13
<unknown>
📕 አቂደቱል ዋሲጥያ
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-13-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-13-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
Forwarded from የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች
💎 የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ) ታሪክ
💎ክፍል ስምንት💎
ከርሱ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የሌለ በሆነው አላህ
ምዬ መናገር እችላለሁ፡፡ በዚህ ዓለም ውስጥ ከነቢያት በስተቀር እንደ አቡበክር ያለ ታላቅ ሰው እስከ አሁን ድረስ አልተፈጠረም።
ብዙ ሙስሊም ወጣቶች ታላላቅ አድርገን የምንቆጥራቸው
ምን አይነት ሰዎችን ነው? እስኪ የአቡበክርን ታሪክ ለመመርመር ጥረት እናድርግ፡፡ ከተራራ የገዘፈ ታላቅነት ጎልቶ ይታየናል። የአስ-ሲዲቅን ሕይወት እንመርምር፡፡
🔰 እስክጠግብ ድረስ እርሳቸው ጠጡ!
አቡበክር አስ-ሲዲቅ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ረዘም ላለ ጊዜ በዋሻው ተሸሽገው ቆዩ፡፡ ሁለቱንም ረሃብና ጥማት ያሰቃያቸው ጀመር፡፡ አንድ እረኛ ከዋሻው ወዲያ ማዶ ሲያልፍ ተመለከቱ፡፡ ጥቂት ወተት ካለው ይሰጣቸው ዘንድ ለመጠየቅ አቡበክር ወጣ አሉ፡፡ መጠነኛ ወተት ከእረኛው አገኙ፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲጠጡ አደረጉ፡፡ አቡበክር ይህን ሁኔታ በተመስጦ ሲተርኩ እንዲህ ይላሉ፦
“ወተቱን እኔ እስክረካና እስክጠግብ ድረስ እርሳቸው ጠጡ፡፡” እንዴት ያለው ፍቅር ነው! የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እርካታ የርሳቸው እርካታ ሆነ፡፡ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጥገብ ለርሳቸውም ጥጋብ ሆነ፡፡ እንዲህ ያለ ፍቅር ታይቶም አይታወቅም! ከዚህ በኋላ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)ና ወዳጃቸው ጉዙዋቸውን ወደ መዲና አቀኑ፡፡ አቡበክር በአካባቢው ታዋቂ ነጋዴ ስለነበሩ በየመንገዱ ያገኙዋቸው ሰዎች ሰላምታ
ያቀርቡላቸዋል።
ስለ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ማንነትም ይጠይቋቸው ነበር። አንዱን ሰላም ሲሉት ይህ ሰው ማነው አቡበክር በማለት ይጠይቃቸዋል ይህ መንገድ የሚመራኝ ሰው ነው በማለት ይመልሳሉ። ጠያቂው ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ለአቡበክር መንገድ የሚመሩት ሰው እንደሆነ እንዲገምት አድርገዋል። በእርግጥ አቡበክርን የሐቅ የእውነትና የጀነት መንገድ ይመሯቸው የነበሩት ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ናቸው። ዑመር ቢን አል-ኸጣብ የአቡበክር መዓዛ እንደሚስክ ሽቶ ያውዳል ይሉ ነበር፡፡
🔰እኔ ተራ ሰው ነኝ
እርሶ ግን የዚህ ዲን ዓርማ ነዎት!
አቡበክር ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ወደ መዲና አብረው በመጓዝ ላይ
እያሉ አንዴ ወደፊት አንዴ ደግሞ ወደኋላ ቆይተው ደግሞ ከግራና
ከቀኝ እየሆኑ ያጅቧቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ምን ሆነህ ነውአቡበክር” ይሏቸዋል። አቡበክርም “መጠበቅ እንዳለብኝ ሳስታውስ ከፊት እሆናለሁ። ከዛም የሚያሳድዱዎትን ሳስታውስ ከኋላ እሆናለሁ ከዚያም በግራዎ በኩል አንድ ነገር እንዳይጎዳዎ እልና በግራዎ እሆናልሁ፡፡" በቀኝ በኩልም ምንም ነገር እንዳያገኝዎ እሰጋና በስተቀኝ እሆናሉ፡፡ ‹‹አቡበክር ይህን ያህል ትወደኛለህ እንዴ?›› ይላሉ፡፡ ‹‹እጀግ በጣም ነው እንጂ ረሱልም (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹በእኔ ቦታ ሆነህ ለመሞት ትፈልጋለህ ማለት ነው?›› ብለው ይጠይቃሉ ‹‹አዎና እኔ ብሞት እኮ ተራ ሰው ነኝ፡፡ እርሶ ግን የማይገኙ የዚህ ዲን አርማ ነዎት፡፡››
🔰አምሳያ የሌለው ሥነ-ምግባር
አቡበክር አስ-ሲዲቅ ከላይ በተጠቀሰው መልኩ እያደረጉ መዲና
እስኪገቡ ድረስ አብረዋቸው ተጓዙ፡፡ ወደ መዲና ሲቃረቡ የመዲና ሰዎች (አንሷሮች) እየጠበቋቸው ነበር፡፡ ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) በመልክ ለይተው አያውቋቸውም። አቡበክር ለጥበቃ ከፊት ከፊት ይጓዙ ስለ ነበር አንሷሮች ሁሉ እርሳቸው መስለዋቸው ነበርና የተጫነበትን ግመል ይዘውላቸው ወደፊት ይመሩ ጀመር፡፡ ይሄን ጊዜ አቡበክር ሁኔታው ይገባቸውና ኩታቸውን ያወልቁና ጥላ ይሆናቸው ዘንድ ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ይከልሉበታል፡፡ አንሳሮችም ወዲያው ነገሩ ይገባቸውና የረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ግመል መሳብ ይጀምራሉ።
🔰የውመል ፉርቃን
ጊዜው ሄዶ ሙስሊሞች መዲና ላይ መሠብሰብ ጀመሩ። ታላቁ የበድር ጦርነት ተከሰተ፡፡ የአስ-ሲዲቅ ልጅ ዐብዱረህማን በወቅቱ ገና አልሰለመም ነበር፡፡ በውጊያው ዕለት ሰይፉን ከአፎቱ መዘዘና "ማነውየሚገጥመኝ?›› ብሎ ፎከረ፡፡ አቡበክር(ረ.ዐ) ተነሱና ««የአላህ መልዕክተኛ ሆይ እኔ እገጥመዋለሁ›› አሉ፡፡ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) "ተወው እኔ እበቃዋለሁ" ብለው ተነሱ፡፡ ዐብዱረህማን ቢን አቡበክር ከሰለሙ በኋላ ለአባታቸው እንዲህ አሏቸው “ያኔ ካንተ ጋር ላለመግጠም ብዬ እየተደበቅሁ ነበር፡፡
አቡበክርም(ረ.ዐ) ‹‹ወላሂ ያኔ ባገኝህ ኖሮ አልምርህም ነበር›› አሉት፡፡
አቡበክር ሰውነታቸው ለስላሳና ክብደታቸው ቀላል ቢሆንም
የቀልባቸው ጥንካሬ ግን ድንቅ ነበር፡፡ የአላህ (ሱ.ወ) ውሳኔ እርሳቸውን የመሰሉ ሰዎች በዓርአያነት ይከተሏቸው ዘንድ ገርና ለስላሳ ሆነው ተፈጠሩ፡፡ ህይወታቸውና ገንዘባቸው የአላህ (ሱ.ወ) ዲን የበላይ ይሆንዘንድ የማያወላውሉ ሰዎች አስ-ሲዲቅን በዓርአያነት መከተል ይኖርባቸዋል፡፡ እርሳቸውን ሞዴል ማድርግ አለባቸው፡፡
የበድርን ውጊያ አቡበክር ጀብድ በተሞላበት ሁኔታ ነው ያሳለፉት፡፡ በወቅቱ ሶሃባዎች ከከህዲያኖች ይከላከልላቸው ዘንድ ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዙፋን ሠርተውላቸው ነበር፡፡ ይህን ሠርተው ካበቁ በኋላ ከረሱል (ስ.ዐ.ወ) ጎን ሆኖ የሚከላከል ሰው ይመርጡ ጀመር፡፡ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ዓልይ ቢን አቡጣሊብ(ረ.ዐ) ሲተርኩ እንዲህ ይላሉ ‹‹ይህንኑ ኃላፊነት ለመውጣት ሁላችንም አፈግፍገን ነበር፡፡ አቡበክር ሰይፋቸውን መዘው መጡና ‹‹የረሱልን ዙፋን እኔ እየጠበቅኩ እከላከላለሁ አሉ፡፡ እስከመጨረሻው የውጊያ ሰዓት ድረስም ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሳይለዩ በተከላካይነት ቆዩ፡፡››
አቡበክር የነበራቸው ወኔ እጅግ ከፍተኛና እንግዳ ነበር፡፡ ለጀነት
በተለይ ደግሞ ለከፍተኛው የፊርደውስ ጀነት የነበራቸው ጉጉት
አስገራሚ ነው፡፡ ይህንን ክስተት እስኪ እናስተውል።
አንድ ቀን ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሃቦቻቸውን (የዕምነት ጓዶቻቸውን)
ሰብስበው ስለጀነት ሰዎች ሁኔታ ይነግሯቸው ነበር፡፡ ‹‹ጀነት ውስጥ የተለያዩ የማዕረግ በሮች አሉ፡፡ እንደየሥራው በየበሩ የሚጠራ ሰው አለ፡፡ የሰላት ሰው በሰላት በር፤ የጾመ ሰው ረያን በሚባል በር፤ ሙጃሂድ ሆነ የሞተ ሰው የጂሀድ በር በሚባለው በኩል፤ የሶደቃ ሰው የነበረ በሶደቃ በር፣ በሚባለው በኩል እንደየሥራው እየተጠራ ይገባል›› ብለው ነገሯቸው፡፡
የጀነት ጉጉታቸው ወደር ያልነበረው አቡበክር እንዲህ በማለት ጠየቁ... ‹‹አንቱ የአላህ መልዕክተኛ በሁሉም በር እየተጠሩ መግባት የሚቻልበት ሁኔታ አለን?›› ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) «እንዴታ አቡበክር አንተ ከእንዲህ ዓይነት ሰዎች እንድትሆን እመኛለሁ፡፡» አሏቸው።
🔰ሁለገብ ማንነት
በአንድ ወቅት ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሙስሊሞችን የፈጅር ሶላት ካሰገዷቸው በኋላ ወደ እነርሱ ተቀጣጭተው ተቀመጡና እንደሚከተለው ጥያቂያዎችን አቅረቡ፡፡ «ከናንተ ውስጥ ማነው ለዛሬ ጾምን ነይቶ ያደረው፡፡ ሁሉም ዝም ሲሉ ሰይድ ዑመር(ረ.ዐ) «አንቱ የአላህ መልእክተኛ! እኔ ለመጾም ነይቼ አላደርኩም›› አቡበክር(ረ.ዐ) ቀበል አደረጉና «እኔ ጾምን ነይቼ ነው ያደርኩት» አሉ፡፡ ረሱልም (ሰ.ዐ.ወ) ጥያቄዎችን እያከታተሉጠየቁ «ከእናንተ ውስጥ ታማሚን የጠየቀ ማነው?» «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ እኛ በቀጥታ የመጣነው ፈጅር ለመስገድ ነው በዚህ ሰዓት እንዴት የታመመን ልንጠይቅ እንችላለን፡፡» በማለት ሰይድ ዑመር....http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid

15
<unknown>
📕 አቂደቱል ዋሲጥያ
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-15-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-15-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
Forwarded from የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች
💎 የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ) ታሪክ
💎ክፍል ዘጠኝ💎
«አንቱ የአላህ መልዕክተኛ እኛ በቀጥታ የመጣነው ፈጅር ለመስገድ ነው በዚህ ሰዓት እንዴት የታመመን ልንጠይቅ እንችላለን፡፡» በማለት ዕይድ ዑመር መለሱ፡፡ አቡበክርም(ረ.ዐ) «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ እኔ ወደ መስጅድ ለመሄድ ከቤቴ ስወጣ ትላንት ወንድሜ አብዱራህማን ቢን ዐውፍ መታመሙን አስታወስኩ፡፡ የርሱ ቤትና የእኔ ቤት በመስጅዱ መካክል ይገኝ ነበር፡፡ ለሪጅር ሶላት መንቃቱን ስላወቅኩ አንድ አፍታ ገብቼ ጠየቅሁትና ወደዚህ ለሶላት መጣሁ» አሏቸው፡፡
ረሱል (ሰዐ,ወ) ቀጠል አደረጉና «ዛሬ ምሽት ከናንተ ውስጥ ሶደቃ የሰጠው ማነው?» ብለው ጠየቁ፡፡ ዑመርም “በዚህ ምሽት ሶደቃ የሰጠነው ማንም ደሃ የለም” ብለው መለሱ፡፡ «አንቱ፡ የአላህ መልዕክተኛ ቢን ዓውፍን ከጠየቅሁ በኋላ ወደ መስጂድ ስገባ ድሃ አገኘሁና በእጄ የተጋገረ ዳቦ ይዤ ስለነበር ለርሱ ሰጠሁት» በማለት አቡበክር ተናገሩ፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ “አንተ አቡበክር ዛሬ አንተን በጀነት
አብስሬሃለሁ ይህን ሁሉ ሥራ የሠራ ሰው ጀነት ሊበሰር ይገባዋል፡፡”
ዑመርም ደንገጥ አሉና “አቡበክር ሆይ! በምንም ነገር አንተን ቀድሜህ አላውቅም" አሏቸው።
🔰ከባዱ ዘመቻ
ሰይድ ዑመር(ረ.ዐ) እንዲህ ይላሉ፡- «በተቡክ ዘመቻ ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደኛ መጡና ለዘመቻው ግልጋሎት ይውል ዘንድ እንድንወድቅ (እንድንመጸውት) ቅስቀሳ እደረጉልን። ይህ ሀሳብ በጣም ተስማማኝ፡፡ የተወሰነ ገንዘብ ስለነበረኝ ዛሬ እበበክርን በመብለጥ አለብኝ ብዬ ወሰንኩ፡፡ ወደ ቤቴ ሄድኩና ካለኝ ገንዘብ ውስጥ ግማሹን ይዤ ተመለስኩና ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ፊት ዘረጋሁት፡፡ እሳቸውም «ለቤተሰቦችህ ምን ያህል
እስቀረህላቸው ብለው ጠየቁኝ። እኔም "ከገንዘቤ ግማሹን ትቼላቸዋለሁ::" አልኳቸው። አቡበክርም(ረ.ዐ) ምንም እንኳ ከዑመር ያነሰ ቢሆንም ቤታቸው ሄደው ገንዘባቸውን ሁሉ አንዲትም ሳያስቀሩ ጠራርገው በማምጣት ነብዩ(ሲ.ዐ.ወ) ፊት ዘረገፉት ነብዩም (ሰዐ,ወ) ለቤተሰቦችህ ምን ያህል አስቀረህላቸው አቡበክር? በማለት ጠየቋቸው:: አበበክርም «ለቤተሰቦቼ ከአላህና ከርሶ በስተቀር ምንም የተውኩላቸው ነገር የለም፡፡" በማለት መልስ ሰጡ። እኔም እንዲህ አልኩኝ "አቡበክር ሆይ! ወላሂ
ከአሁን በኋላ ካንተ ገር ለመፎካከር አልሞክርም።" ሃብት ንብረታቸውን በመሉ ለአላህ (ሱ.ወ) ዲን ሲሉ ለሶስት ጊዜያት ያህል የሰጡት ብቸኛ ጀግና አቡበክር አስ-ሲዲቅ ናቸው፡፡
እስቲ ጥቂት ቆም ብለን ራሳችንን እንጠይቅ! ማነው እስቲ ከኛ
ውስጥ ለአላህ (ሱ.ወ) ብሎ የተቸገሩ ወገኖቹን ለመርዳት ገንዘቡን ሁሉ የሚሰጥ ሰዎች አሁንም ሞልተዋል፡፡ እኔ ራሴ በዐይኔ አንድ በጣም ደካማ ሰው የቦስኒያ ሙስሉሞችን ለመርዳት ራሱ የሚጠቀምበትን ዊልቸር ሲቸር ተመልክቻለሁ፡፡ አንዲት ሴትም ምንም ነገር ስላልነበራት ሙስሊሞችን ለመርዳት የራሷን ጌጣ ጌጦች ስትሰጥ አይቻለሁ፡፡ በዚህ ኡማ ውስጥ የአቡበክርን ዓርአያነት የሚከተል ሰው ሞልቶናል፡፡ ይህ ዓይነቱ ድንቅ ዓርአያነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንመኛለን፡፡
አቡበክር ገንዘባቸውን ሁሉ ለአላህ (ሱ.ወ) ሲሉ ሶስት ጊዜያት
ያህል መጽውተዋል ብለናል፡፡ እነርሱም፡-
-አንዲት ሚስኪን ሴት ከባርነት ነጻ ሲያወጡ፣
- ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ወደ መዲና ሲሰደዱና
- አሁን እንዳልነው በተቡክ ዘመቻ ወቅት ናቸው፡፡
🔰ለአላህህ (ሱ.ወ) የነበራቸው ፍራቻና ክብር
ከዕለታት አንድ ቀን የአስ-ሲዲቅ አገልጋይ ለአቡበክር ምግብ
ያቀርብላቸዋል፡፡ አቡበክርም ትንሽ ቀመስ ያደርጉለታል፡፡ አንድ ምግብ ሲቀርብላቸው የምግቡ አመጣጥ ከየት እንደሆነ የመጠየቅ ልምድ ነበራቸው፡፡ በዚህም መሠረት አገልጋያቸውን የምግቡን ምንጭ ይጠይቁታል፡፡ ‹‹ሙስሊም ከመሆኔ በፊት ለስዎች እጠነቁል ነበር፡፡›› በወቅቱ አንድ የጠነቆልኩለት ሰው የነበረበትን ዕዳ ኣሁን ስለከፈለኝ በዚሁ ገንዘብ ነው ይህን ምግብ የገዛሁት ይላቸዋል፡፡
አቡበክርም በጣም ተደናግጠው «አጥፍተኸኝ ነበር›› ይሉና
ጣታቸውን ወደ ጉሮሮዋቸው ሰድደው የገባውን ለማውጣት ከራሳቸው ጋር መታገል ይጀምራሉ፡፡ ይህን የተመለከቱ ሰዎች በላዩ ላይ በብዛት ውሃ ጠጥተው ካልሆነ ሊወጣሳቸው እንደማይችል ይነግሯቸዋል። ውሃ አምጣልኝ ብለው ያዛሉ፡፡ የመጣላቸውን ውሃ በደንብ ከጠጡ በኋላ እንዲያስታውካቸው በማድረግ የቀመሱትን ጥቂት ጉርሻ ነቅለው ያወጡታል፡፡ ሁኔታውን የሚመለከቱት ሰዎች ‹‹አላህ ይዘንሎት! ትንሽ ነበርች›› ይሏቸዋል፡፡ እርሳቸውም «ወላሂ ነፍስህ ካልወጣች በስተቀር አትወጣም ነበር ብባል እንኳ ጎልገዬ አወጣት ነበር” ይላሉ፡፡
🔰አስገራሚ ትህትናቸው
በመዲና ከተማ ውስጥ ባጋደለ ደሳሳ ጎጆ ውስጥ የምትኖር
አንዲት ድሃ አሮጊት ሴትዮ ነበረች፡፡ አቡበክር አስ-ሲዲቅ(ረ.ዐ) በየሳምንቱ ወደ ቤቷ እየሄዱ ቤቱን አጽድተውላት ይመለሱ ነበር፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ሰይድ ዑመር (ረ.ዐ) የባልቴቷን ደካማነት ይሰሙና ሊጠይቁዋት ቢሄዱ ቤቷ ጥርት ባለ ንጽህና መያዙን ያዩና እንዲህ አድርጎ የሚያጸዳላት ማን እንደሆነ ይጠይቋቸዋል፡፡ ሴትየዋም ማንነቱን የማያውቁት አንድ ሰው በየሳምንቱ እየመጣ እንደሚያጸዳላቸው ይነግሯቸዋል፡፡
ሰይድ ዑመርም የዚህን ደግ ሰው ማንነት ማወቅ ይኖርብኛል
በማለት በሳምንቱ ተደብቀው መጠባበቅ ይጀምራሉ፡፡ ዑመር(ረ.ዐ) ሁኔታውን እንዲህ ይተርካሉ፡፡ «አቡበክር(ረ.ዐ) መጥተው ቤቱን አንኳኩ፡፡ በሩ እንደተከፈተላቸው አሮጊቷን ወደ ውጪ ደግፈው አወጧቸውና ቤቱን ካጸዱ በኋላ ሴትየዋን ወደ ነበሩበት መልስው ወዲያው በመውጣት ወደ መጡበት አቅጣጫ ይሄዳሉ፡፡››
ኧረ ለመሆኑ ! እስኪ ማነው ከእኛ ውስጥ ሃቃቸው የማያልቀውን
እናት አባቱን እንኳ እንዲህ አድርጎ የሚያገለግለውና የሚያግዘው?
ራሳችንን መጠየቅ አለብን፡፡
🔰ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስስል ሲዲቅ የነበራቸው ውዴታ
አንድ ቀን ሶሀባዎች በተሰበሰቡበት ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መስጂድ ገቡና ‹‹አቡበክርስ የታለ?›› ሲሉ ጠየቁ፡፡ አቡበክር ቆም አሉ "ና አጠገቤ ሁን” አሏቸው፡፡ “ዑመርስ የት አለ” ሲሉ አስከተሉ፡፡ እርሳቸውም ቆም ሲሉ ‹‹ና አጠገቤ ሁን›› አሉና የሁለቱንም ሶሀቦች እጅ ይዘው ከፍ
በማድረግ እንዲህ አሉ “በዕለተ ትንሳኤ ልክ እንደዚህ ነው
የምንቀሰቀሰው፡፡”
ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ከሰው ሁሉ ማንን ይበልጥ እንደሚወዱ ሲጠየቁ ‹‹ዓኢሻን› አሉ፡፡ ከወንዶችስ ሲባሉ ‹‹አባቷን አቡበክርን›› አሉና እንዲህአሉ «አቡበክር ሆይ! በዋሻው ውስጥ ጓደኛዬ እንደነበርከው ሁሉ የጀነትን መጠጥ (ሐውድ) ሳከፋፍልም የቅርብ ጓደኛዬ ትሆናለህ፡፡»
ከዕለታት አንድ ቀን ሰይድ ዑመር በአንዲት ንግግር አቡበክርን ያኮርፏቸውና ጥለዋቸው ይሄዳሉ፡፡ አቡበክርም(ረ.ዐ) ከኋላ እየተከተሉ "ዑመር እባክህ አትቆጣ ይቅር በለኝ” ቢሏቸው ዑመር(ረ.ዐ) ዝም ብለዋቸው ሄዱ፡፡
ሰይድ አቡበክር(ረ.ዐ) ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሄዱና እንዲህ አሏቸው «ዑመርን ይቅርታ አድርግልኝ፣ ታረቀኝ ብለው እንቢ አለኝ ከዚያም ዑመር ትንሽ ቆይተው...
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
--------ኢንሻአላህ ይቀጥላል.......
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ🎯

16
<unknown>
📕 አቂደቱል ዋሲጥያ
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-16-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-16-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
17
<unknown>
📕 አቂደቱል ዋሲጥያ
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-17-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-17-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
Forwarded from የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች
ሰይድ አቡበክር ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሄዱና እንዲህ አሏቸው
«ዑመርን ይቅርታ አድርግልኝ፣ ታረቀኝ ብለው እንቢ አለኝ ከዚያም
ዑመር ትንሽ ቆይተው ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መስጂድ ሲገቡ አቡበክር አጠገባቸው እንደተቀመጡ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) በጣም ተቆጥተው ፊታቸው ቀልቶ አዩዋቸው።
አቡበክርም ይህንኑ የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሁኔታ ሲመለከቱ
ያበርዷቸውና ያረጋጓቸው ጀመር፡፡ «ረሱል ሆይ! እባክዎን ይረጋጉ እኔ ነኝ ጥፋተኛ አሉ። ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ “ምን ሆነህ ነው ዑመር እንዴት ለአቡበክር ፊት ትነሳዋለህ?..»
"ሰዎች ሆይ! ይህን ዲን ዤ ስመጣ ሰው ሁሉ ፊት ሲነሳኝ
የተቀበለኝ አቡበክር ነው፡፡ እውነተኛ ነህ ያለኝ አቡበክር ነው፡፡ ገንዘቡን፣ ነፍሱንና ቤተሰቡን አሳልፎ የሰጠኝ አቡበክር ነው፡፡ እባካችሁ ጓደኛዬን እንዳትነኩት፡፡" ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አቡበክርን(ረ.ዐ) ቀና ብሎ ያያቸው ኣልነበረም፡፡
🔰የመዋደድ ውበት
በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)ና በአቡበክር(ረ.ዐ) መካከል የነበረው መዋደድ መለኪያ አልነበረውም። አንድ ቀን በነብዩና (ሰ.ዐ.ወ) በእሜቴ ዓኢሻ መካከል የፍቅር ጭቅጭቅ ይጀመራል፡፡ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ «በመካከላችን ማን እንዲፈርድ ትፈልጊያለሽ፡፡ አቡ ኡበይዳ ይፍረድ?›› ዓኢሻም “አቡኡበይዳ መልካም ሰው ቢሆንም ከመጣ እርሶን ነው የሚደግፈው” ይላሉ ‹‹እሺ አባትሽ ይሁን?› እሜቴ ዓኢሻ ይስማማሉ፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አስ-ሲዲቅን አስጠሯቸው። አቡበክር እንደመጡ እሜቴ እንዲህ ይላሉ «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ እውነቱን ብቻ
ይንገሩት›› አቡበክርም ተቆጥተው ‹‹እርሳቸው ያለእውነት መች ይናገራሉ” ብለው ዓኢሻን ሊመቷት ተጠጉ፡፡ ረሱልም (ስ.ዐ.ወ)
በመሃላቸው ይገቡና ‹‹አቡበክር ይህን እንድታደርግ አላስጠራንህም፡፡ በቃ ተወው›› ይሏቸዋል፡፡
አቡበክር ከወጡ በኋላ ለእሜት ዓኢሻ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ
ይሏቸዋል «በእርሱና በአንቺ መካከል እንዴት ገላጋይ እንደሆነኩ አየሽ አይደል» አቡበክር(ረ.ዐ) ቆየት ብለው ተመልሰው ሲገቡ ሁለቱም ሲሳሳቁ አገኙዋቸውና ‹‹ስትፋለሙ እንደጠራችሁኝ በተስማማችሁ ጊዜም አሳትፉኝ» በማለት ቀለዷቸው፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) «አቡበክር ና ተሳተፍ› አሏቸው፡፡
ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) መውደድ ከአላህ (ሱ.ወ) የሚገኝ በረከትና ጸጋ
ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ባሪያውን ሲወድ ይህን በረከትና ጸጋ ያጎናጽፈዋል፡፡ ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ወደድክ ማለት የአላህን (ሱ.ወ) ሪዝቅና ችሮታ አገኘህ ማለት ነው፡፡ ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ወዳጆች ከሆኑ ሙስሊሞች ጎን መሰለፍም ይጠበቅብናል፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሌሊት ጉዞ ባደረጉበትና ወደሰማይ በመጠቁበት ወቅት የአፍታ ማረፊያ የነበራቸው ቁዱስን ከጥቃት ካልተከላከልን
እንዴት ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) እንወዳለን እንላለን፡፡ ታላቁ አቡበክር ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከእንቅልፋቸው እንዳይነቁ ብለው እባብን የሚያክል ነገር
ሲነድፋቸው ድምጻቸውን ዋጥ ማድረጋቸዉን አይተናል፡፡ እኛ ግን የተቀደሰ የመሰሊም ግዛቶች በጠላት እጅ ሲቆሽሹ ዐይተን እንዳላየ
መስለን እናንቀላፋልን፡፡
አንድ ቀን አቡበክር(ረ.ዐ) ለረቢዓ ቢን ካዕብ ትንሽ የሚያስከፋ ንግግር ይናገሩትና በመካከላቸው አለመግባባት ይፈጠራል፡፡ አቡበክርም(ረ.ዐ) በሁኔታው ያዝኑና «ረቢዓ ግድ የለም የተናገርኩህን መልሰህ ተናገረኝ” ይሉታል፡፡ ‹‹ረቢዓም መልስማ አልሰጦትም» ይላል፡፡ አቡበክርም «ረቢዓ በዚህ ንግግሬ አላህ ፊት እንድከሰስ ትፈልጋለህ?›› ይሉታል፡፡ ሳይናገር ዝም ይላቸዋል፡፡ አቡበክርም ቆጣ ብለው «ከዚህ ቃሌ ጋር አላህ ፊት እንድቀርብ ትወዳለህ ማለት ነው ወላሂ ለረሱል ሄጄ እነግራቸዋለሁ» ይላሉ፡፡
የረቢዓ(ረ.ዐ) ወገኖችም ተገርመው «ራሱ የሚያስከፋ ንግግር ተናግሮህ ሲያበቃ እንደገና ለረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እናገራለሁ ይላል እንዴ?›› ይላሉ። ሪቢዓም «ለመሆኑ የሰውየውን ማንነት አውቃችኋል? ዝም በሉ አስ-ሲዲቅ እኮ ነው! አሁን ለኔ ወግናችሁ እንዲህ ስትናገሩ እንዳይሰማንና እንዳይቆጣን ደግሞ! ከተቆጣ ለረሱል ሄዶ ይናገራላ ረሱልም እርሱን በማስቆጣታችን ይቆጡናል እርሳቸው ከተቆጡ ደግሞ ለእርሳቸው እና ለአቡበክር ቁጣ ሲል አላህም ስለሚቆጣ ረቢዓን ታስጠፋላችሁ፡፡ አሁን ዝም በሉ፡፡››ይላቸዋል ረቢዓ(ረ.ዐ) በስጋት ከአስ-ሲዲቅ(ረ.ዐ) ኋላ እየተከተለ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ ሲደርሱ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ፈገግ ብለው "አል ሲዲቅና አንተ ምን ሆናችሁ?" ይላሉ አንድ የሚያስከፋኝን ቃል ተናገሩኝና እርሱን መልሰህ ተናገረኝ ሲሉኝ እኔ ደግሞ አይሆንም አልኳቸው›› አለ ረቢዓ፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) «ረቢዓ አዎን ልክ ነህ፡፡ ከአቡበክር ጋር መመላለስ የለብህም ይልቁንም አቡበክር ሆይ! አላህ ይማርህ» ብለው» አሉት፡፡
🔰በስንብቱ ዋዜማ
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስልሣ ሶስተኛ ዓመታቸው ላይ ደርሰዋል፡፡
ሠውነታቸው ላይ የድካም ሁኔታ ይተይባቸው ጀምሯል። አንዲት ሴት ወደ ርሳቸው ዘንድ መጥታ የሆነ ነገር እንዲሰጥዋት ጠይቃቸዋለች፡፡ ከዓመት በኋላ እንድትጠይቃቸው ይነግሯታል፡፡ እርሷም «እኔ ስመለስ ባላገኞትስ?›› ትላለች፡፡ ከመድከማቸው የተነሳ እስከ ቀጣዩ ዓመት ሊቆዩ እንደማይችሉ ገምታለች። «እኔን ካላገኘሽኝ አቡበክር ጋር ሄደሽ ትጠይቂዋለሽ ይሏታል። ይህ የመልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) አባባል ከርሳቸው በኋላ አቡበክር እንደሚተካቸው (ሊተኳቸው እንደሚገባ) አመላካች ነው፡፡
ከዚህ ክስተት በኋላ ነበር ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የመሰናበቻውን ሐጅ
ያደረጉትና ተከታዩ የቁርዓን አንቀጽ የወረደው
الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا ۚ
"ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡" (ሱረቱል ማኢዳህ- 3)
ይህ አንቀጽ ሲወርድ ሶሃቦች ሁሉ በደስታ ሲስቁ አስ-ሲዲቅ ብቻ በአንቀጹ ስለ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መሰናበት የሚጠቁም ነገር እንዳለ ስለገባቸው ስቅስቅ ብለው አለቀሱ፡፡
በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሕመም ይጠናባቸው ጀመር፡፡ ዓኢሻ ቤት ሆነው ታስታምማቸው ዘንድ እንዲፈቅዱላቸው ሚስቶቻቸውን ሁሉ
አስፈቀዱ፡፡ ፈቀዱላቸው፡፡ የመጨረሻዎቹ ሰዓታት ሲደርሱ ሶሃቦች ሁሉ በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መስጂድ ተሰባስበው ከፍ ባለ ድምፅ ያዝመትሙ ጀመር። ረሱል (ስ.ዐ.ወ) ድምጻቸውን ሰምተው ምን እንደሆኑ ሲጠይቁ በርሳቸውስጋት ገብቷቸው እንደሆነ ተነገራቸው!! ረሱልም (ሰ.ዐ.ወ) "ያሉበት ተሽክማችሁ ውሰዱኝ» አሉ፡፡
እንደደረሱም ሶሃቦችን እንዲህ አሏቸው «እናንተ ሰዎች ሆይ! የኔ ሁኔታ አስፈርቷችኋልን?» ሶሃቦችም "አዎን አንቱ የአላህ መል
ዕክተኛ» በማለት መለሱላቸው እርሳቸውም እንሚከተለው አሏቸው... «እናንተ ሰዎች ሆይ! የእኔና የእናንተ የቀጠሮ ቦታ ዱኒያ
አይደለችም፡፡ ቀጠሮዋችን ሐውድ ዘንድ ነው፡፡ ከዚሁ ሆኜ እያየሁት ይመስለኛል...
----------ኢንሻአላህ ይቀጥላል-----
📌የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ📌

#የጁምአ_ቀን
ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ .ወሰለም )እንዲህ ብለዋል ፡-
አርብ(ጁመዓ) ቀን፡ ገላውን ታጥቦ መላ ሰውነቱን አፀዳድቶ ፡ቅባትና ሽቶ ከተቀባ በሗላ ጁመአ ለመስገድ ቀደም ብሎ ወደ መስጊድ ፡በመሔድ ሌሎች ሰዎችን ሳይገፋና ሳይረብሺ በፀጥታ ቦታውን ለሚይዝ ፡ከዚያም የቻለውን ያህል (ነፍል) ከሰገደ በሗላ በፀጥታ ኹጥባን(የኢማሙን ንግግር )ለሚያዳምጥ ሰው ከዚያ ጁመዓ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ጁመአ ድረስ በመካከል ያለው ሐጢያቱን አላህ ይተውለታል፡፡ ነብዩ{ሰ,ዐ,ወ} ስለ ጁምአ ቀን ታላቅነት ሲናገሩ የጁምአ ቀን የቀኖች ሁሉ ኑጉስ ነው እነዚህ አምስት ነገሮች በጁምአ ቀን ተከስተዋል ብለዋል። እነሱም
1, አላህ አደምን የፈጠረው በጁመአ ቀን ነው፣
2, አደም ከጀነት የወጡት በጁምአ ቀን ነው፣
3, አደም የሞተውም በጁመአ ቀን ነው፣
4, ቂያማ የምትቆመውም በጁመአ ቀን ነው፣
5, በጁምአ ቀን የሆነች ሠአት አለች።አንድ የአላህ ባሪያ የጠየቀውን ነገር ይሠጠዋል፣ያቺን ሠአት ካገኛት ሀራም ነገር እስካልሆነ ድረስ አላህ ይቀበለዋል። በሌላ የሀድስ ዘገባ አንድ ሰው ታጥቦ ያለውን ጥሩ ልብስ ለብሶ ሽቶ ተቀብቶ ወደ መስጂድ ሄዶ ማንንም አዛ ሳያደርግ ኢማሙ ቁጥባ ሲያደርጉ ዝም ብሎ ከሠማ ጁማአውን ከሰገደ አላህ ካለፈው ጁምአ እሥከ አሁኑ ጁምአ ያለውን ወንጀሉን ያብስለታል። በሌላ የሀድስ ዘገባ የጁምአ እለት በመጀመሪያ ሠአት ወደ መስጅድ የገባ ግመል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ የቀንድ ከብት ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ በግ/ፍየል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ ዶሮ ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ እንቁላል ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታላ። ኢማሙ ሚንበር ላይ ሲወጡ የሚመዘግቡት መላኢኮች የኢማሙን ኹጥባ ለመስማት መስጂድ ይገባሉ።
የአላህ መላእክተኛ(ሰ,ዐ,ወ) እንድህ ብለዋል፦
የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላወትን ማውረድ አብዙ፣ማንኛውም ሠው የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላዋት አያወርድም ሠላዋቱ ቢቀርብልኝ እንጅ።
{አልባኒ ሶሂህ ብለውታል} "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ። መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ።" "ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ። ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡" ((62:910)
[የጁመአ ቀን ሱናወች] ~
~ገላን መታጠብ
~ ጥሩ ልብስ መልበስ
~ሽቶ መቀባት ለወንዶች
~ ሲዋክ
~ ማልዶ በግዜ ወደ መስጅድ መሄድ
~ ሱረቱል ካፍን መቅራት ዱአ ማብዛት ~ በረሱል (ሰ፣ዐ፣ወ) ላይ ሰለዋት ማውረድ።
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد
الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ

💎ክፍል 11 💎
«እናንተ ሰዎች ሆይ! የእኔና የእናንተ የቀጠሮ ቦታ ዱኒያ
አይደለችም፡፡ ቀጠሮዋችን ሐውድ ዘንድ ነው፡፡ ከዚሁ ሆኜ እያየሁት
ይመስለኛል፡፡ ሰዎች ሆይ! የሶላት ነገርን አደራ! በሴቶቻችሁ ላይ አላህን ፍሩ፡፡ እናንተ ሰዎች ሆይ! ድህነት ያገኛችኋል ብዬ አልፈራም፡፡ ይልቁንም በኃብት ትጥለቀለቁና ስትፎካከሩ ያለፉት ሕዝቦች እንደጠፉት ሁሉ እናንተም ሃብት ያጠፋችኋላ ብዬ እፈራላችኋለሁ።
እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ ባሪያውን ከዚህ ዓለምና እርሱ ጋር
ከመገናኘት አማረጠው፡፡ ባሪያውም ከአላህ ጋር መገናኘትን መረጠ፡፡» ሶሃቦች ንግግራቸውን ጸጥ ረጭ ብለው ያዳምጡ ነበር፡፡ ጭንቅላታቸው ላይ ወፍ ቢያርፍ እንኳ ግዑዝ እስኪመስለው ድረስ በድን ሆነው ነበር፡፡
አስ-ሲዲቅ(ረዐ) ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) መጨረሻ የተናገሩት ምን ማለትእንደሆነ ገባቸውና ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ይንሰቀሰቁ ጀመር፡፡ «አባቴም እናቴም ልጆቼም ገንዘቤም መስዋዕት ይሁንሎ!›› እያሉ ማልቀሱን ተያያዙት፡፡ ሶሃቦች ነገሩ አልገባቸው ኖሮ ወደ አስ-ሲዲቅ ዘወር ብለው የረሱልን (ስ.ዐ.ወ) ንግግር በማቋረጣቸው ይወቅሷቸው ጀመር፡፡
ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ ‹‹አቡበክርን ዝም በሉት! አትንኩት! ወላሂ! ከአቡበክር በስተቀር ከእናንተ ውስጥ እኛ ዘንድ ውለታ ኖሮበት ያልመለስንለት የለም፡፡ የአቡበክርን ውለታ ግን የመመለስ አቅሙ የለኝም፡፡ ውለታውን አላህ እንዲመልስለት ትቼዋለሁ፡፡››
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከአቡበክር(ረ.ዐ) ቤት በስተቀር የሁሉም ሶሃቦች ቤት እንዲዘጋ አዘዙና ለሶሃቦች ዱዓ ያደርጉላቸው ጀመር። «አላህ
ያሥጠጋችሁ አላህ ድልን ያጎናጽፋችሁ፡፡ አላህ ያግዛችሁ። አላህ
ይጠብቃችሁ፡፡ አላህ ከፍ ያድርጋችሁ እናንተ ሰዎች ሆይ እስከ እለተ ትንሳኤ ድረስ እኔን ለተከተሉ ሁሉ ሠላምታዬን አድርሱ!››
ወዓለይኩምሰላም ያረሱሉላህ!
ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ተሸክመው ወደ ቤታቸው እስኪያደርሷቸው ድረስ (በል አረፊቂል ኣዕላ በል አረፊቂል ኣዕላ!» ይሉ ነበር፡፡ እሜቴ ዓኢሻ ከዱኒያ ይልቅ የዝንተ ዓለሙን ሕይወት እየመረጡ እንደሆነ ተረዳች፡፡ ከዚያም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “አቡበክርን እንዲያሰግድ ንገሩት” ብለው ሲያዙ እሜቴ ዓኢሻ እንዲህ አለች “አንቱ የአላህ መልዕክተኛ አቡበክር(ረ.ዐ) እኮለስላሳ ሰው ናቸው። ቁርዓንን ከቀሩ በጣም ተንሰቅስቀው ያለቅሳሉ” ብለው ሌላ ሰው እንዲቀይሩ ጎተጎተቻቸው፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ግን ደገሙና «አቡበክር እንዲያስግድ ንገሩት››
አሉ፡፡ እሜት ዓኢሻም ዑመር ቢን አል-ኸጣብ(ረ.ዐ) እንዲቀየሩ አዘዘች፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) ይህን አወቁና እንዲህ አሉ ‹‹አቡበክር ያሰግድ አላልኩም ነበር? አላህም ሆነ መስሊሞች ሌላ ሰው እንዲያሰግድ አይፈቅዱም፡፡ አቡበክር እንዲያሰግድ እዘዙት!››
ከዚያም በታዘዙት መሠረት አቡበክር(ረ.ዐ) ሰዎችን ያሰግዱ ጀመር፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይህንኑ ተመለከቱና የመጨረሻ ፈገግታቸውን ፈገግ አሉ፡፡ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የመጨረሻ ፈገግታ ብልጭ ያለችው ሶላት በፈጠረው ደስታ ነበር፡፡ እስኪ አንተ ፈጅር የማትሰግድ ሰው! ይህን በደንብ አስተውል።
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አቡበክር ሙስሊሞችን ኢማም ሆነው ሲያሰግዱ
ከተመለከቱ በኋላ እጅግ እርካታ ተሰማቸውና ወደ ቤታቸው "በል
አረፊቂል አዕላ" እያሉ ተመለሱ። ከዚያም በእሜቴ ዓኢሻ ደረት ላይ
ጋደም ብለው ተኙ፡፡ እሜቴ ዓኢሻ ይህንን ሁኔታ ስትገልጽ ‹‹ይህንኑ
ቃል ይደጋግሙ ነበር፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኋላ እጃቸው ሸርተት ብሎ
ወደቀ፡፡ ደረቴ ላይ እንዳሉ ይከብዱኝ ጀመር፡፡ ማለፋቸውን ወዲያው
አወቅሁ።
🔰ጠንካራ አቋም
እሜቴ ዓኢሻ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ማለፋቸውን እንዳወቀች የምታደርገው ሁሉ ጠፍቷት ነበር፡፡ የምትሆነው ጠፋት፡፡ ሶሃቦቹ
ወዳሉበት መስጂድ እየተጣደፈች ሄዳ «የአላህ መልዕክተኛ ሞተዋል... የአላህ መልዕክተኛ ሞተዋል" እያለች ጮኸች...
መስጂዱ በቅፅበት በጩኸት ተናጋ፡፡ ዓሊይ ኢብን አቡጣሊብ
መቆም አቃታቸው፡፡ ዑስማን ቢን ዓፋን የሚያደርጉትን ኣጡ፡፡ እንደ
ህፃን ሁለቱንም እጃቸውን ተይዘው ወዲህ ወዲያ ይላሉ፡፡ የነብዩ
(ስ.ዐ.ወ) ልጅ ፋጢማ «ወይኔ አባቴ! የጌታውን ጥሪ ተቀበለ፡፡ ወይኔ አባቴ ፊርደውሰል ጀነት መጠጊያው፡፡ ወይኔ አባቴ! የጅብሪል ጓደኛ" እያለች እሪታዋን አቀለጠችው፡፡
ጀግናው ዑመር ቢን አልኸጣብ እንደ ነበልባል የሚወናጨፈውን
ሰይፋቸውን ምዝዝ አድርገው ሲያወጡት ሁሉም ሰው ረጭ አለ፡፡ "ዝም በሉ! አንድም ሰው ከአሁን በኋላ መሐመድ ሞቱ ቢለኝ ጭንቅላቱን በዚህ ሰይፍ አሽቀንጥሬ እጥለዋለሁ። ሙሳ እንዳደረጉት ሁሉ ጌታቸው ሊያናግሩ ነው የሄዱት። አንድ ሰው ሞቱ ቢለኝ ጭንቅላቱ ይቀነጠስላታል።" አሉ፡፡
ሶሃቦች ሁሉ ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የነበራቸው ፍቅር በጣም ከፍተኛ
ነበር፡፡ የአቡበክር ግን ልክ አልነበረውም፡፡ እየገሰገሱ መጡ፡፡ ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቤት ገቡና የነገሩን ትክክለኛነት ካረጋገጡ በኋላ ጠጋ ብለው በዓይኖቻቸው መካከል ያለውን ቦታ ሳም አደረጓቸውና እንዲህ አሉ «እርሶ ሞተውም ህያውም ሆነው ውብ ነዎት፡፡ ከዚያም እንዲህ ሲሉ ደጋገሙ «ዋ ወዳጄ! ዋ ውዴ! ዋ አፍቃሪዬ! ዋ ነብዬ!››
ከዚያም ወደ መስጂድ ወጡና እንዲህ አሉ ‹‹ ዑመር ዝም በል! ,
ግራ የገባቸው ዑመር ዝም ሊሉ አልቻሉም፡፡ አቡበክር ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ “እናንተ ሰዎች ሆይ መሐመድን ያመልክ የነበረ ሰው ካለ ሙሐመድ ሞቷል፡፡ አላህን ያመልክ የነበረ ሰው ካለ ግን አላህ ምን ግዜም ሕያው ነው። አይሞትም›› ከዚያም የሚከተለውን የቁርኣን አንቀጽ አነበቡ፡፡
وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ ۚ أَفَإِن مَّاتَ أَوْ قُتِلَ انقَلَبْتُمْ عَلَىٰ أَعْقَابِكُمْ ۚ وَمَن يَنقَلِبْ عَلَىٰ عَقِبَيْهِ فَلَن يَضُرَّ اللَّهَ شَيْئًا ۗ وَسَيَجْزِي اللَّهُ الشَّاكِرِينَ
"ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ ታዲያ ቢሞት ወይም ቢገደል ወደ ኋላችሁ ትገለበጣላችሁን ወደኋላው የሚገለበጥም ሰው አላህን ምንም አይጎዳም፡፡ አላህም አመስጋኞቹን በእርግጥ ይመነዳል፡፡" (አል-ኢምራን 144)
ሰይድ ዑመር ሁኔታውን ሲያስታውሱ እንዲህ ይላሉ ‹‹የቁርኣን
አንቀፁን ስሰማ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት ያህል ሆነብኝ፡፡ ሰይፌ ከእጄ ላይ ወደቀ፡፡ ምን እያደረግሁ ነው ብዬ ራሴን ታዘብኩ፡፡ ከዚያም ለብቻዬ ገለል ብዬ ማልቀስ ጀመርኩኝ፡፡››...
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
----------◌◌ይቀጥላል◌◌---------ኢንሻ አላህ
☪የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ☪

18
<unknown>
📕 አቂደቱል ዋሲጥያ
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-18-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-18-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
Forwarded from የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች
💎 የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ) ታሪክ
💎ክፍል 12💎
እስኪ በዚህ ወቅት አቡበክር(ረ.ዐ) ባይኖሩ ኖሮ ምን ሊከሰት እንደሚችል ልብ በሉ! ሶሃቦች ሊረጋጉ አይችሉም ነበር፡፡ ድንጋጤያቸው ምን ሊያደርጋቸው እንደሚችል አስቡ፡፡
ከዚህ በኋላ አጸደ-ሥጋቸው የት ማረፍ አለበት በሚለው ላይም ሶሃቦች አንዳንድ ልዩነቶችን ፈጠሩ። አስ-ሲዲቅ እንዲህ አሉ «ረሱል
(ሰዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ” እኛ ነቢያት የምንቀብረው እዚያው ሞትንበት ቦታ ነው፡፡ ከዚያም ሶሃቦች በነገሩ ተስማሙና የእሜቴ ዓኢሻ አልጋ የነበረበትና የሞቱበት ቦታ ግብዓተ መሬታቸው እንዲፈጸም አደረጉ፡፡
🤚ለኸሊፋው ቃል ኪዳን መግባት
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሕልፈት አማካኝነት ወደ ዝንተ ዓለመ ኑሮ ከተሸጋገሩ በኋላ የርሳቸውን ቦታ ማን ይተካ?› በሚለው ጉዳይ ላይ ሶሃቦች በመጠኑም ቢሆን ለመወሰን መቸገራቸው አልቀረም፡፡ የመዲና ቀደምት ነዋሪ የሆኑት አንሷሮች ይህን ለመወሰን በሰቂፋበኒ ሳዒዳ አዳራሽ ውስጥ ጉባኤ ተቀምጠዋል፡፡ ሃሳባቸው ከነርሱ ውስጥ አንዱ የሆነውንና በመካከላቸው ተሰሚነቱ የጎላውን ሰዒድ ቢን ዑባዳን ለመምረጥ ነበር፡፡ ሆኖም ሰዒድ በወቅቱ ታሞ ስለነበር በቦታው አልተገኘም፡፡
ሰይድ ዑመር ቢን አል ኸጣብ(ረ.ዐ) አንሷሮች በሰቂፍ ጉባኤ መቀመጣቸውን ሲሰሙ አቡበክር አስ-ሲዲቅንና አቡ ኡበይዳህ ቢን አልጀራህን ይዘዋቸው ወደ ሰቂፋ አቀኑ፡፡ እንደ ደረሱም ከአንሷሮች ጋር ውይይት ማድረግ ጀመሩ፡፡
አንሷሮች እንዲህ አሉ ‹‹በዚህ ጉዳይ ላይ (ኸሊፋ በመሆን ጉዳይ ላይ መብቱ ያለን እኛ ነን፡፡ ምክንያቱም ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) የረዳነውም ያስጠጋነውም እኛ ነን፡፡ እኛ ዘንድ ሰዕድ ቢን ዑባዳ ስላለ እርሱን መሾም እንችላለን፡፡»
ሰይድ ዑመር(ረ.ዐ) ሁኔታውን ሲያስታውሱ እንዲህ ይላሉ «በወቅቱ ሰፋ ያለ ንግግር ለማድረግ ተዘጋጅቼ ነበር፡፡ አቡበክር(ረ.ዐ) እንዳልናገር እጄን ያዝ አድርገው ከለከሉኝ፡፡ ከዚያም እንዲህ አልኩኝ "በእርግጥ በመጀመሪያ የረዳችሁና ያሥጠጋችሁት እናንተ ናችሁ፡፡ አሁን ተገቢውን ገር ለመቀየር የመጀመሪያዎቹ አትሁኑ፡፡ እናንተ አንሷሮች ዐረቦች ይህ ጉዳይ ለቁረይሾች ካልሆነ በቀር ለማንም እንደማይገባ ያምናሉ፡፡»
አንሷሮች ««እኛም ዘንድ መሪ አለ። እናንተም ዘንድ መሪ አለ፡፡ አሉ «አቡበክርም ቀበል አደረጉና ‹‹እንዲህማ ተገቢ አይደለም» አሉ። በሺር ቢን ሰዕድ የተባለ የኸዝረጅ ጎሳ አባልና አንሷሪ ተነሳና እንዲህ ሲል አቡበክርን(ረ.ዐ) ደግፎ ተናገረ "እናንተ አንሷሮች! ወላሂ ለዚህ ጉዳይ ከእኛ የበለጠ መብት ያላቸው እነርሱ ናችው። እኔ አመራርን ለመቀበል ቃል እገባለሁ!» ሰይድ ዑመርም(ረ.ዐ) ለአቡበክር “እጅዎን ይዘርጉ!›› አሉና «ቃል እገባሎታለሁ» ብለው ጨበጧቸው። ዑመርን ተከትለው ሁሉም ሶሃቦች በየተራ እየሆኑ ለአቡበክር የኸሊፋነትን ቃልኪዳን (ሙባየን) ገቡላቸው፡፡
ይህን የመሰለው ከበድ ያለ ጉዳይ እንዲህ በእርጋታ ተከናወነ።
ሶሃቦች ልባቸው ከአላህ (ሱ.ወ) ጋር የተቆራኘና ጥልቅ የሆነ መጣጣም ስለነበራቸው ነገሩ በዚሁ ቋጩት፡፡
📋የኸሊፋው ፖሊሲዎች
የኸሊፋነቱን ቦታ አቡበክር አስ-ሲዲቅ ተረከቡ፡፡ ኸሊፋነቱን ገና እንደተረከቡ አቋምና ፖሊሲዎቻቸውን እንደሚከተለው ለሚመሩት
ሕዝብ ይፋ አደረጉ፡፡
"እኔ በእናንተ ላይ የተሾምኩት ከእናንተ በልጬ አይደለም፡፡ እውነት ላይ ሆኜ ካገኛችሁኝ አግዙኝ፡፡ ወደ ሀሰት ስዘነበል ካያችሁ ደግሞ መልሱኝ፡፡ አስተካክሉኝ አላህን እስከታዘዝኩ ብቻ ታዘዙኝ፡፡
አላህን ካመጽኩ ግን መታዘዝ የለባችሁም፡፡ ከእናንተ መካከል ደካማው ድርሻውን እስከሰጠ ድረስ በኔ ዘንድ ኃያል ነው። ኃያሉም የሌሎችን ድርሻ እስኪሰጥ ድረስ በኔ ዘንድ ደካማ ነው፡፡ እናንተ ሰዎች በአላህ መንገድ ላይ መታገል ለሚያቆሙ ሕዝቦች አላህ የሀፍረት ካባ ያከናንባቸዋል፡፡››
አቡበክር አስ-ሲዲቅ በዚህ መልኩ በአመራር ወቅት የሚከተሏቸውን ፖሊሲዎች በግልጽ ይፋ አደረጉ። ገለጻቸው አምስት መሠረታ ነጥቦችን አካቶ ይዟል።
1. መተናነስ (ተዋዱዕ)
2. በእውነት ላይ መተጋገዝ ያለው ተገቢነት፣
3. ስህተትን ማስተካከልና መቃወም ያለው አስፈላጊነት፣
4. ደካማም ቢሆን ተበዳይ እስከሆነ ድረስ መረዳትና የፈለገ
ኃይለኛ ቢሆን በዳይን መከልከል ወሳኝ መሆኑ፣
5. በአላህ መንገድ መታገል(ጂሐድ) የኡማው ክብርና ማእረግ መሆኑናቸው።
አቡበክር አስ-ሲዲቅም በኸሊፋነት በመመረጣቸው ያልወደደ አልነበረም፡፡ ልጅ አዋቂው ሳይቀር ተደሰተ። የአቡበክርን ደግነት ሁሉም ያውቅ ስለ ነበር ሁሉም ተቀበለ። አቡበክር ከአዘኔታቸው የተነሳ አንዳንዴ በመንገድ ሲያልፉ ሕጻናቶች እየመጡ ይጠመጠሙባቸው ነበር፡፡ «አባቴ! እባቴ! ይሏቸዋል። እርሳቸውም ኸሊፋነታቸው ሣያስኮፍሳቸው ሕፃናቶቹን ያቅፏቸውና ይሽከሟቸው ነበር።
ከአቡበክር የተባረኩ የትሁትነት ልምዶች አንዱ ! ባሎቻቸው ሰማዕት ሆነው የተለዪዋቸው ሴቶችን ላሞች በማለብ በሥራ ማገዝ ነበር። አንዴ ባላቸውን በዚህ ሁኔታ ያጡ ሴቶች አቡበክር ኸሊፋ ከሆኑ በኋላ «አሁንሥ ማን ወተት ያልብልናል» ማለታቸውን አቡበክር ይስሙና ወደ ሴቶቹ ሄደው እንዲህ ይሏቸዋል «ያላችሁትን ሁሉ ሰምቻለሁ ወላሂ አቡበክር እስኪሞት ድረስ የላሞቻችሁን ወተት ከማለብ አይወገድም፡፡››
አንድ ጊዜ ሁለት ሰዎች መሬት ይሰጡዋቸው ዘንድ ለመጠየቅ ወደ አቡበክር(ረ.ዐ) ይመጣሉ፡፡ አቡበክርም እነዚህ ሰዎች ቀልባቸው ወደ እስልምና እንዲያዘነብል በማሰብ መሬት ሊሰጡዋቸው ተስማሙ። ሆኖም ግን በጉዳዩ ላይ ሰይድ ዑመር(ረ.ዐ) መስማማት እንደሚኖርባቸው ነግረዋቸው ወደ እርሳቸው ዘንድ እንዲሄዱ ያደርጋሉ፡፡
ዑመር(ረ.ዐ) በጉዳዩ ሳይስማሙ ይቀራሉ። እስልምናን ለማጠናከር በሚል ስዎችን በጥቅማጥቅም ማባበሉ ተገቢ እንዳልሆነና እስልምና በራሱና ብቻውን ጠንካራ መሆኑን በመግለጽ አቋም ይይዛሉ፡፡ ሁለቱ ሰዎችም በሁኔታው ተበሳጭተው ወደ ኸሊፋው ይመለሳሉ፡፡ ‹‹ ለመሆኑ ኸሊፋ እርሶ ኖት ወይስ እርሳቸው?›› በማለት አቡበክርን ይጠይቃሉ። አስ-ሲዲቅም ‹‹ኢንሻአላህ እርሱ ነው» ብለው ይመልሱላቸዋል።
🔰ታሪክ ያልደገመው ሰው
አቡበክር አስ-ሲዲቅ(ረ.ዐ) ለኸሊፋነት በበቁ ማግስት በርካታ ጎሳዎች በእስልምና ሳይ ክህደት ፈጽመው ነበር፡፡ ከመካ እና ከመዲና ወጪ የሚኖሩ ጎሳዎች እስልምናን ክደዋል፡፡
ሰይድ አቡበክር(ረ.ዐ) በሁለት ዓመታት የኸሊፋነት ጊዜያቸው በእስልምና ላይ ያንዣበበውን ይሀን አደጋ ገፈው ለመጣል ችለዋል:: በዓረበ ፔንሱሳ (ጀዚረተል ዐረብ) የተፈፀመውን ክህደት በሙሉ አስቀርተው ጎሳዎቹ በመሉ ወደ እስልምናቸው እንዲመለሱ አድርገዋል፡፡ በዚህ የሁለት ዓመት ዕድሜ ውስጥም የፋርስና የሮም ሀገራትን ማቅናት፣ ቁርኣን በጥራዝ መልክ እንዲሰባስብ ማድረግ ችለዋል፡፡
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
➛➛➛➛ይቀጥላል
ኢንሻ አላህ➛➛➛

19
<unknown>
📕 አቂደቱል ዋሲጥያ
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-19-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-19-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
20
<unknown>
📕 አቂደቱል ዋሲጥያ
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-20-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-20-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
21
<unknown>
📕 አቂደቱል ዋሲጥያ
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-21-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል-21-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
Forwarded from የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች
✍ #ተውበት (ወደ አላህ መመለስ)
ተዉበት በሠራነዉ ስራ ተፀፅተን ወደአላህ መመለስ ከፈጣሪ ምህረትን መጠየቅ
ነው ይችን ዱኒያ ዛሬ ይሁን ነገ መቸ እንደምንለያት አናቅምና ሁሌም መች እና
እንደት እንደሚመጣብን ለማናዉቀዉ ሞት ማስታወስ ግድ ነው በየትኛዉ ሠከንድ
እንደሚመጣ የአላህ ቀጠሮ አናዉቅምና
ተውበት (ወደ አላህ መመለስ)
💫 #ተውበት፡- በአላህ ትእዛዝ ላይ ከማመፅ ለህግጋቱ ወደ መታዘዝ. መመለስ ነው፡፡
💫 #ተውበት፡- ተውበት አላህዘንድ በጣም የተወደደ ነው።
‹‹… ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻳُﺤِﺐُّ ﺍﻟﺘَّﻮَّﺍﺑِﻴﻦَ ﻭَﻳُﺤِﺐُّ ﺍﻟْﻤُﺘَﻄَﻬِّﺮِﻱﻥَ
‹‹ ....አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል
በላቸው፡፡››
አል በቀራህ 222
ተውበት በእያንዳንዱ አማኝ ላይ ግዴታ ነው፡፡
አላህ እንድህ ይላል:-
ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﺗُﻮﺑُﻮﺍ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺗَﻮْﺑَﺔً ﻧَّﺼُﻮﺣًﺎ ﻋَﺴَﻰٰ ﺭَﺑُّﻜُﻢْ ﺃَﻥ ﻳُﻜَﻔِّﺮَ ﻋَﻨﻜُﻢْ ﺳَﻴِّﺌَﺎﺗِﻜُﻢْ
ﻭَﻳُﺪْﺧِﻠَﻜُﻢْ ﺟَﻨَّﺎﺕٍ ﺗَﺠْﺮِﻱ ﻣِﻦ ﺗَﺤْﺘِﻬَﺎ ﺍﻟْﺄَﻧْﻬَﺎﺭُ ﻳَﻮْﻡَ ﻟَﺎ ﻳُﺨْﺰِﻱ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲَّ ﻭَﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﻣَﻌَﻪُ ۖ
ﻧُﻮﺭُﻫُﻢْ ﻳَﺴْﻌَﻰٰ ﺑَﻴْﻦَ ﺃَﻳْﺪِﻳﻬِﻢْ ﻭَﺑِﺄَﻳْﻤَﺎﻧِﻪِﻡْ ﻳَﻘُﻮﻟُﻮﻥَ ﺭَﺑَّﻨَﺎ ﺃَﺗْﻤِﻢْ ﻟَﻨَﺎ ﻧُﻮﺭَﻧَﺎ ﻭَﺍﻏْﻔِﺮْ ﻟَﻨَﺎ ۖ ﺇِﻧَّﻚَ ﻋَﻠَﻰٰ
ﻛُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ﻗَﺪِﻳﺮٌ
‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ ንፁህ የኮነችን ፀፀት በመፀፀት ወደ አላህ
ተመለሱ…..››
አል ተህሪም 8
‹‹… ﻭَﺗُﻮﺑُﻮﺍ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ﺃَﻳُّﻪَ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨُﻮﻥَ ﻟَﻌَﻠَّﻜُﻢْ ﺗُﻔْﻠِﺤُﻮﻥَ
‹‹ ... ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ)
ተጸጸቱ፡፡››
ሱረት አል-ኑር 31
መድህን (ፈላህ) ማግኘት ማለት አንድ ሰው የፈለገውን ማግኘት የሚፈራውን
ነገር መዳን ነው፡፡
ፍፁምና እውነተኛ የሆነ ተውበት፡- ኃጢአቱ የፈለጉትን ያህል ቢከብድና ቢበዛም
እንኳን አላህ # ፍፁምና_እውነተኛ ከሆነ ተውበት ኃጢአቶችን ሁሉ ይቅር ብሎ
ምህረት ያደርጋል፡፡
۞ ﻗُﻞْ ﻳَﺎ ﻋِﺒَﺎﺩِﻱَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺃَﺳْﺮَﻓُﻮﺍ ﻋَﻠَﻰٰ ﺃَﻧﻔُﺴِﻬِﻢْ ﻟَﺎ ﺗَﻘْﻨَﻄُﻮﺍ ﻣِﻦ ﺭَّﺣْﻤَﺔِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ۚ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻳَﻐْﻔِﺮُ
ﺍﻟﺬُّﻧُﻮﺏَ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ۚ ﺇِﻧَّﻪُ ﻫُﻮَ ﺍﻟْﻐَﻔُﻮﺭُ ﺍﻟﺮَّﺣِﻴﻢُ
በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት
ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው
አዛኙ ነውና፡፡
አል-ዙመር - 53
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
SHARE 🔗SHARE
👉የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ👈

💎የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ) ታሪክ
የመጨረሻ ክፍል
🔰የአል-ፋሩቅ መተካት
የአቡበክር አስ-ሲዲቅ ሞት ምክንያት ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡፡ የሞቱት ከፍተኛ ቅዝቃዜ ባለው ውሃ በመታጠባቸው ምክንያት ብርድ በሽታ ታመው ነው የሚሉ እንዳሉ ሁሉ የለም እርሳቸው የሞቱት አንድ አይሁዳዊ የተመረዘ ምግብ አብልቷቸው ለአስራ አምስት ቀናት ያህል ታመው ነው የሚሉም አሉ፡፡ ..
ይህ በእርግጥ ለአይሁዶች አዲስ አይደለም፡፡ ብዙ ነብያትን የመግደል ልምድ አካብተዋል፡፡ ሰይድ ኢሳን (ዐ.ሰ) ለመግደል ሞክረዋል፡፡ ነብዩን (ሰዐ.ወ) ሶስት ጊዜ ለመግደል ሞክረው አልተሳካላቸውም፡፡ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር አድርገው ለዑመር ቢን አል ኸጣብ፣ ለዑስማን ቢን ዓፋን ለጦልሃና ለዙበይር መገደል ምክንያት የሆኑት አይሁዳዊያን ናቸው፡፡
ሰይድ አቡበክር ላይ ሕመም በጠናባቸው ጊዜ ሶሃቦች በርሳቸው ቦታ ላይ ሰይድ ዑመርን እንዲተኩ እያማከሯቸው ነበር፡፡ አስ-ሲዲቅ ዓብዱራህማን ቢን ዓውፍን ስለ ዑመር ሲጠይቋቸው እንዲህ ሲሉ መለሱ፡፡ «አንቱ የረሱል ኸሊፋ ሆይ ዑመር ከምናስባቸው በላይ ጥሩ ሰው ናቸው።››
ዑስማንን ሲጠይቋቸው ደግሞ እንዲህ አሉ... “ከላያቸው በተሻለ ውስጣቸው ጥሩ እንደሆነ አስተምረውኛል፡፡” አቡበክር ሌሎችንም ታላላቅ ሶሃባዎችን ሲያማክሯቸው በጉዳዩ ላይ ተስማሙ።
አንዳንድ ስዎች ደግሞ እንዲህ አሏቸው “ዑመር ኃይለኛነት አለባቸው፡፡ አላህ እንዴት ኸሊፋ አደረግካቸው ብሎ ቢጠይቅዎ ምን ሊመልሱ ነው” አቡበክርም ተቆጡና እንዲህ አሉ... “ደግሞ በአላህ ታስፈራሩኛላችሁ... ወላሂ አላህ ቢጠይቀኝ ከምርጥ ሰዎችህ ምርጥ የሆነውን በእኔ ቦታ ተክቼዋለሁ ብዬ እመልስለታለሁ፡፡”
ከዚያም አቡበክር ዑስማን ቢን ዓፋንን(ረ.ዐ) አስጠሯቸውና እንደሚከተለው እንዲጽፉ አዘዟቸው፡፡... “ይህ ኑዛዜ ከዱኒያ ለመጨረሻ ጊዜ ሲሰናበት ወደ አኼራ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሄድ አቡበክር ቢን አቢ ቁሃፉ ያስተላለፈው ትዕዛዝ ነው። ሐሰተኞች እውነት እንዲናገሩ፣ አመጸኞች አደብ እንዲገዙ፣ ከሃዲዎች እንዲያምኑ ስል ይህን ትዕዛዝ አስተላልፌያለሁ... ተክቼላችኋለሁ...” የተኩትን ሰው በስም ሳይጠቅሱ ራሳቸውን ይስታሉ።
ሰይድ ዑስማን “ዑመር ቢን አል-ኸጧብን ተክቼላችኋለሁ...” የሚል ዓረፍተ ነገር ጻፉ። ዑስማን ይህን ያደረጉት አስ-ሲዲቅ የተኩትን ስው በግልጽ ሳይናገሩ ካለፉ በሙስሊሞች መካከል ውዝግብ ይፈጠራል ብለው ሰግተው ነው። በተጨማሪም አቡበክር( በርሳቸው ቦታ መተካት ያለበት ሰው ማን እንደሆነ መወሰናቸውን ዑስማን(ረ.ዐ) ስለሚያውቁ፡፡
አስሲዲቅ(ረ.ዐ) ትንሽ መለስ እንዳሉ ዑስማን(ረ.ዐ) የጻፉትን እንዲያነቡላቸው አዘዟቸው... “በእኔ ቦታ ዑመር ቢን አል-ኸጣብን ተክቼላችኋለሁ፡፡” የሚለውን አነበቡ። በዚህ ጊዜ ሰይድ አቡበክር እንዲህ አሉ... “አሏሁ አክበር! የተካሁትን ሰው በስም ሳልናገር ሕይወቴ ብታልፍ ሙስሊሞች ይጨቃጨቃሉ ብለህ ስግተህ ነበር ማለት ነው? ለእስልምና እና ለሙስሊሞች ለዋልከው ውለታህ አላህ መልካም ምንዳ ይክፈልህ ዑስማን”
ከዚያም አስ-ሲዲቅ ሶሃቦች እንዲሰባሰቡ አደረጉና እንዲህ አሏቸው... “እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ዱኒያን ተሰናብቼ ወደ አኼራ መጓዜ ነው፡፡ በዚህ ወረቀት ውስጥ እኔን የሚተካ ሰው ገልጬላችኋለሁ፡፡ እርሱን ስሙት ታዘዙትም፡፡ እኔ ለእናንተ የመረጥኩላችሁን ስው ትቀበሉታላችሁን?” ብለው ሲጠይቁ ሁሉም በህብረት “ተደስተናል” አሉ።
ዓሊይ ቢን አቢ ጧሊብ(ረዐ) ተነሱና እንዲህ አሉ... "ዑመር ካልተሾሙ በቀር አንደሰትም...” አስ-ሲዲቅ ፈገግ አሉና "የተሾመው ዑመር ቢን አል-ኸጣብ ነው፡፡ ስሙት ታዘዙትም። ወላሂ ስለርሱ መልካምን እንጂ ሌላ የማውቀው ነገር የለኝም”
🔰የወዳጆች መመሳሰል
አቡበክር ዛሬ ቀኑ ማነው” ሲሉ ጠየቁ፡፡ “ሰኞ ነው” አሏቸው “ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በምን ቀን ነበር ያለፉት" ሲሉ አከሉ፡፡ ሰኞ ቀን፡፡ አቡበክርም እንዲህ አሉ “እላህ ሆይ ሞቴን በዚችው ሌሊት አድርግልኝ ከዚያም እንዲህ ጠየቁ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተከፈኑት በምን ዓይነት ከፈን ነበር” የተከፈኑበትን ነገሯቸው፡፡ “እኔንም በዚያው ዓይነት ከፍኑኝ፡፡ አስክሬኔንም ባለቤቴ አስማእ ቢንት ዑመይስ ትጠበኝ...”
🔰የአስ-ሲዲቅ ጉዞ
እሜቴ ዓኢሻ ወደ ቤት ገብታ ማልቀስ ስትጀምር አስ-ሲዲቅ ከለከሏት። ከዚያም አጠገባቸው ተቀምጣ ግጥሞችን ትገጥም ጀመር፡፡ አቡበክርም ዓኢሻን እሱን ተይና እንዲህ የሚለውን የቁርኣን አንቀጽ አንብቢ
وَجَاءَتْ سَكْرَةُ الْمَوْتِ بِالْحَقِّ ۖ ذَٰلِكَ مَا كُنتَ مِنْه تَحِيدُ (١٩) وَنُفِخَ فِي الصُّورِ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْوَعِيدِ (٢٠)
"የሞትም መከራ እውነቱን ነገር ታመጣለች፡፡ (ሰው ሆይ)፡- «ይህ ያ ከርሱ ትሸሸው የነበርከው ነው» (ይባላል)፡፡ በቀንዱም ውስጥ ይንነፋል፡፡ ያ (ቀን) የዛቻው (መፈጸሚያ) ቀን ነው፡፡" (ቃፍ 19-20)
አስ-ሲዲቅ በመሞቻቸው ዕለት የተናገሯት የመጨረሻዋ ንግግር እንዲህ የምትል ነበረች... "ሙስሊም አድርገህ ግደለኝ፣ ከመልካሞቹም ጋር አስጠጋኝ፡፡" አቡበክር የሞቱት ሰኞ ሌሊት ነበር፡፡ በጀናዛቸው ላይ ያስገዱት ዑመር ቢን አል-ኸጣብ(ረ.ዐ) ናቸው፡፡ መላው የመዲና ከተማ በአቡበክር ሞት ምክንያት ስታነባ ዋለች፡፡ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ካረፉበት መካነ መቃብር አጠገብ ተቀበሩ፡፡ ዓሊይ ቢን አቢጧሊብ(ረ.ዐ) ወደ መቃብሩ ተጠጉና እንዲህ አሉ። “አቡበክር ሆይ አላህ ይዘንልህ፡፡ ወላሂ ከሙስሊሞች አንደኛ አንተ ነበርክ፡፡ በኢማን ጥልቀትና ጥንካሬ አንተን የሚያክል የለም፡፡ ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) በመንከባከብ፣ እስልምናን በመጠበቅ ወደር አልነበረህም፡፡ ለሙስሊሞች ሩህሩህ ነበርክ፡፡ ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ጋር በአፈጣጠርም፣ በስነምግባርም፣ በግርማ ሞገስም ተመሳሳይ ነበርክ፡፡ ለእስልምና እና ለረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የከፈልከውን ውለታ አላህ በመልካም ይመልስልህ። ስዎች ረሱልን (ስ.ዐ.ወ) እምቢ ሲሏቸው ኣንተ አስተናገድካቸው። ተቀበልካቸው፡፡ ሲያገሏቸው አንተ አቀረብካቸው፡፡ ምን ጊዜም ከጎናቸው ነበርክ፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በመጽሐፉ እውነተኛ ብሎ ጠርቶሃል. “ያም በእውነት የመጣው በርሱ ያመነውም” ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ያመጡትን እውነት እውነት ብለህ የተቀበልከው አንተ ነህ፡፡ ወላሂ ለእስልምና ጋሻና መከታ፣ ለከሓዲያን ደግሞ ቅጣት ነበርክ፡፡ ጎርፍም ሆነ አውሎ ንፋስ የማያናጋው ተራራ ነበርክ፡፡ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ስለ አንተ እንደተናገሩት ሰውነትህ ለስላሳ ቢሆንም በአላህ ትዕዛዝ ላይ ግን ጠንካራ ነበርክ፡፡ ለራስህ የምትተናነስ ብትሆንም አላህ ዘንድ ግን ከፍ ያልክ ነህ፡፡ በምድር ላይ ኃያል፣ ሙስሊሞች ዘንድ ደግሞ ታላቅ ነበርክ፡፡ ለእኛ የዋልከውን ውለታ አላህ በመልካም ይመልስልህ፡፡ ባንተ ላይ ቂምም ሆነ ብሶት ያለበት ሰው የለም፡፡ ደካማ የድርሻውን እስካላገኘ ድረስ አንተ
ዘንድ ኃያል ነበር፡፡ ኃያሉ የሌሎችን ድርሻ እስኪሰጥ ድረስ አንተ ዘንድ ደካማ ነበር፡፡ ምንዳህን አላህ አይከልክለን፡፡ ካንተ በኋላም አያጥምመን፡፡”
ረ ዲ የ ሏ ሁ ዐ ን ሁ
🤲ምስጋና ይገባው ለአሏህ ﷻ ይህን ታሪክ አስጀምሮ ላስጨረሰን
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
📚 እዚጋ ተጠናቀቀ📚
☪ የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ☪

Trimmed_22
<unknown>
📕 አቂደቱል ዋሲጥያ
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል- የመጨረሻ ክፍል-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆 ክፍል- የመጨረሻ ክፍል-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
Forwarded from የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች
የዑመር ኢብኑልኸጣብ (ረዐ) 20ምርጥ ምክሮች፤
.
1. ‹የምትጠላውን ሰው ተጠንቀቅ፤›
2. ‹ብልጥ ሰው የእለት ስራዎቹን ከራሱ ጋር ይተሳሰባል፡፡
3. ‹የዛሬን ስራ ለነገ አታሳድር፡፡›
4. ‹ከሰዎች ጥያቄ ተነስተህ አስተሳሰባቸውን መለካት ይቻላል፡፡›
5. ‹ለሌሎች ዳዕዋ በምታደርግበት ወቅት እራስህን አትርሳ፡፡›
.
6. ‹ከዱንያ ትንሽን ብቻ ስትፈልግ ይበልጥ ነፃነትን እያገኘህ ትሄዳለህ፡፡›
7. ‹ወንጀል አለመስራት ከፀፀት ይሻላል፡፡›
8. ‹ታጋሽ ሁን፤ ትዕግስት የእምነት ምሶሶ ነችና፡፡›
9. ‹አሏህን ፈሪ መሆን እድለኛነት ነው፤ ከዚህ ውጭ ያለው እድለቢስ መሆን ነው፤›
10. ‹ወደ አኺራ የሄዱ ሰዎችን ንግግር ጠብቁ፤ እነርሱ የተናገሩት አሏህ እንዲናገሩ ያገራላቸውን ብቻ ነውና፡፡
.
11. ‹አሏህን ፍራ፤ እርሱ ሁሌም ህያው፤ ከርሱ ውጭ ያሉ ሁሉ ጠፊ እና አላቂ ናቸውና፡፡
12. ‹ጥፋቴን በነገረኝ ሰው ላይ የአሏህ እዝነት ይውረድ፡፡
13. ‹እውቀትን ገብያት፤ ከዚያም ለሰዎች አስተምር፡፡›
14. ‹የተከበርክ፣ ታማኝ እና እውነተኛ ሁን፡፡›
15. ‹ትምክህተኛ ምሁር አትሁን፤ ትምክህተኛነት እና እውቀት አንድ ላይ አይሄዱምና፡፡
.
16. ‹ለዚህች አለም ፍቅር ያለው አዋቂ ባየህ ግዜ እውቀቱ አጠራጣሪ መሆኑን ተረዳ፡፡›
17. ‹ትንሽ አውርቶ ብዙ በሚሰራ ሰው ላይ የአሏህ እዝነት ይውረድ፡፡›
18. ‹ታማኝነት ማለት በምትሰራው፣ በተናገርከው እና በምታስበው ነገሮች ልዩነት አለመኖር ማለት ነው፡፡
19. ‹የሰው ልጅ ምንም እንኳ እንደ ቀስት ቀጥ ያለ ስራ ቢሰራ ተቃውሞ አያጣውም፡፡›
20. ‹አዕምሮህ እንዲሰፋ ከፈለግክ፤ ከፈሪሀ አሏሆች ጋር ተቀመጥ፤›
ለወዳጆችዎ ሼር በማድረግ ያካፍሉ
SHARE 🔗SHARE
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
📌 የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ📌