የሚኒስትሪ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች

➊ የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡

❷ በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን ክብ ብቻ መጠቆር አለበት፡፡

➌ ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው ክብ ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡

❹ ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን ክብ በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡

❺ በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ ክብ ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡

❻ ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡

❼ ለመፃፍ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ተፅፎ ወይም ትንሽ ጭረት እና ነጥብ ከተገኘ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ሙሉ  በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

❽ መልስ በሚጠቆርበት ጊዜ እርሳሱ ከተሰጠው የክብ ሳጥን መውጣት የለበትም። ከወጣም በማጥፊያ (Eraser/Rubber) ማጥፋት ይጠበቅባችኋል።

❾ መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡

➓ ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ  የምዕራፍ አካዳሚ ቤተሰቦች እንዲሁም በመላው ዓለም የምትገኙ የእምነቱ ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው  የኢድ አል-አድሃ አረፋ በዓል በሠላም አደረሳችሁ፡፡
     በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እና የደስታ ይሁንላችሁ።

                       ዒድ-ሙባረክ !!!
       
2024/06/26 05:53:04
Back to Top
HTML Embed Code: