Telegram Web Link
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሐምሌ 5 እና 6 ቀን 2015 ዓ/ም አስቸኳይ ስብሰባ ማካሄዱ የታወቀ ሲሆን ይህን ከስብሰባው መጠናቀቅ በኃላ መግለጫ ሰጥቷል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው :-

በትግራይ በሚገኙ አህጉረ ስብከት የተመደቡ አባቶች የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪን ቸል ከማለት ባሻገር ሐምሌ 9 እናደርገዋለን ያሉት የኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ መሆኑን ገልጾ የሚመለከታቸው አካላት ሂደቱን በማስቆም ከቤተክርስቲያን ጎን እንዲቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አቅርቧል።

ይደረጋል የተባለው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና በጦርነት የተጎዳውን ሀብት ንብረቱ የወደመበትን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ የተጎዱበትን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ እንዲቆም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

በትግራይ ክልል ተከስቶ የነበረውን ችግር የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ችግሩን በውይይት የፈቱት መሆኑ እየታወቀ የሰላም ባለቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ሰላም መፈለጓ ያልተቋረጠ ቢሆንም አለመሳካቱ የሚያሳዝን በመሆኑ ለሰላም የሚደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ ድረስ የማይቋረጥ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጿል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ክቡር አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሁም የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየተደረገ ያለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እንዲያስቆሙ ብሎም ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ችግሮቹ በውይይት እንዲፈቱ መንግሥታዊ እገዛ በማድረግ የውይይት መድረክ እንዲያመቻቹ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪውን አቅርቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ፤ " በመላው ዓለም የምትገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ ክርስቲያን እናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ያስተላለፈችውን የሰላም ጥሪ ተግባራዊ ሆኖ አንድነቷ ጸንቶ ይኖር ዘንድ በጸሎት ተግጋችሁ ከቤተ ክርስቲያናችሁ ጎን እንድትቆሙ " ሲል ጥሪ አስተላልፏል።
ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።

(ኤፌሶን 4፥29-31)
👍1
የኛ የፃድቅ አቡነ ኪሮስ ልጆች የአባታችንን በዓለ እረፍት ደሴ ግብርና አኸካባቢ በሚገኘው አውራን የበጎ ፈቃደኞች ህብረት ውስጥ ያሉ አረጋውያን አባቶቻችንን እና እናቶቻችንን ምሳ በማብላት በምርቃናቸው ተደስተን አክብረነዋ ።
ተሹመዋል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለዘጠኝ አህጉረ ስብከት የተመረጡት 9 ቆሞሳት ዛሬ ሐምሌ 9 ቀን 3015 ዓ/ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ከሌሊቱ 9:00 ጀምሮ በተፈጸመ ሥርዓት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት አንብሮት እድ በኤጲስ ቆጶስነት ተሹመዋል።

በዚህም መሠረት
፩-  ቆሞስ አባ ክንፈገብርኤል ተክለማርያም ብፁዕ አቡነ ገሪማ ተብለው ተሠይመው ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

፪-  ቆሞስ አባ ሣህለማርያም ቶላ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ተብለው ተሠይመው ለምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት

፫-  ቆሞስ አባ ስብሐትለአብ ኃይለማርያም ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ተብለው ተሠይመው ዳውሮና ኮንታ ሀገረ ስብከት

፬-  ቆሞስ አባ አምደሚካኤል ኃይሌ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ተብለው ተሠይመው ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት

፭-  ቆሞስ አባ ኃይለማርያም ጌታቸው ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስም ተብለው ተሠይመው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት

፮- ቆሞስ አባ ጥላሁን ወርቁ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ተብለው ተሠይመው በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት

፯-  ቆሞስ አባ ዘተክለሃይማኖት ገብሬ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ተብለው ተሠይመው በሆሮ ጉድሩ ሀገረ ስብከት

፰-  ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ገብሬ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ተብለው ተሠይመው በምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት

፱-  ቆሞስ አባ ወልደገብርኤል አበበ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ ተብለው ተሠይመው በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት መመደባቸውን ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ህ/ግ መረጃ ያመላክታል።
👎21
የፌደራል እና የትግራይ ክልል አመራሮች  በትግራይ ይካሄዳል የተባለው የኤጲስ ቆጰሳት ሹመት ጣልቃ እንዲገቡ የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሳሰበ።

የኢትዮጵያ የሐይማኖት ጉባኤ ተቋሙ እንዳለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጣዊ የአለመረጋጋት ክስተት በተደጋጋሚ እያስተናገደች መሆኗ በእጅጉ አሳስቦኛል ብሏል፡፡ 

በተለይም ከሰሞኑ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፓትሪያርክን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሰላም ልዑካን በትግራይ ክልል፣ በመቀለ ከተማ በመገኘት በክልሉ ካለው የቤተ ክርስቲኒቱ መዋቅር ጋር የተፈጠረውን የግንኙነት ችግር በመፍታት እርቀ ሰላምን ለማድረግ ታሳቢ ተተደረገው ጉዞ ዓላማ ሳያሳካ ወደ አዲስ አበባ መመለሱ እንዳሳዘነውም አስታውቋል።
ምንሼ ነው ምዕመናን 🙄 ከሚሾሙት ሆኑ እንዴ እኒህ ሰውዬ 🤔
ይቺን አንስት "ሒጃብሽን አውልቀሽ ለምን ቲክቶክ ላይ ለዳን*ሻለሽ " በማለት ታላቅ ወንድሟ እንደዚህ ጎድቶታል ።

ኦርቶዶክሳውያን ሰውነታችሁ ገልጣች አንገታችሁ ላይ ደግሞ ማህተበ ክርስትናን አንልጥላችሁ የምትጨፍሩ አንስት ይሄም ሳያንሳችሁ በዓል በዓል በሆነ ቁጥር ነጠላ ለብሳችሁ ካልዘመርን የምትሉ እህቶቻችን ሆይ ክርስትናን አታሰድቡ ። ለበደላችሁ ድንበር አበጁለት። ....ክርስትናችሁን ጠብቁት ።
👍3🤯2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"…መንበረ ሰላማ… አሄሄ አዛኜን ገና ሚስማር ሳያዘንቡብንማ አይቀሩም… ሰብ… ሰብሰብ…

"…ከምር ኑሮ የተወደደው እኮ ምእመኑ ጋር ነው። አሁን ሃገር ፍቅር፣ ብሔራዊ ቲአትርም ተወዛዋዥ አለኝ ብሎ ሊጎር ይሞክር ይሆናል እኮ…?

• በነገራችን ላይ ሁለቱም ወንዶች ናቸው አይደል…? ወንድ ወንድ ላይ እንዲህ ሲተሻሽ ኢደቢራል። ቄስ ሲሆን ደግሞ የበለጠ ኢዳቢራል… አክ… ቱ…!
👎1
ዘንድሮ ኡኡኡ ነው አቦ
🤔2👏1
• ኢስመላብ አል ቅዱስ አላዋሒድ። አሜን

"…ኢዩ ጩፋን ተዉት ከምር እኔ እንደዚህ የምዕራብ ሸዋ ኦሮሞ ልጅ ያሳዘነኝ የለም። ምንአለ እንደው ያንን ቪድዮ ባላወጣሁበት ኖሮ። ምን ነክቶኝ ነው ግን በናታቹ። ከምር ያገኘውን ዲቪ ሎተሪ የሆነ ምርጥ እድል የቀደድኩበት ያህል እየተሰማኝ ነው። ማንም መንገደኛ የሚሾመውን ሹመት፣ ማንም መንገደኛ የሚበላውን የኦርቶዶክስ እንጀራ አመድ ደፍቼበት ምቀኛ ነው የሆንኩበት። ፀፀተኝ።😭😭

"…ይቴ ጭሷ ከድር ሁሴን በናትሽ አፉ በዪኝ ነፍሴ። አለ አይደል ነገሩ ሁሉ እንዲህ መላቅጡ የሚጠፋ ሳይመስለኝ እኮ ነው የገገምኩብህ። ሁለት ዓመት ሙሉ በእጄ ያስቀመጥኩትን የአንተን ቪድዮ እና ፎቶ ስትሾም ጠብቄ አውጥቼ ጉድ አደረግኩህ። አሁን 3 የወለደ ሲሾም እያየሁ አንተ ገና ለገና ሰልመሃል፣ ስትደንስ ታይተሃል፣ ከኤርትራዊት ሴተኛ አዳሪ አንድ ልጅ ወልደሃል ብዬ ሄጵ ማለቴ ዛሬ ላይ ሳስበው ከምር ትክክል እንዳልነበርኩ ተሰምቶኛል። 😂 አንዳንዴ ያው አለአይደል ስትበሰጭ የምታደርገውን አታውቅም አይደል? ኢንዴዣ ኡኖቢኝ ኖ ይቴ። በጣም ኢንቂርታ፣ ኢንቂርታ በጣም ማይ ብሩደር…ብራዘር።

• ጵጵስና ግን እንዴት አባቱ ነው የሚያምርበት በጌታቸው…!
👍2😁2
"መላው ዓለምን ያስደነገጡ ታላላቅ መከራዎች ኹሉ መነሻቸው ትዕቢት ነው፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
👍5
በመጨረሻ ዳታ ተለቀቀ😍
👍2👏21
አንድን በክፉ ምግባር የተያዘን ሰው ወደ መልካም ነገር ልትመልሰው ብትወድድ መጀመርያ ሰላሙን እንዲያገኝ አድርገው፡፡ በፍቅር ቃል ከፍ ከፍ አድርገው። እንዲህ ያለን ሰው ከክፉ ስራው እንዲመለስ ለማድረግ ከዚህ የተሻለ ዘዴ የለምና። ሰው በተግባር የሚያደርገው ፍቅር ሰዎችን የመለወጥ ፍጹም ሀይል አለውና።

ቀጥለህ በፍቅር አንድ ሁለት ቃልን ንገረው፣ በቁጣ አትንገረው። በእርሱ ላይ አንዳች የጠላትነት ስሜት አታሳይ። ፍቅር ሰዎችን ለመለወጥ መንገዱን እርሱ ያውቅበታል። ብቻ እንተ እድሉን ስጠው። የፍቅር ሰውም ሁን።

(መክስምያኖስ ባህታዊ ዘሶርያ - የበረሃ ፈርጦች)
👍3
«ወዳጄ ሆይ! እግዚአብሔር ነዳያንን የሚልክልህ መስጠትን እንድትለማመድ ነው፡፡ ዛሬ በነዳያኑ አድሮ የሚለምንህ ለኋለኛይቱ ቀን ስንቅ እንዲያስቀምጥልህ ወድዶ ነው፡፡ ታድያ ንጉሥ ወደ ቤቱ መጥቶ የሚያባርር ሰው እንደምን ያለ ጎስቋላ ሰው ነው? እንግዲያውስ ነዳያንን ስታይ ወደ አንተ የመጣው ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስ እንጂ ሰው አይደለምና አትግፋው፡፡ በረከትህንም ከቤትህ አውጥተህ አትሸኘው፡፡»

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
👍2
ወነፍሖ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት ለዝንቱ መፅሐፍ ወበጊዜሃ ተደምሰሰ ...።
“እኔ ክርስቲያን ነኝ፡፡ ለሚጠይቁት እንደዚህ ብሎ የሚመልስ ሰው በአንድ ጊዜ በኹሉም ነገሮቹ ላይ ማወጁ ነው፡፡ ሀገሩ የት እንደ ኾነ፣ ሥራው ምን እንደ ኾነ፣ ቤተሰቡ እነማን እንደ ኾኑ መመስከሩ ነው፡፡ ክርስቲያን የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ነዋሪ እንጂ በምድር ላይ ካሉት ከተሞች የአንዲቱም አይደለምና፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
👍5
አዬ ሞት
😢4🤔2
2025/07/12 16:31:19
Back to Top
HTML Embed Code: