Telegram Web Link
#ማሜ_አያልቅበትም #ክፍል_2

የማሜ ህመምን በመነካካት ብቻ ለይቶ ያውቅ እንደ ነበር ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ ?😳

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጡት በመነካት ብቻ የልብ ህመምህ ማወቅ የቻለ ብቸኛ ሰው ነው ።

Hadith

حَدَّثَنَا إِسْحَاقُ بْنُ إِسْمَاعِيلَ، حَدَّثَنَا سُفْيَانُ، عَنِ ابْنِ أَبِي نَجِيحٍ، عَنْ مُجَاهِدٍ، عَنْ سَعْدٍ، قَالَ مَرِضْتُ مَرَضًا أَتَانِي رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَعُودُنِي فَوَضَعَ يَدَهُ بَيْنَ ثَدْيَىَّ حَتَّى وَجَدْتُ بَرْدَهَا عَلَى فُؤَادِي فَقَالَ ‏"‏ إِنَّكَ رَجُلٌ مَفْئُودٌ ائْتِ الْحَارِثَ بْنَ كَلَدَةَ أَخَا ثَقِيفٍ فَإِنَّهُ رَجْلٌ يَتَطَبَّبُ فَلْيَأْخُذْ سَبْعَ تَمَرَاتٍ مِنْ عَجْوَةِ الْمَدِينَةِ فَلْيَجَأْهُنَّ بِنَوَاهُنَّ ثُمَّ لِيَلُدَّكَ بِهِنَّ ‏"‏ ‏.‏

Narrated Sa'd:
I suffered from an illness. The Messenger of Allah (ﷺ) came to pay a visit to me. He put his hands between my nipples and I felt its coolness at my heart. He said: You are a man suffering from heart sickness. Go to al-Harith ibn Kaladah, brother of Thaqif. He is a man who gives medical treatment. He should take seven ajwah dates of Medina and grind them with their kernels, and then put them into your mouth.

Da'if (Al-Albani)

Sunan Abi Dawud, 3875
In-Book Reference: Book 29, Hadith 21
English Reference: Book 28, Hadith 3866
ቴክቶካችንን ደግሞ አለሁ በሉት እንጂ😳

https://www.tiktok.com/@alatyon?_t=8rIZzJFpAgi&_r=1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ አንዲት ነፍስ ወደ አባቷ እቅፍ ተመልሳለች ።

እንኳን ደስ አለን ።

የቅድስት ቤተክርስቲያንን አስተምህሮ እንማማር ዘንድ ለምትሹ ከግሩፑ በተጨማሪ በውስጥ ለማነጋገር ዝግጁ ነን ።

እንኳን ደስ አላችሁ 😍
#ማሜ_አያልቅበትም #ክፍል_3
ቅዱስ ውሸት ዘማሜ አብዱል

የአላህ ቀዳዳ መልዕክተኛ ማሜ ጢሞ ስለሳክስ (ውሸት) ያለውን አቋም እዩልኝ ። ካያችሁ በኋላ ግን ማሜ የቀዳዶች እና ውሸታሞች አባት ነው ። ስትባሉ አትደንግጡ

Hadith

"وعن أم كلثوم بنت عقبة بن أبي معيط رضي الله عنها قالت سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول‏:‏ ‏"‏ليس الكذاب الذي يصلح بين الناس فينمي خيرًا، أو يقول خيرًا‏"‏ ‏(‌‏(‏متفق عليه‏)‌‏)‌‏.‏

و في رواية مسلم زيادة، قالت: "و لم اسمعه يرخصه في شيء مما يقوله الناس الا في ثلاث، تعني: الحرب، و الاصلاح بين الناس، و حديث الرجل امراته، و حديث المرأة زوجها"."

Umm Kulthum bint 'Uqbah (May Allah be pleased with her) reported:
Messenger of Allah (ﷺ) said, 'The person who (lies) in order to conciliate between people is not a liar, when he conveys good or says (something) good".

[Al-Bukhari and Muslim].

The narration in Muslim added: She said, "I never heard him (she meant the Prophet (ﷺ)) giving permission of lying in anything #except in three (things): 👉war, conciliating between people and the conversation of man with his wife and the conversation of a woman with her husband".



Riyad as-Salihin, 249
In-Book Reference: Introduction, Hadith 249
ጥያቄዎች ያሏችሁ እነሆ ጠይቁ አለን
ሌሎች ፕሮዎች ተባበሩት
ክፍል አንድ ይሄው 👇👇👇👇

አልወጣም ከቤቴ!

ክፍል አንድ

ከብዙ አመታት በፊት በአንዲት ሰፈአ አንድ ቤተሰብ በሰላምና በፍቅር ይኖሩ ነበር ። ምንም እንኳ የተለያየ እምነት ቢኖራቸውም ባል ሚስቱ ፈዲላን በጣም ይወዳት ስለነበር ትእዛዘ አምላክን ሳያከብር እንዲሁ አግብቷታል።

እርሷም በጣም ትወደው ነበር ግን ቤተሰቦቿ በጣም ሀይማኖተኛ ስለሆኑና ከእነሱም መሀል አባቷ ኡስታዝ ስለነበር ቤታቸው ውስጥ ስለ ባሏ ሲነሳ ሁሌም ይነቅፏት ነበር ።

"ይህን ሰው አምላኪ ከፊር ለምን አገባሽ? በእዚህ አላህ እንዴት እንደሚያዝንብን ታውቂያለሽ?" ሁሌ ይህን ንግግር ይናገሯት ነበር ልትጠይቅ ስትሄድም በእርሱ የተነሳ ይነቅፏትና ይዘልፏት ነበር።

በክርስቲያን በዓልም በደረሰ ሰሞን የክርስትና በአሉን አብረው ነበር የሚያከብሩት እንዲሁም የሙስሊም በዓል በደረሰ ጊዜ አንዲሁ አብረው ነው የሚያከብሩት።

አባቷ ሁሌም ባሏ ሳሙኤልን በግል ሊያናግረው ይፈልጋል። ግን ፈዲላ ሁሌም አትፈቅድለትም "ስለ ሀይማኖት ከተነሳ ይፈታኛል ጥሎኝም ይሄዳል" ብላ ስለምትፈራ ሁሌም ለብቻቸው የሚገናኙበትን አጋጣሚ ለመቀነስ ከሳሙኤል ስር አትጠፋም ነበር።

ከእለታትም በአንዱ ቀን አባቷ መሀመድ ይሳካልኝ ይሆን ብሎ በጠዋቱ ለሳሙኤል ይደውላል

መሀመድ፡- "አሰላሙ አለይኩም ሰላም ነህ ሳሙኤል"

ሳሙኤል፡- "እግዚአብሔር ይመስገን ሰላም ነው ምነው በጠዋት"

መሀመድ፡- "አዎን ሳሙኤል ስለ አንድ ነገር እንድንወያይ ፈልጌ ነበር።"

ሳሙኤል፡- "እሺ ችግር የለውም ግን በሰላም ነው"

እንዳለም ፈዲላ ከማን ጋር ነው የሚነጋገረው በማለት ወደ ሳሎን ትመጣለች በምልክትም "ማን ነው" አለችው እርሱም አባቷ እንደሆነ ነገራት።

መሀመድ፡- "አዎን በሰላም ከስራ ስትወጣ ብቻህን ወደ ቤት ና!"

ሳሙኤል፡- "እሺ ችግር የለውም እመጣለሁ"

መሀመድ፡- "እሺ መልካም ቻው"

ሳሙኤል፡- "እሺ ቻው"

ፈዲላም ስልኩን እንደዘጋው ፍጥን ብላ

ፈዲላ፡- ምንድን ነው ያለህ?

ሳሙኤል፡- እንድንገናኝ ፈልጎ ነው!

ፈዲላ፡- ለምን?

ሳሙኤል፡- እኔንጃ ምክንያቱን አልነገረኝም ግን ስራ ስትጨርስ ወደ ቤት ና ብሎኛል።

ፈዲላ፡- እሺ በቃ አብረን እንሄዳለን!

ሳሙኤል፡- አይ አይሆንም ሆዴ ብቻህን ና ነው ያለኝ ስለዚህ ብቻዬን መሄድ ነው ያለብኝ

ፈዲላም፡- ምንም ችግር የለም ላንተ ተነግሮ ከእኔ ሚደበቅ ነገር ስለሌለ አብረን ነው የምንሄደው።

ሳሙሴል፡- ይኸውልሽ ውዴ አባትሽ ላንቺ የማይነገር ነገር ባይሆን ሆሮ ብቻህን ና አይለኝም ነበር ስለዚህ አንቺ ብትቀሪ መልካም ነው ባይ ነኝ አባትሽም ብቻህን ና ብሎኝ አንቺን ከአጠገቤ ከተመለከተሽ ደስ አይለውም

ፈዲላ፡- ካልክ እሺ ይኸው ከረባትህን ላድርግልህ

ሳሙኤል፡- እሺ መልካም ቀን ይሁንልሽ ውዴ ሰላም ሁኚልኝ

ፈዲላ፡- ሰላም ሁን ቻው! ብላ መኪናውን አስነስቶ እስኪሄድ ጠብቃ ወዲያውኑ ወደ አባቷ ደወለች። ስለ ሀይማኖት ሊያናግረው እንደፈለገ ገብቷት ነበርና እርሱን ለማስቆም ይህንን ማድረግ ነበረባት። ስልኩንም አነሳው

መሀመድ፡- አሰላሙ አለይኩም

ፈዲላ፡- አባ ለሳሙኤል ለምንድነው የደወልከው?

መሀመድ፡- መጀመሪያ ሰላምታ አይቀድምም ልጄ

ፈዲላ፡- ይቅርታ አባ ማወቅ ስለፈለኩ ነው

መሀመድ፡- እኔ ሳሙኤልን ለምን ጉዳይ የምፈልገው ይመስልሻል

ፈዲላ፡- ከእዚህ በፊት በእዚሁ ነገር በጣም ተነጋግረናል ተው አባ እኔ ትዳሬን ማጣት አልፈልግም አንተ ይህንን ነገር ማታቆም ከሆነ ትዳሬ ሁሌም አደጋ ላይ ነው እባክህ አባዬ

መሀመድ፡- ልጄ ከአንቺ በላይ እኔ አስብልሻለሁ ካፊር ስታገቢም ዝም ብዬሻለሁ ይህ ሁሉ ደስታሽን እንዳታጪ ነው ገባሽ ግን አሁን ባልሽ መቀየር አለበት እኔ ኡስታዝ ሆኜ ሳለሁ ቤተሰቤ ውስጥ የሀይማኖት ቅልቅል እንዲኖር አልፈቅድም ልጅ ትወልዳላችሁ ልጆቻችሁስ ካፊር ነው የሚሆኑት?  ወይንስ ሸሀዳ ነው የሚይዙት ስለዚህ የእኔ ልጅ ሊመጣ ያለውን ምንም አልተረዳሽም ነገሩ ተወሳስቦ ሳይቀድመን መጀመሪያ እቀድመነው ና እንፍታው"

ፈዲላ፡- የእኔን ትዳር በማፍረስ ነው ነገሩን የምንፈታው?

መሀመድ፡- እንደሱ አይደለም የእኔ ልጅ ደግሞም አንቺን ና እኔን ብቻ ሳይሆን ሳሙኤልንም ነው የምጠቅመው ሰውን ከማምለክ ተላቆ የፈጠረውን አላህን የማይወልድ የማይወለድ አምሳያ ቢጤ እንኳ የሌለውን ፈጣሪ ያምልካል አላህ ያዘጋጀልንንም ጀነት ይወርሳል አየሽ ከእኛ ይልቅ እሱ ተጠቃሚ ይሆናል።

ፈዲላ፡- እኔም ምንም አላቅም አባ ትዳሬ እንዳይፈርስ ብቻ ነው የምፈልገው

መሀመድ፡- አያሳስብሽ ልጄ ከእዚህ የበለጠ ደስተኛ ትሆኛለሽ

ፈዲላ፡- እሺ አባ እንዳልከው ይሁን

መሀመድ፡- እሺ ሰላም ዋይ ልጄ

ፈዲላ፡- እሺ ቻው! አለችውና መንፈሷን ትንሽ ለማረጋጋት ሞከረች ሳሙኤል ይሂድ አይሂድ ብላ ከአይምሮዋ ጋር ሙግትን ጀመረች "ሳሙኤል ሄደ እንበል አባ በሀይማኖቱ ሲመጣበት ና አምላኩን ሲናገርበት ምን ይለዋል?" አለችና አስከትላም "አይ አባማ ነገሩን አድበስብሶ ስለሚጀምር አያስቀይመውም። ግን የሆነ ነገር ቢለውስ?"

"አብሬው ከሳሙኤል ጋር ወደ ቤት መሄድ አለብኝ ብቻ የሆነ ምክንያት ፈጥሬ አብሬው እሄዳለው" የቤቱን ስራ መስራት ቀጠለች የቤት እመቤት ናትና ስራ ከጨረሰች በኋላ መፅሀፍ ማንበብ የዘወትር ስራዋ ነው።

አንዳንዴ ሳሙኤል ቢሮ ውስጥ የሚገኘውን መፅሀፍ ቅዱስ እያወጣች ታነብ ነበር። ከመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሌም ለልቦናዋ ስትነግረው የሚያስደንቃት ቃል አለ እርሱም ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰዎች የላከው መልእክት ላይ የሚገኝ ሲሆን ❝ስለዚህ ስለ ቍጣው ብቻ አይደለም ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው።❞
  —ሮሜ 13: 5

ይህንን ቃል ወደ ራሷ ሀይማኖት በማዞር አላህን በህሊና እንጂ ከመቅሰፍት ለመዳን ብቻ ብላ እንደማትገዛው ታስባለች። ይህን ብቻ አይደለም መፅሀፍ ቅዱስን ማንበብ "ምንም ባላምንበትም ወደ ጥሩ ስነምግባር ይመራኛል" ብላ ታምናለች።

ሳሙኤል ግን መፅሀፍ ቅዱስን እንደምታነብ ምንም አያውቅም ሁሌም በቦታው ስለሚያገኘው ይነካዋል ብሎ የሚያስበው ሰው የለም ምክንያቱም በዙሪያው ምንም ክርስቲያን የለም እርሱ ብቻ እንጂ።

ስራውንም እንደጨረሰ ወደ ፈዲላ ቤተሰብ ቤት አመራ። ፈዲላም ሰአቱ እንደደረሰ አውቃ ቴምር ገዛችና በፍጥነት ወደ ቤተሰቦቿ ቤት መሄድ ጀመረች ግን እንደደረሰች ሳሙኤል ቤት ቁጭ ብሎ ነበር ።

ይቀጥላል........
እንዲቀጥል 15 ሰው ይቀጥል ይበለኝ
15 አልሞላችሁም 😜
አልወጣም ከቤቴ!

ክፍል ሁለት

ፈዲላ፡- እንዴት ናችሁ ለለሊቱ ምርጥ ቴምር ይዤላችሁ መጥቻለሁኝ

የፈዲላ እናት(ዘሀራ)፡- እንኳን ደህና መጣሽ ልጄ ባልሽም እዚህ ነው

ፈዲላ፡- አዎ ልመጣ አላሰብኩም ነበር ነገር ግን ዛሬ ይሄን ለሊት አብረን እንድናሳልፍ ብዬ ነው

ዘሀራ፡- አይ መልካም አድርገሻል ልጄ ነይ ተቀመጪ

ሳሙኤል፡- ውዴ እንኳን ደህና መጣሽ ዛሬ እዚህ ልታድሪ ነው ማለት ነው?

ፈዲላ፡- አዎን ግን እኔ ብቻ ሳልሆን አንተም አብረኸኝ ነው የምታድረው።

ሳሙኤል፡- ነገ እኮ ስራ አለኝ ውዴ ባይኖረኝ አድር ነበር ግን ዛሬ ቢሮዬ ውስጥ የምሰራቸው ብዙ ስራዎች ስላሉኝ መሄድ አባን አነጋግሬው አለብኝ። ሲል አባቷ መሀመድ ከመኝታ ቤት ወጥቶ "ወዴት ነው ደግሞ የምትሄደው" እንዳለም ፈዲላን ከዘሀራ ጎን ተቀምጣ ተመለከታት።

መሀመድ፡- እንዴ ልጄ መጥተሻል እንዴ

ፈዲላ፡- አዎ አባ ዛሬ ለሊቱን አብረን እንድናሳልፍ ብዬ ነው

መሀመድ፡- እሺ መልካም ጥሩ አድርገሻል እና አሁን ሳሙኤል ወዴት ሊሄድ ነው?

ፈዲላ፡- እ... እ ... ነገ ስራ ስላለበት ሊሄድ ነው

መሀመድ፡- እንዴ ይህ ምን ማለት ነው? ሳሙኤል! አሁን ልትሄድ ነው?

ሳሙኤል፡- አዎ አባ በጣም ይቅርታ ስለ ጉዳያችን ተነጋግረን እሄዳለው ፈዲላ ዛሬ እዚህ ነው የምታድረው እኔም እንዳላድር ነገ ስራ አለኝ ቤት የምሰራውም ብዙ ነገር አለኝ ለዛ ነው።

መሀመድ፡- እንደሱስ ከሆነ ምንም ማድረግ አይቻልም ላንተም ብትሄድ ይሻልሀል!

ሳሙኤል፡- አመሰግናለሁ አባ

ፈዲላ፡- ቆይ እራት ላሰራልህ እዛ ገና አሙቀህ ከምትበላ እዚሁ በልተህ ሂድ

ሳሙኤል፡- እሺ ውዴ አመሰግናለሁ! አለና አየር ለመቀበል ወደ በረንዳው ዘለቀ መሀመድም ተከትሎት ወጣ

ሳሙኤል፡- አባ ዛሬ ስለምን ልትነግረኝ ነበር በጠዋት የደወልከው

መሀመድ፡- ትልቅ ጉዳይ ነው ልጄ በእዚች አጭር ደቂቃ አንጨርሰውም ስለዚህ አንጀምረው! ሌላ ሰፊ ሰአት ስናገኝ እንወያይበታለን

ሳሙኤል፡- እሺ መልካም እንደዛ ከሆነ ጥሩ

መሀመድ ያለውን ነገር ቢያነሳና እዛው ቢያፍረጠርጥለት ምኞቱ ነበር ግን ካለው ሰአትና ሁኔታ አንፃር ምንም መናገር አልቻለም። ስለዚህም ልቡ እየጋለ "ሳሙኤል ልጄ በቃ ወደ ውስጥ እንግባ " አለውና ወደ ቤቱ ገባ።

ሳሙኤልም ከሁኔታው ተገረመና "እውነት ይህ ሰው ስለ ሀይማኖት ሊያነሳብኝ ባልሆነ ግን ከሆነ ከእዚሁ ሰአት ጀምሮ ይህን ቤተሰብ መሰናበት አለብኝ ማለት ነው ድሮም ኦ የአምላክን ፈቃድ ሽሬ ነው እሷን ያገባሁት ግን የፍቅር አምላክ ስለ ፍቅር ያውቃልና ይቅር ይለኛል"።

ሳሙኤልም እራቱን እነፈዲላ ቤተሰብ ጋር በላና ወደ ቤቱ ተመልሶ ስራውንም ጨረሰና ተኛ። ይህ አጋጣሚ ያበሳጨው የፈዲላ አባት ለብቻዋ ጠርቶ

መሀመድ፡- ልጄ ምን እያደረግሽ ነው? ባልሽ እንዲድን አትፈልጊም?

ፈዲላ፡- አሁንም እስከቻልኩት መጠን ድረስ እንዳትገናኙ አደርጋለሁ አባ አንተ ምንም አትረዳኝም በእኔ ቦታ ሆነህ ሁሉን ስላላየኸው እኔ ላይ መፍረድ አትችልም በቃ ተወው እርሱም በሀይማኖቱ እኔም በሀይማኖቴ!

መሀመድ፡- ተይ ልጄ እንዲህ አትበይ እኔ ከአንቺ በላይ ስለ አንቺ አስባለሁ ለዚህም ነው እስካሁን እየሞከርኩ ያለሁት ልጁን ልቀቂው እውነት ካለው ስላመለከው ነብይ ይመስክር እውነት ከሌለው ደግሞ ያፈግፍግ

ፈዲላ፡- እሱ እንዲፈጠር አልፈቅድም!

መሀመድ፡- ሁሌም እንደማስብልሽ አትዘንጊ አንቺን የሚጎዳ ነገር ቢሆን አንዳችም እርምጃ አልራመድም ነበር ግን ይህ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው።

አላትና በተቀመጠችበት ጥሏት ወጣ ፈዲላም በጣም ተጨነቀች "አባ መቼም የሚያቆም አይመስለኝም ምን ባደርግ ይሻለኛል" እያለች ክፍሉን ትዞረው ነበር።

ሁለተኛ ቀን፡-

ሳሙኤል ከእንቅልፉ ሲነቃ የድካም ስሜት እየተሰማው ነበርና ከአልጋው ለብዙ ሰአታት ያህል ቆየ። ፈዲላም ወደ ቤት በተመለሰች ጊዜ መኪናውን ተመለከተች እስካሁን አልሄደም እንዴ ብላ ቤት በገባች ሰአት አልጋ ላይ ተመለከተችው

ፈዲላ፡- ሳሚ ሳሚ ተነሳ በጣም ረፍዷልኮ

ሳሙኤል፡- በጣም ደክሞኛል ውዴ የምነሳ አይመስለኝም

ፈዲላ፡- ምነው አመመህ እንዴ?

አለችና እጇን በራሱ ላይ ጫነችበት

ሳሙኤል፡- አይ አታስቢ ውዴ ደህና ነኝ ትንሽ የድካም ስሜት ነው

ፈዲላ፡- እና ዛሬ ስራ ቀረህ ማለት ነው? አይዞህ አሁን ቁርስ ምን ልስራልህ

ሳሙኤል፡- ፍሪጅ ውስጥ ያለውን ሽሮ አሙቂልኝ

ፈዲላ፡- አይ አዲስ ነገር ነው መብላት ያለብህ እንቆላል ፍርፍር ልስራልህ?

ሳሙኤል፡- እሺ

ይቀጥላል.......

@nubeberhanuenmelales
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from yordi ዘዮሐኒ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሀጅዋ ሌላ ታሪክ ውስጥ ናቸው 😁😂😂

ሾይጣንን ቀጠቀጡት እኮ😂
ሰሞኑን እስኪ አመቻችቼ የማቴዎስ ወንጌልን አብረን እናጠናለን ።

መምህር አጥሮናል ከቻላችሁ መምህራንን ብትጋብዙልን
ታላቁ ጅብሪል ሰላም ብሎችኋል
አልወጣም ከቤቴ !

ክፍል 3

ቁርሱንም መስራት ጀመረች። እንደተለመደውም አባቷ ለሳሙኤል ደወለ

ሳሙኤል፡- ሄሎ አባ ሰላም አደርክ

መሀመድ፡- እንዴት አደርክ ትላንት በሰላም ወደ ቤትህ ገባህ?

ሳሙኤል፡- አዎ እግዚአብሔር ይመስገን

መሀመድ፡- ጥሩ በቃ ዛሬ እንደትላንትናው ከስራ ስትወጣ እንገናኛለን

ሳሙኤል፡- ዛሬ ስራ አልሄድም አባ

መሀመድ፡- ምነው በሰላም ነው የቀረኸው ?

ሳሙኤል፡- አዎን በሰላም ትንሽ ደክሞኝ ነው

መሀመድ፡- እንደሱ ከሆነማ ወደ አራት ሰአት ላይ ለምን አንገናኝም

ሳሙኤል፡- እሺ ይቻላል የት እንገናኝ

መሀመድ፡- የምናዘወትረው ካፌ ቢቻልህ መፅሀፍ ቅዱስህን ይዘህ ና!

ሳሙኤል፡- መፅሀፍ ቅዱስ ደግሞ ለምንድን ነው ይዤ የምመጣው?

መሀመድ፡- ስትመጣ እነግርሀለው

ሳሙኤል፡- እንደሱ ነው ነገሩ መልካም ገብቶኛል

መሀመድ፡- እሺ እስከዛው ሰላም ዋል

ሳሙኤል፡- ሰላም ዋል!

ሳሙኤልም በጣም በመገረም "እስኪ እናያለን" አለና ከአልጋው ተነስቶ ወደ ሻውር ቤት ገባ ። በመስታውት እራሱን እየተመለከተም "ዛሬ አምላክ ሊጠራህ እያሰበ ነው ትመሰክርለትም ዘንድ ጠርቶሀል ራስህን እንዳታሳፍር ለሚጠይቅህ ጥያቄ በሙሉ ለመመለስ የተዘጋጀህ ሁን!" አለና ሻውር ወስዶ ወጣ።

ፈዲላም ሰርታ ጨርሳ ነበርና በፍቅር መንፈስ እየተወያዩና እየተጫወቱ ቁርሳቸውን አብረው በሉ። በመጨረሻም

ሳሙኤል፡- ውዴ ወደ አራት ሰአት ላይ እወጣለሁ

ፈዲላ፡- የት?

ሳሙኤል፡- ከአባትሽ ጋር ቀጠሮ አለኝ ስለትላንትናው ጉዳይ ዛሬ ነው የምንወያየው።

ፈዲላም በድንጋጤ፡- ምን ማለት ነው የትላንትናው ጉዳይ ምንድን ነበር?

ሳሙኤልም፡- እኔንጃ ዛሬ ነው የምሰማው ' በማለት ዋሻት

ፈዲላ፡- እሺ ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆንክ አብሬህ ልምጣ

ሳሙኤል፡- ለምንድን ነው ግን ሁሌ አባትሽን ለብቻዬ እንዳላገኘው የምታደርጊው? የምትፈሪው ነገር አለ እንዴ?

ፈዲላ፡- ኧረ እንደሱ አይደለም ስላመመህ ብዬ ነው

ሳሙኤል፡- ዛሬ ስላመመኝ ነው ሌላውን ቀንስ?

ፈዲላ፡- መስሎህ ነው ሳሚ እኔ እናተን ለመለያየት ያደረግኩት ነገር የለም።

ሳሙኤልም በመገረም፡- እሺ እንደሱ ከሆነ ጥሩ አሁን ልብሴን ልቀይር 'ብሎ ተነሳ

ፈዲላም ሁኔታውን በቆራጣ ትከታተል ነበር በልቧም "አሁን ምንም አማራጭ የለኝም ሳሙኤልን ላስቀረው አልችልም ነገሩ በከፊሉ ገብቶታል መሰለኝ ከአሁኑ እኔን መጠራጠር ጀምሯል ጉዴ ፈላ የፈራሁት ከደረሰ እኔ ያለሱ መኖር አልችልም" አለች

ሰአቱም በደረሰ ጊዜ ሳሙኤል ቻው ሳይላት ከቤቱ ወጣ ምክንያቱም የሆነ ነገር ፈጥራ ልታስቀረው እንደምትችል ልቦናው አውቆት ነበርና ቻው አላላትም።

ካፌም እንደደረሰ መሀመድ ምልክት ሰጠው አይቶትም ወደ ተቀመጠበት ቦታ አመራ

መሀመድ፡- እንኳን ደህና መጣህ ሳሙኤል

ሳሙኤል፡- እንኳን ደህና ቆየኸኝ አባ

መሀመድ፡- ሻይ ቡና?

ሳሙኤል፡- ሻይ

መሀመድ፡- እንግዲህ ውይይታችንን ስንጀምር ለምንድም እንደጠራሁህ በስልክ ከነገርኩህ ነገር ላይ ትንሽ ሹክ ብዬሀለው

ሳሙኤል፡- አዎን ስለ ሀይማኖት ልትናገረኝ እንደሆነ ግልፅ ነው

መሀመድ፡- ጥሩ እውነት የሆነውን ነገር መከተል መልካም ስለሆነ ብዬ ነው።

ይቀጥላል........

@nubeberhanuenmelales
ቀጣዩ እንዲለቀቅ የግሩፓችን አባላት ቁጥር 12,500 መሆን አለበት ። 😎😂
2024/11/16 13:35:14
Back to Top
HTML Embed Code: