Telegram Web Link
የጊኒዋ ባለ ውቃቢ እንስት ውሸት ተጋለጠ🙊🇬🇳

⚡️የጊኒዋ ባለ ውቃቢ ራሷን ሩቅ አዋቂ ነኝ በማለት ከአላህ የተሰጣት ልዩ ተሰጥኦ ያላት በማስመሰልና አንድ ውቅያኖስ በማምራት ከመካከል ላይ ወደ ፈጣሪዋ በልዩ ተዓምር የምትቃረብ ለመምሰል የሰራችው ድራማ በሐገሪቱ ፖሊሶች ውሸቱ ተጋልጧል።

⚡️እንስቷ ከውቅያኖሱ መካከል ላይ አንጥፋ የምትሰግድበትን ሁኔታ የተመለከቱ ብዙዎች በሰዓቱ አምነውባት የነበረ ሲሆን የማጭበርበር ጥቆማው የደረሰው የጊኒ ፖሊስ ከስፍራው ደርሶ የምትሰግድበትን ሙሰላ ሲገልጠው ከውስጥ ጠረጴዛ በመዘርጋት የውሸት ተዓምሯ አጋዢ ለማድረግ የተጠቀመችበት ያገጠጠ ውሸት በተከታዮቿ ፊት ተጋልጧል።

⚡️ፖሊስም እንስቷን በቁጥጥር ስር አውሎ ወደ ፍርግርጉ ሲዎስዳት ተዓምሯን ለማዬት የታደሙት ተከታዮቿ በስድብ ሸኝተዋታል። 😡
አቶ ወይስ ዲያቆንና ዘማሪ

ወንድማችን የቀድሞው ዲያቆን ሐዋዝ በኋላም የተሀድሶ ዋና አቀንቃኝ የነበረው ሐዋዝ በንስሃ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ለመመለስ መንገድ ላይ መሆኑን በዚሁ በማህበራዊ ሚዲያ ሰማን። መልካም ነው የዕውነት ከሆነ ይህንን ላደረገ አምላክ ክብር ምስጋና ይግባው።

መመለሱ መልካም ነው ነገር ግን እንደ ቀድሞው ዲያቆን ሆኖ ነው የሚመለሰው ወይስ ምዕመን ሆኖ አቶ ዕዝራ ተብሎ ነው? እኛስ እንዴት ብለን እንቀበለው? በአቶ ዕዝራነት ወይስ በዲያቆንና ዘማሪነት?

ቤተክርስቲያኒቱን ሰድበው ለሰዳቢ ሲሰጡና ሲያሰድቡና ሲሰድቡ ኖረው አይናቸውን በጨው አጥበው ሲመጡ እልል ብለን ብንቀበላቸውም ማለፍ የሌለብን መስመር ግን ሊኖር ይገባል ብዬ አስባለው።

በተረፈ አቶ ሐዋዝ እንኳን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ህብረት ተመለስክ። እንኳን ደስ አለህ
+++ የጽሙና ጊዜ አለህ? +++

የቆርቆሮና የብረት ጩኸት ጋጋታ ባለበት ውብና ለስላሳ የሆነውን የዋሽንት ድምጽ መስማት የሚቻለው ማን ነው? ሁከትና ረብሻ በሚነግስበት፣ የማይቋረጥ ግፊያና አለመረጋጋት ባለበት የሰዎች ግርግር ውስጥ ሆነህ እንዴት የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ ልትሰማ ትችላለህ? የእግዚአብሔርን ድምጽ በአውሎ ነፋስ ፋጨት፣ በምድር መናወጥ፣ በሚያስገመግም የእሳት ድምጽ ውስጥ አታገኘውም። እርሱ የሚናገረው ከእነዚህ ሁሉ በኋላ በሚሆነው "ትንሽ የዝምታ" ጊዜ ነው።(1ኛ ነገ 19፥12)

ልክ የመድኃታችንን የልብሱን ጫፍ በስውር ነክታ ከቁስሏ እንደ ተፈወሰችው ሴት፣ አንተም የነፍስህን ቁስል ለማድረቅ በመቅደሱ የሞላውን የጌታን የልብሱን ዘርፍ በምሥጢር የምትዳስስበት የብቻ ጊዜ ያስፈልግሃል።

ከእሾህ ወይን ከኩርንችትም በለስ እንደማትለቅም፣ ራስህን ከዚህ ዓለም ሁከት የምትለይበት ጊዜ ሳይኖርህ እውነተኛ የነፍስ መጽናናትን ልታገኝ አትችልም። ለዚህም ነው ጌታችን በወንጌል "ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ" በማለት ያስተማረን። ላዘነችው ነፍስህ መጽናናትን፣ ለልቡናህ ዕረፍትን ትፈልጋለህ? ስለ ኃጢአትህ የምታፈሰው የንስሐን እንባስ ትሻለህ? እንግዲያውስ ከሰው ርቀህ በርረህ ወደ ፈጣሪ የምትሄድበት የጽሙና ጊዜ ይኑርህ።

ጌታን ያጠመቀውና ለብዙዎች በብርሃኑ ደስ የሚያሰኝ "የሚነድ መብራት" የነበረው ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ ሁሉ በፊት ብቻውን ከአምላኩ ጋር በበረሃ ነበር። የሐዲስ ኪዳኑ ባለ ራእይ ቅዱስ ዮሐንስ እነዚያን ሁሉ ሰማያዊ ምሥጢራት የተመለከተው ብቻውን በፍጥሞ ደሴት ሆኖ ነው። ስሙን በአሕዛብ፣ በነገሥታቱና በእስራኤል ልጆች ሁሉ ፊት ይሸከም ዘንድ የተመረጠው ቅዱስ ጳውሎስ፣ ከሁሉ አስቀድሞ ግን የመረጠው አምላኩ መንፈሳዊውን ኃይል ያስታጥቀው ዘንድ የገዛ ድክመቶቹን ተሸክሞ ብቻውን ወደ አረብ በረሃ ገስግሶ ነበር።

ያንተስ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በመንፈስ የምትጎለምስበት በረሃህ ፣ እንደ ወንጌላዊው ዮሐንስ ጣዕመ መንግስተ ሰማያትን የምትዘከርበት ፍጥሞ ደሴትህ፣ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ በነፍስ ታድሰህ የምትወጣበት አረባዊ ገዳምህ የት ነው? መቼ መቼስ ወደዚያ ትወርዳለህ?

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
በሰሜን ወሎ ሃገረስብከት በሚሊኒየም አዳራሽ ከተገኙት ሊቃነ ጳጳሳት በከፊል ።

የተቻለንን ድጋፍ እናደርግ ዘንድ እነሆ አካውንቱ።
አቡኬ ሚሊኒየም ተከስቷል 😍

ትልቅ ሰው በለናል 👍
ቃዲ ኢያድ እንደዚህ ይላሉ-
"አንዲት ሴት (የነቢዩን) ሽንታቸውን እንደጠጣች ተመሳሳይ ነገር ተዘግቧል። ነቢዩም 'ከዚህ በኋላ መቼም የሆድ ቁርጠት አያስቸግርሽም' አሏት።...[1] አፋቸውን እንዲታጠቡም ሆነ ደግመው እንዳይጠጡ አላዘዙም። ሽንታቸውን የጠጣችው ሴት ሀዲስ #ሶሂህ ነው ፤ አድ'ዳርቁቱኒም ሙስሊምና ቡሃሪን ተከትሎ ሶሂህ ብሎ ዘግቦታል።የሴትየዋ ስም ባራካ ነበር ስለ ዘር ሀረጓ ግን ልዩነት አለ። አንዳንዶች ነቢዩን ታገለግል የነበረችው ኡም አይማን ነበረች ይላሉ ፤ (እሷ) እንደዚህ አለች- 'ነቢዩ ሽንት ለመሽናት ይጠቀሙበት የነበረ የእንጨት ሳህን ነበራቸው ፤ አንድ ምሽት ተነስተው ሸኑበት ጠዋት ሲነሱ ግን ባዶ ነበር።' ባራካን ስለ ጉዳዩ ጠየቋት እሷም  ' ሌሊት ተነስቼ ውሃ ጠማኝ እናም ባለማወቅ ጠጣሁት።' ይህ ሀዲስ በኢብን ጁራዪና ሌሎችም ተዘግቧል።"

[1] አልሃኪም ዘግቦታል ፤ አቡ ዳሃቢና አድ'ዳርቁቱኒም አረጋግጠውታል።

(አሽ'ሺፋ ሸሪፍ አልቃዲ ኢያድ ክፍል 1 ምዕራፍ 2 ሴክሽን 3)
127 ነብዮች ተመረቁ

ለአንድ ዓመት በነብይ ሔኖክ ግርማ ፕሮፌትክ ፋውንዴሽን ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ አንድ መቶ ሃያ ሰባት (127) ተማሪዎች ነብይ ሔኖክ ግርማ እጅ የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል!
በነገራችን መሃል…!
የነቢያት ምረቃ ዜና ተከታትለን እንመለሳለን።

"…Senior prophet ሄኖክ ግርማ ለ አንድ ዓመት ያሰለጠናቸውን 127 የጌታ ወንድና ሴት ነብያትን በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመርቋል። የ jPS prophetic foundation class 2023 graduates 🎓 እንኳን ደስ አላችሁም ተብለዋል።

"…የሰማዕታት ምርቃት ብሎ ነገር በዚያ ቤት የለም እንጂ ከነቢያት ምረቃ ቀጥሎ የሐዋርያት እና የመጋቢ፣ ተመጋቢ ምርቃት ሳይኖርማ አይቀርም የሚሉም መተርጉማንም አሉ።

"…ጋሽ ነቢዩ ሄኖክ ግርማ የሴቶች ቀሚስ በመልበስ ወንዶችን መስበክ ያዘወትራልም ተብሏል። ወሴ…😂😂
ነብይነት እናሰለጥናለን እንሾማለን።
ማስቀደስ እየቻልን ሳናስቀድስ በቤታችን ብንጸልይ ጉዳቱ ምንድን ነው?

“ወደ ቤተ ክርስቲያን ሳንኼድ በቤታችን ኾነን መጸለይ እንችላለን” የሚ ሉ ሰዎች አሉ፡፡

ሰው ሆይ! ራስህን አታስት! እርግጥ ነው, አንድ ክርስቲያን በቤቱ ውስጥ መጸለይ _ ይችላል፡፡ ነገር ግን _ ጸሎቱ በቤተ ክርስቲያን እንደሚደረገው ጸሎት በፍጹም እኩል አይኾንም፡፡ በቤተ ክርስቲያን የሚጸልዩት ጸሎት በአንድነት ኾነው የሚያደርሱት እንደዚሁም እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው እየጮኹ ልባቸውን ወደ እግዚአብሔር የሚሰቅሉ ብዙ ሰዎች ናቸውና ያሉት፡፡ ብቻህን በቤትህ ኾነህ የምታደርሰው ጸሎት ከወንድም እኅቶችህ ጋር በአንድ ነት በቤተ ክርስቲያን ኾነህ የምትጸልየውን ያህል በእግዚአብሔር ዘንድ የመሰማት ኃይል የለውምና፡፡ ለምን ቢሉ በቤትህ ውስጥ ካለው ይልቅ በቤተ ክርስቲያን ከፍ ያለ አንድነት፣ የፍቅር ገመድ፤ ከምንም በላይ ደግሞ የካህናት ጸሎት አለና፡፡

ካህናት በፊታችን ይቆማሉ፡፡ ስለዚህ የሕዝቡ ጸሎት ደካማ ቢኾን እንኳን ከእነርሱ ኃያል ጸሎት ጋር ይዋሐዳል፣ ወደ ሰማያትም ያርጋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ከውኅኒ ቤት ነጻ የወጣው በቤተ ክርስቲያን ስለ ተደረገለት ጸሎት ነው፡፡ … እንግዲህ ንገረኝ! የቤተ ክርስቲያን ጸሎት ለሐዋርያው ጴጥሮስ እንኳን አስፈላጊው ከነበረ፣

እንደዚህ ያለ የእምነት ዓምድ የኾነውን ቅዱስ ከወኅኒ እንዲወጣ ካደረገው ለምን እንደዚህ ያለውን ኃይል ትንቃለህ? ለዚህ የምታመጣው አመክንዮስ እንደ ምን ያለ አመክንዮ ነው?

ሰዎች በአንድነት ኾነው ሲጸልዩ እግዚአብሔር እንዲራራ ምሕረቱም እንዲያበዛ እንደሚያደርጉት እርሱ እግዚአብሔር ራሱ የተናገረውን አድምጥ፤ ለነቢዩ ዮናስ እንዲህ ብሎታልና፡- “ከመቶ ሃያ ሺሕ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?” (ዮና.4፡11)፡፡

የሕዝቡን ቍጥር ጠቅሶ የተናገረው እንዲሁ ለከንቱ አይደለም፤ በአንድነት የሚደርስ ጸሎት እጅግ ኃያል እንደ ኾነ ታውቅ ዘንድ ነው እንጂ።


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️
ንግስታቸው የሩጫ ውድድር አድርጋለች😂

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተደረገ በተባለው ወድድር ንግስቷ በመሰናክል ይሁን በማራቶን የተወዳደሩት የተገለጠ ነገር የለም😂

ዘንድሮ ሃይማኖታዊ ቀልደኞች የበዙበት ጊዜ ነው
✝️እንደዚህ ነዉ መታደል 🙏ሸር🙏Shet🙏✝️

👉ወጣቶች ፣ነጋዴዎች ፣ማህበራት እና ሰራተኞችን የሚያስተምር ተግባር 🙏✝️

👉 ቤተ ክርስቲያንን እወዳታለሁ ላንች እሞታለሁ ከማለት ባሻገር እንደዚህ በጉብዝና ወራት ክርስትናን የማስቀጠያ ሀዲድ የሰዉ ፊት ሳያሳፍራቸዉ ክብራቸዉ ሳያስጨንቃቸዉ እንደዚህ በአደባባይ ስለ ቅድስት ሥላሴ ብሎ ለምኖ አብያተ ክርስቲያናት የሚያሳንፁ ወጣቶች መሆን ይጠበቃል ።
👉 የደብረኝነት እና የጎጥ አጥር ሳይከልላቸዉ አሀቲ ቤተ ክርስቲያን ብለዉ ከተወለዱበት አካባቢ ዉጭ እንደዚህ ሰዉ በሌለበት አስታዋሽ ባጣዉ በደሳሳ ጎጆ ፈጣሪያችን መጋቢያችን ቅድስት ሥላሴ አይቀመጥም በማለት የቤቱ ቅናት ቢያቃጥላቸዉ እነሆ ይህን የመሰለ አብያተ ክርስቲያን እያሳነፁ ይገኛሉ ።
👉ከደሴ 89 ኪ/ሜ እርቀት ላይ ጊምባ ጭሮ የሚገኝዉ ጥቂት ክርስቲያኖች ብቻ ያሉበት የጭሮ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን እዚህ ደረጃ ደርሶ በቀጣይ ለማስመረቅ እንደዚህ በህብረት ደጆችሽ አይዘጉ ዘ ወሎ እና አብይ ኮሚቴ በጋራ እየተንቀሳቀሱ ነዉ ።
✝️እርስዎም የበኩልዎን በማድረግ ከቅድስት ሥላሴ ረድኤት በረከት ይሳተፉ።🙏🙏🙏
2024/09/30 05:31:25
Back to Top
HTML Embed Code: