Telegram Web Link
⭐️#ሚሰጥርህን_ለሁለቱም_ተው
☞ለጌታህና
☞ለራስህ

#ምድር_ላይ_ሁለት_ሰዎች_እንዲወዱህ_ጣር
☞እናትና
☞አባትህ

⭐️#ሁለት_ሃይለኛ_ነገሮች_ላይ_ዘውትር
☞ሰላት እና
☞ትዕግስት

⭐️#ሁለት_ነገሮችን_አትፈራ
☞ርዝቅ እና
☞ሞትን ለምን ሁለቱም በአላህ እጃ ስለሆኑ

⭐️#ሁለት_ነገሮችን_ምንም_አታስታውሳቸው
☞ለሰዎች የዋልከው በጎ ነገር እና
☞ሰዎች አንተ ላይ ያደረጉት መጥፎ ነገር

#ሁለት_ነገሮችን_ምንም_አትርሳቸው
🌿አላህን እና
🌿የመጨረሻይቱን ቀን🌴

☞ከፈጣሪህ ብዙ ስትርቅ፥ በፈጠራቸው ፍጡራን ክፉኛ ትፈተናለህ

:#ላራህማኑ_ጥራት_ይገባው_ምስጋና
፡##ሙስሊም_አርጎ_ለፈጠረን_ለረቡና
##ከቶ_አናፍርም_እምነታችነው_እስልምና
፡##ቁርአን_ነው_የኛ_የህይወት_መመርያ!!
وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ
(إبراهيم)

http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🇪🇹የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ🇪🇹
አምስት ነገሮች ከአምስት ነገሮች በፊት ተጠቀምባቸው

🖊ከሞትህ በፊት= ህይወትህን


🖍ከህመምህ በፊት=ጤንነትህን


🖌ከእጦትህ በፊት= ሃብትህን


🖊 ከትጋትህ በፊት= ዕፎይታህን


🎯ከዕርጅናህ በፊት=ወጣትነትህን

http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🇪🇹የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ🇪🇹
#ምላሳችን #ከእርግማንና ከስድብ እንቆጥብ!
"ሙስሊም ተሳዳቢም ሆነ ተራጋሚም አይደለም"

💫 አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፦
"ነቢዩ( ﷺ) ተሳዳቢ፣አስቀያሚ ንግግርን ተናጋሪ ሆነ ተራጋሚ አልነበሩም።"
��【ቡኻሪ ዘግበውታል】

💐 የአላህ መልክተኛ( ﷺ) እንዲህ ይላሉ፦
"እኔ ተራጋሚ ሆኜ አልተላኩም…።"
【ሙስሊም ዘግበውታል】

💐የአላህ መልክተኛ( ﷺ) እንዲህም ብለዋል፦
"አንድ የአላህ ባሪያ አንዳችን ነገር በሚራገም ግዜ ፦እርግማኗ ወደ ሰማይ ከፍ ብላ ትወጣለች፣ ከዚያም የሰማያት በር ይዘጉባታል፣ከዚያም ወደ ምድር ዝቅ ብላ ትወርድና በሮች በሙሉ ጥርቅም ብለው ይዘጋሉ፣ከዚያም ወደቀኝና ግራ ትመለከታለች ፣ መግቢያ ስታጣ ወደ ተረጋሚው ትመለሳለች ለእርግማን ተገቢ ከሆነ እርግማኑ ይደርስበታል፣ ካለሆነ ግን ወደ ተራጋሚው ትመለሳለች።"
��【አቡ ዳዉድ ዘግበውታል】


💫💫"አንድን አማኝ መርገም ነፍሱን እንደ ማጥፋት ይቆጠራል።"

【ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል】

ለወዳጆቾ ሼር ያደርጉላቸው!

SHARE 🔗SHARE
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
▪️ጁሙዓ ነው ፤ ሰለዋት እናብዛ

🔻የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ ሰው ፤ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል። ] (ሙስሊም ዘግቦታል).
____
اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد.
የጁምዓ ሰላት ሸሪዓዊ ብይኑና ማስረጃዎቹ

የጁምዓ ሰላት በያንዳንዱ ሙስሊም በሆነ ወንድ ላይ ግዴታ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡›› (ጁምዓ 9)

ነብዩም (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ‹‹አቅመ አዳም በደረሰ በያንዳንዱ ሰው ጁምዓ ግዴታ (ዋጂብ) ነው››ነሳኢይ 1371በሌላም ሐዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል‹‹ሠዎች ጁምዓን ከመተው የማይታቀቡ ከሆነ አላህ ልቦናቸውን ያሽግና ዝንጉዎች ይሆናሉ››ሙስሊም 865


ጁምዓ ግዴታ የሚሆንባቸው ሰዎች

ጁምዓ በእያንዳንዱ ወንድ፣ ከባርነት ነፃ በሆነ፣ አቅመ አዳም በደረሰ፣ የአእምሮ ጤነኛ በሆነና ወደ ጁምዓ የመምጣት ችሎታ ባለው ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው፡፡ በአንፃሩ በባሪያ፣ ሴት ልጅ፣ ያልደረሰ ልጅ፣እብድ፣ህመምተኛና መንገደኛ ላይ ግዴታ አይደለም፡፡

ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ጁምዓን በህብረት መስገድ ከአራት ሰዎች በስተቀር በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው፡- ባሪያ፣ ሴት ልጅ፣ ህፃንና ህመምተኛ››አቡዳውድ 1ዐ54 መንገደኛ የሆነ ሰው ላይ ጁምዓ ግዴታ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ነብዩ (ﷺ) ባደረጓቸው ጉዞዎች ላይ አንድም ቀን ጁምዓ አልሰገዱም::

ነብዩ (ﷺ) ባደረጉት የመሰናበቻ ሐጅ ላይ ጁምዓ ገጥሟቸው ነበር ነገር ግን የሰገዱት ዙህርና ዓስርን በማቆራኘት እንጂ ጁምዓን አልነበረም፡፡ ይሁንና አንድ መንገደኛ ሙስሊምች ጁምዓ የሚሰግዱበት ቦታ ላይ በአጋጣሚ ቢገኝ ከነሱ ጋር አብሮ ጀምዓ መስገድ አለበት፡፡ ባሪያ፣ ሴት፣ልጅ፣ህፃን፣ህመምተኛ ወይም መንገደኛ ጁምዓ ተገኝተው ከሰገዱ ዙህርን መስገድ አይጠበቅባቸውም::

የጁምዓ ወቅት

የጁምዓ ሰላት ወቅት ልክ እንደ ዙህር ፀሀይ ወደ ምዕራብ ዘንበል ካለችበት ወቅት አንስቶ የአንድ ነገር ከፀሐይ የሚያገኘው ጥላ በቁመቱ ልክ እስከሚሆን ድረስ ነው፡፡ አነስ ኢንብ ማሊክ እንዳሉት ‹‹ነብዩ (ﷺ) ጁምዓ የሚሰግዱት ፀሐይ ዘንበል ስትል ነበር››ቡኻሪ 9ዐ4 በዚህ ወቅት ጁምዓ መስገድ የሰሃቦች የተለመደ ተግባር እንደነበርም ተዘግቧል፡፡

በዚህ መሰረት ወቅቱ ከማብቃቱ በፊት አንድ ረከዓ የመስገጃ ያህል ጊዜ ላይ የደረሰ ጁምዓን ይሰግዳል፡፡ ወቅቱ ያለፈበት ከሆነ ግን መስገድ ያለበት ዙህርን ነው፡፡

የጁምዓ ኹጥባ

ኹጥባ ነብዩ (ﷺ) በሰገዷቸው ጁምዓዎች ሁሉ የፈፀሙትና ትተውት የማያውቁ በመሆኑን የጁምዓ መሰረት ነው፡፡ ስለዚህ ጁምዓ ያለ ኹጥባ መሰረተቢስ ነው:: በጁምዓ የሚደረጉት ኹጥባዎች ሁሉት ኹጥባዎች(ሁለት ኹጥባዎች የሚባሉት ኢማሙ አንደኛውን ኹጥባ ካደረገ በኋላ በመሃል ተቀምጦ ለሁለተኛ ጊዜ ቆሞ የሚያደርጋቸው ናቸው)ሲሆኑ መስፈርቱም ከሰላት አስቀድሞ ማድረግ ነው፡፡

የኹጥባ ሱናዎች

ለሙስሊሞች ዱንያዊና ሀይማኖታዊ ጉዳዮች መስተካከልና ለመሪዎች ዱዓ ማድረግ የተወደደ ነው፡፡ ነብዩ (ﷺ) የጁምዓ ዕለት ኹጥባ ሲያደርጉ በጣታቸው ወደ ላይ እየጠቆሙ ዱዓ ሲያደርጉ ሰዎችም አሚን ይሉ ነበር፡፡ ኹጥባና ሰላት በአንድ ሰው ቢፈፀሙ ይወደዳል፤ ኹጥባ አድራጊው በተቻለ አቅም ድምፁን ከፍ ቢያደርግ የተወደደ ነው፤ ኹጥባን ቆሞ ማድረግ የተወደደ ነው፡፡ ጃቢር ኢብን ሰሙራ እንዳሉት ‹‹ነብዩ (ﷺ) ቆመው ኹጥባ ካደረጉ በኋላ በመሀል ተቀምጠው ከዚያ እንደገና ቆመው ያደርጉ ነበር››ሙስሊም 862

ኹጥባን አጠር ማድረግና የሁለተኘውን ኹጥባ ከመጀመሪያው ይበልጥ አጠር ማድረግ፡፡ ዓማር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ‹‹የአንድ ሰው ኹጥባ አጠር ማለቱና ሰላቱን ረዘም ማድረጉ የአዋቂነቱ ምልክት ነው፡፡ ሰላትን አስረዝሙ ኹጥባን አሳጥሩ››ሙስሊም 869 ኹጥባ አድራጊው ወደ ህዝቦች ዞር ብሎ ሠላምታን ማቅረብ፡- ጃቢር እንዳሉት ‹‹ ነብዩ (ﷺ) ሚንበርየኹጥባው መድረክ (ምኹራብ) ላይ ሲወጡ ሠላምታ ያቀርቡ ነበር” አዛን አድራጊው አዛኑን እስኪያጠናቅቅ ሚንበር ላይ መቀመጥ ኢብን ዑመር እንዳሉት ‹‹ነብዩ (ﷺ) በሚንበር ላይ ወጥተው አዛን አድራጊው አዛኑን እስኪጨርስ ሚንበር ላይ ይቀመጡና ሲጨርስ ተነስተው ኹጥባ ያደርጉ ነበር››

በጁምዓ ክልክል የሆኑ ተግባራት

ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ መናገር አይፈቀድም፡፡ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ ‹‹በጁምዓ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ የተናገረ መፅሐፍ እንደተሸከመ አህያ ነው››አህመድ 1/23ዐ በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል ‹‹ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ለጓደኛህ ዝም በል ካልክ ከንቱ ንግግር ተናገርኽ›› በተቀመጡ ሰዎች ትከሻ በኩል በመሸጋገር መተላለፍ :

ነብዩ (ﷺ) የሰዎችን ትከሻ እየተሸጋገረ ሲያልፍ ለተመለከቱት ሰው ‹‹ተቀመጥ ሰውን አስቸገርክ›› ብለውታል:: በዚህ ተግባር ሰውን ማስቸገርና ኹጥባን የሚያደምጥን ማዘናጋትም ይፈጠራል:: ኢማሙ ግን የሠዎችን ትከሻ እየተሸጋገረ ካልሆነ ወደ ቦታው የሚደርስበት ሌላ አማራጭ ከሌለው ይህን ሊፈፅም ይችላል፡፡ ሁለት ሰዎችን በመለየት በመካከላቸው መቀመጥም አይፈቀድም፡፡

ነብዩ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል የጁምዓ ሰላት ገላውን ታጥቦ በጊዜ ወደ ጁምዓ የሄደ ከዚያ በኋላ በሰዎች መካከል ሳይለይ አላህ የወሰነለትን የሰገደ በዕለቱና በሚቀጥለው ጁምዓ መካከል የሚፈፀሙ ኃጢአቶች ይማርለታል (ቡኻሪ 91ዐ)
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
SHARE 🔗SHARE
🇪🇹የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ🇪🇹
እዉቀት በምን ያምራል?
እውቀት ያለ ሶስት ነገር አያምርም

1⃣ የተማርከውን/ ያወቅከውን ደጋግሞ ማየት

2⃣ የማታውቀውን ለማወቅ መጣር

3⃣ የተማርከውን/ ያወከውን ማስተላለፍ

http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
📌የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ📌
#ወርቃማ #አባባሎች 🔘
~
🔹ከልምዶች ሁሉ ጎጂ☞ጭንቀት
🔹የሚያኮራ ስራ. ☞ሰወችን መርዳት
🔹አስቀያሚ ባህሪ. ☞ራስ ወዳድነት
🔹መጥፎ ልማድ ☞መስረቅ
🔹ትልቅ የተፈጥሮ ሀብት☞ወጣትነት
🔹ትልቅ መሳሪያ ☞ ብርታት
🔹መጥፎ ፀባይ ☞ ይሉኝታ
🔹ቆንጆ ጌጥ ☞ፈገግታ
🔹አደገኛ ስብከት☞አሉባልታ
🔹ትልቅ ስጦታ ☞ምክር
🔹የሰዉ ልጅ እንቆቅልሽ ☞ኑሮ
🔹አደገኛ መሳርያ☞ ምላስ
🔹ራስን የመጉዳት ዘዴ ☞ማልቀስ
🔹በሀይል የተሞላ ቃል ☞እችላለሁ
🔹ልንፈታዉ የሚገባን ችግር ☞ፍርሀት
🔹ዉጤታማ የእንቅልፍ ክኒን ☞የአእምሮ እረፍት
🔹መጥፎ የዉድቀት በሽታ ☞ከስህተት ይቅርታን
አለመጠየቅ
🔹የህይወት ሀይለኛ ጉልበት ☞ አእምሮ
🔹ከህይወት ልምዶች የምድር ታላቅ ደስታ ☞መስጠት
⚂ወዳጀ ሆይ⚂
ትላንት ታሪክ ነዉና ተርከዉ
ዛሬ ቁምነገር ነዉና ተጠቀምበት
ነገ ምስጢር ነዉና ድረስበት
★ለመነሳት ከፈለክ መዉደቅህን አምነህ ተቀበል★
🔘
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯አረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ🎯

SHARE 🔗SHARE

      
✔️✔️ #ቀልድ መሳይ ቁም ነገር ላካፍላችሁ።

አንድ ሙስሊም ያልሆነ ሰው ወደ አንድ ሸህ...መጣና የምከተሉትን ጥያቄዎች ጠየቃቸው።

#በኢስላም ሴት ልጅን መጨበጥ የተከለከለው ለምንድን ነው??

🏿 #ሸህ፦.አንተ የንጉስ
ኤልሳቤጥን እጅ መጨበጥ ትችላለህ?
ሙስሊም ያልሆነ ፦በርግጥ አልችልም አንዳንድ ሰዎች አሉ የምጨብጧቸው።

🏿 #ሸህ፦ ሴቶቻችን ንግስቶች ናቸው ። ንግስት ደግሞ የእንግዳ ( የተከለከለ) ሰውን እጅ አትጨብጥም ።

ሙስሊም ያልሆነ፣፦ የሙስሊም ሴቶች ለምንድን ነው የምሸፋፈኑት?

🏿 #ሸህ.፦ ፈገግ ብለው ሁለት ከረሜላዎችን አወጡና አንዱን ሽፋኑን ገልጠው ሌላውን ሸፍነው አቧራ ላይ ጣሏቸው ። ከዚያም የትኛውን ትመርጣለህ? አሉት

#እሱም ፦ የተሸፈነውን አለ።

🏿 #ሸህ.፦ እኛ ሴቶቻችንን እንደዚህ ነው የምናየውና የምንከባከበው። ሴት ልጅ እንደ ጨራቃ መሆን የለባትም ሁሉም እንደ ልቡ የሚያያት እና የሚመኛት፤ እንደ ጸሃይ መሆን አለባት አይቶ እይታውን የሚቀንስ።

ሙስሊም ያልሆነ ፦ ፈጣሪ አለ ካላችሁ አሳዩኝ ..

🏿 #ሸህ፦.እስቲ ወደ ላይ ቀና በልና ጸሃይን እያት .

#ካፊሩ፦አልችልም ጨረሯ ከባድ ነው ።

🏿 #ሸህ ፦ የሱን ፍጥረት ማየት ካልቻልክ እንዴት ፈጣሪን ማየት ትችላለህ አሉት? በመጨረሻም ወደ ቤቱ ወሰዳቸውና የወይን ፍሬ ሰጠቸው ።

🏿 እሳቸውም ተመገቡ ( በሉ) እንደገና ወይን ጠጅ አመጣና ሰጣቸው ።

🏿 #እሳቸውም #አልጠጣም አሉት።

እሱ ፦ወይን ፍሬ ከበሉ ለምን ወይን ጠጅ አይጠጡም ሲል ጠየቃቸው ?

🏿 #ሸህ..፦ ሴት ልጅ አለህ አሉት ?
#እሱም፦ አዎ አለ።

🏿 #ሸህ፦ ልጅህን ታገባታለህ አሉት?
እሱም፦ በፍጹም አለ።

🏿 #ሸህ፦ ሱብሃን አሏህ ..እናቷን አግብተሃታል ልጅህን ግን አታገባትም የተወለደችው ግን ከርሷ ነው በማለት የኢማን ጥልቀታቸውን አሳዩት፡፡
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
SHARE 🔗SHARE
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
👑़ ታላቋ ሴት ़👑
ुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुु
.
ከዕለታት በአንዱ ቀን ነብያችን ﷺ ታላላቅ ከሚባሉት የአንሷርና የሙሃጂር ሰሃቦች ጋር መስጂድ ውስጥ ተቀማምጠው ሳለ አንዲት ሴት ድንገት በሩ ላይ ብቅ አለች ፡፡ በቀጥታም ነብያችን ﷺ ወደተቀመጡበት አምርታ ከፊት ለፊታቸው ቆመችና ሃያዕ በተጫነው ድባብ ‹‹ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ እኔ ዝሙት ፈፅሜያለሁ አንፁኝ ›› አለቻቸው ፡፡
ይህን እንደሰሙ ነብያችን ﷺ ፊታቸው ደም የሚያዘንብ እስኪመስል ቀላ ፡፡ ከዛ ፊታቸውን ወደ ቀኝ አዞሩ ምንም ያልሰሙ መስለውም ዝም አሉ ፡፡ ሴትየዋ ከንግግሯ ትመለስ ዘንድም ከጀሉ ፡፡
ነገር ግን ይቺ ኢማን በደም ስሯ የሰረፀ ታላቅ እንስት ...‹‹ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ማዒዝ ኢብን ማሊክን እንደመለሱት ሊመልሱኝ ይፈልጋሉን ( ? ) በአላህ ይሁንብኝ እኔ ከዚና አርግዤያለሁ ››... አለቻቸው ፡፡ ነብያችን ﷺ ይህንን አስደንጋጭ ዜና ሲሰሙ ..‹‹ እስክትወልጂው ድረስ ሂጂ ››.. ብለው ሸኟት ፡፡ እርሷም ውሳኔዋን ተቀብላ ወደመጣችበት ተመለሰች ፡ እስክትወልደውም በትዕግስት ፣ በፀፀትና በሀዘን ጠበቀች ፡፡ እንደወለደችውም በቀናቶች እድሜ ያለውን ልጇን ታቅፋ ወደ ነብያችን ﷺ በመምጣት ..‹‹ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ አንፁኝ ››.. አለቻቸው ፡፡
የዚህኔ የእዝነቱ ነብይ ﷺ ወደ ህፃኑ በሀዘንና ትካዜ ከተመለከቱ በኀላ ይቺ ሴት ላይ ቅጣቱን ተፈፃሚ ካደረግን ይህንን ህፃን ማን ያጠባዋል ' ማንስ ይንከባከበዋል ብለው አሰቡና ..‹‹ ተመልሰሽ ....... አጥቢውና ጡት ሲጥል ነይ ››.. ብለው ሸኟት ፡፡ ልክ እንደ ቀደመው ጊዜ አሁንም ወደመጣችበት ተመለሰች ፡፡ ከዚያም ልጇ ጡት እስኪጥል አጠባችው ፡፡ ይህንን ካደረገች በኀላም በቀጠሮዋ መሰረት ልጇን ዳቦ አስይዛ ነብያችን ﷺ ዘንድ መጣች ፡፡ ከዚያም ..‹‹ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ይኸው ( ልጄ ) ጡት ጥሏል አንፁኝ ››.. አለቻቸው ፡፡
የዚህኔም ሆደ ባሻ የሆኑት ነብያችንም ﷺ ልጇን ተቀበሏትና ..‹‹ ይህንን ልጅ የሚያሳድግ በጀነት ከኔ ጋር ይሆናል ››.. አሉ ፡፡ ይህንን ሲናገሩ ከአንሷሮች መሃል አንዱ እኔ አሳድገዋለሁ አለ ፡፡

በመቀጠልም እስከ ደረቷ ተቀብራ በድንጋይ እንድትቀጠቀጥ ተደረገ ፡፡ ከሞተች በኀላም የፍጥረተ ዐለሙ ምርጥ ነብያችን ﷺ ሰገዱባት ፡፡
የዚህኔ ታላቁ ሰሃባ ዑመር ( ረዲየ ' ሏሁ ዐንሁ ) ..‹‹ አንቱ የአላህ ነብይ ሆይ ዚና ሰርታ ይሰግዱባታልን ( ? ) ››.. አላቸው ፡፡
እሳቸውም ﷺ ..‹‹ በእርግጥ ( ይቺ ሴት ) ሰባ ለሚሆኑ የመዲና ሰዎች ቢከፋፈል የሚበቃን ተውባ ቶብታለች ››.. በማለት መለሱለት ፡፡

http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
📌የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ📌
የኡለማኦች ደረጃ :በኢስላም እይታ
በ ሸይህ ያቁት አብዱል መጂድ
ነገ ማታ አንድ ሰዐት በአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች የዩቱዩብ ይለቀቃል። ዕንድትከታተሉ
https://youtu.be/a0fVMTYSpT4
የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
وَالضُّحَىٰ
በረፋዱ እምላለሁ፡፡

وَاللَّيْلِ إِذَا سَجَىٰ
በሌሊቱም ጸጥ ባለ ጊዜ፤

مَا وَدَّعَكَ رَبُّكَ وَمَا قَلَىٰ
ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም፡፡

وَلَلْآخِرَةُ خَيْرٌ لَّكَ مِنَ الْأُولَىٰ
መጨረሻይቱም (ዓለም) ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት፡፡
وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَىٰ
ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡

أَلَمْ يَجِدْكَ يَتِيمًا فَآوَىٰ
የቲም ኾነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)፡፡

وَوَجَدَكَ ضَالًّا فَهَدَىٰ
የሳትክም ኾነህ አገኘህ መራህም፡፡

وَوَجَدَكَ عَائِلًا فَأَغْنَىٰ
ድኻም ኾነህ አገኘህ፤ አከበረህም፡፡

فَأَمَّا الْيَتِيمَ فَلَا تَقْهَرْ
የቲምንማ አትጨቁን፡፡

وَأَمَّا السَّائِلَ فَلَا تَنْهَرْ
ለማኝንም አትገላምጥ፡፡

وَأَمَّا بِنِعْمَةِ رَبِّكَ فَحَدِّثْ
በጌታህም ጸጋ አውራ፤ (ግለጻት)፡፡
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
#አንተ #የጥቁር #ሴት #ልጅ!“ ተብለህ ብትሰደብ፣ምላሽህ ምን ይሆናል?

🌿ቢላል(ረዐ) እንዲህ ነው የመለሰው....
በአንድ ወቅት፣ የረሱል (ሰዐወ) ባልደረቦች (ረዐ) ሰብሰብ ብለው
ረሱልን (ሰዐወ) እየጠበቁ ነበር። በወቅቱ ከነበሩት ውስጥ፣ ኻሊድ ኢብን
ወሊድ፣
አብዱራህማን ኢብን አውፍ፣ ቢላል ኢብን ረባህና አቡዘር (ረዐ)
ይገኙበታል።
ከነዚህ ውስጥ ደግሞ ቆዳው ጥቁር የሆነ ሰው #ቢላል አል ሀበሽ (ረዐ)
ብቻ ነበር። አቡዘር (በዘገባው ውስጥ ስለምን እንደሆነ በግልጽ
ስላልተቀመጠ
ጉዳይ) መናገር ይጀምርና ቢላል ደግሞ ያርመዋል። አቡዘር(ረዐ) በዚህ
ክስተት በጣም ይበሳጭና😡 “ አንተ የጥቁር ሴት ልጅ! ልታርመኝ
ትሞክራለህ?”
ሲል ያንባርቅበታል። ቢላል(ረዐ)፣ አቡዘር (ረዐ) በተናገረው ነገር
እንደተከፋ በሚያስታውቅ ሁኔታ ከተቀመጠበት ተነሳና “በአላህ
ይሁንብኝ፣ ለረሱል
(ሰዐወ) እከስሀለሁ!” ብሎ ሄደ። ሄዶም ለረሱል (ሰዐወ) ስለሆነው
ነገር ነገራቸው።

💐💐ረሱልም (ሰዐወ) በሰሙት ነበር በጣም ተበሳጩ። አቡዘር (ረዐ)
እየተቻኮለ መጥቶ ረሱልን (ሰዐወ) አገኛቸውና “አሰላሙ አለይከ ያ
ረሱሉላህ”
ይላቸዋል። (በዛ ወቅት የነበረውን ነገር አቡዘር ራሱ ሲናገር እንዲህ
ይላል)
”እጅግ በጣም ከመናደዳቸው የተነሳ፣ ለሰላምታዬ እንኳ መልስ
የሰጡኝም አይመስለኝም” ከዛም እንዲህ አሉ “አንተ አቡዘር! በእናቱ
ምክንያት (ቢላልን) አዋረድከው? #በእርግጥ አንተ የጃሂሊያ ባህሪይ
ከውስጥህ ያለ ሰው ነህ!” (ይህን ሲሉ በመስማቱ) አቡዘር (በፀፀት)
አለቀሰ!😭😭
“የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አላህ እንዲምረኝ ይለምኑልኝ!” ሲልም
ተማፀናቸው። ይህን ብሏቸው እያለቀሰ ከመስጂድ ሲወጣ፣ ቢላልን
(ረዐ)
አገኘው! (ከቢላል ፊት ለፊት) መሬት ላይ ፊቱን ደፍቶ “ቢላል ሆይ!
እግርህን አንስተህ ጭንቅላቴ ላይ እስካለደረግክ(እስካልረገጥከኝ) ድረስ ከዚህ
ቦታ አልነሳም። አንተ ክቡር ነህ፤ እኔ ደግሞ የተዋረድኩ (ትንሽ) ነኝ”
ይለዋል።
ቢላል (ረዐ) በክስተቱ በጣም በማዘኑ ማልቀስ 😥😥ይጀምራል። አጎንብሶም
የአቡዘርን ጉንጭ እየሳመ “ለአላህ (ሱወ) ሱጁድ ያደረገ ፊት ፈጽሞ
አይረገጥም፤ ይሳማል እንጂ!” ብሎታል። (ቡኻሪ ዘግበውታል)
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
SHARE 🔗SHARE
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
✔️አይሳካልህምና ዘላለም ለመኖር አትሞክር"

✔️ስንኖር ችግርና መከራን ለምን እንጠላለን???

☞ዲንጋይ በመዶሻ ተከርክሞ ነዉ ለከተማ
ድምቀት የሚሠጠዉ

☞ህፃን ልጅ በመቆም የሚፀናው ብዙ ወድቆ ተነስቶ ነው

☞ተርበው የበሉት ምግብ ይጣፍጣል

☞ተጠምተው የጠጡት ውሀ ያረካል

☞ላብን አንጠፍጥፈው ያገኙት ገንዘብ በረከት ይበዛዋልና

☞ችግርን በመጥፎ ጎኑ ብቻ አናስብ
ጨለማን ጥቁረቱን ብቻ አንመልከት

ፈጣሪ እንድህ ይላል"
ከችግር በኃላ በዕርግጥ ምቾት አለ።
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
SHARE 🔗SHARE
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
2024/09/28 22:20:50
Back to Top
HTML Embed Code: