Telegram Web Link
• በአጠቃላይ የተፈጸመው ሕገ ወጥ ተግባር በሕገ ሰብእም ሆነ በሕገ እግዚአብሔር ሚዛን የተወገዘ ከመሠረተ እምነት የተለየ፣ በአበው ቀኖና፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን እና በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር  ተቀባይት የሌለው ነው፡፡ ስለዚህ
1ኛ. በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 138 መሠረት ሐምሌ 16 እና ሐምሌ 23 ቀን 2015 ዓ.ም በክልል ትግራይ በማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ውስጥ 

1. ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ የመቀሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የእንቅስቃሴው ሰብሳቢ

2. ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በክልል ትግራይ የማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

3. ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ የአዲግራት ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

4. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

   የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ባልተሰጣቸው ስልጣን 9 ኤጴስ ቆጰሳትን ሾመናል፤ ሲኖዶስ አቋቁመናል በማለት በተለያዩ ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫና በክልሉ መንግሥት ሚዲያ በተላለፈው የቀጥታ ስርጭት የተረጋገጠ በመሆኑ በዚሁ ድርጊታቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያንን በማታለል የክህደት እና የኑፋቄ ተግባር በመፈጸማቸው በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ፤ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ ለይቷቸዋል፡፡
  በመሆኑም፡- 

ሀ. ሥልጣነ ክህነታቸውና የማዕረግ ስማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ውሳኔ የተነሣ ስለሆነ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቀድሞ ዓለማዊ ስማቸው እንዲጠሩ፤

ለ. በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያም በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን ለይቷቸዋል፡፡

• ይሁን እንጅ ከላይ በስም ተጠቅሰው የተወገዙት ግለሰቦች በሠሩት የቀኖና ጥሰት ተጸጽው ይቅርታን ቢጠይቁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምህረት ደጆች ሁል ጊዜ ክፈት መሆናቸውና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የምንቀበላቸው መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳውቃል፤  
  
2ኛ. የቅዱስ ሲኖዶሱንና የቤተ ክርስቲያኒቱን ልዕልና በመዳፈር እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ በተነሳሱ ግለሰቦች አማካኝነት የኤጲስ ቆጶስነት ሹመት አግኝተናል፤ ተሹመናል እያሉ የሚገኙ 9 መነኮሳት

፩. አባ ዘሥላሴ ማርቆስ

፪. አባ ኃይለ ሚካኤል አረጋይ

፫. አባ እስጢፋኖስ ገብረ ጊዮርጊስ

፬. አባ መሓሪ ሀብቶ
  
፭. አባ ኤልያስ ታደሰ ገብረ ኪዳን

፮. አባ ጽጌ ገነት ኪዳነ ወልድ

፯. አባ ዘርአ ዳዊት ብርሃነ

፰. አባ ዮሐንስ ከበደ

፱.  አባ የማነ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል
በሕገ ወጥ መንገድ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንን ጥሰው የተገኙ በመሆኑ አስቀድሞ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸው ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት ተሽሮ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያ በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን ለይቷቸዋል፡፡
  
3ኛ. ይህ ህገወጥ ሢመት እንዲፈጸም ከመጀመሪያው ጽንሰ ሀሳብ ጀምሮ መሪ ተዋናይና ቀስቃሽ በመሆን ኢትዮጵያን ኤልዛቤል በማለትና ስሟን የሚጠራ የተረገመ ይሁን በማለት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር የዶግማ ልዩነት አለን በማለት የኑፋቄ ትምህርት በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተናገሩትና በህገወጥ ሢመቱ ላይም በእጩነት ተመርጠው በሂደት ላይ ያሉት አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤልና ሂደቱን በዋና አስፈጻሚነት በመምራትና መግለጫ በመስጠት ላይ ያሉት መ/ር ተስፋዬ ሐደራ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተወግዘው ከቤተክርስቲያን ተለይተዋል።

ከላይ በስም ተጠቅሰው የተወገዙት ግለሰቦች በሠሩት የቀኖና ጥሰት ተጸጽው ይቅርታን ቢጠይቁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምህረት ደጆች ሁል ጊዜ ክፈት መሆናቸውና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የምንቀበላቸው መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳውቃል።

4ኛ. “መንበረ ሰላማ” የሚለው ሕገወጥ ሥያሜን በተመለከተ በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ትውፊትም ሆነ በቀደምት አብያተ ክርስቲያናት ትውፊት የማይታወቅ፣ ሃይማኖታዊ መሠረት የሌለው፣ ከቀኖና የወጣ፣ አስተዳደራዊ መዋቅርን የሚያዛባ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም፤ በተጨማሪም ከአንዲት፣ ቅድስት፣ ሐዋርያዊትና ዓለም አቀፋዊትየሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ መንበር መሠረተ እምነት፣ ታሪክና ቀኖና፣ ከአስተዳደር እና ሕግ ባፈነገጠ ሁኔታ ትውፊትን በመዳፈር ጎሣን መሠረት አድርጎ የተፈጠረ ሕገ ወጥ አደረጃጀት በመሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አውግዞታል፡፡ ይሕንንም የክርስትናን ትውፊት እና ሐዋርያዊ መሠረት የሚዛባና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የማይወክል መሆኑ ታውቆ በመላው ዓለም ለሚመለከተው ሁሉ በደብዳቤ እንዲገለጽ እንዲደረግ፤

6. በየደረጃው የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎች፤ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ መነኮሳት፤ አገልጋይ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፤ ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ማህበራት እና ምእመናን እና ምእመናት ይህን ሕገ ወጥ አድራጎት ከመከላከል እና የቤተ ክርስቲያናችሁን ደህንነት ከመጠበቅ በተጨማሪ ለዚህ ሕገ ወጥ አድራጎት ልዩ ልዩ ድጋፍ የሚያደረግ ተቋማት እና ግለሰቦችን አስፈላጊውን ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ የመከላከል ሥራችሁን እንድትወጡ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

8. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስምን ከፊትም ሆነ ከኃላ በመጨመር እና በመቀነስ በከፊልም ሆነ በሙሉ መጠቀም፤ ዓርማዋን፤ አድራሻዋን፤የአምልኮ እና የሥርዓት መፈጸሚያ የሆኑ ንዋያ ቅዱሳትንና አልባሳት እንዲሁም መጻሕፍት መገልገል የማይችሉ መሆኑ ታውቆ ይህንን ጉዳይ በየደረጃው ያሉ መንግሥታዊ አካላት እና የቤተ ክርስቲያኒቱ  የሥራ ኃላፊዎች ተከታትለው እንዲያስፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን በተጨማሪም ይህን ውሳኔ ተላልፈው በሚገኙ ማናቸውም ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ ተገቢውን ሕግ አግባብ ተከትሎ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ዓለማት የሚያስፈጽም ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሕግ ባለሙያዎች በመመደብ ተገቢውን ሁሉ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በኩል እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

9. በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚገኙ መንግስታዊም ሆነ መነግስታዊ ያልሆነ ተቋማት፤ አኃት አቢያተ ክርስቲያናት፤ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት፤ የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት፤ የዓለም አቢያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት፤ የመላው አፍሪካ አብያት ክርስቲያናት ጉባዔ እና ሌሎች የአብያተ ክርስቲያናት እና የሃይማኖት ጉባኤዎች በሙሉ እነዚህ የተወገዙት ግለሰቦች የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ እና ምንም አይነት የሥራ ግንኙነት የሌላቸው መሆኑ ታውቆ ማናቸውም ግንኙነት በቤተ ክርስቲያኑቱ ስም እንዳያደርጉ በጽሑፍ አንዲገለጽ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
  
11. እነዚህ ግለሰቦች የፈጸሙት ተግባር ሃይማኖቱን የሚወድ፣ አባቶቹን የሚያከብር እና አስተዋይ የሆነውን የትግራይ ሕዝብ የማይወክል፣ የራሳቸውን የሥልጣን ጥማት ለማርካት ያደረጉት ሕገወጥ የቀኖና ጥሰት መሆኑ እንዲታወቅ፤ በተጨማሪም ለሚያሠራጩት የሐሰት አሉባልታ ወደፊት ተገቢው መልስ እንዲሰጥበት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

12. ይኽ ሕገወጥ አደረጃጀት ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የታሰበበት፤ በየጊዜው የነበሩ የፖለቲካ እና የመንግሥት ኃላፊዎች በመታገዝ ሥር የሰደደ ድብቅ አጀንዳ በሚያስፈጽሙ ግለሰቦች የተቀናበረ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተገንዝቦ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞታል፡፡ በመሆኑም ሕገ ወጥ አደረጃጀትን ማምከን እና ቤተ ክርሰቲያንን ነፃ ማድረግ የሚቻለው ጠንካራ ውስጣዊ አደረጃጀት እና ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ሲደረግ በመሆኑ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጀምሮ ሊቃውንት፣ መላው ውሉደ ክህነት፣ ወጣቶች ሰንበት ትምሀርት ቤት አባላት፣ መንፈሳውያን ማኅበራት፣ ምእመናን እና የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች በሙሉ በመጾም፣ በመጸለይ፣ የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮና መዋቅር በጠበቀ መልኩ  በመደራጀት አፍራሽ እና የጥፋት መረጃዎችን፣ በመሰብሰብ፣ በመተንተን፣ ለውሳኔ በማቅረብ የቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ደኅንነት እስኪረጋገጥ ድረስ ያለማቋረጥ በመንፈሳዊ ተጋድሎ መበርታትና የመጣብንን ፈተና በጽናት መታገል እንደሚገባ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡ 

13.  በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በተለያዩ ክፍሎች እየተከሠተ ያለውን የሰላም መደፍረስ እና የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወትና የንብረት ውድመት የተፈጠረ አለመግባባት ካለፈው ስህተታችን በመማር ችግሩን ተቀራርቦ በውይይትና በእርቅ እንዲፈታ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም አካላት የሰላም ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡

14.  እንደ ሀገር የገጠመንን የሰላም መደፍረስ በተመለከተ ዘላቂ መፍትሔ በማፈላለግ እንደ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሰላም ጉዳይ የሚሠሩ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ምሁራን ያካተተ ዐቢይ ኮሚቴ በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ተቋቁሞ ሥራው እንዲሠራ ወስኗል፡፡ 
  
በመጨረሻም እስከ አሁን ድረስ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጎን በመሆን አጋርነታችሁን ያሳያችሁ፣ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት እና ሉዐላዊነት መከበር የበኩላችሁን በመወጣት መግለጫ የሰጣችሁ ሁሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እያመሰገንን ለወደፊቱም በጸሎታችሁ እና በመልካም አጋርነታችሁ ከጎናችን እንድትሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

             እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
                ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. 
                     አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ለአፍሪካ መሪዎች ንገሯቸው

ነብዩ ሙሐመድ ጥቁር ሰዎች የተፈጠሩት ለግሃነም እሳት ነው 
መልካቸውም የሰይጣን ምሳሌ ነው ብሏል

Mishkat al-Masabih 119
Abud Darda' reported God’s messenger as saying, “God created Adam when He created him and struck his right shoulder and brought forth his offspring white like small ants. And he struck his left shoulder and brought forth his offspring black as though they were charcoal. Then He said to the party on his right side, ‘To paradise, and I do not care’ and He said to the party in his left shoulder, ‘To hell, and I do not care’.”
አቢ ደርዳዕ እንደዘገቡት የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ አሉ" አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) አደምን ፈጠረ : ከዚያም አደምን ከፈጠረው በሗላ የቀኝ ትከሻውን መታው ያኔም ነጫጭ ጉንዳን የመሰሉ ዝርያዎች ወጡ : እንዲሁም የግራ ትከሻውን ሲመታው ጥቁር ዝርያዎች ልክ ከሰል የመሳሰሉ ወጡ
:በቀኝ በኩል ላሉት ቡድኖች እንዲህ አላቸው እናንተ ወደ ጀነት(ገቢዎች ናቸሁ) : እኔም "አያገባኝም" እንዲሁም በግራ ትከሻው በኩል ላሉት ወደ ጀሃነም
(ገቢዎች) ናቸሁ እኔም አያገባኝም::
وَعَنْ أَبِي الدَّرْدَاءَ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: «خَلَقَ اللَّهُ آدَمَ حِينَ خَلَقَهُ فَضَرَبَ كَتِفَهُ الْيُمْنَى فَأَخْرَجَ ذُرِّيَّةً بَيْضَاءَ كَأَنَّهُمُ الذَّرُّ وَضَرَبَ كَتِفَهُ الْيُسْرَى فَأَخْرَجَ ذُرِّيَّةً سَوْدَاءَ كَأَنَّهُمُ الْحُمَمُ فَقَالَ لِلَّذِي فِي يَمِينِهِ إِلَى الْجَنَّةِ وَلَا أُبَالِي وَقَالَ للَّذي فِي كَفه الْيُسْرَى إِلَى النَّارِ وَلَا أُبَالِي» . رَوَاهُ أَحْمَدُ
Grade:
Isnād Hasan (Zubair `Aliza'i)
صَحِيح   (الألباني) حكم   :
إسنادہ حسن   (زبیر علی زئی)
Reference
: Mishkat al-Masabih 119
In-book reference
: Book 1, Hadith 11

ዘረኛው ነብዩ ሙሐመድ  ጥቁር ሰው የሰይጣን ምሳሌ መሆኑን ገልጿል

“ነቢዩ እንዲህ አሉ፡- ‹‹ሰይጣንን ማየት የሚፈልግ ሰው ነብጣል ኢብን አል-ሐሪሥን ይመልከተው!›› ጥቁር ሰው ሲሆን የተንጨባረረ ረጅም ፀጉርና ጥቁር መንጋጋዎች አሉት፡፡” Ibn Ishaq, Sirat Rasulallah, translated as, The Life of Muhammad by A. Guillaume, page 243
Ustaze Yusuf Elyas
"ከዚህ በፊት የዚህ ዓለም መሪዎች ስለ ምድራዊ ሥልጣን ሲሉ መልካም ምግባርን ሳይኾን ሀብትን፣ ዕድሜንና የዘር አድልዎን እንደ መመዘኛ ሲጠቀሙ በማየቴ ወቅሻቸው ዐውቃለሁ፡፡ ይህ ከንቱነት ወደ እኛ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች መምጣቱን ስሰማ ግን የዓለማውያኑን ግብር መንቀፍ አቆምሁ፡፡ ...

በእነዚህ ነገሮች ሳይወቀሱ ራሳቸውን ነጻ ማድረግ የሚገባቸው የቤተክርስቲያን ሰዎች ከዓለም ሰዎች ተሽለው ካልፈጸሙት፥ ይልቁንም በሰማያዊ ግብር ላይ ተሰማርተው ሳለ ምድራዊ ሀብትን ወይም ይህን የመሰለ ነገር እንደሚቀራመቱ ኾነው ከተሻሙ፥ የዚህ ዓለም ሰዎች እንደዚህ ያለ ነገር ቢፈጽሙ'ማ ምን ይደንቃል?"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ በእንተ ክህነት መጽሐፍ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ  የተረጎመው)
"እውነትና ፍቅር ሊለያዩ የማይችሉ ክንፎች ናቸው እውነት ያለ ፍቅር መብረር እንደማይችል ሁሉእንዲሁም ፍቅር ያለ እውነት ወደ ላይ ሊወነጨፍ አይችልም የስምምነት ቀንበራቸው አንድ ነው።"
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለሀገር ሰላም እና አንድነት ከጳጉሜን 1-6/2015 ዓም የጾም እና የጸሎት አዋጅ አውጃለች።
ስለክርስቶስ አምላክነት ውይይት
ኑ በብርሃኑ እንመላለስ
በውዱ ወንድማችን አብርሐም (አብርሽ) እና በወንድም ሷቢር የተደረገ ውይይት እንደወረደ
ስልጤ የግራኝ ዘመድ መሆኗን አስረግጣለች ። ታሪክ ....
ነገ ጷጎሜን የታወጀውን ፆም እንዳትረሱ 🥰 ከ1 - 6 እንፆም ዘንድ ቤተክርስቲያን አዛናለችና
በስልጤ የኦርቶዳክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆኑ ቤቶች ተለይተው ተቃጠሉ።

ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ አስተዳደር ትናንት ማታ የኦርቶዳክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆኑ ቤቶች ተለይተው መቃጠላቸውና አሁንም በምእመናን ላይ ማስፈራራት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ተገልጿል።

የሙስሊም ተማሪዎች ላይ ድግምት ተደርጓል በሚል ምእመናን ለወራት ዛቻና ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው የቆየ ሲሆን በትላንትናው እለት ነሐሴ 29 ማታ ግን ቤታቸው ተለይቶ እንደተቃጠለ እና የንግድ ሱቆቻቸው ላይም ቃጠሎና ዝርፊያ መፈጸሙን ነው የተገለጸው።

የጸጥታ ኃይሎች በመድረስ ለጊዜው መቀነስ ቢችልም አሁንም ቤተ ክርስቲያን እናቃጥላለን ፤ ምእመናንንም እንጎዳለን በማለት የውስጥ ለውስጥ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው የሚል መረጃ እየደረሰን በመሆኑ ስጋት ላይ ነን ፤ በርካታ ምእመናንም ከቤታቸው እየሸሹ ነው ብለዋል ሲል ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት ዘግቧል።

በተለያዩ ጊዜያት ለከተማ አስተዳደሩና ለሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ቢቆዩም ይሄ ነው የሚባል ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል ፤ በስልጤ ዞን አስቀድሞም በተለያዩ ዓመታት አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸው፣ ምእመናን መገደላቸውና መሰደዳቸው ይታወቃል።

#Ethiopia
#Tewahedo_Media_Center
#TMC_Addia_Ababa

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
#በኦርቶዶክሳውያን_ላይ_የተከፈተው_ጥቃት_ወደ_ስልጤ_ዞን_አምርቷል
በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ አስተዳደር ትናንት ማታ የኦርቶዳክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆኑ ቤቶች ተለይተው መቃጠላቸውና አሁንም በምእመናን ላይ ማስፈራራት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ተገለጸ።

ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በስልክ መረጃ ያደረሱን ምእመናን እንደተናገሩት አስቀድሞ ለወራት ዛቻና ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው እንደነበረና በነሐሴ 29 ማታ ግን ቤታቸው ተለይቶ እንደተቃጠለ፣የንግድ ሱቆቻቸው ላይም ቃጠሎና ዝርፊያ መፈጸሙን ተናግረዋል።

የጸጥታ ኃይሎች በመድረስ ለጊዜው መቀነስ ቢችልም አሁንም ቤተ ክርስቲያን እናቃጥላለን፤ ምእመናንንም እንጎዳለን በማለት የውስጥ ለውስጥ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው የሚል መረጃ እየደረሰን በመሆኑ ስጋት ላይ ነን፤ በርካታ ምእመናንም ከቤታቸው እየሸሹ ነው ብለዋል።

በተለያዩ ጊዜያት ለከተማ አስተዳደሩና ለሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ቢቆዩም ይሄ ነው የሚባል ምላሽ አለማግኘታቸውንም አብራርተዋል።

በስልጤ ዞን አስቀድሞም በተለያዩ ዓመታት አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸው፣ ምእመናን መገደላቸውና መሰደዳቸው ይታወቃል።

ተጨማሪ መረጃዎች እንደደሩስን እናቀርባለን።
ነገረ ስሉስ
ኑ በብርሃኑ እንመላለስ
በእኔ በKeba Man መካከል የተደረገ ውይይት
በስልጤ ዞን የነበሩ ከ500 በላይ የሚሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ከአካባቢያቸው ተሰደው በቡታጅራ ከተማ ይገኛሉ።

ጳጉሜን 1 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ምክንያት በዞኑ ይኖሩ የነበሩ ከ500 በላይ የሚሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ከአካባቢያቸው ተሰደው በቡታጅራ ከተማ ይገኛሉ።

በዞኑ የነበሩት ኦርቶዶክሳውያን አሁናዊ ሁኔታን በተመለከተ ተ.ሚ.ማ የሐዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ከሆኑት ከመልአከ ሕይወት ንጉሤ ባወቀ ጋር ባደረገው የስልክ ቆይታ ፤ ሥራ አስኪያጁ በከተማው 20 የምእመናን ቤቶች ተቃጥለው ፈርሰዋል ሲሉ ገልጸዋል።

ከተሰደዱት ምዕመናን ጋር የቅድስት ድንግል ማርያም ጽላትም አብሮ መሰደዱን ፤ በቡታጅራ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ተጠልለው እንደሚገኙ እና ብዛት ስላላቸውም የዕለት ጉርስ ማግኘት እንደሚቸገሩ ፤ ችግሩን ለመፍታት በሆሳዕና በስብሰባ ላይ እንደሚገኙ የገለጹ ሲሆን ለተፈናቃዮቹ ምን ይደረግ? የእለት ጉርስ እንዴት አስተባብረን እንድረስላቸው? ወደ ቤታቸው ይመለሱ ቢባል ቤት እና ንብረት ስለሌላቸው እንዴት ይመለሳሉ? በሚለው ጉዳይ ዙሪያ በውይይት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ጥቃቱ ድንገት የተፈጠረ እንዳልሆነ እና ከሁለት ወር በፊትም ጥቃት ሲፈጸም ወደ ከፋ ጉዳት እንዳያድግ በማሰብ ለዞኑ ፣ ለወረዳው ፣ ለሃይማኖት ተቋማት እና ለፖሊስ ሴክተሮች ጥንቃቄ እንዲደረግ ስንል በደብዳቤ አሳውቀን የነበረ ቢሆንም ምንም አይነት ምላሽ አላገኘንም ፤ ጉዳት አድራሾቹ ላይም ምንም አይነት እርምጃ አልተወሰደባቸውም ነበር ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ።
2024/09/30 21:41:47
Back to Top
HTML Embed Code: