Telegram Web Link
✝️✝️✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን✝️✝️✝️
@mehereni_dngl
✝️ጥቅምት ፲፩ (11)✝️
@mehereni_dngl
✝️✝️እንኩዋን ለአባ "ያዕቆብ ስዱድ" እና ለእናታችን "ቅድስት ዺላግያ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ✝️✝️✝️
@mehereni_dngl
✝️#አባ_ያዕቆብ_ስዱድ✝️
@mehereni_dngl
=>"ዻዻስ" ማለት "አባት - መሪ - እረኛ" ማለት ነው::
በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ በሐዲስ ኪዳን
የመንፈሳዊ ስልጣን ደረጃዎች በጥቅሉ 3 ናቸው::
እነሱም ዲቁና: ቅስና: ዽዽስና ሲሆኑ በሥራቸው ወደ 9
ያህል ክፍሎች አላቸው:: ከእነዚህም ከፍተኛው ስልጣን
ዽዽስና ነው::

+ዽዽስና ማለት የክርስቶስን መንጋ እንደ ባለቤቱ
አድርጐ መጠበቅ ማለት ነው:: ሥልጣኑ በምድር
"ሸክም: ዕዳ" ሲሆን በሰማይ ግን "ክብር" ነው::
ማንም በሥጋው ላይ ካልጨከነ በቀር ዽዽስናን
አይመኝም::
@mehereni_dngl
+ቅዱስ ዻውሎስ "ሠናየ ግብረ ፈተወ - ማንም
ዽዽስናን ቢመኝ መልካም ሥራን ተመኘ" (1ጢሞ. 3:1)
ማለቱን ይዞ "ሹሙኝ" ማለት ወደ ማይጠፋ እሳት
የሚያስጥል ከባድ ውሳኔ ነው:: ምክንያቱም አንድ
ክርስቲያን የሚጠየቅ በራሱ ኃጢአት ሲሆን አንድ ካህን
ደግሞ ስለ ልጆቹ ይጠየቃል:: የከፋው ግን የዻዻሱ
ነው::

+አንድ ዻዻስ ቢጾም ቢጸልይም እንኩዋ ለድኅነቱ በቂ
አይደለም:: ምክንያቱም በመንበሩ ላይ ያስቀመጠው
መንጋውን እንጂ ራሱን እንዲያድን አይደለምና:: ጌታ
እንዳለ መልካም እረኛ "ይሜጡ ነፍሶ ቤዛ አባግኢሁ -
መልካሙ እረኛ ስለ በጐቹ ቤዛ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ
ነው::" (ዮሐ. 10) ስለዚህም ክህነት ( ዽዽስና)
ሐዋርያዊ አገልግሎት ከባድም ኃላፊነት ነው::
@mehereni_dngl
✝️አባቶቻችን ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ሐዋርያውያን
ታላላቅ የዽዽስና መንበሮችን መሥርተው: ትምሕርቱን ከነ
ወንበሩ አስተላልፈዋል:: ከእነዚህ መንበረ ዽዽስናዎች
4ቱ የበላይ ናቸው::

እነዚህም የቅዱስ ዼጥሮሱ የሮም: የቅዱስ ዮሐንሱ
የአንጾኪያ: የቅዱስ ማርቆሱ የእስክንድርያና የቅዱስ
ዻውሎሱ የኤፌሶን መናብርት ናቸው::
@mehereni_dngl
✝️እነዚህ መንበሮችም ከክርስቶስ ዕርገት እስከ 443
(451) ዓ/ም: ጉባኤ ኬልቄዶን ድረስ በአንድነት ቆይተው
ተለያይተዋል:: ከእነዚህ መናብርት መካከል
የእስክንድርያው (የግብጹ) እና የአንጾኪያው (የሶርያው)
ዛሬም ድረስ በተዋሕዶ እምነት የጸኑ ናቸው::

✝️የእኛ ቤተ ክርስቲያንም ሐዋርያዊት እንደ መሆኗ
ሐዋርያትን መስለው: ሐዋርያትን አህለው የተነሱ አበው
ዻዻሳትን በየጊዜው በበዓላት ታስባለች: ታከብራለች::
@mehereni_dngl
✝️በተለይ ደግሞ የእስክንድርያና የአንጾኪያ በርካታ
አባቶችን እናከብራለን:: እነርሱ ለቀናች ሃይማኖትና
ለመንጋው ሲሉ ብዙ መከራን በአኮቴት ተቀብለዋልና::
ከእነዚህም መካከል አንዱ አባ ያዕቆብ ሲባሉ በ5ኛው
መቶ ክ/ዘመን አካባቢ የአንጾኪያ መንበር ፓትርያርክ
ነበሩ::

✝️ቅዱሱ በገዳማዊ ሕይወት የተመሠከረላቸው:
በትምሕርት የበሰሉና ለመንጋው የሚራሩ በመሆናቸው
በምዕመናን ይወደዱ ነበር:: ነገር ግን ተረፈ
አርዮሳውያንና መለካውያን ከነገሥታቱ ጋር አብረው ብዙ
አሰቃዩዋቸው:: በመጨረሻም ከመንበራቸው አፈናቅለው
ወደ በርሃ አሳድደዋቸዋል:: ከስደት በሁዋላም አባ
ያዕቆብ በዚህች ቀን ዐርፈዋል::
@mehereni_dngl
✝️#ቅድስት_ዺላግያ_ገዳማዊት✝️
@mehereni_dngl
=>ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚል እግዚአብሔር የኃጥኡን
መመለስ እንጂ ሞቱን አይፈልግም:: በጠፋው በግ
መገኘት ደስ ይለዋል:: በእግርህ ሒድ እንኩዋ
አይለውም:: ይልቁኑ በትከሻው ተሸክሞ ከጐረቤቶቹ ጋር
ደስ ይለዋል እንጂ::

+ቤተ ክርስቲያን ካፈራቻቸው ቅዱሳን አንዳንዶቹ ጭንቅ
ከሆነ የኃጢአት ሕይወት የተመለሱ ናቸው::

ግን ድንቅ በሆነ ንስሃቸው "ቅዱሳን" ከመባል ደርሰዋል::
ከእነዚህም አንዷ ቅድስት ዺላግያ ናት::
@mehereni_dngl
=>ይህቺ ቅድስት እናት በልጅነቷ በመልኩዋ ምክንያት
ስሕተት ያገኛት ናት:: አምላክ የፈጠረውን መልክና ገላ
እንዴት መጠቀም እንዳለብን እየተማርን አይደለምና
በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረውን ገላችን ለዲያብሎስ
ሰጥተነዋል::

+ይህቺ እናትም ችግሯ ይኼው ነበር:: ስለ ገጽታዋና
ገላዋ የነበራት የተሳሳተ አመለካከት መጀመሪያ ወደ
ትውዝፍት (ምንዝር ጌጥ): ቀጥሎም ወደ ዝሙት
ከተታት:: ለዘመናትም የሰይጣን ወጥመድ ሆና ኑራለች::
@mehereni_dngl
✝️ፈጣሪ ግን ለሁላችንም የመዳን ቀን ጥሪ አለውና
እሷንም ጠራት:: ምናልባትም በዘመኗ የብዙ ሰባክያንን
ትምሕርት ሰምታለች:: አንዱም ግን ወደ ልቧ አልገባም::

+ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ያላደረበት አስተማሪ በጥሩ
አማርኛ ልባችን ደስ ያሰኝ ይሆናል እንጂ ሊለውጠን
አይችልም::
@mehereni_dngl
✝️በዘመኑም የሚታየው ትልቁ ችግር ይኼው
ይመስለኛል:: እግዚአብሔር የሾማቸው አባቶቻችን
ተቀምጠው ወጣቶች መድረኩን የሙጥኝ ብለነዋል::

+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ዺላግያ አንድ ቀን
የሰማችው የደጉ ዻዻስ ትምሕርት ግን ፈጽሞ ዘልቆ
ተሰማት:: ተጸጸተች: አለቀሰች:: ወደ ዻዻሱ ሔዳ
"ማረኝ" አለች: ንስሃ ሰጣት:: እርሷም ንብረቷን ሁሉ
መጽውታ በርሃ ገባች::
@mehereni_dngl
✝️አንገቷን ደፍታ በጾምና በጸሎት ሰይጣንን ድል ነሳችው::
ከሃገሯ ሶርያ ወደ ቀራንዮ ደርሳ ተመልሳ ለ30 ዓመታት
ዘጋች:: ተባሕትዎዋን ስትፈጽም በጸጋ እግዚአብሔር
ተአምራትን ሠርታ: ለኃጥአን መንገድ ጧፍ ሆና አብርታ
በዚህች ቀን ዐርፋለች::

=>አምላከ ቅዱሳን የሚያስተውለውን የንስሃ አእምሮን
ያድለን:: ከወዳጆቹ በረከትም አያርቀን::
@mehereni_dngl
=>ጥቅምት 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ቅዱስ አባ ያዕቆብ (ስደተኛው ሊቀ ዻዻሳት)
2.ቅድስት ዺላግያ ገዳማዊት
3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
4.ቅዱስ አርማሚ ሰማዕት
@mehereni_dngl
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ብፁዐን ኢያቄምና ሐና
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
@mehereni_dngl
=>✝️✝️መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና
ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ
ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም
ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም
በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ
'የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ
ይበላችሁ' ይላቸዋል:: እላችሁአለሁ: እንዲሁ ንስሃ
ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ
በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል::✝️✝️
(ሉቃ. 15:3-7)

(ወስብሐት ለእግዚአብሔር)

✝️መሐርኒ ድንግል✝️
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
#ጥቅምት (፲፪) 12/02/2014 ዓ.ም

✝️✝️✝️በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✝️✝️✝️

✝️ዘነግህ✝️
✝️#ምስባክ✝️
መዝ ፹፥፲፱(80፥19)
ወአልዐልኩ ኅሩይየ እምሕዝብየ
ወረከብክዎ ለዳዊት ገብርየ
ወቀባዕክዎ ቅብዐ ቅዱስ


✝️#ወንጌል✝️
ወንጌል ዘማቴዎስ ፲፱፥፩-፲፮(19፥1-16)
ወኮነ እምዘፈጸመ ኢየሱስ…


✝️#ምንባባት_ዘቅዳሴ✝️

✝️#ዲያቆን✝️
✝️ኀበ ጢሞቴዎስ ፩ ም ፭፥፲፱-፳፭(5፥19-25)
በላዕለ ልሒቅ ኢትስማዕ ውዴተ…


✝️#ንፍቅ_ዲያቆን✝️
✝️ይሁዳ ፩፥፱-፲፬(1፥9-14)
ወሚካኤልኒ ሊቀ መላእክት…


✝️#ንፍቅ_ካህን✝️
✝️ግብረሐዋርያት ፲፫፥፳፪-፳፱(13፥22-29)
ወእምድኅሬሁ አንገሠ ሎሙ…



✝️#ምስባክ_ዘቅዳሴ✝️
እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ
ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል
ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን

✝️#ትርጉም✝️
መዝሙረ ዳዊት ም. ፹፬ ቊ. ፮ - ፯

፮ በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወሰነው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና።

፯ ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ፤ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።



✝️#ወንጌል_ዘቅዳሴ✝️
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፱ ቊ. ፱ - ፴፪

፱ ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና። ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው።

፲ በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ እነሆ፥ ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች መጥተው ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብረው ተቀመጡ።

፲፩ ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን። መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል? አሉአቸው።

፲፪ ኢየሱስም ሰምቶ። ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤

፲፫ ነገር ግን ሄዳችሁ። ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና አላቸው።

፲፬ በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት።

፲፭ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።

፲፮ በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።

፲፯ በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።

፲፰ ይህንም ሲነግራቸው፥ አንድ መኰንን መጥቶ። ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች እያለ ሰገደለት።

፲፱ ኢየሱስም ተነሥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተከተለው።

፳ እነሆም፥ ከአሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም የሚፈስሳት ሴት በኋላው ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤

፳፩ በልብዋ። ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ፥ እድናለሁ ትል ነበረችና።

፳፪ ኢየሱስም ዘወር ብሎ አያትና። ልጄ ሆይ፥ አይዞሽ፤ እምነትሽ አድኖሻል አላት። ሴቲቱም ከዚያች ሰዓት ጀምራ ዳነች።

፳፫ ኢየሱስም ወደ መኰንኑ ቤት በደረሰ ጊዜ፥ እምቢልተኞችንና የሚንጫጫውን ሕዝብ አይቶ።

፳፬ ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ፈቀቅ በሉ አላቸው። በጣምም ሳቁበት።

፳፭ ሕዝቡን ግን ከአስወጡ በኋላ ገብቶ እጅዋን ያዛት፥ ብላቴናይቱም ተነሣች።

፳፮ ያም ዝና ወደዚያ አገር ሁሉ ወጣ።

፳፯ ኢየሱስም ከዚያ ሲያልፍ ሁለት ዕውሮች። የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረን ብለው እየጮሁ ተከተሉት።

፳፰ ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፥ ኢየሱስም። ይህን ማድረግ እንድችል ታምናላችሁን? አላቸው። አዎን፥ ጌታ ሆይ አሉት።

፳፱ በዚያን ጊዜ። እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ ብሎ ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ።

፴ ዓይኖቻቸውም ተከፈቱ።

፴፩ ኢየሱስም። ማንም እንዳያውቅ ተጠንቀቁ ብሎ በብርቱ አዘዛቸው። እነርሱ ግን ወጥተው በዚያ አገር ሁሉ ስለ እርሱ አወሩ።

፴፪ እነርሱም ሲወጡ እነሆ፥ ጋኔን ያደረበትን ዲዳ ሰው ወደ እርሱ አመጡ።



#ቅዳሴ ✝️ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ✝️


✝️መሐርኒ ድንግል✝️
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
✝️✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን✝️✝️

✝️ጥቅምት ፲፪ (12)✝️

✝️✝️እንኩዋን ለልበ አምላክ "ቅዱስ ዳዊት":
ለቅዱስ "ማቴዎስ ሐዋርያ" እና ለቅዱስ "ድሜጥሮስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ✝️✝️

✝️#ቅዱስ_ዳዊት_ልበ_አምላክ✝️

=>ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ይላል:-
"እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ:
አይጸጸትም::" (መዝ. 131:11) አሁን በእግዚአብሔር
መጸጸት ኑሮበት አይደለም:: ቅዱስ ዳዊት የማያጸጽት
ፍጹም ወዳጅ መሆኑን ሲገልጥ ነው እንጂ:: ጌታ ቅዱስ
ዳዊትን "እንደ ልቤ የሆነ: ፈቃዴን የሚፈጽም: ባሪያየን
ዳዊትን አገኘሁት" (መዝ. 88:19) ብሎ ሲናገር ሰምተን
እጅግ አደነቅን::

እንደ አምላክ ልብ ሆኖ መገኘት ምን ይረቅ?! ምንስ
ይደንቅ?! ለዚህ አንክሮ ይገባል !! ጌታ ይቀጥልና ደግሞ
"ዳዊትን እንዳልዋሸው አንድ ጊዜ በቅዱስነቴ
ማልሁ" (መዝ. 88:35) ይላል:: *" አቤት አባታችን
ዳዊት!!! . . .
ክብር: የክብር ክብር: ውዳሴና ስግደትም ላንተ በጸጋ ይገባል "* እንላለን::

ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ዳዊት 7 ሃብታት ሲኖሩት:-
1.ሃብተ ትንቢት
2.ሃብተ መንግስት
3.ሃብተ ክህነት
4.ሃብተ በገና (መዝሙር)
5.ሃብተ ፈውስ
6.ሃብተ መዊዕ (ድል መንሳት)
7.ሃብተ ኃይል ተብለው ይታወቃሉ::

በ7ቱ ስሞቹም:-
1.ጻድቅ
2.የዋህ
3.ንጹሕ
4.ብእሴ እግዚአብሔር
5.ነቢየ ጽድቅ
6.መዘምር እና
7.ልበ አምላክ ተብሎ ይጠራል::

ይህች ቀን ለእሥራኤል የነገሠባት ቀን ናት::
እግዚአብሔር ሳዖልን ከናቀው በሁዋላ ከእሴይ ልጆች
መካከል "እንደ ልቤ የሆነውን ቀብተህ አንግስልኝ"
ቢለው በዚህች ቀን ነቢዩ ሳሙኤል ቤተ ልሔም
ገብቷል::

በዚያም ከኤልያብ እስከ አሚናዳብ: 7ቱን የእሴይን
ልጆች ቢፈትን አልሆነም:: በቅዱስ ሚካኤል ጠቁዋሚነት
ግን ከእረኝነቱ ዳዊት ተጠራ::
ገና ከርቀት ሲመጣ የዘይት ቀርኑ ቦግ ብሎ ተከፈተ::

በቅዱስ ዳዊት ራስ ላይም እንደ እሳት ፈላ:: በአምላክ
ምርጫም በ12 ዓመቱ ንጉሥ ተባለ:: የቅዱሱ ዜና ብዙ
ነውና ለታሕሳስ 23 ይቆየን:: በቸር ቢያደርሰን በዚያው
ቀን ከክብሩ እንካፈላለንና::

✝️#ቅዱስ_ማቴዎስ_ሐዋርያ✝️

=>ቅዱሱ በቀዳሚ ስሙ "ሌዊ": በቀዳሚ ግብሩ ደግሞ "ቀራጩ" ይባል ነበር:: ወንጌል እንደሚል ጌታችን የጠራው ከሚቀርጥበት ቦታ ሲሆን (ማቴ. 9:9) ከ12ቱ ሐዋርያት ደምሮ (ማቴ. 10:1) ስሙን "ማቴዎስ" ብሎታል:: ትርጉሙም "ኅሩይ" (ምርጥ) እንደ ማለት ነው::

ጌታችንን በዘመነ ሥጋዌው በፍጹም ምናኔ ከማገልገሉ
ባለፈ ከዋለበት እየዋለ: ካደረበት እያደረ: የእጁን
ተአምራት ተመልክቷል:: የቃሉንም ትምሕርት ሰምቷል::
በጌታ ሕማማት ጊዜ ምንም በፍርሃት ከተበተኑት አንዱ
እሱ ቢሆን አመሻሽ ላይ ወደ ማርቆስ እናት ቤት (ጽርሐ ጽዮን) ሒዶ ወንድሞቹን ሐዋርያትን ተቀላቅሏል::

የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ከሙታን ተነስቶ ትንሳኤውን ሲገልጥም ቅዱስ ማቴዎስ
ነበረ:: ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን
ተምሮ በጌታ ዕርገት ጊዜ ሊቀ ዽዽስናን ተሹሟል::
በ50ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜም ጸጋውንና
71 ልሳናትን ተቀብሎ በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ወንጌልን
ሰብኩዋል::

ሐዋርያት ወንጌልን ለዓለም ለማዳረስ እጣ በተጣጣሉ
ጊዜ ለቅዱስ ማቴዎስ ምድረ ፍልስጥኤም ደረሰችው::
ሃገረ ስብከቱን ካዳረሰ በሁዋላም ወደ ሌሎች ሃገራት
ተጉዞ ሰብኩዋል::

ለምሳሌ በገድለ ሐዋርያት ላይ በኢትዮዽያ: በፋርስና
በባቢሎን አካባቢ ማስተማሩን ይገልጻል:: የሚገርመው
ደግሞ ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆን ነገር ሃገራችን ውስጥ
መኖሩ ነው::

ወደ አክሱምና አካባቢዋ ቅዱሳት መካናትን ለመሳለም
በሔድንበት ወቅት በጻድቃነ ዴጌ/ዶጌ ገዳም ውስጥ
(አክሱም አካባቢ የሚገኝ የ3ሺ ስውራን ቦታ ነው)
የቅዱስ ማቴዎስን በትረ መስቀል መመልከት ችለናል::
አባቶችም ቅዱስ ማቴዎስ በዘመነ ስብከቱ አክሱም
አካባቢ መጥቶ እንደ ነበር ነግረውናል::

ቅዱሱ ሐዋርያ በአይሁድ: በአሕዛብና በአረሚ መካከል
እየተመላለሰ አስተምሮ በርካታ ተአምራትን ሠርቷል::
የጣዖት ካህናትንና ነገሥታትን ጨምሮ እልፍ አእላፍ
ነፍሳትን ወደ ክርስትና መልሷል::

ስለዚህ ፈንታም እጅግ ብዙ መከራዎች
ተፈራርቀውበታል:: ጌታችንም በየጊዜው እየተገለጸ
ያጽናናው ነበር:: በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያውን
ወንጌል በምድረ ፍልስጥኤም ሲጽፍ: ዘመኑም ጌታ ባረገ
በ8ኛው ዓመት (ማለት በ43 ዓ/ም) አካባቢ ነው::

ወንጌሉ 28 ምዕራፎች ሲኖሩት በጌታ የዘር ሐረግ
ጀምሮ የጌታችንን ትምሕርቱንና ተአምራቱን በሰፊው
ያትታል:: በመጨረሻም ከምሴተ ሐሙስ እስከ ትንሳኤ
ድረስ አትቶ ይጠናቀቃል::

ቅዱስ ማቴዎስ ከ12ቱ ሐዋርያት በአንድ ነገሩ
ይለያል:: ከ5ቱ ዓለማት አንዱን (ብሔረ ብጹዓንን)
ያስተምር ዘንድ ተመርጧል:: ዘወትር እሑድ በደመና
እየተነጠቀ ኃጢአት ወደ ሌለበት ዓለም ገብቶ ብጹዓንን
ያስተምር ነበር::
"ሰላም ለማቴዎስ በደመና ሰማይ ዘተነጥቀ:
ኅሩያነ ይርዓይ ዘብሔረ ብጹዓን ደቂቀ::" እንዲል::

በዚያም ዘወትር ጌታችንን ያየው ነበር:: ቅዱስ ማቴዎስ
እንዲህ ከተመላለሰ በሁዋላ በፍጻሜው ለጊዜው
ባልለየናት አንዲት ሃገር ውስጥ አረማውያን አስረው
አሰቃይተውታል:: በዚህች ቀንም ገድለውታል::

✝️#ቅዱስ_ድሜጥሮስ✝️

=>ቅዱስ ድሜጥሮስ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ:
በመንፈሳዊ ለዛ ከአጐቱ ደማስቆስ ጋር ያደገ የዘመኑ
ደግ ሰው ነበር:: በዘመኑ ክርስቲያኖች በሰማዕትነት
ያለቁበት በመሆኑ ቤተሰቦቹ የአጎቱን ልጅ ልዕልተ ወይንን
እንዲያገባ ግድ አሉት::

ቅዱስ ድሜጥሮስ የነርሱን ፈቃድ ለመፈፀም ጋብቻውን
በተክሊል ፈፀመ:: የፈጣሪውን ፈቃድ ለመፈፀም ደግሞ
ከቅድስት እናታችን ልዕልተ ወይን ጋር ተስማምተው ለ48
ዓመታት በአንድ አልጋ ላይ እየተኙ: አንድ ምንጣፍና
ልብስ እየተጋሩ በድንግልና ኑረዋል:: ቅዱስ ሚካኤልም
ስለ ክብራቸው ከመካከላቸው ሆኖ ቀኝ ክንፉን ለርሱ:
ግራ ክንፉን ለርሱዋ ያለብሳቸው ነበር::

ከ48 ዓመታት በሁዋላ ቅ. ድሜጥሮስ የግብፅ 12ኛ
ሊቀ ዻዻስ ሆኖ ተሹሞ ምስጢር በዝቶለት ባሕረ-
ሐሳብን ጽፎ ሠርቷል:: ሰይጣን በሰዎች አድሮ ቅዱሱን
ሚስት አለው በሚል ቤተ ክርስቲያን ላይ ሁከት
በመፈጠሩ ቅዱስ ድሜጥሮስ በመልዐኩ ትእዛዝ ሕዝቡን
ሰብስቦ: እሳት አስነድዶ: ከቅድስት ልዕልተ ወይን ጋር
እሳቱ ውስጥ ገብተው ለረዥም ሰዓት ጸልየዋል::

ሕዝቡም ይሕን ተአምር አይተው: የቅዱሳኑን ንጽሕና
ተረድተው: ማረን ብለው በፍቅር ተለያዩ:: መጋቢት 12
ቀን ድንግልናው ተገልጧል::

ቅዱስ ድሜጥሮስና እናታችን ልዕልተ ወይን ተረፈ
ዘመናቸውን በቅድስና አሳልፈዋል:: በተለይ ሊቀ ዻዻሳቱ
ድሜጥሮስ ብዙ ድርሳናትን ደርሷል:: እነ አርጌንስ
(Origen) ና ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ (Clement of Alexandria) የመሰሉ መናፍቃንንም አውግዟል::

ከጣዕመ ስብከቱም የተነሳ አርጅቶ እንኩዋ ምዕመናን
እየተበሰቡ ይማሩ ነበር:: በአልጋ ተሸክመውም
ይባርካቸው ነበር:: ቅዱሱ በ107 ዓመቱ ያረፈው በ3ኛው
መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ በዚህች ቀን ነው::

=>አምላከ ዳዊት ፍቅሩን አምላከ ማቴዎስ
አገልግሎቱን: አምላከ ድሜጥሮስ ንጽሕናውን
ያሳድርብን:: ጸጋ በረከታቸውን ደግሞ ያትረፍርፍልን::

✝️መሐርኒ ድንግል✝️
join @mehereni_dngl
join @mehereni_dngl
join @mehereni_dngl
=>ጥቅምት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ (የነገሠበት)
2.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቅ
4.ቅድስት ልዕልተ ወይን
5.ቅዱስ ሳሙኤል ነቢይ
6.ጻድቃን ዼጥሮስ ወዻውሎስ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
6.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

=>✝️✝️ከሕዝቤም የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግሁ::
ባሪያየን ዳዊትን አገኘሁት::
ቅዱስ ዘይትም ቀባሁት::
እጄም ትረዳዋለች::
ክንዴም ታጸናዋለች::
ጠላት በእርሱ ላይ አይጠቀምም::
የዓመጻ ልጅም መከራ አይጨምርበትም::
ጠላቶቹን ከፊቱ አጠፋለሁ::
የሚጠሉትንም አዋርዳቸዋለሁ::✝️✝️ (መዝ. 88:20)

(ወስብሐት ለእግዚአብሔር)

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
️#️የስሞች_ትርጉም ✝️✝️

1.እግዚኣብሄር --------=ስላሴ
እግዚእ.....ወልድ & ጌታ
ኣብ.........ኣብ & ኣባት
ሄር.......... መንፈስ ቅዱስ & ቸር
2.ኢየሱስ -----------=መድሃኒት
3.ማርያም---------=ከሁሉ የሚጣፍጥ
እንደ "ማር" በምድር የሚጣፍጥ
እንደ "ያም" በገነት የሚጣፍጥ
የለምና።
4.ሚካኤል----=ማን እንደ እግዚአብሔር
5.ገብርኤል---=ሰው እና ኣምላክ
6.ኣማኑኤል---=እግዚኣብሄር ከኛጋ ሆነ
7.ኣዳም-------=መልከ መልካም
8.ሄዋን--------= የህያዋን ንግስት
9.ዮሃንስ-------=ደስታ (ፍስሃ፣ሃሴት)
10.መዝሙር---=ምስጋና፣ፀሎት
11.ፀሎት----=ፈጣሪና ፍጥረት ማገናኛ
12.ኪሩቤል---=ብርቱዎች (ሃያላን)
13.ሱራፌል---=እሳታውያን
14.እስጢፋኖስ--=ዘውድ፣ከፍታ፣ኣክሊል
15.ዳንኤል-----=እግዚኣብሄር እውነተኛ
ፈራጅ ነው
16.ሳሙኤል-----=እግዚኣብሄር ፀሎቴን
ሰማኝ
17.ጴጥሮስ------=ኣለት
18.መክብብ------=ሰባኪ
19.ኣረጋዊ--------=ኣዋቂ
20.አብርሃም------=የብዙዎች ኣባት
21.ሳራ -------------=የብዙዎች እናት
22.ሙሴ----------=በባህር የተገኘ
23.ሱላማጢስ----=የሰላም መገኛ
24.ዮርዳኖስ---=ህዝብና ኣህዛብ
25.ቅዱስ------=ልዩ፣የተመረጠ
26.ኤልያስ---=እግዚኣብሄር ኣምላክ ነው
27.ሕዝቅኤል--እግዚኣብሄር ብርታት ነው
28.ኢዮሳፍጥ----=እግዚኣብሄር ፈርዷል
29.ሳሙኤል---=የእግዚኣብሄር ስም ነው
30.ክርስቶስ---=መሲህ፣እውነተኛ ንጉስ
31.ኤል----=እግዚኣብሄር (ኃያል ኣምላክ
32.ኣቤል----=የዋህ፣ኣዛኝ
33.ዮናስ-----=የዋህ እንደ እርግብ
34.እስራኤል----=የእግዚአብሔር ህዝብ
35.ዘርኣብሩክ---=የተባረከ ዘር


✝️መሐርኒ ድንግል✝️
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
#ቅዱሳን_ነገሥታት_አብርሃ_ወአጽብሓ
❖ Forward ያድርጉ!
@mehereni_dngl

አባታቸው ታዜር እናታቸው ሶፍያ (አህየዋ) ይባላሉ፡፡ መንትዮች የሆኑት እነዚህ ቅዱሳን የተወለዱት ጌታችን በተወለደባት ዕለት በታኅሣሥ 29 ቀን 312 ዓ.ም ነው፡፡ በታላቁ አባት በአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን እየተማሩ አድገው በእሳቸው እጅ በ330 ዓ.ም መጋቢት 29 ቀን ተጠመቁ፡፡ በእነርሱም ጊዜ አማናዊው ጥምቀትና ቁርባን መጣልን፡፡ በሀገራችን 154 አብያተ ክርስቲያናትን ያሠሩ ሲሆን 44ቱ ፍልፍል ናቸው፡፡ በተለይም ገርዓልታ ያለው ቀመር ዓርባዕቱ እንስሳ ፍልፍል ቤተ መቅደስ በሩ በራሱ ጊዜ ይከፈታል ይዘጋል እንጂ ሰው አይከፍተውም አይዘጋውም፡፡
አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን በአክሱም ሲኖሩ ከሳምንቱ ቀናት ውስጥ ቅዳሜና እሁድ ብቻ የዛፍ ቅጠሎችን ከመመገብ በቀር ሌላ ምግብ ባለመመገብ በታላቅ ተጋድሎ ይኖሩ ነበር፤ አህልም አይቀምሱም፤ በየቀኑም አምስት ሺህ ስግደትን ይሰግዳሉ፡፡ በእርሳቸውም የተጋድሎ ዘመን ደጋግ የሆኑ ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃና አጽብሓ ነገሡ፡፡

ነገሥታቱም ሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃንን እጅግ በጣም ይወዷቸው ነበር፡፡ አባታችንም በእንዲህ ዓይነት ተጋድሎ ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ ለአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ተገልጣላቸው ‹‹ዲቁናና ቅስናን መቀበል ይገባሃል፣ ለጵጵስና ተዘጋጅ፣ እግዚአብሔር ይህችን ከፍ ያለችውን ማዕረግ ሰጥተሃልና የልጄ ወዳጅ ሆይ በጸሎትህና በልመናህ በስብከትህም የኢትዮጵያ ሰዎች ሁሉ ይድናሉ፣ በእጅህ ጥምቀትንና ሥጋ ወደሙን ይቀበላሉ›› አለችው፡፡ ጌታችንም እንዲሁ ተገልጦላቸው ‹‹ወደ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አትናቴዎስ ሄደህ ከፍ ያችውን ማዕረግ ተቀብለህ የኢትዮጵያን ሰዎች አጥምቅልኝ፣ ነቢዩ ዳዊት ስለ እነርሱ ‹ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች› ብሎ ተናግሯልና›› አላቸው፡፡ ነገሥታቱ አብርሃንና አጽብሓ ነገረ ክርስቶስን እያሰቡ ስለ ጥምቀት ልጅነት ይጨነቁ ነበር፡፡ ከሊቀ ካህናቱም ጋር በዚህ ጉዳይ ሲጨዋወቱ ሊቀ ካህናቱ ስለ አቡነ ሰላማ ነገሯቸው፡፡ ነገሥታቱም አቡነ ሰላማን አስጠርተው ስለነገረ ክርስቶስ ምሥጢር እንዲያስረዷቸው ጠየቋቸው፡፡ አባታችንም ‹‹ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ይወለዳል ካሉበት ጀምሮ የልደቱን፣ የትምህርቱን የጥምቀቱን፣ የስቅለቱን፣ የሞቱን፣ የትንሣኤውንና የእርገቱን ነገር ሌላውንም ሁሉ ተንትነው አስተማሯቸው፡፡ ሐዋርያትም በጌታ ተሾመው ዓለምን ዞረው ማስተማራቸውን እንዲሁ ተረኩላቸው፡፡ ነገሥታቱም ይህንን በሰሙ ጊዜ እጅግ ደስ ብሏቸው ፍሬምናጦስን ‹‹ወንድማችን ሆይ! ይህን ሥርዓት በሀገራችን እንድታስፋፋ›› አሏቸው፡፡ አባታችን ግን ‹‹ለዚህ የሚያበቃ ሥልጣን ያለው እንጂ ለእኔ አይቻለኝም›› አሉ፡፡ ነገሥታቱም ‹‹ይህን የሚችል ማነው?›› ብለው ቢጠይቋቸው ‹‹በእስክንድርያ ጳጳሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን የሚሾም አባት አለ አሏቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ነገሥታቱ ወደ እስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቅዱስ አትናቴዎስ ደብዳቤ በመጻፍ ‹‹አባታችንና መምህራችን ሆይ! የምንጠይቅህን እሺ በጀ በለን ይኸውም ወደ ጽድቅ ጉዳና የሚመራንን ጳጳስ ሹምልን›› በማለት ብዙ ወርቅና ብር ገጸ በረከት አስይዘው ከብዙ ሊቃውንት ጋር ፍሬምናጦስን ወደ እስክንድርያ ላኳቸው፡፡

ከዚህም በኋላ አባታችን ከነገሥታቱ አብርሃና አጽብሓ ጋር ተማክረው ወደ እስክንድሪያ ሄደው በቅዱስ አትናቴዎስ እጅ በአገራችን ላይ ሊቀ ጳጳስ ሆነው ታኅሳስ 18 ቀን ተሾሙ፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ ከሾሟቸውና ከመረቋቸው በኋላ ለአቡነ ሰላማና አብረውት ለነበሩ ሊቃውንት መጻሕፍተ ብሉያትን፣ መጻሕፍተ ሐዲሳትንና ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን፣ ታቦተ ማርያምን፣ ታቦተ ሚካኤልንና ታቦተ ገብርኤልን አስይዘው ለነገሥታቱም ደብዳቤ ጽፈው ከብዙ ገጸበረከት ጋር በታላቅ ክብር ሸኟቸው፡፡ ቅዱሳን የሚሆኑ ሁለቱ ነገሥታትም አቡነ ሰላማ ከእስክንድርያ ተሾመው መምጣታቸውን በሰሙ ጊዜ ‹‹የኢትዮጵያ ሰዎች ሁላችሁ እስከ 40 ቀን ተሰብሰቡ›› ብለው አዋጅ አስነገሩ፡፡ አባታችንንም በደብረ ሲናም ሄደው አገኟቸውና ከዚያች ቀን ጀምሮ ሕዝቡም ሁሉ እስከ 40 ቀን ድረስ ተጠመቁ፡፡ በዚያችም ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚያች በደብረ ሲና አገር ላይ ወረደና ሕዝቡን ሁሉ ባረኮ ተመልሶ ሲያርግ ከአባ ሰላማ በቀር ያየው አልነበረም፡፡ ወደ አክሱምም ሄደው ቅዱሳን ነገሥታቱም የአድባራት ሁሉ የበላይ የምትሆን የቅድስት ጽዮንን ቤተ ክርስቲያን በወርቅና በዕንቊ ሠሯትና አባ ሰላማ ባርከው ቀደሷት፡፡ ታቦተ ጽዮንም ከድንኳን ወጥታ ማንም ካህን ሳይሸከማት አብርሃና አጽብሓ ወዳሠሩላት ቤተ መቅደስ ራሷ በመንፈስ ቅዱስ ገብታ ተገኘች፡፡
አባታችን በእመቤታችንም በዓለ ዕረፍት ጥር 21 ቀን በውስጧ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀድሱ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በግራ በቀኝ እየተራዷቸው እርሳቸውም ከምድር ሦስት ክንድ ከፍ ብለው ሥርዓተ ቅዳሴውን ፈጽመው ለነገሥታቱና ለሕዝቡም ሁሉ አቆረቧቸው፡፡ የዚያን ዕለትም እጅግ ታላቅ በዓልን አደረጉ፡፡ እነዚህም ቅዱሳን ነገሥታት ትምህርተ ወንጌልን እየሰጡ በአክሱም ቤተ መንግሥታቸው ሳሉ ከዕለታት አንደኛው ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ በአክሱም ‹‹ማይ ኰኩሐ›› በሚባል ተራራ ላይ ቁሞ አብርሃ ወአጽብሓን ጠርቶ ‹‹በዚህች ቦታ ላይ ቤተ መቅደሴን አንጹልኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም ቦታው ባህር ላይ ነው በየት እናንጽልህ?›› አሉት፡፡ ጌታችንም በጥበቡ ከገነት ጥቂት አፈር አምጥቶ በባሕሩ ላይ ቢበትንበት ባሕሩ ደርቆ ሜዳ ሆነ፡፡ በዚህ ጊዜ ጌታችን ‹‹ቤተ መቅደሴን በዚህ ሥሩ›› ብሏቸው ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ጌታችንም በቆመባት ዓለት ላይ የእግሩ ጫማ ቅርጽ እስከ አሁን ሳይጠፋ በግልጽ ይታያል፡፡ ቦታውም ከዚያ ወዲህ ‹‹መከየደ እግዚእ›› እየተባለ ይጠራል፡፡

በመሐርኒ ድንግል ብቻ ይከታተሉን በቴሌግራም
አብርሃ ወአጽብሓ ከመንግሥት አስተዳደሩ ጋር ክርስትናንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በመላ ኢትዮጵያ በማዳረስ እጅግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርገዋል፡፡ ካህናትንና ዲያቆናትን ይዘው በመላ ኢትዮጵያ ሐዋርያዊ ጉዞ በማድረግ ሕዝቡን ሁሉ እያስተማሩ፣ ሃይማኖትን እያጸኑ፣ ሥርዓተ ጥምቀትን እያስፋፉ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል፡፡ በሀገራችን በአራቱም አቅጣጫ ወንጌልን አስፋፍው ሕግ ሠርተዋል፡፡ የከበሩ ቅዱሳን ነገሥት አብርሃ ወአጽብሓ በእንዲህ ዓይነት ግብር ጸንተው በመኖር እግዚአብሔርንም ሰውንም አገልግለው ለሀገራችንም ብርሃን አብርተውላት ነው ያለፉት፡፡ ታላቁ አብርሃ በ364 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን እሁድ ዕለት ዐረፉ፡፡ ከ15 ዓመት በኋላ ታናሹ አጽብሓ በ379 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን ዐረፉ፡፡ ልደታቸውም ሆነ ሞታቸው አንድ ቀን ነው-የዕረፍታቸው ዓመቱ ይለያይ እንጂ፡፡ የተቀበሩበት ቦታም አንድ ነው፡፡ የንግሥና ስማቸው ኢዛናና ዛይዛና ይባላል። የቅዱሳን ነገሥታት የአብርሃ ወአጽብሃ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
@mehereni_dngl

✥✞✥ ጽሑፉን ሌሎች እንዲያነቡትም Forward ፤ በዚህ መንፈሳዊ ቻናሉን Join / Follow ሌሎችንም ወደ ግሩፓችን ይጋብዙ።

👇 በቴሌግራም ወዳጅ እንሁን? 👇
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
ማንኛውንም ጥያቄ ወይሞ አስተያየት ካለ
👉 @mehereni_dngl_bot
👉 @mehereni_dngl_bot
👉 @mehereni_dngl_bot

ወይንም በውስጥ መስመር

👉 @nebaaye
👉 @nebaaye
👉 @nebaaye

channel
👉 @mehereni_dngl
👉 @mehereni_dngl
👉 @mehereni_dngl

Group
👉 @mehereni_dngl_21
👉 @mehereni_dngl_21
👉 @mehereni_dngl_21
#ጥቅምት (፲፰) 18/02/2014 ዓ.ም

✝️✝️✝️በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✝️✝️✝️

✝️ዘነግህ✝️
✝️#ምስባክ✝️
መዝ ፺፬፥፱(94፥9)
ዘአመከሩኒ አበዊክሙ
ፈተኑኒ ወርእዩ ምግባርየ
አርብዓ ዓመመተ ተቈጣዕክዋ ለይእቲ ትውልድ


✝️#ወንጌል✝️
ወንጌል ዘማርቆስ ፲፪፥፲፫-፲፱(12፥13-19)
ወፈነዉ ኀቤሁ እምፈሪሳውያን…


✝️#ምንባባት_ዘቅዳሴ✝️

✝️#ዲያቆን✝️
✝️ኀበ ቲቶ ፩፥፯-፲፪(1፥7-12)
ወርቱዕሰ ይሠየም ጳጳስ…


✝️#ንፍቅ_ዲያቆን✝️
✝️ጴጥሮስ ፩ ም ፩፥፮-፲(1፥6-10)
ወባሕቱ ኅዳጠ ይእዜ…


✝️#ንፍቅ_ካህን✝️
✝️ግብረሐዋርያት ፳፥፴-፴፰(20፥30-38)
ወይእዜኒ ትግሁ ወተዘከሩ…


✝️#ምስባክ_ዘቅዳሴ✝️
ወይረውዩ እምጠለ ቤትከ
ወትሠቅዮሙ እምፈለገ ትፍሥሕትከ
እስመ ኀቤከ ነቅዐ ሕይወት

✝️#ትርጉም✝️
መዝሙረ ዳዊት ም. ፴፮ ቊ. ፰ - ፱

፰ ከቤትህ ጠል ይጠጣሉ፥ ከተድላም ፈሳሽ ታጠጣቸዋለህ::

፱ የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን::


✝️#ወንጌል_ዘቅዳሴ✝️
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፳፪ ቊ. ፲፭- ፳፪

፲፭ ስለዚህ ፈሪሳውያን ሄዱና እንዴት አድርገው በነገር እንዲያጠምዱት ተማከሩ::

፲፮ ደቀ መዛሙርታቸውንም ከሄሮድስ ወገን ጋር ላኩበት፥ እነርሱም። መምህር ሆይ፥ እውነተኛ እንደ ሆንህ በእውነትም የእግዚአብሔርን መንገድ እንድታስተምር እናውቃለን፥ ለማንምም አታደላም፥ የሰውን ፊት አትመለከትምና፤

፲፯ እንግዲህ ምን ይመስልሃል? ንገረን ለቄሣር ግብር መስጠት ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም? አሉት::

፲፰ ኢየሱስም ክፋታቸውን አውቆ። እናንተ ግብዞች፥ ስለ ምን ትፈትኑኛላችሁ?

፲፱ የግብሩን ብር አሳዩኝ አለ:: እነርሱም ዲናር አመጡለት::

፳ እርሱም። ይህች መልክ ጽሕፈቲቱስ የማን ናት? አላቸው::

፳፩ የቄሣር ነው አሉት። በዚያን ጊዜ። እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ አላቸው::

፳፪ ይህንም ሰምተው ተደነቁ፥ ትተውትም ሄዱ::


#ቅዳሴ ✝️ዘባስልዮስ (እግዚኦ መሐረነ)✝️

✝️መሐርኒ ድንግል✝️
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
✝️✝️✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን✝️✝️✝️

✝️✝️✝️ጥቅምት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት✝️✝️✝️

#️ቅዱስ_ቴዎፍሎስ_ሊቅ✝️

✝️✝️✝️በምድረ ግብጽ ከተነሱና ለቤተ ክርስቲያን አብዝተው ከደከሙ አባቶች አንዱ አባ ቴዎፍሎስ ነው:: የተወለደው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ሲሆን ቴዎፍሎስ (ታኦፊላ) በመባል ይታወቃል:: ገና ልጅ እያለ ቴዎዶስዮስ ከሚባል ባልንጀራው ጋ በተመሳሳይ ሌሊት ተመሳሳይ ሕልምን ያያሉ::

+2ቱ ሕጻናት ያዩት እንጨት ሲለቅሙ ነበር:: ሕልምን የሚተረጉመው ሰውም ቴዎዶስዮስን "ትነግሣለህ" ሲለው ቴዎፍሎስን "ፓትርያርክ ትሆናለህ" አለው:: ለጊዜው አልመሰላቸውም::

+ከዚያም ወደ ት/ቤት ገብተው: መጻሕፍትን ተምረው ቴዎዶስዮስ ወደ ንጉሡ ከተማ ቁስጥንጥንያ ሲሕድ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ግን የታላቁ ሊቅ አባ አትናቴዎስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: በዚያም ከቅዱሱ እየተማረ: እያገለገለ ዘመናት አለፉ::

+ቅዱስ አትናቴዎስ ካረፈ በኋላም ለ2 ፓትርያርኮች ረዳት ሆኖ ተመርጧል:: በመጨረሻ ግን ሕልም ተርጉዋሚው ያለው አልቀረምና ቴዎዶስዮስ 'ታላቁ' ተብሎ በቁስጥንጥንያ ላይ ሲነገሥ ቅዱስ ቴዎፍሎስም ፓትርያርክ (ሊቀ ዻዻሳት) ተብሎ በመንበረ ማርቆስ ላይ ተቀመጠ::

+በ384 ዓ/ም የእስክንድርያ 23ኛው ሊቀ ዻዻሳት ከሆነ በኋላ የመጀመሪያ ሥራው በዘመኑ ገነው የነበሩ መናፍቃንን መዋጋት ነበር:: ለዚህም ይረዳው ዘንድ የእህቱ ልጅ የሆነውን ቅዱስ ቄርሎስን ወስዶ አስተማረው:: 2ቱ አባቶች እየተጋገዙም ቤተ ክርስቲያንን ከአራዊት (መናፍቃን) ጠበቁ:: ዛሬ በሃይማኖተ አበው የምናውቀውን ጨምሮ ቅዱሱ በርካታ ድርሰቶችንም ደረሰ::

+ቅዱስ ቴዎፍሎስን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል ጥቂቶቹን እንመልከት:-

1.ቅዱሱ በዘመኑ ከመንበረ ዽዽስናው በር ቁጭ ብሎ ይተክዝ ነበርና አንዲት ባለ ጸጋ ሴት መጥታ "አባቴ! ምን ያስተክዝሃል?" ስትል ጠየቀችው::

+ሊቁም "ልጄ! እዚህ የቆምንበት ቦታ ውስጥ ወርቅ ተቀብሮ ሳለ ነዳያን ጦማቸውን ያድራሉ:: አባቴ አትናቴዎስ እንዳዘነ አለፈ:: እኔም ያው ማለፌ ነው" አላት:: ባዕለ ጸጋዋም "አባ አንተ ጸሎት: እኔ ጉልበትና ሃብት ሁነን እናውጣው" አለችው::

+"እሺ" ብሏት ሱባኤ ገባና ከመሬት በታች 3 ጋን ሙሉ ወርቅ ተገኝቶ ደስ አላቸው:: ግን በላያቸው ላይ ተመሣሣይ "ቴዳ: ቴዳ: ቴዳ" የሚል ጽሑፍ ነበረውና ማን ይፍታው:: በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ወደ እመቤታችን አመልክቶ ምሥጢር ተገለጠለትና ሲተረጉመው ማሕተሞቹ ተፈቱ::

+ሲተረጐምም ቴዳ 1 "ክርስቶስ" ማለት ሆነ:: ይሔም ለነዳያን ተበተነ:: ቴዳ 2 "ቴዎፍሎስ" ማለት ሆነ:: አብያተ ክርስቲያናት ታነጹበት:: ቴዳ 3 ደግሞ "ቴዎዶስዮስ" ሆነ:: 'የቄሣርን ለቄሣር' እንዲል 3ኛው ጋን የአቡነ ኪሮስ ወንድምና የገብረ ክርስቶስ መርዓዊ አባት ለሆነው ለደጉ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ተላከለት::

+ንጉሡ ግን ከወርቁ ጥቂት ለበረከት ወስዶ ለአባ ቴዎፍሎስ መለሰለት:: አብያተ ጣዖቶችን እያፈረሰ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲያንጽም ስልጣን ሰጠው:: ቅዱስ ቴዎፍሎስም በዚህ ገንዘብ በመቶ የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናትን እንዳነጸበት ይነገራል::

+በተለይ ደግሞ የቅዱስ ሩፋኤልን ቤት በአሣ አንበሪ ጀርባ ላይ ያነጸው እርሱ ነው:: (ድርሳነ ሩፋኤል) የድንግል ማርያምን ሲያንጽም እመቤታችን ተገልጣለታለች::

+የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቁን አጽም አፍልሦ ከነቢዩ ኤልሳዕ ጋር ቤቱን ሲቀድስለትም ተአምራት ተደርገዋል:: የሠለስቱ ደቂቅን ቤተ ክርስቲያን አንጾ የቀደሰ ጊዜ ደግሞ ቅዱሳኑ ከሰማይ ወርደውለታል::

2.ቅዱስ ቴዎፍሎስ እመቤታችንን ይወዳት ነበርና ለ8 ጊዜ ያህል ተገልጣ አነጋግራዋለች:: "ደፋሩ አርበኛ" ስትል ጠርታ: ሙሉ ዜና ስደቷንና ሕይወቷን አጽፋዋለች:: (ተአምረ ማርይም)
3.ሕጻናትን ሲያጠምቅም ከብቃት የተነሳ የብርሃን መስቀል ይወርድለት ነበር:: ቅዱስ ቴዎፍሎስ በሊቀ ዽዽስና በቆየባቸው 28 ዓመታት እንዲህ ተመላልሶ በ412 ዓ/ም ዐርፎ ቅዱስ ቄርሎስ በመንበሩ ተተክቷል:: ነገር ግን አንዳንድ የዘመናችን 'ጸሐፊ ነን ባዮች' የመናፍቃንን መጻሕፍት እየገለበጡ ቅዱሱን ይሳደባሉና ብንጠነቀቅ እመክራለሁ::

✝️#ቅዱስ_ሮማኖስ_ሰማዕት✝️

✝️✝️✝️ይህ ቅዱስ ሰማዕት ብዙ ጊዜ "ኃያሉ" እየተባለ ነው የሚጠራው:: በዘመነ ሰማዕታት ከራሱ አልፎ ብዙ ክርስቲያኖችን በድፍረት ያጸናቸው ነበር:: በወቅቱ በምድረ ግብጽ መከራው እጅግ ስለ በዛ ብዙዎቹ አልቀው: እኩሉም ተሰደው: አንዳንዶቹ ደግሞ መካዳቸውን ሲሰማ ቅዱሱ ለጸሎት ከተወሰነበት ቦታ ወጥቶ: ሕዝቡን ሰብስቦ መከራቸው::

+"ወገኖቼ! ልቡናችንን በክርስቶስ ፍቅር ካጸናነው ሞት ቀላልና አስደሳች ነገር ነው" ብሎም አበረታታቸው:: ይህን የሰማ መኮንኑ ግን ተቆጥቶ አስጠራው:: በዓየር ላይ ዘቅዝቆም ኢ-ሰብአዊ በሆነ ጭካኔ ደሙ እስኪንጠፈጠፍ ድረስ አሰቃየው::

+ይህ ሁሉ እየሆነበት ቅዱስ ሮማኖስ ልቡ በአምላኩ ፍቅር ተመስጦ ነበርና አንዳች አልመለሰም:: መኮንኑ ግን ገርሞት "እንዴት ይህ ሁሉ እየሆነብህ ዝም አልክ?" ቢለው የ3 ዓመት ሕጻን ጥራና ስለ እውነተኛው አምላክ ጠይቀው" አለው::

+አንድ ሕጻን አስመጥቶ በአደባባይ ጠየቀው:: ሕጻኑም መለሰና "አዕምሮ የጐደለህ መኮንን ሆይ! አስተውል:: ከክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ሲል ገሰጸው:: መኮንኑ በቁጣ ሕጻኑን በዓየር ላይ አሰቅሎ አስገረፈው:: ሕጻኑ ሕጻኑ ደሙ ሲፈስ እናቱን "ውሃ አጠጪኝ?" አላት:: እርሷ ግን "ልጄ! እኔ ውሃ የለኝም:: ወደ ሕይወት ውሃ ክርስቶስ ሒድ" አለችው::

+በዚያን ጊዜ መኮንኑ የሕጻኑን ራስና የቅዱስ ሮማኖስን ምላስ አስቆረጠ:: ቅዱሱ ግን መንፈሳዊ ልሳን ተሰጥቶት ፈጣሪውን አመሰገነው:: የሚያደርገውን ያጣው መኮንኑም በዚህ ዕለት ቅዱሱን ገድሎታል::

✝️✝️✝️አምላከ ቅዱሳን ጸጋውን ክብሩን አይንሳን:: የአባቶቻችንንም በረከት ያብዛልን::

+ጥቅምት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሊቅ
2.ቅዱስ ሮማኖስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ዮሐንስ ሰማዕት
4.ቅድስት አስማኒትና 7ቱ ልጆቿ

++"+ ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን: ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን:: ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን:: +"+ (ሮሜ. 6:5)

(ወስብሐት ለእግዚአብሔር)

✝️መሐርኒ_ድንግል✝️
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
#ጥቅምት (፲፱) 19/02/2014 ዓ.ም

✝️✝️✝️በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✝️✝️✝️

✝️ዘነግህ✝️
✝️#ምስባክ✝️
መዝ ፸፬፥፬(74፥4)
ወእለሂ ይኤብሱ ኢያንሥኡ ቀርኖሙ
ወኢያንሥኡ ቀርኖሙ ውስተ አርያም
ወኢይንብቡ ዓመፃ ላዕለ እግዚአብሔር


✝️#ወንጌል✝️
ወንጌል ዘማቴዎስ ፲፥፴፪-፵፪(10፥32-42)
ኵሉ ዘየአምን ብየ በቅድመ ሰብእ…


✝️#ምንባባት_ዘቅዳሴ✝️

✝️#ዲያቆን✝️
✝️ኀበ ቲቶ ፫፥፰-፲፪(3፥8-12)
እሙን ነገር…


✝️#ንፍቅ_ዲያቆን✝️
✝️ዮሐንስ ፩ ም ፪፥፳፪-፳፱(2፥22-29)
ወመኑ ውእቱ ሐሳዊ…


✝️#ንፍቅ_ካህን✝️
✝️ግብረሐዋርያት ፳፥፳፰-፴፩(20፥28-31)
ወይእዜኒ ዕቀቡ ርእሰክሙ…

✝️#ምስባክ_ዘቅዳሴ✝️
ወሶበሂ ይትዋቀሥ ይፃእ ተመዊዖ
ወጸሎቱሂ ትኩኖ ጌጋየ
ወይኩና መዋዕሊሁ ኅዳጠ

✝️#ትርጉም✝️
መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፱ ቊ. ፯ - ፰

፯ በተምዋገተም ጊዜ ተረትቶ ይውጣ፤ ጸሎቱም ኃጢአት ትሁንበት።

፰ ዘመኖቹም ጥቂት ይሁኑ፤ ሹመቱንም ሌላ ይውሰድ።


✝️#ወንጌል_ዘቅዳሴ✝️
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፰ ቊ. ፲፭ - ፳፩

፲፭ ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤

፲፮ ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤

፲፯ እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።

፲፰ እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።

፲፱ ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል።

፳ ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።

፳፩ በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን? አለው።

✝️#ቅዳሴ ✝️ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)✝️

✝️መሐርኒ ድንግል✝️
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
✝️✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን✝️✝️✝️

✝️✝️✝️ጥቅምት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት✝️✝️✝️

✝️#ቅዱስ_ይምርሐነ_ክርስቶስ_ንጉሥ✝️

✝️✝️✝️የሰው ልጅ 'ንጉሥ' ተብሎ 'ቅዱስ' መባል ግን ምን ይደንቅ?! ይህ ታላቅ ኢትዮዽያዊ መሪ ንጉሥ ሲሆን: እንደ ደናግል ድንግል: እንደ ባሕታውያን ገዳማዊ: እንደ ቀስውስት ካህን: እንደ ሐዋርያት ሰባኪ ሆኖ መገኘቱ ይደንቃል::

+የሚያሳዝነው ይህንን እንቁ ንጉሣችን ብዙ ኢትዮዽያውያን መዘንጋታችን ብቻ ነው:: የላስታ አካባቢ እጅግ የታደለችና የተቀደሰች ናት:: እንደ ሌሎቹ የሃገራችን ክፍሎች ሁሉ እሷም መካነ ቅዱሳን ናትና::

+ቅዱስ ይምርሐ የዘር ሐረጉ ከዛግዌ ነገሥታት ሥር ሲሆን አባቱ ግርማ ስዩም ይባላል:: ይኸውም በመጀመሪያው ሺህ ዓመት (Millenium) መጠናቀቂያ ላይ ነግሶ የነበረ ነው:: ዣን ስዩም
(የላሊበላ አባት): ጠጠውድም (ንጉሡ) እና ግርማ ስዩም ወንድማማቾች ናቸው::

+ቅዱሱ ሲወለድ አባቱ በሕይወት አልነበረም:: እናቱና የወቅቱ አባቶች "ይምርሐነ ክርስቶስ-ክርስቶስ ይምራን" አሉት:: ገና ከሕጻንነቱ መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና ረቡዕና ዓርብ ቀን እስከ 9 ሰዓት ድረስ የእናቱን ጡት አይቀምስም ነበር:: እናቱ ግን ባለመረዳት ትጨነቅ ነበር::

+የወቅቱ ንጉሥ ጠጠውድም "ከእኔ ቀጥሎ የሚነግሠውን ባወኩት" እያለ ሲመኝ በሕልሙ "ሕጻኑ ይምርሐ ነው" የሚል በማየቱ ሕጻኑን አስመጣው:: ከደም ግባቱ የተነሳም ቅንዓት አድሮበት አማካሪዎቹን "ምን ላድርገው?" አላቸው::

+እነርሱም "ብትገድለው እግዚአብሔር በደሙ ይጠይቅሃል:: ግን እንዳይወርስብህ ከፈለክ እረኛ አድርገው" አሉት:: (የዋሃን! ቅዱስ ዳዊት ከእረኝነት መጠራቱን ዘንግተውታል) ከ7 ቀናት በኋላ ግን መጥተው "ንጉሥ ሆይ! ፈጣሪ ካለ የሚቀር ነገር የለምና በቃ ዝም ብለህ ግደለው" አሉት::

+በዚያች ሰዓት ቅዱስ ሩፋኤል ከሰማይ ወርዶ እናቱን "ይምርሐን ስጭኝ" አላት:: እናት ናትና ጨነቃት:: መልአኩ ግን እንደሚጠብቀው ቃል ገብቶላት ከላስታ ነጥቆ ኢየሩሳሌም አደረሰው::

+ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስም ለዓመታት ተምሮ ዲቁናን ተቀበለ:: በኢየሩሳሌም አካባቢም በጾምና በጸሎት ተወስኖ ፈጣሪውን እያገለገለና ወንጌልን እየሰበከ የወጣትነት እድሜውን ገፋ::

+አንድ ቀን ግን መድኃኒታችን ተገልጦ "ወዳጄ ይምርሐ! ሚስት አግብተሀ: ቅስና ተቀብለህ አገልግለኝ" አለው:: ቅዱሱ ይህንን ሲሰማ አዝኖ "ጌታየ! የእኔስ ፈቃዴ በድንግልና አገለግልህ ዘንድ ነው" አለው:: ጌታችንም "ግዴለህም! ሁሉም አይቀርብህም" ብሎ አንዲት ሕዝባ የምትባል ደግ እሥራኤላዊት ጠቆመው::

+ቅዱስ ይምርሐም ቅድስት ሕዝባን በተክሊል አግብቶ: ቅስናን ተቀበለ:: ግሩም የሚያሰኘው ግን 2ቱ ቅዱሳን ከ40 ዓመታት በላይ በትዳርም: በድንግልናም መኖራቸው ነው:: "ለሚያምን ሁሉ ይቻላል" ይል የለ ቅዱስ መጽሐፍ!

+ቅዱሳኑ ወዲያው ለአገልግሎት ወደ ግብጽ ወረዱ:: በዚያ ለጥቂት ዓመታት እንደቆዩ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ወደ ኢትይዽያ መመለስ ፈለገ:: አንድ ቀን ሕዝቡ ተሰብስበው ጸሎተ ኪዳንን ሲመራ "እግዚአብሔር አብ ወሐቤ ብርሃን-ብርሃንን የምትሰጥ እግዚአብሔር አብ" ከሚል ሲደርስ ወደ ሰማይጮኸ::

+ከሰማይም "አቤት ልጄ ሆይ!" የሚል መልስ መጣለት:: ይምርሐም "ምነው ጌታየ በሰው ሃገር ረሳኸኝ?" ቢለው "አልረሳውህም:: ይልቁኑ ሊገድልህ የሚፈልግህ ንጉሥ ሙቷልና ሒደህ ንገሥ" ሲል አዘዘው::

+ቅዱሱም ሚስቱን ሕዝባን ይዞ ላስታ ሲደርስ ሕዝቡ በዕልልታ ተቀብሎ ወዲያው አነገሠው:: በዚያም ለ15 ዓመታት ቅዱስ ሩፋኤል እየተራዳው: ሕብስትና ጽዋዕ ከሰማይ እየወረደለት ቀድሷል:: ሃገሪቱንም መርቷል::

+አንድ ቀን ግን ክፉ መካሪዎች "ተጨማሪ ሚስት አግባ" ቢሉት ተቆጣቸው:: በኋላ ደግሞ 'ለምን ተቆጣሁ' ብሎ አዘነ:: ስለዚህም ሃሳቡ ሰማያዊው ስጦታ ቀረበት::

+እያለቀሰ ጌታን ቢማጸን ጌታችን "ስላሰብከው ክፉ ሃሳብ (ለምን ተቆጣሁ ማለቱ ወደ ምክራቸው ማዘንበሉን ያሳይነበርና) ይቅር ብየሃለሁ:: ነገር ግን እኔ ወደ ማሳይህ ቦታ ካልሔድክ 2ኛ አይወርድልህም" አለው::

+ቅዱሱ ለጊዜው ትንሽ ቢከራከርም "እሺ" ብሎ በቅዱስ ሩፋኤል መሪነት ዛሬ ወደ ምናውቀው አካባቢው ሔደ:: በዚያም አራዊትን በጸሎቱ አድክሞ: መሠሪዎችን አስተምሮ: ሕዝቡንም አሳምኖ አጠመቃቸው::

+ጌታም ከኢየሩሳሌም በደመና እየጫንክ በዚህ ባሕር ላይ ቤቴን ሥራልኝ" አለው:: ቅዱስ ይምርሐም መስከረም 13 ቀን (በበዓለ ባስልዮስ) ጀምሮ ሰኔ 20 (በበዓለ ሕንጸታ) ፈጸመና ታቦተ ገብርኤልን ሰኔ 21 ቀን ቀደሰው::

+ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ግን በዚያ ቦታ እየቀደሰ ለ25 ዓመታት ሃገሪቱን አስተዳደረ:: አንድ ጊዜ ቅዱስ ሩፋኤል ለንጉሡ ከሰማይ ሕብስትና ጽዋዕ ሲያወርድለት 1 ባሕታዊ አይቶ "ለምን?" ብሎ ተቆጣ:: መልአኩ ግን የንጉሡን ክብር ነግሮ "እየዞርክ ስበክ" ብሎታል::

+በዚያ ባሕታዊ ስብከትም ከመላው ዓለም ብዙ ሺህ ሰወች መጥተው ቅዱስ ይምርሐን "ቀድሰህ አቁርበን?" ብለውለምነውታል:: ቅዱሱም ሲያቆርባቸው በመምሸቱ ጸሐይን አቁሟታል::

+ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ እንዲህ ባለ ጣዕመ ሕይወት ኑሮ: ለ40 ዓመታት ሃገራችንን አስተዳድሮ ጥቅምት 19 ቀን ዐርፎ በዚያው ሥፍራ ተቀብሯል:: ጌታችንም "መታሰቢያህን ያደረገውን: ደጅህን የረገጠውን እምርልሃለሁ" ብሎታል::

✝️#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘጸይለም✝️

✞✞✞ በምድረ ግብጽ በዘመነ ጻድቃን የተነሳው ታላቁ አባ ዮሐንስ "ሐዋርያዊ ጻድቅ" ይባላል:: ወላጆቹ ደጋግ: የተወለደው በጾምና ጸሎት: ያደገውም በሥርዓት ነው:: በወጣትነቱ ከቤተሰቦቹ ጠፍቶ: በርሃ ገብቶ የአባ ስምዖን ደቀ መዝሙር ሆኗል::

+በዚያም በፍጹም ትሕርምት ሲኖር ባልንጀሮቹ ይጠፉበታል:: እነሱን ሊፈልግ ሲሔድ ግን አረማውያን ይዘው አሠሩት: አሰቃዩት:: መንገድ ላይ ውሃ ጠምቷቸው ሲጨነቁ "ውሃ ባጠጣችሁሳ?" አላቸው:: "እንለቅህ ነበር" አሉት::

+ጸልዮ: ውሃ አፍልቆ ቢያጠጣቸው "አንተማ ታስፈልጋለህና አንለቅህም" አሉት:: ወስደውም ጸይለም በምትባል ሃገር ለባርነት ሸጡት:: በዚያ ሲያሰቃዩት ተአምራትን አድርጐ በክርስቶስ አሳምኗቸዋል::

+ወደ ጐረቤት ሃገር ሔዶም ዛፍ ሲያመልኩ አገኛቸው:: "ወደ ክርስቶስ ተመለሱ" አላቸው:: "እንቢ" ሲሉት ምሳር (መጥረቢያ) ይዞ: ወደ ዱሩ ውስጥ ገብቶ ጸለየና ምሳሩን አነሳ::

+"በስመ ሥላሴ እገዝመክሙ" ብሎ ቢቃጣቸው አጋንንት የሠፈሩባቸው 10,000 ዛፎች ባንዴ ወደቁ:: በዚህ ምክንያትም 400,000 ሰዎች አምነው ተጠምቀዋል:: ወደ ሌላ ሃገር ሒዶም ስቃይን ታግሦ: ተአምራትን ሠርቶ ብዙዎችን አሳምኗል:: በቅድስና ኑሮም በዚህች ቀን ዐርፏል::

✝️አምላከ ይምርሐ ደጉን መሪ: አምላከ ዮሐንስ ቸሩን አስተማሪ ያምጣልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

+ጥቅምት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ (ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ዘጸይለም
3.አባ ስምኦን ገዳማዊ
4.ቅዱሳን በርተሎሜዎስና ሚስቱ (ሰማዕታት)
5.አበው ኤዺስ ቆዾሳት (ሳምሳጢን ያወገዙ)
6.ጻድቃን እለ መጥራ

✝️መሐርኒ ድንግል✝️
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
2024/09/27 11:19:24
Back to Top
HTML Embed Code: