Forwarded from ISLAMINDSET
ሰዎች በህይወት ኖረው እንደሞቱ ይቆጠራሉ። በተቃራኒው ደግሞ ሞተው በሰዎች መሀል ይኖራሉ። የሰዎችን ደረጃ የሚወስነው ለሰዎች ስብዕናቸው ሲሆን በአላህ ፊት ደግሞ ዚክር(አላህን በምላሳቸው ማስታወስ)ስንችሉ ብቻ ነው። ለዚያም ነው "እነዚያ አላህን የሚያስታዉሱ እና የማያስታዉሱ ምሳሊያቸው በህይወት እንደሚኖሩ እና እንደሞቱ አምሳያ ናቸው ያሉት ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁአለይሂ ወሰለም!)
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
Forwarded from ISLAMINDSET
ዱንያ የሰው ልጆች ይሄን ያክል ትኩረት አድርገውባት ለፍተውባት ካልሞላች ያውም ከ40-60 አማካኝ እድሜ ለመኖር አኪራ ሳይለፋበት ይገኛል ብሎ የሚያስብ ካለ ተሳስቷል። አዕምሮው ራሱ ባልተገነዘበው ነፃ ሀሳብ ታሟል። ለሁሉም ህመም ደግሞ መድሀኒት አለው። ለደነዚህ አይነቱ በሽታ መድሀኒቱ ቁርአን ማንበብ እና በጥልቀት ማስተንተን ነው።
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
Forwarded from ISLAMINDSET
የአይናችን ተዓምሩ በብርሃን ነፀብራቅ የነገሮችን ምስል በቀለማቸው አማካኝነት መመልከት ማስቻሉ ነው። እንደዚህ አይነቱ ብርሃን የትኛውም ፍጥረት አይን እስካለው ድረስ መመልከት ይችላል። የልብ ብርሃን ግን ለአይን ከሚሰጠው ብርሃን ፍፁም የተለያየ ነው። ይሄም ብርሃን ያለው በቁርአን ውስጥ ብቻ ነው። የቁርአንን ብርሃን ያገኘ አይኑም ልቡም ይመለከታል። ያጣው ግን አጥቶታል። ለዛ ነው ብዙዎች በአይናቸው ማየት ችለው በልባቸው መመልከት ያቃታቸው!
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
Forwarded from ISLAMINDSET
ብዙዎች ነፃ መውጣትን ከጉልበት እና ከገንዘብ ጋር አያይዘው ይመለከቱታል። ጥቂቶች ደግሞ ከሞት በኋላ አላህ ቃል ስለገባው ጀነት እና ከቅጣት መዳንን ነፃ መውጣትን በማሰብ ነፃ ነን ይላሉ።ነገር ግን የተወሰኑ ሰዎች በዱንያ ላይ የማያልፍን ነገር በሚያልፈው ሰዓታቸው ስራን ሰርተው ነፃ የወጡ ሰዎች አሉ።ነፃ መውጣት ማለት አላህ በባሮቹ ላይ ግዴታ ካደረገው በላይ ትሩፋቶችን ጨምሮ መስራት ነው።ለዛ ነው እነዚያ የተወሰኑ ሰዎች ሳይሞቱ ዱንያን ላይ አላህ ጀነት ውስጥ የሚያስቀምጣቸው።...ምንኛ ያማረ ነፃነት ነው! አላህ ይወፍቀን!
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
Forwarded from ISLAMINDSET
"በአንድ ቀን ውስጥ ሱበሀነላህ ወቢሀምዲሂ 100 ግዜ ያለ ሰው ወንጀሉን አላህ ይምርለታል።ወንጀሉ እንደ ባህር አረፋ ቢበዛም!" ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ).
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
Forwarded from ISLAMINDSET
ትልቅ ሰው ማለት ራሱ የሚድንበትን መንገድ ለማግኘት ሰበብ የሚያደርግ ነው። ብዙዎች ራሳቸውን ለማዳን ሁሌም ይሯሯጣሉ።ነገር ግን "ከምንድን ነው የምናድነው!?" የሚለው ጥያቄ ይለያያቸዋል።ሰዎች እዚህ ላይም ነው የሚለያዩት! ሙስሊም በባዶ ተስፋ ሳይሆን የኢኺራ እርግጠኝነትን(የቂንን) በልቡ ስላረጋገጠ, ሩጫው ሰላረጋገጠው አለም ብቻ ነው። አላህም ባረጋገጠው ኒያ መሰረት ይመነደዋል። ምክንያቱም ሙኽሊስ ባሪያው መሆኑን በተግባር ለአላህ አሳይቷልና!
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
Forwarded from ISLAMINDSET
ገንዘብ ሲገኝ ሊያስደስት ይችል ይሆናል። ያስደስት እንጂ የውስጥን እርካታና መረጋጋትን በፍፁም አይሰጥ።ለዛ ነው ገንዘብ የሌላቸው ሰዎች ገንዘብን ሲያገኙ በፊት ላይ ከነበሩበት አላህ የሚወደው ቦታ የምናጣቻው። ገንዘብ ያላቸው ከሌላቸው ሰዎች ይበልጥ ሩጫ እና ጭንቀት ውስጥ ይገባሉ።አላህ ያዘነላቸው ሰዎች ሲቀሩ!...እንዲሁ ገንዘብ ሲታጣ ሊጠብ እና ሊያጨናንቅ ይችል ይሆናል። ነገር ግን አያስደነግጥም። ምክንያቱም መታጣቱ ቋሚ አይደለም።ግዜውን ጠብቆ ይመጣል። በነዚህ በሁለቱ ተቃራኒ ጎኖች አንድ ሙዕሚን ገንዘብን ሲያገኝ የሁሉ የበላይ እንደሆነ አያስብም...ሲያጣም ከሁሉ የበታች እንደሆነም አይሰማውም። ሙስሊም ገንዘብ ሲያገኝ ሆነ ሲያጣ አንድ አይነት ባህሪ ብቻ ነው ያለው... እሱም በአላህ ፈተና ላይ እንደሆነ ያስተነትናል።
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
Forwarded from ISLAMINDSET
በየ አመቱ...በየ ወሩ...በየ ሳምንቱ...በየቀኑ...በየሰዓቱ..በየደቂቃው እንዲሁም በየሴኮንዶች አላህ በኛ ላይ እዝነቱን ፀጋው ምህረቱን ይውልልናል። ልባችን ከድንጋይ በላይ ስትደርቅ ከሰጠን ይልቅ በአብዘሀኛው ያልሰጠን ነገር እንዳለ እያስመሰልን አላህን"አልሀምዱሊላህ!!!" ከማለት እንኮራለን።ነገር ግን ልባችን የመርጠቧ ምልክት የትኛውንም የዱንያ ህመም ላይ እንሁን አላህ በሰጠን ፀጋ ስለምንሽር "አልሀምዱሊላህ!!" ከማለት አናርፍም። ምክንያቱም ፀጋውን በውስጡ ላመነ ሰው "አልሀምዱሊላህ!" እንዲ ያስገድደዋል። እንዳለመታደል ሆኖ ግን የአላህ አመስጋኝ ባሮቹ ትንሽ ሆነው በፀጋው የሚክዱት በዙ!
አላህ ከጥቂት ባሮቹ ያድርገን!...ምክንያቱም አመስጋኝ ባሮቹ ጥቂት ናቸውና!
➙ መልካም የጁሙኣ ግዜ ይሁንልን።
ISLAMINDSET
አላህ ከጥቂት ባሮቹ ያድርገን!...ምክንያቱም አመስጋኝ ባሮቹ ጥቂት ናቸውና!
➙ መልካም የጁሙኣ ግዜ ይሁንልን።
ISLAMINDSET
Forwarded from ISLAMINDSET
Forwarded from ISLAMINDSET
ሁሉም ነገር ያልፋል።ሲያልፍ ግን ግዜ በክንውን ነው...እንጂ ክንውን በግዜ አይደለም። ሁሉም ነገር ሲፈፀም ግዜን ተከትሎ ነው የሚፈፀመው! አላህ ፈፅሙ ያለንን ስንፈፅም አፈፃፀማችን ግዜ አለው። ለዚያ ነው ግዴታ፣ሱና፣ዋጂብ እንዲሁም ፈረድ የሚባሉት በግዜ ላይ ጥገኛ የሆኑት።ከተገበርናቸው በግዜ ተጠቀምን ይባላል። በተቃራኒው አራም፣ ሙነከር፣ ቢድዓ እንዲሁም ኩፍር የሚባሉት ሰዎች ሲተገብሯቸው ባላቸው ግዜ ላይ ነው። ከተተገበሩ ግዜ ባከተነ ይባላል። አንድ ሰው ግዜውን ከሚያባክኑ ሰዎች ውስጥ ነው, አልያም ግዜያቸውን ከሚጠቀሙ ሰዎች ውስጥ ነው።ልብ በሉ መሀል ሰፋሪ የሚባል ነገር በዚች አለም ላይ እንደሌለ! ለዚያም ነው አላህ ስለሰራነው ስራ የቂያማ ቀን ሲጠይቀን ሁሉም ጥያቄዎቹ ከግዜ ጋር የተያያዙ ናቸው።ለዚህም ረቂቅ ምክንያቱ ግዜ ማለት ህይወት ስለነበረ ነው!
ትክክለኛ ሙስሊም ሁሌም ግዜውን ይጠቀምበታል..ምክንያቱም ለዚያ የአላህ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሆኑት ዘንድ ማለት ነው።
------------------- መልካም ግዜ ------------------
ISLAMINDSET
ትክክለኛ ሙስሊም ሁሌም ግዜውን ይጠቀምበታል..ምክንያቱም ለዚያ የአላህ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሆኑት ዘንድ ማለት ነው።
------------------- መልካም ግዜ ------------------
ISLAMINDSET
Forwarded from ISLAMINDSET
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጁመዓ ቀናችሁ እጃችሁን አንስታችሁ በዚህ ዱዓ አላህን ለምኑት...ኢንሻአላህ ሩህሩህ የሆነው አላህ(ሱ.ወ) ያስደስተናል።ከዱዓ አንዘናጋ ..ቀኑ ጁሙዓ ነውና! ብዙዎች ያላገኙት አሉ።
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
Forwarded from ISLAMINDSET
https://youtu.be/en_gxqRbdYI
ማክሰኞ ➙ ከምሽቱ 11:30 ይለቀቃል!
ማክሰኞ ➙ ከምሽቱ 11:30 ይለቀቃል!
YouTube
በኢስላም ላይ አታደባልቅ| ሳይኮ-ኢስላም ዳዕዋ | #foryou #viral_video
EPISODE ➙ 11
Forwarded from ISLAMINDSET
" ኢስላም በህይወታችን እየጠቀመን ነውን!"
ISLAMINDSET ሜንቶር
Episode ➙ 08
እርግጠኛ ነኝ ርዕሱን ስታነቡት አብዘሃኞቻችን ብዙ ነገር እንደጠቀማችሁ ትመሰክሩ ይሆናል። ነገር ግን "የጠቀማችሁን ዘርዝሩት!" ብትባሉ አትዘረዝሩትም። ለምን ቢባል አላህ ያዘነለት ሰው ካልሆነ በስተቀር የአብዘሀኛው ሰው ህይወቱ በአሁን ሰዓት ላይ የተጠቀመውን ከማስተንተን ይልቅ ወደፊት ይጠቅመኛል ብሎ በሚያስበው ነገር ላይ የተገነባ ነው። ለዛ ነው ኢስላም እንደሚጠቅመን ብናምንም አሁናችንን እና ወደፊቲችንን እዚህ ግባ በማይባሉ ነገሮች ምኞታችን ስለተሞላን ኢስላምን ቦታ የማንሰጠው! ...ብንሰጠውም በተግባራችን እንደሚያመላክተን እንደተጨማሪ ነገር የምናስበው!....
የቪዲዮ ዝግጅቱን በቅርብ ቀን ይጠብቁን!
ISLAMINDSET.
#join #like #shrae
ISLAMINDSET ሜንቶር
Episode ➙ 08
እርግጠኛ ነኝ ርዕሱን ስታነቡት አብዘሃኞቻችን ብዙ ነገር እንደጠቀማችሁ ትመሰክሩ ይሆናል። ነገር ግን "የጠቀማችሁን ዘርዝሩት!" ብትባሉ አትዘረዝሩትም። ለምን ቢባል አላህ ያዘነለት ሰው ካልሆነ በስተቀር የአብዘሀኛው ሰው ህይወቱ በአሁን ሰዓት ላይ የተጠቀመውን ከማስተንተን ይልቅ ወደፊት ይጠቅመኛል ብሎ በሚያስበው ነገር ላይ የተገነባ ነው። ለዛ ነው ኢስላም እንደሚጠቅመን ብናምንም አሁናችንን እና ወደፊቲችንን እዚህ ግባ በማይባሉ ነገሮች ምኞታችን ስለተሞላን ኢስላምን ቦታ የማንሰጠው! ...ብንሰጠውም በተግባራችን እንደሚያመላክተን እንደተጨማሪ ነገር የምናስበው!....
የቪዲዮ ዝግጅቱን በቅርብ ቀን ይጠብቁን!
ISLAMINDSET.
#join #like #shrae
እንደዛሬው ባለ ቀን... ለይሉ ጁምዓ ሲሆንና የኸሚስ ጀንበር ወደ ማደሪያዋ ስትሸኝ፤ የመልከ ብዙ ትሩፋት ከንዝ የሆነው የሶለዋት ሞገድ አየሩ ላይ ይናኛል። አላህ ያገራለት አማኝ ደግሞ እንዲህ ባለ ቀን ከእንቅልፍ ተኳርፎ፤ የከውኑን ሞገስ፣ የዓለሙን ዓይነታ የሚያወድሱ ዓይነተ ብዙ ሶለዋቶችን ያለመታከት እየተቀኘ ሌቱን ሕያው አድርጎ ያነጋል።
አዎ! እንደዛሬው ባለ ምሽት ከነፋሱ ጋር የሚነፍሰው ሶለዋት ዳር እስከ ዳር በቅብብሎሽ ሲከረር፤ የዩኒቨርሱ ብሔራዊ መዝሙር የሆነ ያህል ልብ ያሞቃል።
اللَهُمَّ صلِّ وسَلِم وبَارِك على سيدنا محمد (ﷺ)
youtube// @arebgenda_mesjid
www.tg-me.com// @arebgendamesjid
Instagram // arebgenda_mesjid
tik tok //arebgenda_mesjid
Facebook //mesjid5043
በመጎብኘት የማህበረሰብ ሚዲያዎቻችንን በሚለቀቁ ትምህርቶች እና ጠቃሚ ምክሮች ይከታተሉ።
የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች የሚዲያ ማዕከል
አዎ! እንደዛሬው ባለ ምሽት ከነፋሱ ጋር የሚነፍሰው ሶለዋት ዳር እስከ ዳር በቅብብሎሽ ሲከረር፤ የዩኒቨርሱ ብሔራዊ መዝሙር የሆነ ያህል ልብ ያሞቃል።
اللَهُمَّ صلِّ وسَلِم وبَارِك على سيدنا محمد (ﷺ)
youtube// @arebgenda_mesjid
www.tg-me.com// @arebgendamesjid
Instagram // arebgenda_mesjid
tik tok //arebgenda_mesjid
Facebook //mesjid5043
በመጎብኘት የማህበረሰብ ሚዲያዎቻችንን በሚለቀቁ ትምህርቶች እና ጠቃሚ ምክሮች ይከታተሉ።
የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች የሚዲያ ማዕከል