Telegram Web Link
ቅዱስ አባ ጳውሊ ከሰይጣን ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ!

👉 @mehereni_dngl

ክፍል-2(፪)

👉 @mehereni_dngl

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

ያ ሰው ወደ ባልንጀሮቹ ከሄደ በኋላ አባ ጳውሊ ከእርሱ ጋር ያለውን ዲያቆን እንዲህ አለው፡፡ ወንድሜ የዚህች ሀገር ሰዎች ኃጢአታቸው ታላቅ ነው አለው፡፡
ሌሊት በሆነ ጊዜ በመንገድ የተገናኛቸው መነኮሳቱና ዲያቆኑ ተኝተው ሳለ አባ ጳውሊ ቀስ ብሎ ተነስቶ እየጸለየ ወደዚያ ዳንስ ቤት ከበር ቆመ ፤ ራቁታቸውን ሆነው ባየ ጊዜ ፈጽሞ አዘነ ፤ ጽኑዕ ልቅሶም አለቀሰ፡፡ ባለ ዳንስ ቤቱም ከውጭ ቁሞ ባየው ጊዜ ከሰዎች ጋር ወደ ዳንስ ቤቱ ያልገባኸው ለምንድነው ብሎ ጠየቀው፡፡ እርሱም በሆነ ምክንያት እንዳልገባ ነገረው፡
ከዚህ በኋላ የዳንስ ቤቱ ባለቤት ወደ ውስጥ ገባ፡፡ በገባም ጊዜ የዳንስ ቤቱን በር ዘግቶ መብራቱን አጠፋ፡፡ ያን ጊዜ አባ ጳውሊ በልቦናው እያዘነና እየጸለየ በምድር ላይ ይሰግድ ጀመር፡፡ በዳንስ ቤቱ ውስጥ ያሉት ሰዎች በዱር እንዳሉ እንደጠገቡ ፈረሶች ሲጮኹ ሰማቸው፡፡

አቤቱ ድንቅ ተአምራትን የምታደርግ አንተ ነህ፡፡ ስለቀደሙ ሰዎች ኃጢአት የጥፋት ውሃን በምድር ላይ ያመጣህ አንተ ነህ (ዘፍ. ፯:፲፯)፡፡ ስለ ኃጢአታቸውም ክፋት በሰዶምና በገሞራ ላይ እሳትን ያዘነምክ አንተ ነህ፡፡ (ዘፍ.፲፱፥፳፬)፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ለሌሎች የኃጢአት አብነት እንዳይሆኑ ታጠፋቸው ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ መዓትህንም በላያቸው ላይ ፈጥነህ አድርግ ፣ አጥፊ የሆነውንም ሰይጣን በኃይልህ አጥፋው እያለ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡

እግዚአብሔርም ጸሎቱንና ልመናውን ሰማው፡፡ ጸሎቱንም ከጨረሰ በኋላ ሰይጣን ጥቁር ሰው መስሎ እንደ እሳት የሚንቦገቦግ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ራቁቱን ከዳንስ ቤት ሲወጣ ታየው፡፡
ያም ሰይጣን በማስፈራራት ከዳንስ ቤቱ በር ቆመ፡፡ አባ ጳውሊም አንተ ማነህ? ማንን ትፈልጋለህ? ሰይፍህ በእጅህ የተመዘዘው ለምንድን ነው? አለው፡፡
ሰይጣንም የምትሻውን ንገረኝ ጠይቀኝ እንጂ አንተ ማነህ አትበለኝ፡፡ ከፈጣሪህ ከጌታህ የለመንከውን አንተ ታውቃለህና አለው፡፡
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#share

👉 @mehereni_dngl
👉 @mehereni_dngl
Profile and wallpaper
ቅዱስ አባ ጳውሊ ከሰይጣን ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ!

👉 @mehereni_dngl

ክፍል-3(፫)

👉 @mehereni_dngl

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

አባ ጳውሊም ሰይጣን ያለውን በሰማ ጊዜ የአንተን ሥራ የሚሠሩትን ወዳጆችህን እንዴት ታጠፋለህ አለው፡፡ ሰይጣንም እኔ ከፈጣሪ ታዝዣለሁ ፤ የአዛዤን ትእዛዝ እተላለፍ ዘንድ አይቻለኝም አለው፡፡
አባ ጳውሊም ፦ ብዙ ጥያቄ እጠይቅሃለሁና እንዳትዋሸኝ በሕያው እግዚአብሔር ስም አምዬሐለሁ አውግዤሃለሁ አለው፡፡
ሰይጣንም የምትሻውን ጠይቀኝ ትዕዛዝህን አልተላለፍም ኃይሌ በጸሎትህ ደክሟልና አለው፡፡

አባ ጳውሊም ሰይጣንን ፦ ከመጀመሪያው ከሰዎች በአንዱ አድረህ በኃጢአት ትጥለው ዘንድ አጋዥ የሚሆንህ ምንድነው አለው፡፡
ሰይጣንም ፦ ሰው በእግዚአብሔር ሕግ ጸንቶ ሳለ በማንም ላይ ማደር አይቻለንም፡፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ሕግ ትንሽ ፈቀቅ ቢል ፤ እንዲሁ ደግሞ በየጊዜው ስሙን ባይጠራ ያን ጊዜ በእርሱ ለማደር ኃይል እናገኛለን፡፡

የእግዚአብሔር ስም መጥራት ያልኩህም በፍጹም ሃይማኖት ሆኖ ፦ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ማለት ነው፡፡ ሕፃንም ቢሆን ከመጠመቁ በፊት እናቱ በላዩ ላይ የእግዚአብሔርን ስም የማትጠራና በመስቀልም ምልክት በላዩ ላይ የማታማትብ ከሆነ እኛ እናድርበታለን፡፡ ዳግመኛም ወላጆችና አሳዳጊዎች ይህን መንፈሳዊ ሥራ ካልሠሩ በሕፃናት ላይ ለማደር ሥልጣን አለን አለው፡፡

ዳግመኛ ሴትና ወንድ ለመጋባት በወደዱና በፈቀዱ ጊዜ አስቀድመው በካህናት ጸሎትና በክርስቶስ ሥጋና ደም አንድ ከሆኑ ስልጣን የለንም፡፡ በመኝታቸው አንድ በሚሆኑበት ጊዜም ስሙን በመጥራት ወደ ፈጣሪያቸው ወደ እግዚአብሔር ቢጸልዩ በዚህ መልካም ሥራቸው ኃይላችን ይደክማልና በእነርሱም በልጆቻቸውም ላይ ስልጣን የለንም፡፡ ነገረ ግን ከዚህ ሁሉ መንፈሳዊ ሥራ ቢርቁ እኛ በእነርሱም በልጆቻቸውም ላይ እናድርባቸዋለን፡፡ እንሰለጥንባቸዋለን፡፡ ሰላምን እናሳጣቸዋለን ኑሮአቸው ጠብና ክርክር ፤ መጨረሻውም መለያየት ይሆናል፡፡
ሰው ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም እየጠራ ካልጸለየ የወደድነውን ሁሉ እናደርግበታለን፡፡ ዓለሙን ሁሉ ድል አድርገን እንገዛ ዘንድ ባለን ዐቅማችን እንታገላለን አለው፡፡

👉 @mehereni_dngl
👉 @mehereni_dngl
#Add በማረግ የኦርቶዶክስ ቁጥርን እጨምር !

group
👉 @mehereni_dngl_21
👉 @mehereni_dngl_21
#ጥያቄ

የአብርሃም ልጅ ማን ይባላል ?

#ምርጫ

⚫️ ያዕቆብ

🟣ጴጥሮስ

🔵ይሳቅ

🟢ማቴዎስ
#ሁላቹን_ይመለከታችኋል

በመሐርኒ ድንግል ውስጥ ምን አይነት መርሐ ግብር እዲቀርብላችሁ ትፈልጋላችሁ ሀሳባችሁን አሳውቁን በመሐርኒ group እና bot


👉 @mehereni_dngl_bot
👉 @mehereni_dngl_bot

👉 @mehereni_dngl_21
👉 @mehereni_dngl_21
የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ጥያቄዎች ይቀጥሉ የምትሉ !




👉 @mehereni_dngl
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
  †   መሐርኒድንግል

[ እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ! ]


" በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው ፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም

እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።

በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል ፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል ፥ ያቃጥሉአቸውማል።"

[ ዮሐ.፲፭፥፬ ]


አሁንም ከኦርቶዶክስ ጎን ነን!

          † † †
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
እኛ የመሐርኒ ድንግል ተከታዮች እና አድሚኖች ግበረ ሰዶምን እንቃወማለን!

ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር

We, the followers and admins of Meharni Dungal, are against Gebre Sodom!

Long live Orthodoxy
#share
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
#ታላቅ_የበረከት_ጥሪ_ለፍልሰታ

እንኳን ለፍልሰታ ፆም አደረሶት !

የወልድያ መባ እጥረት ላለባቸው የገጠር አብያተ ክርስቲያናት የሚውል መባ የማሰባሰብ ሥራን በመሥራት ላይ ስለሆንን በዚህ የበረከት ሥራ መሣተፍ የምትችሉ ሁሉ ትሳተፉ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ጥሪ እናስተላልፋለን።

መሳተፍ የምትፈልጉ @natansolo በውስጥ መስመር ማናገር የምትችሉ መሆኑን አሳውቃለሁ።

የተለያዩ ለቤተክርስቲያን ገቢ እና የተለያዩ ክብረ በዓል እናስታውቃለን ደግሞ በነፃ ነው!

አናግሩን👉 @mehereni_dngl_bot

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
ስለ ቻናላችን እና ግሩፓችን የተለያዩ አስተያየት እና ቅሬታ ከላቹ ከ አሁን ሰዓት ጀምሮ እዚው ግሩፕ ላይ ወይም የምትፈሩ ከሆነ 👉 @mehereni_dngl_bot ያናግሩን
እንኳን ለደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የቡሄ መዝሙር በቅርቡ ይለቀቃል ጠብቁን !

@mehereni_dngl
ከርዕስ ውጪ |

የፋሽስቱን ሰራዊት መውጫ መግቢያ ያሳጡት ንጉስ እና ንግስታችን ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ የተወለዱት በዚህች ቀን ነው።

እምዬ ምኒሊክ × ብርሀነ ዘ ኢትዮጵያ 💚💛❤️

የኢትዮጵያ ከፍታዎች !

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
2024/11/15 11:43:48
Back to Top
HTML Embed Code: