በሥጋው ወደ መቃብር ገብቶ መበስበስ (ሞተ ሥጋ)፤ በነፍሱ ወደ ሲኦል መግባት ነው (ሞተ ነፍስ) ዋናው ሞተ ነፍስ ከእግዚአብሔር መለየት ገጥሟቸዋል። ስለ ርግማን ሞት ስናነሣ በዋነኛነት የነፍስ ከሥጋ መለየትን ብቻ ሳይኾን የሥጋን ወደ መቃብር ገብቶ መበስበስ፣ የነፍስን ከእግዚአብሔር መለየት (ሞታ ለነፍስ ርሒቅ እም እግዚአብሔር እንዲል ሊቁ ቅዱስ ያሬድ) ይህን ይመለከታል። የሐዲስ ኪዳንን ሞት ለመረዳት "ዐይነ ልቡና" የምትለውን መጽሐፌን ይመልከቱ። እነዚህ በመሠረታዊነት ሰውነትን የጎዱና ያደከሙ ናቸው።

-በባሕርዩ መጎሥቆል ምክንያት የመጡ ጎጂ ያልኾኑ ኹኔታዎች ወይም ሕማማት ዘአልቦቱ ኃጢአት (blemeless Passions) ኃጢአት አልባ ሕማማትን መቀበል ግን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስለኛ ተብሎ በፈቃዱ ለቤዛነት ብሎ የተቀበላቸው ናቸው፤ እመቤታችን ደግሞ ሰው እንደ መኾኗ ያን እንድትቀበል ልጇ ወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቅዷል። ስለዚህም ተርባለች፣ አዝናለች፣ ተሠቃይታለች፣ ሞታለች። እነዚህ ኹኔታዎች በራሳቸው ኃጢአቶች አይደሉም። እንደ ነውርና ርኲሰትም አይቆጠሩም። ጌታችንም እነዚህን ስለኛ ብሎ የተቀበለው በዚህ ምክንያትና ስለኛ ቤዛ ሊኾነን ነው። ይሄን የተቀበለው ደግሞ ሥግው ቃል እንደ መኾኑ ነው። ስለኛ መራቡን፣ መጠማቱን፣ መገረፉን፣ የእሾህ አክሊል መቀዳጀቱን፣ መራራ ሆምጣጤ መጠጣቱን፣ በመስቀል ላይ ዕርቃኑን መሰቀሉን፣ መሞቱን በእውነት የተቀበላቸው ቤዛ ሊኾነን እንጂ ያን በመቀበሉ ምክንያት የጎሠቆለ ባሕርይን ለብሷል ለመሰኘት አይደለም። ቃል ከሥጋ ከተዋሐደ በኋላ ሥግው እንደ መኾኑ ለቤዛነት የተቀበላቸውን ነገሮች የማዳን ሥራ (Economy of Salvation) እንላለን እንጂ በሌላ መንፈስ እንዲታይ ፈጽሞ አናደርግም።

እነዚህን ነገሮች ሥግው ቃል በፈቃዱ ያደረጋቸው ናቸው። ብዙ ቅዱሳን ሊቃውንትም ቅዱስ ቄርሎስ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ፣ ቅዱስ ያሬድ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ... "ኅሥሩ" -"ጉሥቁል" ሥጋን ነሣ ሲሉ በአንድ በኩል ከደካማው አዳም ሰውነት የተከፈለውን ሰውነት መንሣቱን ለማሳየት ሲኾን በሌላ በኩል በፈቃዱ ሕማም፣ መከራና ሞት የሚስማማውን ሰውነት ገንዘብ ማድረጉን ለማመልከት ነው። ከዚህ ውጭ ከላይ በዋነኛነት የወደቀ ባሕርይን የሚገልጡ ነገሮች ያሉበትን ሰውነት ለበሰ ለማለት አይደለም። ለዝርዝሩ "ዐይነ ልቡናን" ይመልከቱ። በነገራችን ላይ አኹን እንኳን እኛ ኦርቶዶክሳውያን አምነን፣ ተጠምቀን በቅብዐ ሜሮን ከብረን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን የክርስቶስ አካል ከኾን በኋላ blemeless passions የሚባሉት ያልቀሩልን በራሳቸው ክፉዎች ስላልኾኑ ነው። እነዚህ ነገሮች አዲስ ሰውነትን ገንዘብ አለማድረግን የሚያመለክቱ አይደሉም። ይኸውም ማለት በጥምቀት ከአሮጌ ማንነት ወጥተን ክርስቶስን ለብሰን አዲስ የምንኾን መኾናችንን የሚያስቀሩ አይደሉምና። ከአሮጌ ማንነት በጥምቀት ከተላቀቅን በኋላ መልሰን ባረጀ ሰውነት ውስጥ እንዳለን አድርገን አንናገርም። በትንሣኤ አኹን ከለበስነው የበለጠ የከበረ ኢመዋቲ ኢድኩም ወኢሕሙም የኾነ ሰውነትን መልሳችንን ፍጽሙ ድኅነት ከትንሣኤ በኋላ መኾኑን የሚያረጋግጥ እንጂ አኹን ብትጠመቁም አሮጌ ማንነት ውስጥ ነው ያላችሁ የሚያስብል አይደለም። ሌላው ቀርቶ ያን አዳም በገነት እያለ ያወለቀውን የብርሃን ልብስ ስንጠመቅ እንለብሰዋለን (በተለይ ቅዱስ ኤፍሬምና ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በትኩረት ይህን ያስተምራሉና) ነገር ግን ለኛ ለዐይነ መጭማጮች ከተጠመቅንም በኋላ ያን የብርሃን ልብስ መልበሳችን አለመታየቱ ያለመልበሳችን ማረጋገጫ ሊኾን አይችልም። ነገር ግን በግልጽ አኹን ያን ልብስ መልበሳችንን ማየት ባንችልም ከትንሣኤ በኋላ ተገልጦ እናየዋለን። ያኔ የሚገለጠው ግን ላልተጠመቁ ሳይኾን በጥምቀት ለከበሩት ክርስቶስን ለለበሱ ነው። ይህን ልብ ማለት ይገባል።

- አካላዊ ቃል የተዋሐደው ሥጋ ንጹሕ ሥጋ ነው። ምንም ዓይነት ነውርና ነቀፋ የለበትም። መንሣትና መዋሐድ ያለመቀዳደም የኾነ ስለ ኾነ ከእመቤታችን የነሣው ሰውነት ንጹሕና ነውር ነቀፋ የሌለበት ነው። የኃጢአት ጠባሳም አላገኘውም። ጸጋን የተመላ፣ መልክአ እግዚአብሔሩ ያልደከመ፣ ኃጢአት ያልገዛው፣ መርገም ያላረፈበት ንጹሕ ሰውነት ነው። ቅድስት ድንግል ማርያም የተጠበቀችው የጉሥቁልና ውጤት ከኾነው ከጸጋ መራቆት፣ ከመልክአ እግዚአብሔር መድከም፣ ለኃጢአት ከማዘንበል፣ ከመርገመ ሥጋ ወነፍስ፣ ከልማደ አንስት በወሊድ ጊዜ ከሚመጣ ምጥ ኹሉ ነው። ይህ ከእርሷ በቀር ከሰው ወገን ለማንም ቀድሞ የተደረገ አይደለም። ስለዚህም ምክንያት በዋነኛው የውድቀት ምልክት አንጻር አድርገን ስናይ እርሷ የወደቀ ሰውነትን ገንዘብ እንዳታደርግ ልጇ ጠብቋታል እንላለን። የእርሷን ሕይወት በልዩ ኹኔታዎች እንዲመላ ያደረገው እርሱ አምላኳ ነውና። የጎሠቆለ ሰውነትን አልለበሰችም ስንል ሕማም፣ ኀዘን፣ መከራ፣ ሞት የማይስማማውን ሰውነት ገንዘብ አድርጋለች ማለታችን አይደለም። ይህን የሚልም አይኖርም ይልቅስ ከላይ እንዳልኹት ከዋነኛው የጒሥቁልና ውጤት መጠበቋን ማዕከል በማድረግ የወደቀ ሰውነትን አልለበሰችም እንላለን። አበውም ያስተማሩት በዚህ አግባብ ነው። በዝርዝር የእርሷን ጉዳይ ለመረዳት "ዐይነ ልቡና" ይነበብ። ልጇ በፈቃዱ ስለኛ የሞተው በማስመሰል ሳይኾን በአማን ነው። ሞትንም በፈቃዱ የተቀበለው ያ ሥጋ የዕሩቅ ብእሲ ሥጋ ሳይኾን የሥግው ቃል ሥጋ ነውና። ሞትን ስለኛ የተቀበለው ሥጋ ራሱ ለኛ ሕይወትን የሚያድል ነው። የሞተውም ሊበሰብስ ሳይኾን ሞትን በሞቱ ገድሎ ሞት የወረሰውን ሰውነት ሕይወት ሊያለብሰው ነው። ይህ የቅዱስ አትናቴዎስና የቅዱስ ቄርሎስ የትምህርት ማዕከል ነው።

እመቤታችን ለምን ሞተች? መልሱ በአጭሩ፦
1) የሞተችው ለመበስበስ ሳይኾን የትንሣኤን አካል ገንዘብ ለማድረግ ነው። ይኸውም ኢመዋቲ አካልን ገንዘብ ለማድረግ እንጂ ለመበስበስ አይደለም። ይህ ዮሐንስ ዘደማስቆ በመደነቅ የገለጸው ነው። ሰውነቷ እንዲበሰብስ ልጇ አለመፍቀዱን ሞታ መበስበስ ሳያገኛት ከልጇ ትንሣኤ በኋላ በልጇ ሥልጣን በሦስተኛው ቀን መነሣቷን ብዙዎቹ ቅዱሳን ሊቃውንት የገለጹት እና እኛም የምናምነው ነው።

2) የሞተችው ሰው ስለ ኾነች ነው። አምላክ በመውለዷ ምክንያት በሕሊናቸው ሰው አይደለችም የሚሉ ሰዎች እንዳይኖሩና በእርሷ ሰው የመኾን ጉዳይ ጥርጣሬ እንዳይፈጠር ሞትን ትቀምስ ዘንድ ልጇ ፈቅዷል። ይህ እነ አብሮኮሮስ በአጽንዖት ያስረዱት ነው። ይህ ምክንያት ቃል ሰው አልኾነም የሚለውን ክሕደትናና እርሷም ሰው አይደለችም የሚለው ስሕተት የሚያርም ነው።

3) ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዳለው ያረፈችው የልጇን የሞት ጽዋ ለመቅመስ ነው። ይህም እንዲኾን የእርሱ ፈቃድ ነው።

4) ሞቷ የመሸነፍ ሳይኾን የክብር እና የድል እንደ ኾነ እንድናውቅ ነው። ይህን ለመረዳት የሞቷን ዜና ከልጇ ዘንድ የተላከው ቅዱስ ገብርኤል ሊያበሥራት ሲመጣ የድል ምልክት የኾነውን የዘንባባ ዝንጣፊ ይዞ መምጣቱን እነ ማክሲሞስ ተናዛዚው የቀደሙ ትውፊቶችን ማዕከል አድርገው "The Life of The Virgin" በሚለው መጽሐፍ ዘግበዋልና።

5) ሞቷ ተራ ሞት ሳይኾን በመደነቅና በመገረም የሚናገሩት ሞት ነው። ቅዱስ ያሬድ "ማትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኲሉ" - ሞትማ ለሚሞት ይገባል የማርያም ሞት ግን ለኹሉ ያስደንቃል" የሚለው ለዚህ ነው። እንደ በሥጋና በደም ኾነን በድፍረት ከመናገር ልንቆጠብና ልናደንቅ ይገባል።
ማሜይዝም ይለምልም 💪😜
😁6
40 ገርፈን ቀይደር ካልተጠመቁ እና ቀኖና ካልተሰጣችሁ .....
😢8🥱2👍1🤯1
ቅዳሜ እና እሁድ መስቀል አደባባይ ሰለዋት ካልሰገዳችሁ የሚል ወሂ ወርዶልኛል 😎


እኔ እምለው ክርስቲኖች ላይ የሚያቅራሩት #አብዱሎች እኛ በሶ የጨበጥን መስሏቸው ነው 😳
👍2
ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ የመጡት Franklin Graham ትውልድ ቀዬያቸው መለኮታዊ ጥሪ ርቆታል።
Franklin አሜሪካዊ ናቸው። በሀገራቸው አሜሪካን ሀገር 65 በመቶ ከቁጥጥራቸው ውጪ ነው (ፕሮቴስታንት የሚለውን እንደው ብንቀበለው)። የሚገርመው ደግሞ እግዚአብሔር የለም የሚል Etheist 95 ሚሊዮን ፤ በአምላክ ስጦታ አናምንም በማለት ጾታቸውን የቀየሩ፤ ግብረ ሰዶም ጋብቻ የፈጸሙና ጠቅላላ LGBTQ ደግሞ 23 ሚሊዮን ሕዝብ በጉያቸው ታቅፈዋል። ከዚያው ስንወጣ እሳቸው በተወለዱባት አሜሪካ ግዛት Asheville, North Carolina ከጠቅላላ 94,589 ሰዎች 50% ብቻ ነው ፕሮቴስታንት፤ 35% አምላክ የለምና ወደ ላይ የሚሸኑ ሲሆን የቀረችው 15% ሌላ ሃይማኖት የሚከተሉ ነው።
እንደው ይታያችሁ! ከ2019 ጀምሮ ብቻ ወደ 4,500 የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች ከተዘጉበት ከተማ ነው የመጡት። በSouthern Baptist Convention (SBC) ደግሞ (ጥናቶች እንደሚያሳዩት) በ2022 ብቻ 50,423 ፕሮቴስታንት ቸርቾች ተዘግተዋል።
ተመልከቱ! ብያንስ የትውልድ ቦታቸውን፤ ከፍ ብለው የሚኖሩባትን ሀገር ወንጌል ሳያሳምኑ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው መለኮታዊ ጥሪ ልያቀብሉን። እጅግ በጣም የሚያሳዝነውና ጉዳዩ ትንኮሳ እንደሆነ የሚያረጋግጥልን ደግሞ ትክክለኛ ሥርዓተ አምልኮ ለመፈጸም ሳይሆን መቆሚያ፤ ከበሮና ጸናጽል በመያዝ ወደ መስቀል አደባባይ ወጥተው ጊዜ የሰጣቸው ቅሎች ድንጋይ ለመስበር መሞከራቸው ነው። ጸናጽልና መቆሚያ ለመያዝ ብያንስ ቅዱስ ያሬድን ማወቅና መቀበል ያስፈልጋል።
4👍3🤔1
ይህ መሳለቅና መንግስታዊ ድጋፍን በመተማመን የተደረገ ድፍረት እንጂ ንጹህ አምልኮ አይደለም፤ በዚህ ደግሞ እግዚአብሔር አይከብርም። ነገ ሌላ ቀን ነው!
አንጋፋው የግጥም ደራሲ ይልማ ገ/አብ እንዲህ ብሎ ነበር👇
አበባም አብቦ ሲበቃው ይደርቃል፣
ልብስም አጊጦበት እያጠቡት ያልቃል፤
ሰውም ይክረም እንጂ ቦታውን ይለቃል።
©ደግነህ ዘርፉ
1👍1🤔1
በቤተ መንግስቱ አዳራሽ 1200 ፓስተሮች ሲሰለጥኑበት ዋሉ

በብልፅግና መንግስት ድጋፍ እና ትብብር ዛሬ በቤተ መንግስቱ አዳራሽ 1200 ፓስተሮች " ስልጠና ተሰጥቷቸዋል ።

የስልጠናው ዋና ጭብጥ እግዚአብሔርን ከተከተልክ በቁሳዊ ሀብት መበልፀግ የመባረክህ ምልክት ነው የሚል ነው።
DEWOL ደወል ሚዲያ
👍3
አይ ኢቲቪ ስብከት ማስተላለፉ ሳያንስ ጭራሽ ለአፅዕኖተ ነገር እንዲሆን ቆርጦ በድጋሚ “የፍራንክሊን ግራሃም ስብከት” ብሎ ጫነ።

በነገራችን ላይ እንዲህ ያለ መድረክ ቀርቶ በዓመት በሚታወቁና በካሌንደር በሚዘጉ ሃይማኖታዊ በዓላት አከባበር በሚኖር የቀጥታ ሥርጭት የetv ኤድቶሪያል ፖሊሲ ጥቅል ሃሳብ ይህ ነው።

ማንኛውም የሃይማኖት በዓል የቀጥታ ሥርጭት ላይ ስብከት ወይንም ሃይማኖታዊ ትምህርቶች አይተላለፉም። ይህ ግን መልእክቶችንና ክዋኔዎችን አይመለከትም።

ለዚህም ነው ካያችሁ መስቀል ወይ ጥምቀት አከባበር በቀጥታ ሲሰራጭ ስብከት መርሐ ግብር ላይ ጋዜጠኞቹ ተሳታፊ እንግዳ በማስገባት ተሯሩጠው ሚያቋርጡት።

ዛሬ እንደመንፈሳዊ ጣቢያ የእገሌ ስብከት ቢል የቀድሞ ቤቴ ምን አገኘው ብዬ ነው እንጂ ለማን አማው ነበር?

ደግሞም አምቼውም አላውቅ!
😁7👍1
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የጥቃት ዓላማ ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮች እንዲቆሙ ምእመናን ጠየቁ !

መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዒላማ ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮች እና መልእክቶች በአፋጣኝ እንዲቆሙ እና መንግስትም ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ቲኤምሲ ያነጋገራቸው ምእመናን ገልጸዋል።

ማናቸውም ቤተ እምነቶች መብቶቻቸው እንዲከበር እንደሚፈልጉትና የሃይማኖታቸውን አስተምህሮ በነጻነት ማስተላለፍ ሕገ መንግስታዊ መብታቸው እንደሆነ የጠቆሙት አስተያየት ሰጪ ምእመናኑ በተመሳሳይም ሁሉም ቤተ እምነቶች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነት እና አስተምህሮ ባከበረ መልኩ ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት ነጻነታቸውን ተጠቅመው በማናቸውም መልኩ ሃይማኖታቸውን ማራመድ ሕገ መኖግስታዊ መብታቸው ቢሆንም የሌላውን እምነት ማንቋሸሽ፣ ማኮሰስ እና ማጥላላት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እና ግጭት ቀስቃሽና ጸረ ሰላም እንቅስቃሴ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ባለፉት ጊዜያት ከአንዳንድ ቤተ እምነት ተከታዮች ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለ ቅዱሳን፣ ስለ ንዋያተ ቅድሳት ብሎም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት በምታስተምቸው ትምህርቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮች ሲተላለፉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።

በተለይም መዋቅራዊ ድጋፍ እየተሰጠው በሚመስል መልኩ የጥላቻ ንግግሮች ተባብሰው መቀጠላቸው እና ይኸው ጥላቻም በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ብቻ ሳይሆን በሜንስትሪም እና በመጽሐፍትም ጭምር ሲካሄድ መቆየቱ እና እየተካሄደ መሆኑ በርካታ ምእመናንን ያሳዘነና ያስቆጣ መሆኑ ተመላክቶአል።
👍4
መንግስት እነዚህን የጥላቻ አራማጆች እና ጸረ ሃይማኖት ግለሰቦችን በሕግ አግባብ እንዲጠይቅም ምእመናን ጥሪ አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተሠጠ መግለጫ

“የሃይማኖት ንጽጽር - በከፍተኛ የሃይማኖት ሊቃውንቶች መካከል በሕግ፣ በሥርዓት እና በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚመራ በዶግማዊ ጉዳዮች ላይ የሚደረግ የሰከነ ውይይት ነው፤ በአማኞች መካከል የሚደረግ ሥርዓት የለሽ እና አንዱ ሌላውን የሚያውገዝ፣ የሚያጠልሸ እና ክብረ-ነክ መሆን ወንጅል ነው፤” ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የማኅበራዊ ሚዲያውን እድገትና ተደራሽነት መስፋትን ተከትሎ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ አጀንዳዎች ላይ በአወንታዊነት እና በአሉታዊነት የሚፈረጅ ይዘት ያላቸው ሥራዎች ተሠርተው አየር ላይ ሲውሉ እናያለን፤

አንዳንዶች ደግሞ የራሳቸውን የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ በመክፈት የተለያዩ ግለሰቦችን ወደመድረካቸው በመጋበዝ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በደጋፊነት እና በነቃፊነት ላይ ተሰልፈው የጦፈ ክርክር ሲደርጉም እንመለከታለን፡፡

ዘርፉና የመገናኛ መድረኩ የራሱ የሆነ የአጠቃቀም መመሪያ ያለውና በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ የሚጠበቅ ቢሆንም አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች መድረኩን ከዓላማው ውጪ ለሆነና ለግልና ቡድናዊ ፍላጎታቸው መጠቀሚያ በማድረግ በተለያዩ ሃይማኖት/እምነት ተከታዮች መካከል መተማመኑ እና መከባበሩን የሚሸረሽሩ ይዘቶችን፣ ክብረ ነካዊ በሆነ አቀራረብ ግልፅ ጥላቻን የመስበኩ ልምምድ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ ይገኛል፡፡

ይህ ዓይነቱ አቀራረብና ልምምድ አልፎ አልፎ በአንዳንድ የሃይማኖት ተቋማት ውስጥ በመደበኛ የአምልኮ መርሀ ግብር ላይ በፊት ለፊት መድረኮች ሲቀርብ አይተናል፡፡ ልምምዱና አቀራረቡ ከወዲሁ ሊታረምና በሕግና ሥርዓት ሊከናውን እንደሚገበው ጉባኤያችን በጽኑ ያምናል፡፡ ከዚህ አንፃር ከሰሞኑ የሁለቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች የተቀደሰ የጾም፣ የጸሎትና በከፍተኛ ደረጃ የመንፈሳዊ እነፃ ላይ በሚገኙበት ጊዜ ከመንፈሳዊነትና ከሃይማኖቶች መሠረታዊ ዕሴት ጋር የሚቃረን ተግባር በማኅበራዊ ሚዲው በስፋት እየተሠራጨ ይገኛል፡፡

በተለይም አንዳንድ የኦርቶዶክስ ክርስትና አማኝ ነን የሚሉ ግለሰቦች፣ የእስልምና ሃይማኖት ነቢይ በሆኑት በነቢዩ መሐመድ (የአላህ እዝነትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና) ላይ ድፍረት የተሞላበት ክብረ ነክና ጽያፍ ንግግር ሲያደርጉ ታየረተዋል፡፡ ይህም ሙስሊሙን ወገን ብቻ ሳይሆን ሰላም ወዳዱን ወገን ሁሉ አሳዝኗል፡፡

ጉባኤችንም ይህ ዓይነቱ ኢ-ሥነምግባራዊ እና ሕገ ወጥ ተግባር የትኛውንም የሃይማኖት ተቋም የማይወክል፣ ይልቁንም የሚወገዝ ተግባር መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንዳንድ የኦርቶዶክስ አማኝ ነን የሚሉ ወንድሞችና እህቶች የግለሰቡን ሕገ-ወጥ ተግባር ተቋማዊ ለማድረግ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያጤኑና ግለሰብንና ተቋምን እንዲለዩ እንመክራለን፡፡

በአንፃሩ አንዳንድ ሙስሊም ነን የሚሉ ግለሰቦች ተደፈርን በሚል ስሜት የክርስትና አስተምህሮንና የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር የሚነቅፍና የሚያጠለሽ፣ መላውን ክርስቲያን በሚያዋርድ መልኩ ምላሽ ሲሠጡ እና ድርጊቱን በፈፀመው ግለሰብ ላይ የደቦ ፍርድ ሲያስተላልፉ ይታያሉ፡፡

ይህም ሕገ-ወጥነትን ከማስፋፋት ባለፈ ጥፋትን በሌላ ጥፋት ማረም ፈጽሞ የማይቻል መሆኑን ተገንዝበው ከድርጊታቸው በመታረም የሕግ የበላይነትን እንዲስቀድሙ ጉባኤያችን በአጽንኦት ይመክራል፡፡ በየትኛውም አካል የተፈፀሙትና የሚፈፀሙት ይህን መሠል ሕገ-ወጥ ተግባራት በሁሉም ሃይማኖቶች አስተምህሮ ተቀባይነት
የሌላቸው ብቻ ሳይሆን የሚወገዙ ተግባራት መሆናቸውን ጉባኤያችን እያስገነዘበ ድርጊቱ በወንጀል የሚስጠይቅ ስለመሆኑም ለማስታወስ ይወዳል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሀ ሀይማኖት መገኛና መኖሪያ ከመሆኗ አንፃር የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የትኛውንም ዓይነት የሃይማኖት ተቋማትን፣ አስተምህሯቸውንና መገለጫዎቻቸውን የሚያንቋሽሹና የሚያዋርዱ ንግግሮችንም ሆነ ተግባራትን በጽኑ ያወግዛል። እንዲህ ያሉት ክብረ-ነክ የሆኑ ተግባራትና አስተያየቶች ሁሉ ድርጊቱ ለተፈፀመባቸው እምነት ተከታዮችን በእጅጉ የሚያስቆጡ ብቻ ሳይሆኑ መላ ኢትዮጵያዊያንን በእጅጉ የሚያስቆጡ ናቸው፡፡ የመከባበርና የአብሮነት እሴቱን በመሸርሸር በሀገራችን የሰላምና የሰላማዊ ማህበረሰብ ግንባታ ሂደቱንና ጥረቱን እንዳይያሳካ ያደርጋሉ፡፡

ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አንዱ የሌላውን እምነት ለመስደብ ወይም ለማዋረድ በፍፁም ጥቅም ላይ መዋል የለበትም። የእምነት ነፃነት እና የማምለክ መብት ለሁሉም ማህበረሰቦች የተጠበቀ ሲሆን ይህ መብት የሌሎች አማኞችን መብት በመጋፋና ስሜት በመንካት ለጠብ ማነሳሽነት ሲውል በዝምታ ሊታለፍ አይገባውም፡፡
ይህንን ከባድ ጥፋት በዘላቂነት እንዲታረም የሚመለከታቸው አካላት አግባብነት ባላቸው ሕጎች መሰረት ይህንንና ተመሳሳይ ተግባር በፈፀሙና በሚፈጽሙ አካላት ላይ አፋጣኝ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን። ለእንደዚህ አይነት ወንጀሎች ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ለወደፊቱ የሃይማኖትን ስም ማጥፋት ለመከላከልና የሁሉም እምነት ተከታዮች ክብርን ለመጠበቅና
ለማስጠበቅ በእጅጉ ይረዳል።

በተጨማሪም የሃይማኖት መሪዎች፣ የሃይማኖት ምሁራን እና መላ ሕብረተሰቡ በሃይማኖቶች መካከል መከባበር፣ መግባባትና መረዳዳት ይበልጥ ሊያጠናክሩ በሚያስችሉ የጋራና የተመረጡ አጀንዳዎች ላይ በሕግ፣ በሥርዓትና በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚመሩና ግልጽ ዓላማና ግብ የተቀመጠላቸው ውይይቶችና ምክክሮች በተጠናከረ መልኩ በማከናውን በሃይማኖቶች መካከል ትብብራቸውንና አጋርነታቸውን እንደ ሚያጠናክሩ ይጠበቃል፡፡

በቅርቡ ጉባኤያችን ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በመዳሰስና በመተንተን ሀገራዊ ዓውዱንና ተግዳሮቶች ታሳቢ በማድረግ፣ እንዲሁም ተቋሙ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል የመተዳደሪያ ደንቡን አሻሽሏል፡፡ የተሻሻለው ደንብም በተቋማት መካከል አለመከባበርን፣ አለመቻቻልን የሚሰብኩ፣ ጥላቻን የሚቀሰቅሱና ግጭትን የሚያባብሱ ተንኳሽና ክብረ-ነክ ንግግሮችንና ተግባራትን የሚፈፅሙ ግለሰቦችና ቡድኖች በራሳቸው ተቋም ተጠያቂ የሚያደርግ ሥርዓት እንዲኖር የሚያደርግ ድንጋጌ በደንቡ ላይ እንዲካተት ተደርጓል፡፡

የችግሩ ስፋትና ጥልቀት እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞም ችግሮን በዘላቂነት ለመፍታትም ከአባል የሃይማኖት ተቋማት የሚወከሉ የሕግና አግባብነት ያላቸው ባለሙያዎች የሚካተቱበት የተከላካይ ግብር-ኃይል አደረጃጀት በጊዜያዊነትና በቋሚነት በማደራጀት የቅደመ መከላከል ሥራዎች ለመስራት ተዘጋጅቷል፡፡

ግብር-ኃይሉም ችግሮችንና የችግር አዝማሚያዎችን በማሰባሰብ፣ በመተንተንና የመፍትሔ ሀሳቦችን በመስጠት ሙያዊ እገዛ በማድረግ ሕግና ሕጋዊነትን የማስጠበቅ ሥራ በመስራት የሀገር ሰላምንና የሃይማኖት ተቋማትን ክብርና ልዕልና የማስጠበቅ ኃላፊነቱን ይወጣል፡፡

የሁለቱም እምነት ተከታዮች እና አማኞች በማኅበራዊ ሚዲያው ባለው አሉታዊ ዘመቻና በተፈጠረው ወቅታዊ ችግር ሳይረበሹ የጾም፣ ጸሎትና የንስሀና ተግባሮቻቸው ላይ እንዲያተኩሩ ጉባኤያችን ይመክራል፡፡

የሕግ አስከባሪ አካሉም፣ በአማኞች መካከል ያለው ሰላምና መከባበር የሚያውኩ፣ ሕገ-ወጥ ግለሰቦችና ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲታረሙ በማድረግ ሕግና ሥርዓት የማስጠበቅ የተለመደ ሕጋዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጉባኤያችን ጥሪውን ያቀርባል፡:

በመጨረሻም ሁላችንም የሃይማኖት ተቋሞቻችንንና የአስተምህሯችንን ክብር፣ ልዕልናና ቅድስና እንጠበቅ በማለት ጉባኤያችን የአደራ መልዕክቱንና ጥሪውን ያቀርባል፡፡
👍1
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ - ለሰላም፣ ለመተባበር እና ለአብሮነት
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ
መጋቢት 2 ቀን 2017
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
2025/07/08 15:33:38
Back to Top
HTML Embed Code: