Telegram Web Link
✝️✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን✝️✝️✝️

✝️✝️✝️ጥቅምት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት✝️✝️✝️

✝️#ቅዱስ_ይምርሐነ_ክርስቶስ_ንጉሥ✝️

✝️✝️✝️የሰው ልጅ 'ንጉሥ' ተብሎ 'ቅዱስ' መባል ግን ምን ይደንቅ?! ይህ ታላቅ ኢትዮዽያዊ መሪ ንጉሥ ሲሆን: እንደ ደናግል ድንግል: እንደ ባሕታውያን ገዳማዊ: እንደ ቀስውስት ካህን: እንደ ሐዋርያት ሰባኪ ሆኖ መገኘቱ ይደንቃል::

+የሚያሳዝነው ይህንን እንቁ ንጉሣችን ብዙ ኢትዮዽያውያን መዘንጋታችን ብቻ ነው:: የላስታ አካባቢ እጅግ የታደለችና የተቀደሰች ናት:: እንደ ሌሎቹ የሃገራችን ክፍሎች ሁሉ እሷም መካነ ቅዱሳን ናትና::

+ቅዱስ ይምርሐ የዘር ሐረጉ ከዛግዌ ነገሥታት ሥር ሲሆን አባቱ ግርማ ስዩም ይባላል:: ይኸውም በመጀመሪያው ሺህ ዓመት (Millenium) መጠናቀቂያ ላይ ነግሶ የነበረ ነው:: ዣን ስዩም
(የላሊበላ አባት): ጠጠውድም (ንጉሡ) እና ግርማ ስዩም ወንድማማቾች ናቸው::

+ቅዱሱ ሲወለድ አባቱ በሕይወት አልነበረም:: እናቱና የወቅቱ አባቶች "ይምርሐነ ክርስቶስ-ክርስቶስ ይምራን" አሉት:: ገና ከሕጻንነቱ መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና ረቡዕና ዓርብ ቀን እስከ 9 ሰዓት ድረስ የእናቱን ጡት አይቀምስም ነበር:: እናቱ ግን ባለመረዳት ትጨነቅ ነበር::

+የወቅቱ ንጉሥ ጠጠውድም "ከእኔ ቀጥሎ የሚነግሠውን ባወኩት" እያለ ሲመኝ በሕልሙ "ሕጻኑ ይምርሐ ነው" የሚል በማየቱ ሕጻኑን አስመጣው:: ከደም ግባቱ የተነሳም ቅንዓት አድሮበት አማካሪዎቹን "ምን ላድርገው?" አላቸው::

+እነርሱም "ብትገድለው እግዚአብሔር በደሙ ይጠይቅሃል:: ግን እንዳይወርስብህ ከፈለክ እረኛ አድርገው" አሉት:: (የዋሃን! ቅዱስ ዳዊት ከእረኝነት መጠራቱን ዘንግተውታል) ከ7 ቀናት በኋላ ግን መጥተው "ንጉሥ ሆይ! ፈጣሪ ካለ የሚቀር ነገር የለምና በቃ ዝም ብለህ ግደለው" አሉት::

+በዚያች ሰዓት ቅዱስ ሩፋኤል ከሰማይ ወርዶ እናቱን "ይምርሐን ስጭኝ" አላት:: እናት ናትና ጨነቃት:: መልአኩ ግን እንደሚጠብቀው ቃል ገብቶላት ከላስታ ነጥቆ ኢየሩሳሌም አደረሰው::

+ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስም ለዓመታት ተምሮ ዲቁናን ተቀበለ:: በኢየሩሳሌም አካባቢም በጾምና በጸሎት ተወስኖ ፈጣሪውን እያገለገለና ወንጌልን እየሰበከ የወጣትነት እድሜውን ገፋ::

+አንድ ቀን ግን መድኃኒታችን ተገልጦ "ወዳጄ ይምርሐ! ሚስት አግብተሀ: ቅስና ተቀብለህ አገልግለኝ" አለው:: ቅዱሱ ይህንን ሲሰማ አዝኖ "ጌታየ! የእኔስ ፈቃዴ በድንግልና አገለግልህ ዘንድ ነው" አለው:: ጌታችንም "ግዴለህም! ሁሉም አይቀርብህም" ብሎ አንዲት ሕዝባ የምትባል ደግ እሥራኤላዊት ጠቆመው::

+ቅዱስ ይምርሐም ቅድስት ሕዝባን በተክሊል አግብቶ: ቅስናን ተቀበለ:: ግሩም የሚያሰኘው ግን 2ቱ ቅዱሳን ከ40 ዓመታት በላይ በትዳርም: በድንግልናም መኖራቸው ነው:: "ለሚያምን ሁሉ ይቻላል" ይል የለ ቅዱስ መጽሐፍ!

+ቅዱሳኑ ወዲያው ለአገልግሎት ወደ ግብጽ ወረዱ:: በዚያ ለጥቂት ዓመታት እንደቆዩ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ወደ ኢትይዽያ መመለስ ፈለገ:: አንድ ቀን ሕዝቡ ተሰብስበው ጸሎተ ኪዳንን ሲመራ "እግዚአብሔር አብ ወሐቤ ብርሃን-ብርሃንን የምትሰጥ እግዚአብሔር አብ" ከሚል ሲደርስ ወደ ሰማይጮኸ::

+ከሰማይም "አቤት ልጄ ሆይ!" የሚል መልስ መጣለት:: ይምርሐም "ምነው ጌታየ በሰው ሃገር ረሳኸኝ?" ቢለው "አልረሳውህም:: ይልቁኑ ሊገድልህ የሚፈልግህ ንጉሥ ሙቷልና ሒደህ ንገሥ" ሲል አዘዘው::

+ቅዱሱም ሚስቱን ሕዝባን ይዞ ላስታ ሲደርስ ሕዝቡ በዕልልታ ተቀብሎ ወዲያው አነገሠው:: በዚያም ለ15 ዓመታት ቅዱስ ሩፋኤል እየተራዳው: ሕብስትና ጽዋዕ ከሰማይ እየወረደለት ቀድሷል:: ሃገሪቱንም መርቷል::

+አንድ ቀን ግን ክፉ መካሪዎች "ተጨማሪ ሚስት አግባ" ቢሉት ተቆጣቸው:: በኋላ ደግሞ 'ለምን ተቆጣሁ' ብሎ አዘነ:: ስለዚህም ሃሳቡ ሰማያዊው ስጦታ ቀረበት::

+እያለቀሰ ጌታን ቢማጸን ጌታችን "ስላሰብከው ክፉ ሃሳብ (ለምን ተቆጣሁ ማለቱ ወደ ምክራቸው ማዘንበሉን ያሳይነበርና) ይቅር ብየሃለሁ:: ነገር ግን እኔ ወደ ማሳይህ ቦታ ካልሔድክ 2ኛ አይወርድልህም" አለው::

+ቅዱሱ ለጊዜው ትንሽ ቢከራከርም "እሺ" ብሎ በቅዱስ ሩፋኤል መሪነት ዛሬ ወደ ምናውቀው አካባቢው ሔደ:: በዚያም አራዊትን በጸሎቱ አድክሞ: መሠሪዎችን አስተምሮ: ሕዝቡንም አሳምኖ አጠመቃቸው::

+ጌታም ከኢየሩሳሌም በደመና እየጫንክ በዚህ ባሕር ላይ ቤቴን ሥራልኝ" አለው:: ቅዱስ ይምርሐም መስከረም 13 ቀን (በበዓለ ባስልዮስ) ጀምሮ ሰኔ 20 (በበዓለ ሕንጸታ) ፈጸመና ታቦተ ገብርኤልን ሰኔ 21 ቀን ቀደሰው::

+ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ግን በዚያ ቦታ እየቀደሰ ለ25 ዓመታት ሃገሪቱን አስተዳደረ:: አንድ ጊዜ ቅዱስ ሩፋኤል ለንጉሡ ከሰማይ ሕብስትና ጽዋዕ ሲያወርድለት 1 ባሕታዊ አይቶ "ለምን?" ብሎ ተቆጣ:: መልአኩ ግን የንጉሡን ክብር ነግሮ "እየዞርክ ስበክ" ብሎታል::

+በዚያ ባሕታዊ ስብከትም ከመላው ዓለም ብዙ ሺህ ሰወች መጥተው ቅዱስ ይምርሐን "ቀድሰህ አቁርበን?" ብለውለምነውታል:: ቅዱሱም ሲያቆርባቸው በመምሸቱ ጸሐይን አቁሟታል::

+ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ እንዲህ ባለ ጣዕመ ሕይወት ኑሮ: ለ40 ዓመታት ሃገራችንን አስተዳድሮ ጥቅምት 19 ቀን ዐርፎ በዚያው ሥፍራ ተቀብሯል:: ጌታችንም "መታሰቢያህን ያደረገውን: ደጅህን የረገጠውን እምርልሃለሁ" ብሎታል::

✝️#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘጸይለም✝️

✞✞✞ በምድረ ግብጽ በዘመነ ጻድቃን የተነሳው ታላቁ አባ ዮሐንስ "ሐዋርያዊ ጻድቅ" ይባላል:: ወላጆቹ ደጋግ: የተወለደው በጾምና ጸሎት: ያደገውም በሥርዓት ነው:: በወጣትነቱ ከቤተሰቦቹ ጠፍቶ: በርሃ ገብቶ የአባ ስምዖን ደቀ መዝሙር ሆኗል::

+በዚያም በፍጹም ትሕርምት ሲኖር ባልንጀሮቹ ይጠፉበታል:: እነሱን ሊፈልግ ሲሔድ ግን አረማውያን ይዘው አሠሩት: አሰቃዩት:: መንገድ ላይ ውሃ ጠምቷቸው ሲጨነቁ "ውሃ ባጠጣችሁሳ?" አላቸው:: "እንለቅህ ነበር" አሉት::

+ጸልዮ: ውሃ አፍልቆ ቢያጠጣቸው "አንተማ ታስፈልጋለህና አንለቅህም" አሉት:: ወስደውም ጸይለም በምትባል ሃገር ለባርነት ሸጡት:: በዚያ ሲያሰቃዩት ተአምራትን አድርጐ በክርስቶስ አሳምኗቸዋል::

+ወደ ጐረቤት ሃገር ሔዶም ዛፍ ሲያመልኩ አገኛቸው:: "ወደ ክርስቶስ ተመለሱ" አላቸው:: "እንቢ" ሲሉት ምሳር (መጥረቢያ) ይዞ: ወደ ዱሩ ውስጥ ገብቶ ጸለየና ምሳሩን አነሳ::

+"በስመ ሥላሴ እገዝመክሙ" ብሎ ቢቃጣቸው አጋንንት የሠፈሩባቸው 10,000 ዛፎች ባንዴ ወደቁ:: በዚህ ምክንያትም 400,000 ሰዎች አምነው ተጠምቀዋል:: ወደ ሌላ ሃገር ሒዶም ስቃይን ታግሦ: ተአምራትን ሠርቶ ብዙዎችን አሳምኗል:: በቅድስና ኑሮም በዚህች ቀን ዐርፏል::

✝️አምላከ ይምርሐ ደጉን መሪ: አምላከ ዮሐንስ ቸሩን አስተማሪ ያምጣልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

+ጥቅምት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ (ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ዘጸይለም
3.አባ ስምኦን ገዳማዊ
4.ቅዱሳን በርተሎሜዎስና ሚስቱ (ሰማዕታት)
5.አበው ኤዺስ ቆዾሳት (ሳምሳጢን ያወገዙ)
6.ጻድቃን እለ መጥራ

✝️መሐርኒ ድንግል✝️
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl

++"+ አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል::በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል:: የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው::የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም:: በበጐ በረከት ደርሰህለታልና::ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ:: ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም::ለረጅም ዘመን ለዘለዓለሙ:: በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው:: +"+ (መዝ. 20:1-5)

(ወስብሐት ለእግዚአብሔር)

Join @mehereni_dngl
Join @mhereni_dngl
“እንደ እባብ ልባሞች ኹኑ”
ማቴ.10÷16

እባብ ራሱን (ጭንቅላቱን) ለማዳን ሲል ሌላው ሰውነቱን ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ኹሉ አንተም እንዲህ አድርግ፡፡ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን ወይም ሰውነትህን ወይም የዚህ ዓለም ሕይወትህን ወይም ያለህን ኹሉ እንኳን መስጠት ካለብህ ይህን በማድረግህ በፍጹም አትዘን! አንተ ሃይማኖትህን ይዘህ ወደ ወዲያኛው ዓለም ስትሔድ እግዚአብሔር ደግሞ ኹሉም ነገር እጅግ ውብ አድርጎ ይመልስልሃል፤ ሰውነትህን በታላቅ ክብር ያስነሣልሃል፤ ከሀብት ከንብረት ይልቅም ከመግለጽ ኃይል በላይ የኾኑ በጎ በጎ ነገሮችን ይሰጥሃል፡፡ ኢዮብ ዕራቁቱን ኾኖ በአመድ ላይ ከሞት እልፍ ጊዜ የሚከፋ ሕይወትን እየመራ የተቀመጠ አይደለምን? ነገር ግን ሃይማኖቱን ስላልጣለ አስቀድሞ የነበረው ኹሉ እጅግ በዝቶ ተመልሶለታል፤ ጤናውና ውብ የኾነ ሰውነቱ፣ ልጆችን፣ ሀብቱን፣ ከዚህ ኹሉ የሚበልጥ ደግሞ አክሊለ ትዕግሥትን አግኝቷል፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

✝️መሐርኒ ድንግል✝️
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
#በበረሃው በሀሩሩ

በመሐርኒ ድንግል

በበረሃው በሀሩሩ
በሚያስፈራው በባህሩ
እስራኤልን የታደገው
በክንፎቹ የጋረደው ሚካኤል ነው
=======================

ሚካኤል ነው አፅናኝ ደጋፊዬ
" " በዱር በበረሃ
" " ነፍሴን ያረካልኝ
" " ከአለቱ ውሃ
የፊቴ ፈገግታ የውስጤ ፍስሐ
ከአምላክ የተሰጠኝ በረከት አምሐ
======================

ሚካኤል ነው መብረቅ ያወረደው
" " ጠላት ድል የነሳው
" " የባህራን ወዳጅ
" " ሀዘኑን ያስረሳው
ቤቱን የሰራለት በእግሮቹ ያቆመው
እንደ እናት እንደ አባት ደግሶ የዳረው

= = = = = = = =
ሚካኤል ነው ክሴን ያስቀደደ
" " የበደሌን እዳ
" " በአማላጅነቱ
" " ያዳነኝ ከፍዳ
በመንገዴ ሁሉ እኔን እየረዳ
ፍቅሩን ጽፎት አልፏል በልቤ ሰሌዳ

መሐርኒ ድንግል
Join & share
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
እግዚኦ ረሰዮ ለውእቱ ሚካኤል እምኲሎሙ መላእክት ይትለአል መንበሩ።

እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ለአመታዊ በዓል በሰላም፣ በጤና እና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን !

ቅዱስ ሚካኤል ሀገራችንን ኢትዮጵያን ይባርካት።

መሐርኒ ድንግል
Join & share
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
Forwarded from ዘ ተዋህዶ
አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ !!!

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።
ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ለተሚማ አረጋግጠዋል።

በሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ፣ ጥር 14 ቀን 1972 ዓ.ም. ከተሾሙት 15 ብፁዓን አባቶች አንዱ የኾኑት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፤ እስከ ዕርግና ዘመናቸው ከቆዩበት ደብረ ብርሃን ቀደም ብሎ፣ በአርሲ እና በመቐለ አህጉረ ስብከት ተመድበው ጉልሕ ሐዋርያዊ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡

በረከታቸዉ ይደርብን
🌹ዘተዋህዶ🌹
💐@tewhodox💐
💐@tewhodox💐
💐ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ 💐
በዚኽ ቻናል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተዘጋጁ መዝሙራት እንዲሁም ሥዕለ ቅዱሳን እና ምርጥ እና የሚመቹ ደስ የሚሉ ፎቶዎች ይለቀቅበታል
ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት ካለ እንዲሁም አንዲለቀቅ የምትፈልጉትን ፎቶዎች እና መዝሙሮችን በዚህ ሊንክ አድርሱን 👉👉👉 @Mtrsetbot👈👈👈
https://www.tg-me.com/mertephoto
2024/09/27 11:24:58
Back to Top
HTML Embed Code: