Telegram Web Link
+ የተሠጠህን ቁጠር +

ሔዋን ከዕባብ ጋር እየተነጋገረች ነው። የመጀመሪያ ጥፋትዋ ካለደረጃዋ ወርዳ ከዕባብ ጋር ወዳጅነት መጀመርዋ ሳይሆን አይቀርም። ዕባብ ደግሞ የስይጣን አንደበት ነበረ።

ሰይጣን እንዲህ አላት:- በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት። ልብ አድርጉ እግዚአብሔር "ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ" አላለም። የከለከለው አንዲት ዛፍ ነው:: ሰይጣን ግን ሁሉን ተከልክላችሁዋል? ብሎ እንዳላዋቂ ጠየቀ። ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ንግግሩን የከፈተው በውሸት ነበረ።

ዓላማው ከሔዋን መረጃ ለማግኘት አልነበረም። ሔዋን እስከዛሬ ያላሰበችውን ማሳሰብ ነበር። ብሉ ተብሎ ከተሠጣቸው ብዙ ሺህ ዛፍ ይልቅ የተከለከሉትን አንዲት ዛፍ አሳይቷት ሔደ። ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ስላልተሠጣት ማሰብ ጀምራ ደስታዋን አጣች። የተከለከለችውን በልታ የተሠጣትን ብዙ ሥጦታ ከነሠጪው አጣች።

ወዳጄ የቀደመው እባብ ዛሬም መርዙን ይረጫል

በሕይወታችን ከተሠጠን ብዙ ነገር ይልቅ ያልተሠጠንን ጥቂት ነገር እናስባለን። ገንዘብ እንደሌለህ እያሰብክ ጤና እንዳለህ ትረሳለህ። ጫማ እንደሌለህ እያሰብክ እግር እንዳለህ ትረሳለህ። አልጋ እንደሌለህ እያሰብክ እንቅልፍ እንዳለህ ትረሳለህ። ስለዚህ ውስጥህ ያለውን የዕባቡን ድምፅ  አትስማ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ይበልጣልና የተሠጠህን ቁጠር።

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
"አንተ ገሊላዊ አሸንፈሃል"

ቄሣር ዮልያኖስ (361 -- 363 ዓ.ም)

ቄሣር ዮልያኖስ በሮም ዘመነ መንግስቱን ላይ ተደላድሎ የነበረ ቄሣር ነው ። በስልጣን ላይ በተቀመጠባቸው ሁለት ዓመታት ውስጥ ክርስቲያኖችን ከሌሎቹ አረማውያን ቄሳሮች ለየት ባለመልኩ መከራን አድርሶባቸው ነበር ። ግን አሸንፋቸዋለሁ ብሎ በግፍ ደማቸው ሲያፈስ፣በዋሉበት ማሳደሪያ ባደሩበትም መዋያ አሳጥቶ  የነበረው  ይሄ ግፈኛ ዓረማዊ ቄሳር በመቅሰፍተ እግዚአብሔር ተቀጥቶ ነፍሱ ከስጋው  ልትለይ ባለችበት ሰዓት የተናገረው ንግግር ይሄ ነበር ""አንተ ገሊላዊ አሸንፈሃል"" ።

ገሊላዊ ብሎ የጠራው በስጋ ተገልጦ የድህነታችን ቤዛ የሆነው ቅዱሱ አምላካችን "ክርስቶስ ኢየሱስ" ነው ። ዮልያኖስ ትክክል ነው ። ገሊለዊ የናዝሬቱ ክርስቶስ ኢየሱስ ሳይታገል ያሸንፋል ። ስይደክም ይረታል ። ሳይወርድ ይሰብራል ። ሳይወጣ ያደቃል ።

አዎ " ገሊላዊው ያሸንፋል " ክብር ምስጋና አምልኮት እና ውዳሴ ከምድር እስከ አርያም ከፀሐይ መውጫ እስከመግቢያው ድረስ ለቅዱስ ስሙ ይሁን ።

                  🤲   አሜን🤲

@alatyon15
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በዳሰነች ወረዳ ከ1200 በላይ አዳዲስ አማንያን አጠመቁ
__
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ 1200 በላይ አዳዲስ አመንያንን ዛሬ ሐምሌ 06 ቀን 2016 ዓ.ም በዳሰነች ወረዳ አጥምቀው ወደ እናት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አምጥተዋል። ተጠማቂዎቹ በሀገረ ስብከቱ፣ በወረዳ ቤተክህነቱ፣ በማኅበረ ቅዱሳን ትብብር በአካባቢው በተሰማሩ የቋንቋ ሰባክያን ጥረት ለጥምቀት የሚያበቃቸውን መሠረታዊ የነገረ ሃይማኖት ትምህርት ሲማሩ ቆይተው በዛሬው ዕለት ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጅነት ተቀላቅለዋል።

ብፁዕነታቸው ለአካባቢው አዳዲስ አማኞች የሚገለገሉበት አዲስ ቤተክርስቲያን ለመገንባት ትናንት ሐምሌ 06 ቀን 2016 ዓ.ም በዳሰነች ወረዳ የመርመርቴ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

ከዚህ በፊት በሀገረ ስብከቱ ከ185,000 በላይ አዳዲስ አማንያን መጠመቃቸው የሚታወስ ነው።
That which was from the beginning, which we have heard, which we have seen with our eyes, which we have looked upon, and our hands have handled, concerning the Word of life-- - 1 John 1:1

Read the testimony of John: "That which we have seen, which we have heard, which we have looked upon with our eyes, and our hands have handled, of the Word of life."
But the very same apostles testify that they had both seen and "handled "Christ.
"That "says John, "which we have seen with our eyes, which we have looked upon, and our hands have handled, of the Word of life."
But what is that which, in a certain way, has been grasped by hand.
To God their beauty, to God their youth (is dedicated). With Him they live; with Him they converse; Him they "handle"

- Tertullian of Carthage
መኑ ነገሮ ለእግዚእዬ
ውእቱ እግዚአብሔር ወውእቱ ሰምዐኒ 😍
"የተራበውን ማብላት፥ የተጠማውንም ሰው ማጠጣት የሞተ ሰውን ከማስነሣት ይበልጣል፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
አላችሁ እንግባ ?
“ዘወትር በዐይንህ ፊት ፈሪሃ እግዚአብሔር ይኑር፤ ሕይወትና ሞት የሚሰጠውን አዘክረው፡፡ ዓለምንና በዓለም ያለውን ሁሉ ጥላው፤ ከሥጋ የሚመጣውን ደስታና ሰላም አትሻ፤ ለዚህኛው ኑሮ ሙትና ለእግዚአብሔር ሕያው ሁን፤ ለእግዚአብሔር ቃል የገባኸውን አትርሳ፤ ያም በፍርድ ቀን ካንተ ይፈለግብሃል፡፡ ረኀብን በጸጋ ተቀበለው፤ ተጠማ፥ ተራቆት፥ ንቁና በሐዘን የምትኖር ሁን፡፡ በልቡናህ አልቅስና ጩኽ፤ ለእግዚአብሔር የምትመች መሆን አለመሆንህን ፈትን፤ ሥጋህን ቀጥተህ ነፍስህን ታድናት ዘንድ፡፡”

(አባ እንጦንስ)
ጉድ ሞርኒንግ
ትርፍሽ ምንድን ነው ?
ልባም ሴት 😍
ለልባም ሴቶች የተዘጋጀ ልዩ ትምህርት 😍
እንዴት ናችሁልኝ ተወዳጆች ።

አሁን add member challenge ልጀምር ነው ። ከፍተኛ ሰው ላስገባው ሰው የ50 ብር የሞባይል ካርድ አሁኑኑ አስተላልፋለሁ ።
እስካ ጠዋት 2:00 ድረስ ቻሌንጁ ይቆያል ።


ዳይይ
2024/09/27 15:25:12
Back to Top
HTML Embed Code: