Telegram Web Link
✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣
▬▬▬❤️ "ፍቅር"❤️▬▬▬

ይህ ፍቅር የሚሉት ለምን ተፈጠረ
አንጀት እየበላ ልብ እያሳረረ
ሃኪም ያልተረዳው መድን የታጣለት
እየበሉ ረሃብ እየጠጡ ጥማት
በፍቅር ተለክፎ ልቡ እየተመታ
እንደኔ ሚያቃስት ጥዋት እና ማታ
ይሀው እና እኔም ባንቺ ከተያስኩኝ
ሰዉ የማይረዳኝ በሽተኛ ሆንኩኝ
ህመሜ እንዲጨምር እየነካካሽኝ
ተኮጠረ አመት በፍቅር ስታሽኝ
የስ ልኩ ምልልስ የቃል ልዉውጡ
ከእርካታዉ ይልቅ ያመዝናል ምጡ።

Ⓕⓞⓡⓔ ⓞⓡⓔ Ⓑⓔ Ⓞⓤⓡ Ⓕⓐⓜⓘⓛⓨ

@miny_quotes
~የፍቅር _ሀይል~

ከሳ እራቅ ዞር በል፣ ብለው ላስፈራሩኝ
ይባሱን ቀረብኩሽ.....
እሳን ማፍቀር አቁም፣ ብለው ለዛቱብኝ
ደግሜ አፈቀርኩሽ
ሚሰሩብኝ ሴራ፣ ብርታት እየሆነች ይሄው
አለው ከደጅሽ
ገለሀለው ብለው መልዕክትም ቢልኩ
ወደኔ ለመምጣት ፣እርምጃ ቢለኩ
እኔ መች ገዶኝ......
ፍርሀቴም ስጋቴም ተመን አልባ ሆኖ
ምንንም አከለ
አንቺን በማፍቀር ውስጥ ሞትን
የማይፈራ ንፁህ ፍቅር አለ!!

@miny_quotes
✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣

°°ሁሉም ምክንያት አለው°°

አንዳችም አይሆንም ያለምክንያት ከቶ
የሰው ልብ አይከፋም ከመሬት ተነስቶ
ሰው ሰውን አይወድም ሳያይ አይኑን ከፍቶ
ወይ ባይኑ አይቶ ነው ወይም ሲሉ ሰምቶ
ሰው ሰውን አያማም ስራ መስራት ትቶ
ወይ ግራ ገብቶት ነው ወይም ስራ ጠፍቶ
ሌላው ካልተረዳው ከልብ ጆሮ ሰቶ
የሰው ስሜት ለሰው አይታይም ጎልቶ
ሌላ የለምና ለሰው ልጅ ወዳጅ
ቢወድቅ የሚያነሳ ቢሰበር ሚያበጅ
ቢያዝን የሚያጽናና ቢቸገር ሚረዳ
ጉዳዬ ነው ብሎ ሰምቶ የሚረዳ
ሳንሰማ ሳናይ ከምንጎዳዳ
ጠጋ ብለን እንይ እንስማ የልቡን
ምክንያቱን አለውና እንወቅ ሰበቡን
ቀርበን ብንጠይቀው እንድያ እንደመሆኑ
እንወደው ይሆናል ከነ ምናምኑ

by @mon_son

Please share Please share🙏
@miny_quotes
@miny_quotes
@miny_quotes
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

✣◦◦እውነት ፍቅር አለ?◦◦✣

በባዶ ቦታ ላይ ምንም በሌለበት
ሳይገባ ሳይወጣ ተቀምጠው ባሉበት
ኮቴ ሳያሰማ ሳይታይ ለማንም
ሳይመርጥ ይይዛል ትነሽ ትልቁንም
ተያዝኩኝ ይላሉ እኔ ምን አውቃለው
እጆቹን ዘርግቶ ሲይዝ አላየነው
ተሸነፍኩ ይላሉ ምንም አይገባኝም
ከሰው ጋር ሲታገል ከቶ አልሰማሁኝ

እውነት ይሄ ፍቅር እውነት በህይወት አለ
የታሉ እግሮቹ እጁሳ የታለ
የቱጋ ሆኖ ነው ሰውን የሚይዘው
እንደተመታ ሰው የሚያደነዝዘው
ለምን አይታይም ይደበቃል እንዴ
ሰውን ያየበትን አይኑን ልያ አንዴ
የማይታይበት ምንድነው ሚስጥሩ
ሰዎች ያወራሉ እንደሆነ ጥሩ
ታድያ ለምን ፈራ ለሰው መታየት
መልካምነት ካለው የሚኮራበት

ይሄን ሁሉ ብዬ እራሴን ጠየኩኝ
ሰዎችን ብጠይቅ ከቶ መልስ አልሰጡኝ
አንድ ቃልን ሁሌ ይደጋግማሉ
በፍቅር ተያዝኩኝ ይዞኛል እያሉ
ገብቶአቸው ይሁን አይሁንም አላውቅም
እኔ ግን ገብቶኛል ባለኝ ትንሽ አቅም

ለካ የፍቅር ቤት የሰው ልጅ ልብ ነው
ለካ የሚኖረው በልቤ ውስጥ ነው
በሰው ውስጥ ሆኖ ነው
ሰውን ሚያሸንፈው
ከምድር ከፍ አርጎ ልብን የሚያከንፈው
የተሸነፍኩለት በፍቅር ጉልበት
የተሸነፍኩላት ፍቅር ስላላት

እንደዚ ነው ለካ ተያዝኩኝ የሚሉት
ይሄን ቃል ሁልጊዜ የሚደጋግሙት
የፍቅርን መኖር አምኛለው እኔ
በልቤ ውስጥ ነው ባላየውም ባይኔ።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ⒷⓎ @mon_son
Please share
@miny_quotes
@miny_quotes
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻

❖◈◦ግን...ለምን◦◈❖

በአንድ ክፉ ቀን መልካም በመሰለ
ላዩን አሳምሮ ውስጡ በከሰለ
ሀገር ሰላም ብዬ ከቤቴ ወጣሁኝ
ግልብጦሽ ሆነና ሰላሜን አጣሁኝ

እንደወትሮው ሁሉ እየተደሰትኩኝ
ወደሞቀው ቤቴ ልሄድ ተነሳሁኝ
ቤቴ ስደርስ ግን ልቤ በቅሬታ
እቤቴ ጨለመ ራቀ ከኔ ደስታ

አልፎም ደስታ መቶ ልቤን ይሞላዋል
ደግሞ ሀዘን መቶ ይቆጣጠረዋል
አሁንም ይቦርቃል አንድ ሀሳብ አስቦ
ይቆዝማል ደግሞ በሀዘን ተስቦ

.........ግን ለምን

ስለምን ታየሺኝ በመንገዴ ለይ
ለምንስ ተሰወርሽ ደግሜ እንዳላይ
ልቤን ወስደሽዋል በፍቅር አይተሽው
ማሰብም ትቻለው ሀሳቤን ወስደሽው
የአእምሮዬም ስራ አንቺን ማሰብ ሆኗል
እቤቴም ካላየሽ ላይነጋ ጨልሟል

ይሄን ሁሉ ብዬ የልቤን ብነግራት
ስሜቴን ሳልደብቅ ሀሳቤን ባጋራት

ዓይኔን ፊት ነሳችው በአሉታ መልሷ
ልቤ ታች ወረደች እላይ ከመድረሷ
ቤቴ ብቻ ሳይሆን ህይወቴም ጨለመ
መድሀኒት ላያገኝ ልቤ እጅግ ታመመ

ግንምን ይሆን ነበር ውስጥሽ ብታስገቢኝ
ትወጂኝ ነበረ አንዴ ብታስቢኝ
እኔ ግን አልክድም ባንቺ መሸነፌን
ዛሬም ከመናገር አልቆጥብም አፌን
ላፍታ ሳልዘነጋሽ ሁሌ አፈቅርሻለው
ትመጫለሽ ብዬም እጠብቅሻለው
⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
✦ BY @Mon_son
@miny_quotes
@miny_quotes
Please share🙏
▣▣▣▣▣▣❤️❤️❤️❤️▣▣▣▣▣▣

▬✦ቅምሻ✦▬

🌹🌹ፍቅር ተአምር አይደል🌷
🌹🌹....ሚስጥር አይደል🌷
🌺መላመድ ነው አብሮ መዋል🌺
😍😘መለዋወጥ ቃላት በቃል😘😍
❤️❤️ያለምንም በምንም ላይ❤️❤️
🌹 ሀሳብ ጥሎ ሀሳብ መሳል🌹
▣▣▣▣▣▣❤️❤️❤️❤️▣▣▣▣▣▣
@miny_quotes
@miny_quotes


▢ከሌለሽ የለሁም▢

ያንቺን መኖር ሳስብ በልቤ
በሀሳብ ፍቅርሽን ተርቤ
የኔን መኖር አስበዋለው
በሀሳቤ ውስጥሽ እራሴን አያለው

ካንቺ ውጪ ራሴን ሳየው በሀሳቤ
የሞትኩኝ የሞትኩኝ ይመስለዋል ልቤ
ይጨነቃል ውስጤ እስር ቤት እንዳለ
ይናገራል ልቤ ጨነቀኝ እያለ

......ያላንቺ ራሴን ሳየው

ይቆጣጠረኛል ጨለማ እንደመሸ
ይሰማኛል ውስጤ እንደተረበሸ
ከላይም ከታችም ከግራም ከቀኝ
ይሰማኛል ሀዘን ሲቆጣጠረኝ

ደግሜ አላስብም ካንቺ ውጪ ራሴን
ከቶ አልፈርድባትም ልትጨነቅ ነብሴን
ካንቺ ውጪ ስሆን ደስታን አላየሁም
ካለሽ እኖራለው ከሌለሽ የለሁም።


ተፃፈ በ @mon_son
@miny_quotes
@miny_quotes

የተመቻቹ ❤️ እየነካቹ
2024/09/27 02:22:32
Back to Top
HTML Embed Code: