አልወጣም ከቤቴ!
ክፍል 8
መሀመድ፡- እሺ ሳሙኤል አፅናኙ ማን ነው ከአንተ መልስ እንጀምር
ሳሙኤል፡- እሺ መፅሀፍ ቅዱሳችን እንደሚነግረን ከክርስቶስ በኋላ ይመጣል የተባለው አፅናኝ መንፈስ ቅዱስ ነው። አንተ ማን ነው ትላለህ?
መሀመድ፡- እንደ እውነቱ መንፈስ ቅዱስስ አይደለም ይህ ይላካል የተባለው ነብያችን መሀመድ ሰ . ወ. ሰ ነው
ሳሙኤልም ፈገግ አለ አስከቶም
ሳሙኤል፡- እሺ ለእዚህ ማስረጃህ ምንድነው?
መሀመድ፡- ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ በመፅሀፋችሁ ኢሳ ሲጠመቅ ነበር በእርግብ አምሳል የወረደው እና አንተ እንዳልከው ከወሰድን መንፈስ ቅዱስ ሁለት ጊዜ ነው የወረደው ያስብለናል
ሳሙኤል፡- አይ አይደለም እዚህ ጋር ተሳስተሀል መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ ለክርስቶስ ብቻ ነው የወረደለት እሱም ላይ ብቻ ነው ያረፈው ክርስቶስ ሳይወሰድ በፊት መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ዘንድ አልነበረም።
መሀመድ፡- ለእዚህ ማስረጃህ ምንድነው?
ሳሙኤል፡- የማመጣልህ መረጃ ከዮሀንስ ወንጌል ላይ ሲሆን
ዮሐንስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
❝³⁸ በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ።
³⁹ ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ ገና አልወረደም ነበርና።❞
እዚህ ጋር እንደምንመለከተው ክርስቶስ ኢየሱስ በእሱ ለሚያምኑት ደቀ መዛሙርቱ ስለ ሚያጠምቃቸው መንፈስ ቅዱስ እየተነበየ ነው ይህም የሚያሳየን ክርስቶስ ኢየሱስ በምድር በሚመላለስበት ሰአት መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ዘንድ እንደሌለ ነው።
መሀመድ፡- እሺ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃል ነው ያልከው የሱንም መረጃ እግረ መንገድህን?
ሳሙኤል፡- መልካም ከአንድም ሁለት አመጣልሀለው።
❝እኔም አላውቀውም ነበር፥ ዳሩ ግን በውኃ አጠምቅ ዘንድ የላከኝ እርሱ፦ መንፈስ ሲወርድበትና ሲኖርበት የምታየው፥ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ እርሱ ነው አለኝ።❞
—ዮሐንስ 1: 33
እዚህ ጋር የመጥምቁ ዮሀንስን ምስክረት እንመለከታለን ክርስቶስ ኢየሱስም እራሱ ቃል በቃል የተናገረበትን ቦታ ላምጣልህ
ሐዋርያት 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
❝⁴ ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፥ ነገር ግን፦ ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቁ፤
⁵ ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ አለ።❞
መሀመድ፡- መልካም ልጅ ሳሙኤል ያ መንፈስ አሁን የታል አሁን እንዴት ነው የሚያፅናናው?
ሳሙኤል፡- ችግር የለውም ስለሱም እንደርሳለን ግን አሁን ውይይት እንደመሆኑ መጠን እኔም እንድጠይቅ ይፈቀድልኝ
መሀመድ፡- እሺ ችግር የለውም
ሳሙኤል፡- መሀመድ ነው ስለማለትህ መረጃ አምጣልኝ
መሀመድ፡- ከእኔ በኋላ የሚመጣው እያለ ሲናገር የነበረው ስለ መሀመድ ነው ፍፃሜውን እንግዲህ የመፅሀፉ ሰዎች እንደፈለጉ በርዘውታል
ሳሙኤል፡- በርዘውታል? እሺ መልካም ፍፃሜውን ካልተበረዘው መፅሀፍ ታመጣልኛለህ ማለት ነውፍ
መሀመድ፡- ቁርአንና ሀዲሳት ማስረጃ ይሆናሉ ነብያችን ኢሳ አፅናኙ ሲል የነበረው ስለ መሀመድ ነው!
ሳሙኤል፡- እሺ እንደዛ ከሆነ ጌታ ኢየሱስ የተናገረለትን አፅናኝና የመሀመድን ማንነት እያመሳሰልን አፅናኙ እርሱ ነው አይደለም የሚለውን እንወስናለን አይሻልም?
መሀመድ፡- እሺ ጥሩ
ሳሙኤል፡- እሺ ክርስቶስ ስለ አፅናኙ የተናገረበትን ቃል እንየው የመጀመሪያው መስፈርት
ዮሐንስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
❝¹⁵-¹⁶ ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤
¹⁷ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።❞
አንደኛው አፅናኙ አለም የማያየው መንፈስ እንደሆነ ይናገራል ይህንን መስፈርት መሀመድ ያሟላል ወይ? መሀመድ መንፈስ ነው? በሰዎች ውስጥ ይኖራል?
መሀመድ፡-.....................
ሳሙኤል፡- አያሟላም ምክንያቱም መሀመድ ሰው እንጂ መንፈስ አይደለም ሰውም በሰው ውስጥ ሊኖር አይችልም!
መሀመድ፡- መንፈስን መፅሀፍ ቅዱስ በአንድ መንገድ ብቻ አልገለፀውም በአንዳንድ ቦታላይ ነብያትንም መንፈስ ብሏል
❝ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።❞
—1ኛ ዮሐንስ 4: 1
ሳሙኤል፡- ይህ ደግሞ ሀሰተኛ ነብያቶች ተገለጠልን ብለው ከሚያመጡት ተረት ተረትና የውሸት መንፈስ እንድንርቅ የሚሰጥ ማድጠንቀቂያ እንጂ ከምናወራው ነገር ጋር ምንም አይገናኝም
ነብያቶች በእግዚአብሔር መንፈስ ተመልተው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራሉ ይፅፋሉ ሀሰተኛ ነበያቶች ደግሞ በውሸት መንፈስ እግዚአብሔር ተናገረኝ እያሉ ሰውን ያስታሉ ይህ ነው ሌላ አዲስ ነገር የለውም።
❝ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።❞
—2ኛ ጴጥሮስ 1: 21
መሀመድ፡- እሺ በሁለተኛው መስፈርት እንቀጥል
ሳሙኤል፡- እሺ የአንደኛው መስፈርት ውድቅ መሆኑ ይህ ቃል ለመሀመድ እንዳልሆነ ከሆኑት ማስረጃዎች እንደ አንዱ ይወሰድልኝ በተጨማሪም ይህ አፅናኝ የተባለው መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ከነ ማስረጃ ማቅረብ እችላለሁ
አለም አያየውም፡- ❝በሁሉም መንፈስ ቅዱስ #ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።❞
—ሐዋርያት 2: 4
በሰዎች ውስጥ ይገባል እንጂ አንዳችም ሰው አያየውም!
በሰው ውስጥ ይኖራል፡- ❝በዚያን ጊዜ እጃቸውን ጫኑባቸው መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ።❞
—ሐዋርያት 8: 17
መሀመድ፡- ሁለተኛው መስፈርት?
ሳሙኤል፡- እሺ ወደ ሁለተኛው መስፈርት እንሄዳለን
❝አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።❞
—ዮሐንስ 14: 26
እዚህ ጋር የሚላከው አፅናኝ ክርስቶስ ስለሰበከው ነገር እንደሚያሳስብ ነው መሀመድ ክርስቶስ ስለተናገረው ነገር ያሳሰበው ነገር አለ?
መሀመድ፡- ................
ሳሙኤል፡- አሁንም መልስ የለም? በእዚሁ ውይይታችንን እናብቃ መንፈስ ቅዱስ ነው ብለን እንደምድመው?
መሀመድ፡- ልጅ ሳሙኤል መሀመድ መስፈርቱን አላሟላም ማለት የግድ መንፈስ ቅዱስ ነው ማለት አይደለም ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ስለመሆኑ የፍፃሜውን መረጃ አላመጣህም
ሳሙኤል፡- ምንም ችግር የለው የሱንም ማስረጃ ላመጣልህ እችላለሁ
ሐዋርያት 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
❝¹ በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥
² ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።
³ እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።
⁴ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።❞
ይህ መንፈስ ቅዱስ ከክርስቶስ በኋላ የወረደበት ቦታ ነው። ይኸው ማስረጃው
መሀመድ፡- ለዛሬ ውይይታችን ይብቃን መሰለኝ
ሳሙኤል፡- ጥያቄው ተመለሰልህ
መሀመድ፡- ብዙ ያልተመለሱልኝ ነገሮች ቢኖሩም ሙከራህ ጥሩ ነው
ሳሙኤልም ፈገግ አለ ይሄንን ጥያቄ የጠየቀው አዎ የሚል

👍12😁1
Forwarded from ልባም ሴት 😍
ሚካኤል ሚካኤል ስምህን ስጠራ
ይወገዳል ሸክሜ ይርቃል መከራ
አሁንም "ሚካኤል" ወዳጄ እና ቅርቤ
ፈዋሼ ፣ ታጋሼ ፣ቅርቧ ነህ ለልቤ
"ሚካኤል" "ሚካኤል" "ሚካኤል" ነህ ስንቄ
መንገዴን ጠራጊ ለድካሜ ትጥቄ
ሚካኤል ምርኩዜ የኃዘኔ መርሻ
ክፉን ቀን ማለፊያ ጭንቄን ማስታገሻ
ሚካኤል ሚካኤል ስምህን ስጠራ
ቀለል ይላል ሃዘን ይርቃል መከራ
እንኳን አደረሳችሁ ።
ይወገዳል ሸክሜ ይርቃል መከራ
አሁንም "ሚካኤል" ወዳጄ እና ቅርቤ
ፈዋሼ ፣ ታጋሼ ፣ቅርቧ ነህ ለልቤ
"ሚካኤል" "ሚካኤል" "ሚካኤል" ነህ ስንቄ
መንገዴን ጠራጊ ለድካሜ ትጥቄ
ሚካኤል ምርኩዜ የኃዘኔ መርሻ
ክፉን ቀን ማለፊያ ጭንቄን ማስታገሻ
ሚካኤል ሚካኤል ስምህን ስጠራ
ቀለል ይላል ሃዘን ይርቃል መከራ
እንኳን አደረሳችሁ ።
❤3🥰3👍1🙏1
አልወጣም ከቤቴ!
ክፍል 9
ሳሙኤልም መሀመድን ቤቱ ካደረሰው በኋላ ወደ ቤቱ ገባ መክሰሱንም በላና ሳይመሽበት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደ ።
መንግስተ አብ የተባሉትም ካህን ቁጭ ብለው እየጠበቁት ነበር ሳሙኤልም እንደደረሰ
ሳሙኤል፡- እንደምን ዋሉ አባ
መንግስተ አብ፡- እግዚአብሔር ይመስገን እንደምን ዋልክ ልጄ ናቁጭ በል
ሳሙኤል፡- እሺ አመሰግናለሁ
አላቸውና ቁጭ አለ። ነገሩን ከየት መጀመር እንዳለበት እንኳ ግራ ገብቶት አይኑን ከግራ ወደ ቀኝ ላት ታች ያደርገው ጀመር። ካህኑም ውስጡ ያለውን ሀሳብ ተረድተው
መንግስተ አብ፡- ልጄ ያደረግኸውን ነገር ሁሉ ንገረኝ
ሳሙኤል፡- እሺ አባ ከአህዛብ ጋር ቤተሰብ መስርቻለሁ እና አሁን ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም የሚስቴም አባት ብዙ ጊዜ እየተገናኘኝ እኔን ለመቀየር ይሞክራል እና ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም በእዚህ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት እንዳለኝ አስባለሁ በዛ በኩል ደግሞ ትዳሬ እንዳይፈርስ እፈልጋለሁ ከአህዛብ ጋር እየኖርኩኝ እንዴት ከእግዚአብሔር ጋር መቀላቀል እችላለሁ?"
መንግስተ አብ፡- መልካም ልጄ ከጥፋትህ ስንጀምር መጀመሪያ ያጠፋኸው ጥፋት ከአህዛብ ጋር ቤተሰብ መመስረትህ ነው አንተ ብርሀን ሆነህ ሳለህ ከጭለማ ጋር ህብረት ማድረግህ ነው ግን አሁን ከሁለት አንድ ሆናችኋል አንተና ባለቤትህ ሁለት ሳትሆኑ አንድ ናችሁ አንድ የሆነን ነገር ማናጠል እንደ መምህርነቴም ህሊናዬም ቢሆን አይፈቅድም ልጄ ይህ የአንተ ውሳኔ ነው የሚሆነው ጥፋት ሰርተሀል ያን ጥፋት ግን ማሻሻል ያለብህ አንተው ነህ ወይ ክርስቶስን ወይ ባለቤትህን ምረጥ ስለ አለም ነፍሱን የሚሰጥ ያጠፋታል ልጄ ግን ነፍሱን ስለክርስቶስ የሚያጠፋ ፈፅሞ ያድናታል።
ሳሙኤል፡- እሺ አባ አመሰግናለሁ ጥሩ ምክር መክረውኛል እግዚአብሔር ያክብርልኝ በእውነት እራሴን እንድመረምር አድርገውኛል
መንግስተ አብ፡- መልካም የእኔ ልጅ ተባረክልኝ ያልኩህ ነገር ግን በደንብ ገብቶሀል አይደል?
ሳሙኤል፡- አዎ አባ አመሰግናለሁ
መንግስተ አብ፡- እሺ ልጄ በማንኛውም ሰአት እዚሁ ቤተ ክርስቲያን ልታገኘኝ ትችላለህ
ሳሙኤል፡- እሺ ሰላም አምሹ አባ መሄዴ ነው
መንግስተ አብ፡- እሺ ልጄ ሰላም ሁንልኝ
ሳሙኤልም አናግሯቸው ወደ ቤቱ እየተመለሰ ብዙ ነገር አሰበ
"አሁን ግራ ተጋብተሐል ሳሙኤል በመጀመሪያም ከአህዛብ ጋር ቤተሰብ መመስረትህ ትክክል ባይሆንም ግን ስለ ክርስቶስ መመስከርህ ትልቅ የፅድቅ ስራ ሆኖልሀል።
ነገር ግን እስከመቼ ነው በእዚህ ሁኔታ የምትቀጥለው? ወደ ውሳኔ መቅረብ አለብህ ወይ ፈዲላን ወይ አምላክህን ምረጥ!" አለና ወደ ቤቱ ገባ መሽቶም ስለነበር ፈዲላን ጥሏት እራቱን በልቶ እንቅልፉን ተኛ። ብዙም ሳትቆይ ወደ ቤት መጣች ግን ሳሙኤል እንቅልፍ ወስዶት ነበር።
ሳትቀሰቅሰው ቀስ ብላ ወደ አልጋው ወጣችና አጠገቡ ተኛች።
አምስተኛ ቀን
ሳሙኤልም ከእንቅልፉ ተነሳ ሀሳቡ ወደ ስራ ሳይሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ነበር። ልብሱንም ለባብሶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደ ከእግዚአብሔርም ጋር በጣም ብዙ ነገር ተነጋገረ በመጨረሻም ፈዲላን ለመፍታትና ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ወስኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ።
ፈዲላም ጣፋጭ ቁርስ ሰርታ ጠበቀችው አብረው በሰላምም በሉ እንደጨረሱም ፈዲላን ስለ አንድ ነገር ሊያነጋግራት እንደሚፈልግ ነገራት ለውይይቱ እስክትዘጋጅ ቢሮው ቁጭ ብሎ ጠበቃት።
እሷም "ምን ሊለኝ ይሆን በሚል ሀሳብ" በፍርሀት በሩን አንኳኩታ ጠራችውና ሶፋ ላይ ቆጭ ብላ ጠበቀችው እሱም ወደ ሳሎን ተመልሶ ሶፋው ላይ ቁጭ አለ።
እሷም ወዲያው "እሺ ሳሚ ስለምን ጉዳይ ልትወያየኝ ነበር የፈለከው?"
ሳሙኤል፡- እንደምታውቂው ሁለታችንም የተለያየ ሀይማኖት ተከታዮች ነን
ፈዲላ፡- አዎን
ሳሙኤል፡- ስንጋባም ይህ ነገር በህይወታችን ላይ የሚፈጥረው ችግር አይኖርም ብለን ነበር
ፈዲላ፡- አዎን ነበር ብቻ ሳይሆን እስካሁን የፈጠረው ችግር የለም አይኖርምም አይደል?
ሳሙኤል፡- ብዙ የፈጠረው ችግር አለ
ፈዲላ፡- ምን?
ሳሙኤል፡- አዎን! እየውልሽ ነገሮችን እያበዛው ግራ አላጋባሽ ፍቺ እፈልጋለሁ ፈዲላ
ፈዲላ፡- ምን ማለት ነው?
ሳሙኤል፡- እንድንፋታ እፈልጋለሁ ፈዲላ ከእዚህ በላይ ፈጣሪዬን ማስቀየም አልፈልግም!
ፈዲላ፡- ቆይ ከእኔ ምን አጥተህ ነው ?
ሳሙኤል፡- እንደ ሚስትነት ያልሰጠሽኝ ነገር የለም እርሱን አውቃለሁ ግን እሱ አይደለም ችግሩ
ፈዲላ፡- ታዲያ ምንድነው ችግሩ
ሳሙኤል፡- ይህንን አባትሽን ለምን አትጠይቂውም? ከእኔ በላይ ያስረዳሻል!
ፈዲላ፡- ሳሚ የእኔና አንተ ነገር በእዚህ መጠናቀቅ ነበረበት?
ሳሙኤል፡- ፈዲላ እባክሽን ተረጋጊ እና ማለት የፈለኩትን ተረጂኝ?
ፈዲላ፡- ከእዚህ በላይ እንዴት ልረዳ? ልፋታ አልከኝ! ቆይ እኔ ያንተ ሚስት ለመሆን የሚጎድለኝ ነገር ምንድነው?
ሳሙኤል፡- እባክሽ ለመረጋጋት ሞክሪ እኔ ለሚስትነት አነስሽ አላልኩም!
ፈዲላ፡- እሺ ተረጋጋሁ! በል አስረዳኛ? እኔ ለሚስትነት ካላነስኩ ከኔ ጋር ለመፋታት ያነሳሳህ ምክንያት ምንድነው??
ሳሙኤል፡- ሁለታችንም የተለያየ ሀይማኖት ውስጥ ሆነን አብረን መቆየት አንችልም! ካንቺ ጋር መሆኔ ክርስቶስን እያሳዘንኩት እንደሆነ ስለተሰማኝ አሁን አዲስ የንሰሐ ህይወት እፈልጋለሁ
ፈዲላ፡- አንተም እኔም በሀይማኖታችን መኖር እንችላለን
ሳሙኤል፡- ይህ ይሁን ብዬ አብሬሽ መኖር ጀምሬ ነበር ግን አባትሽ አንቺ እንደምታስቢው አያስብም ሁሌም ሊለውጠኝ ይሞክራል..... አይሆንም! አልክድም ክርስቶስን አልወጣም ከቤቴ! ይህንን ማሳየት ያለብኝ በከፊሉ እርሱን ባለመካድ ብቻ ሳይሆን ስጋዬንም ለሱ በማስገዛት ነው ስለዚህ ይህንን ለማድረግ የግድ መፋታት ይኖርብናል!
ፈዲላ፡- ተው ሳሚ አትጨክንብኝ በኋላ ይቆጭሀል
ሳሙኤል፡- አሁን የምወጣው ከአለማዊ ቤቴ ነው ፈዲላ ግን ከዘላለማዊ ቤቴ መቼም አልወጣም!
አላትና ወደ መኝታ ቤት ሄደ እሷም ሶፋው ላይ ቁጭ እንዳለች ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች። እየሮጠችም ወደ መኝታ ቤት ገብታ "ከአንተ ጋር እንድሆን የሚያስደርገኝ ነገር ኢሳን ማምለክ ከሆነ አመልከዋለሁ ሳሚ ጥለኸኝ አትሂድ!"
ሳሙኤልም ሁኔታዋ በጣም አሳዘነው ልቡም ደማ "አይ! ፈዲላ ተይ እባክሽ ለእኔ ብለሽ ሀይማኖትሽን መቀየር የለብሽም እንዲህም እንድታደርጊ እኔ አልፈቅድልሽም ኢየሱስን ምታመልኪው ከእኔ ጋር ለመሆን ሳይሆን እውን አምላክ ነው ብለሽና ህይወት እንደሚሰጥሽ በማመን ነው።"
ይቀጥላል........
@nubeberhanutemelalesu

❤2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንድም ያልተጨመረ ፣ ያልተቀነሰ ፣ ለማሜ የተሰጠው ያልተበረዘው ቁርዓን በሸሆች እይታ(AKA most respected scholars )
አልወጣም ከቤቴ!
ክፍል 10
ፈዲላም እየሮጠች በመውጣት ለአባቷ ደውላ የተፈጠረውን ነገር ሁሉ ነገረችው መሀመድም በፍጥነት መኪናውን አስተስቶ ወደነ ፈዲላ ቤት ሄደ። ሳሙኤልም ቁጭ ብሎ ቀጥሎም ምን ሊፈጠር እንደሚችል ያስብ ነበር። ፈዲላም ልቧ እጅጉን ተሰብሮ እዛው በረንዳ ደረጃው ላይ ቁጭ ብላ ታለቅስ ነበር።
መሀመድም እንደደረሰ "ልጄ! .... " እያለ ወደ በረንዳአ በፍጥነት ደረሰ ፈዲላም መሀመድ ላይ ጥምጥም ብላ "አባ ሳሚ ጥሎኝ ሊሄድ ነው!" ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ።
መሀመድ፡- አታልቅሺ ልጄ ለምን ታለቅሻለሽ ሳሚ ጥሎሽ ወዴትም አይሄድም
ፈዲላም፡- አይ አባ ሊሄድ ነው ይህም ያንተ ምክንያት ነው አንተ ስለ ሀይማኖት ባታነሳበት ኖሮ እንዲህ ባላደረገ ነበር።" ብላ ጮኸችበት
መሀመድ፡- ተረጋጊ ልጄ ቆይ ሳሚን ላናግረው
አላትና ወደ ቤት ገባ ሳሎን ማንም የለም ነበርና መኝታ ቤት ይሆናል ብሎ ሲሄድ አገኘው።
መሀመድ፡- ሰላም ነው ሳሙኤል እንደምን አደርክ?
ሳሙኤል፡- ውይ አባ መጣህ እንዴ? እግዚአብሔር ይመስገን
መሀመድ፡- ጥሩ ሳሙኤል ከፈዲላ የምሰማው ነገር ምንድነው?
ሳሙኤል፡- አዎን አባ እኔና ፈዲላ ልንፋታ ነው!
መሀመድ፡- ለምን?
ሳሙኤል፡- ከእዚህ በላይ አምላኬን ላሳዝነው አልፈልግም
መሀመድ፡- ይህ ምን ማለት ነው?
ሳሙኤል፡- ይህ ማለት ከዛሬ ጀምሮ የንሰሀ ይወት ልጀምር ነው ማለት ነው
መሀመድ፡- ይህንማ እኔ ልሰጥህ ነበር ድክመትህ ነው እንጂ ማምለክ ያለብህን የአለማትን አምላክ ላሳውቅህ ነበር
ሳሙኤል፡- አየህ አባ አንዱም ይህ ነው ከፈዲላ ጋር እንድፋታ የሚያደርገኝ ነገር
መሀመድ፡- እሺ እሺ ተወው በቃ ልጅ ሳሙኤል! ከፈዲላ ጋር እርቅ አውርዱ
ሳሙኤል፡- መጀመሪያውንም አልተጣላንም አባ መፋታት ማለት መጣላት አይደለም
መሀመድ፡- እሺ አትፋቱ
ሳሙኤል፡- አልችልም!
መሀመድ፡- የፍቅር መስዋእት እስከዚህ ድረስ ነው በቃ?
ሳሙኤል፡- የፍቅርን መስዋእትማ በመስቀል ከተሰዋው በላይ ያሳየኝ የለም እኔም ስለሱ እሰዋ ዘንድ ነፍሴን እጠብቃለሁ
መሀመድ፡- አይ ልጅ ሳሙኤል ተረጋግተህ አስብበት በኋላ ሊከነክንህ ይችላል
ሳሙኤል፡- አስብቤታለሁ አሁን ሻንጣዬን ላዘጋጅ ነው ካላስቸገርኩህ ሄደህ ፈዲላን በወረቀቱ ላይ የፍቺን ፌርማ እንትፈርም አስማማት
መሀመድ፡- ኧረ ልጅ ሳሙኤል ተው! እንደ አባትነት ነው ምመክርህ ለትንሽ ነገር ብለህ ትዳርን የሚያህል ነገር አታፍርስ
ሳሙኤል፡- ለኔ ትንሹ ነገር የእዚህ አለም ህይወት ነው እኔ ለእዚህ አለም እንግዳ ነኝ እንግዳም በሰው ቤት አይቆይም ሌላ የሚሄድበት ቤት አለው በእንግዳነት ባለበት ቤት ሆኖ ሳለ ግን የሚጠብቀውን ቤቱን ከረሳው ከዛ ቤት ተባሯል
መሀመድ፡- ከምትለው አንዳችም አልገባኝም ግን እሺ ይሁን ፈዲላ ጋር ልሂድ
ሳሙኤልም ሻንጣ አዘጋጀና ቁምሳጥን ውስጥ ያሉትን ልብሶቹን ወደ ሻንጣው ይከት ጀመር። መሀመድም ወደ ፈዲላ ሄደ ቁጭ ብላ ትተክዝ ነበር
መሀመድ፡- ልጄ ተይ እንጂ
ፈዲላ፡- ሳሚ ጥሎኝ ሊሄድ ነው
መሀመድ፡- ይሂዳ በአለም ውስጥ ሳሙኤል ብቻ አይደለም ወንድ ያለው እራስሽን እሱ ላይ ጥገኛ አታድርጊ ልጄ አሁን ቀጥሎ ሊመጣ ላለው ነገር አስቢ
ፈዲላ፡- አባ ነግሬህ ነበር አይደል? ይህ የማን ጥፋት ነው?
መሀመድ፡- ተይ ልጄ ጥፋቱን በእኔ አታድርጊው ሳሙኤል ሊፋታሽ የፈለገው አምላኩን ማሳዘን ማቆም እንዳለበት አስቦ እንጂ እኔ ስለ ሀይማኖት ስላነሳሁበት አይደለም እሱንም ነግሮኛል
ፈዲላ፡- እሺ አሁን ምን ሊውጠኝ ነው?
መሀመድ፡- ምንም የሚያስፈራ ነገር የለም ነይ ተነሺ ልጄ ተረጋጊ ያለ ነገር ነው።
ፈዲላ፡- እሺ አባ
መሀመድ፡- እኛ ጋር ትቆያለሽ ወይንስ?
ፈዲላ፡- መፋታት ካለብን እሱ ሳይሆን እኔ ነኝ ከቤት መውጣት ያለብኝ ምክንያቱም ቤቱን እኔን ከማግባቱ በፊት በላቡ የሰራው ነው
መሀመድ፡- እንደሱ ካልሽም ጥሩ ልጄ እኛ ቤት እስከፈለግሽበት ቀን ድረስ መቆየት ትችያለሽ
አላትና ወደ ቤት ይዟት ገባ። ሳሙኤልም ልብሱን ከቶ ከጨረሰ በኋላ ወደ ሳሎን ሻንጣውን እየነዳ መጣ ፈዲላም ስታዬው በድጋሚ ፊቷ በእምባ ተመላ።
መሀመድ፡- ልጄ ቁጭ ብለህ ግን ብታስብበት አይሻልም?
ሳሙኤል፡- መናገር ያለብኝን ተናግሬያለው አባ ፈዲላ ከእኔ ጋር በመፋታቷ እንዲህ ስሜቷ ሊጎዳ አይገባም በእዚህ ፀባዩኣ ከእኔ የተሻለ ጥሩ ባል ታገኛለች........ ተይ ፈዲላ የምትወጂኝ ከሆነ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማኝ አታድርጊ ምክንያቴ ሰልችተኝ ወይም አስጠልተሽኝ እንዳልሆነ ደጋግሜ ነግሬሻለሁ ልቦናሽም ያውቀዋል!
መሀመድ፡- አዎ ልጄ እንዲህ ልትጎጂ አይገባም
ፈዲላ፡- እሺ ግን አንተ ሳትሆን እኔ ነኝ ከእዚህ ቤት መውጣት ያለብኝ ይህ ያንተ ቤት ነው
ሳሙኤል፡- ተይ ፈዲላ እኔ ሆቴል አርፋለሁ ችግር የለውም ይህን ቤት እንደ ስጦታ ቁጠሪው
ፈዲላ፡- አይሆንም ! ና አባ ልብስን በመክተት አግዘኝ
አለችና ወደ መኝታ ቤት ገባች አባቷም ተከትሏት ገባ። ሳሙኤልም በእዚህ ሁኔታዋ ሊከራከራት ስላልፈለገ ሶፋው ላይ ቁጭ አለ። ልብሷንም ከአባቷ ጋር አዘገጃጅታ ከጨረሰች በኋላ ወደ ሳሎን ሻንጣውን እየነዳች መጣች።
ፈዲላም ልቧ እየተሰበረ "ለነበረን ጊዜ ሁሉ አመሰግናለሁ" አለችና እያለቀሰች ወደ ውጪ ወጣች። መሀመድም ሻንጣውን እየነዳ "በል ልጅ ሳሙኤል ሰላም ሁን ውሳኔህ ወደ መጥፎ ነገር እንደማይመራህ ተስፋ አደርጋለሁ"።
ሳሙኤልም እዛው ቁጭ እንዳለ ስለ ብዙ ነገር አሰበብ
ይቀጥላል.............
@nubeberhanuenmelales

👍6