Telegram Web Link
“እንደ እባብ ልባሞች ኹኑ”
ማቴ.10÷16

እባብ ራሱን (ጭንቅላቱን) ለማዳን ሲል ሌላው ሰውነቱን ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ኹሉ አንተም እንዲህ አድርግ፡፡ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን ወይም ሰውነትህን ወይም የዚህ ዓለም ሕይወትህን ወይም ያለህን ኹሉ እንኳን መስጠት ካለብህ ይህን በማድረግህ በፍጹም አትዘን! አንተ ሃይማኖትህን ይዘህ ወደ ወዲያኛው ዓለም ስትሔድ እግዚአብሔር ደግሞ ኹሉም ነገር እጅግ ውብ አድርጎ ይመልስልሃል፤ ሰውነትህን በታላቅ ክብር ያስነሣልሃል፤ ከሀብት ከንብረት ይልቅም ከመግለጽ ኃይል በላይ የኾኑ በጎ በጎ ነገሮችን ይሰጥሃል፡፡ ኢዮብ ዕራቁቱን ኾኖ በአመድ ላይ ከሞት እልፍ ጊዜ የሚከፋ ሕይወትን እየመራ የተቀመጠ አይደለምን? ነገር ግን ሃይማኖቱን ስላልጣለ አስቀድሞ የነበረው ኹሉ እጅግ በዝቶ ተመልሶለታል፤ ጤናውና ውብ የኾነ ሰውነቱ፣ ልጆችን፣ ሀብቱን፣ ከዚህ ኹሉ የሚበልጥ ደግሞ አክሊለ ትዕግሥትን አግኝቷል፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

✝️መሐርኒ ድንግል✝️
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
#በበረሃው በሀሩሩ

በመሐርኒ ድንግል

በበረሃው በሀሩሩ
በሚያስፈራው በባህሩ
እስራኤልን የታደገው
በክንፎቹ የጋረደው ሚካኤል ነው
=======================

ሚካኤል ነው አፅናኝ ደጋፊዬ
" " በዱር በበረሃ
" " ነፍሴን ያረካልኝ
" " ከአለቱ ውሃ
የፊቴ ፈገግታ የውስጤ ፍስሐ
ከአምላክ የተሰጠኝ በረከት አምሐ
======================

ሚካኤል ነው መብረቅ ያወረደው
" " ጠላት ድል የነሳው
" " የባህራን ወዳጅ
" " ሀዘኑን ያስረሳው
ቤቱን የሰራለት በእግሮቹ ያቆመው
እንደ እናት እንደ አባት ደግሶ የዳረው

= = = = = = = =
ሚካኤል ነው ክሴን ያስቀደደ
" " የበደሌን እዳ
" " በአማላጅነቱ
" " ያዳነኝ ከፍዳ
በመንገዴ ሁሉ እኔን እየረዳ
ፍቅሩን ጽፎት አልፏል በልቤ ሰሌዳ

መሐርኒ ድንግል
Join & share
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
እግዚኦ ረሰዮ ለውእቱ ሚካኤል እምኲሎሙ መላእክት ይትለአል መንበሩ።

እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ለአመታዊ በዓል በሰላም፣ በጤና እና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን !

ቅዱስ ሚካኤል ሀገራችንን ኢትዮጵያን ይባርካት።

መሐርኒ ድንግል
Join & share
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
Forwarded from ዘ ተዋህዶ
አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ !!!

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።
ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ለተሚማ አረጋግጠዋል።

በሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ፣ ጥር 14 ቀን 1972 ዓ.ም. ከተሾሙት 15 ብፁዓን አባቶች አንዱ የኾኑት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፤ እስከ ዕርግና ዘመናቸው ከቆዩበት ደብረ ብርሃን ቀደም ብሎ፣ በአርሲ እና በመቐለ አህጉረ ስብከት ተመድበው ጉልሕ ሐዋርያዊ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡

በረከታቸዉ ይደርብን
🌹ዘተዋህዶ🌹
💐@tewhodox💐
💐@tewhodox💐
💐ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ 💐
በዚኽ ቻናል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተዘጋጁ መዝሙራት እንዲሁም ሥዕለ ቅዱሳን እና ምርጥ እና የሚመቹ ደስ የሚሉ ፎቶዎች ይለቀቅበታል
ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት ካለ እንዲሁም አንዲለቀቅ የምትፈልጉትን ፎቶዎች እና መዝሙሮችን በዚህ ሊንክ አድርሱን 👉👉👉 @Mtrsetbot👈👈👈
https://www.tg-me.com/mertephoto
ኦርቶዶክሳዊ የወጣቶች ህይወት !

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

👉 @mehereni_dngl

#ማግባትን_ለምትሹ !

👉 @mehereni_dngl

" ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው ? ለምንድነው እግዚአብሔር ጋብቻን የሰጠን ? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው ፤ እንዲህ ያለውን ፦ "ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑሮው ፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት" [ ፩ኛ ቆሮ.፯፥፪ ]

" ከድህነት ይወጣ [ ትወጣ ] ዘንድ " ነው የሚለውን ? ወይስ " ሀብት ለማግኘት ሲባል " ነው የሚለውን ? አይደለም ! ታዲያ ምንድነው የሚለው? ከዝሙት እንጠበቅ ዘንድ ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው ፤ ይኼ ነው የጋብቻ ጥቅሙ፡፡

ስለዚህ ልጆቼ ! እማልዳችኋለሁ ፦ ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡የትዳር አጋርን ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና ነው ፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊ ሀብቱን ተመልከቱ፡፡ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡

አባቶች ሆይ ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት ፦ ሀብትን አላየም ፤ የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም ፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም ፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡

እናቶች ሆይ ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡ እናንተ ማግባትን የምትሹ ወጣቶች ሆይ ! ይስሐቅን ምሰሉት ፦ ዘፈንን ፣ ዳንኪራን ፣ ሳቅና ስላቅን ፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን ፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ ፣ ዝሙት ፣ ቅናት ፣ ጭቅጭቅ ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም ፥ አትነዋወፁም፡፡

እናንተ ልጃገረዶች ሆይ ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር ፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡

የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን ፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም ፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት ፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡"


(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

Join & share
👉 @mehereni_dngl
👉 @mehereni_dngl
👉 @mehereni_dngl
Enter a caption here!
2024/11/15 18:03:57
Back to Top
HTML Embed Code: