Telegram Web Link
✝️✝️ እንኳዋን #ለቅዱስ_ጐርጐርዮስ_መነኮስ_ለቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ_እና_ለቅዱስ_አድሊጦስ_ሐዋርያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ✝️✝️✝️

✝️✝️#ቅዱስ_ጐርጐርዮስ_መነኮስ✝️✝️

=>በዚህ ስም ተጠርተው: ለምዕመናን አብርተው ያለፉ አባቶቻችን ብዙ ናቸው:: ለምሳሌም:-
*ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ
*ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
*ጐርጐርዮስ ዘሮሜ
*ጐርጐርዮስ መንክራዊ
*ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ
*ጐርጐርዮስ ረዓዬ ኅቡዓትን መጥቀስ እንችላለን::

✝️ከእነዚህ ዐበይት ጐርጐርዮሶች አንዱ ገዳማዊው ቅዱስ ዛሬ የሚከበረው ነው:: ቅዱስ ጐርጐርዮስ የተወለደው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በላይኛው ግብጽ አካባቢ ነው:: ወላጆቹ እጅግ ባለ ጠጐች በመሆናቸው የሚፈልገውን ሁሉ አሟልተው አሳድገውታል::

✝️በተለይ ደግሞ ሥጋዊ (የዮናናውያንን ጥበብ) እንዲማር አድርገው ወደ #ቤተ_ክርስቲያን ሰደውታል:: በዚያም ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን ከሥርዓቱ ጋር አጥንቶ እጅግ አንባቢ ስለ ነበረ #አናጉንስጢስ (አንባቢ) ሆኖ ተሾመ::

✝️አንባቢ በሆነባቸው ዘመናትም ወጣ ገባ ሳይል ያገለግል ነበርና ጣዕመ #መንፈስ_ቅዱስ አደረበት:: ስለዚህም አንደበቱ ጥዑም (ለዛ ያለው) ነበር:: ትንሽ ቆይቶም አበው 'ይገባሃል' ብለው ዲቁናን ሾሙት:: አሁንም ታጥቆ ያለ ዕረፍት ማገልገሉን ቀጠለ::

✝️ዘመኑ ነጫጭ ርግቦች (የተባረኩ መነኮሳት) የበዙበት ነበርና ቅዱስ ጐርጐርዮስ አዘውትሮ ወደ ገዳም እየሔደ ይጐበኛቸው: በእጆቻቸውም ይባረክ ነበር:: በተለይ #ሊቀ_ምኔት ታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ (#አባ_ባኹም) በቅርቡ ነበርና ሁሌ እየሔደ ይጨዋወተው ነበር::

✝️ትንሽ ቆይቶ ግን ቅዱሱ የምናኔ ፍላጐቱ እየጨመረ ሔደ:: አንድ ቀን ከገዳም ውሎ ሲመለስ ወላጆቹ ጥያቄ ጠየቁት::
"ልናጋባህ እንፈልጋለንና ምን ትላለህ?" አሉት:: እርሱም ጭራሹኑ እንደማይፈልግ መለሰላቸው:: ሊያሳዝኑት አልፈለጉምና ድጋሚ አልጠየቁትም::

✝️ትንሽ ቆይተውም ተከታትለው ዐረፉ:: ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወላጆቹን ቀብሮ: ሃብት ንብረቱን ሸጦ ጉዞ ጀመረ:: ወደ #አባ_ዻኩሚስ ደርሶም ያን ሁሉ ገንዘብ በታላቁ ቅዱስ ፊት አፈሰሰው:: "ምን ላድርገው ልጄ?" ቢለው "አባቴ! ፈጣሪህ ያዘዘውን" አለው::

✝️አባ ዻኩሚስም መነኮሳት በመብዛታቸው ቤት አልነበረምና ብዙ ቤቶችን አነጸበት:: የቅዱሱ ገንዘብ ገዳም ከታነጸበት በሁዋላ ምናኔን አንድ ብሎ ጀመረ::
ቅዱሱ ባጭር ታጥቆ: በጾምና ጸሎት: ውሃ በመቅዳት: በመጥረግ: ምግብ በማዘጋጀት: እግዚአብሔርንም አበውንም አስደሰተ:: ቅዱሱ ምንም ቢናገሩት አይመልስም:: ማንንም ቀና ብሎ አያይም::

✝️"እሺ" ከማለት በቀር ትርፍ ቃል አልነበረውም:: በጸሎት እንባው: በስግደት ደግሞ ላቡ ይንቆረቆር ነበር:: ፍቅሩ: ትዕግስቱ: ትሕትናውና ታዛዥነቱ እጅግ ብዙ ዓለማውያንን ማረከ:: ስለ እርሱ የሰሙ ኃጥአን ሔደው ምንም ሳይናገራቸው በማየት ብቻ ይማሩ ነበር:: ፊቱ ብሩህ: ደግና ቅን በመሆኑ እርሱን ማየቱ በቂ ነበር::

✝️ለ13 ዓመታት በገዳመ ዻኩሚስ ከተጋደለ በሁዋላ ወደ ገዳመ #ቅዱስ_መቃርስ ከ2ኛው አባ መቃርስ ጋር ተጉዋዘ:: በዚያም በዓት ወስኖ ከሰው ጋር ሳይገናኝ 7 ዓመታትን አሳለፈ:: በጸጋ ላይ ጸጋ: በበረከት ላይ በረከት ሆኖለት በ22ኛ ዓመቱ አባቶችን ሰበሰባቸው::

✝️መንገድ ሊሔድ መሆኑን ነግሯቸው "በጸሎት አስቡኝ" አላቸው:: በማግስቱ በዚህ ቀን ሲመጡ ግን በፍቅር ዐርፎ አገኙት:: መነኮሳትም በክብር ገንዘው: ከበረከቱ ተሳትፈው: በታላቅ ዝማሬ ቀብረውታል::

✝️✝️#ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ✝️✝️

=>ኢትዮዽያዊቷ #ቅድስት_እናት_ክርስቶስ_ሠምራ ቅንነቷ: ደግነቷና ቅድስናዋ እጅግ የበዛ ነው:: አንድ ቀን ግን ገና በትዳር ውስጥ እያለች: ከአገልጋዮቿ አንዷን ትጠራትና ታዛታለች:: ያቺ አገልጋይ ግን የታዘዘችውን ጀሮ ዳባ ልበስ ብላ ሳትታዘዛት ትቀራለች::

✝️ደጋግማ ብትነግራትም ልትሰማት አልቻለችም:: ያን ጊዜ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልትገስጻት ብላ ጠጠር ብትወረውርባት ያች አገልጋይ ወድቃ ሞተችባት:: ቅድስቲቱ እጅግ ደንግጣ አለቀሰች:: የምታደርገውንም አጣች::

✝️ወዲያው ግን ፈጠን ብላ: ወገቧን ታጥቃ ትጸልይ ጀመረች:: "ጌታየ ሆይ! ከሞት አስነሳልኝና ዓለምን ትቼ በቀሪ ዘመኔ አንተን አገልለግልሃለሁ" ብላ ፈጣሪን በብዙ እንባ ተማጸነችው:: ያን ጊዜም አገልጋዩዋ ከሞት ተነሳችላት::

✝️ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ጊዜን አላጠፋችም:: ልጆቿን በቤት ትታ: ሃብትን ብረቷን ንቃ: አንድ ልጇን አዝላ: ቤቷን እንደ ተከፈተ ትታው ወደ ገዳም ወጣች:: በዚህ ዕለትም (መስከረም 24 ቀን) ወደ #ደብረ_ሊባኖስ ገዳም ገባች::

✝️✝️#ቅዱስ_አድሊጦስ_ሐዋርያ✝️✝️

=>ቅዱሱ ሐዋርያ ተወልዶ ያደገው በግሪክ #አቴና (ATHENS) ውስጥ ሲሆን በነገድ እሥራኤላዊ ነው:: በአደገባት አቴና ከተማ ሥርዓተ ኦሪትን ከወገኖቹ: የግሪክን ፍልስፍና ደግሞ ከአርዮስፋጐስ ተምሯል:: #መድኃኔ_ዓለም ዘመነ ስብከቱ ሲጀምር ግን አድሊጦስ ወደ #ኢየሩሳሌም ሔዶ አደመጠው: ተማረከበትም::

✝️ወዲያውም "ጌታ ሆይ! ልከተልህ?" ሲል ጠየቀው:: ልብን የሚመረምር ጌታም ፈቅዶለት ከ72ቱ አርድእት ደመረው:: ከዚያም ከጌታችን ዘንድ ተምሮ: መንፈስ ቅዱስንም ተቀብሎ: ለወንጌል አገልግሎት ተሠማርቶ በርካታ አሕዛብን አሳምኗል:: በመጨረሻም ተወልዶ ባደገባት አቴና በዚህች ቀን ገድለውታል::
=>አምላከ ቅዱሳን በትእግስት: በፍቅርና በትሕትና ይሸልመን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

=>መስከረም 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ገዳማዊ
2.ቅድስ ክርስቶስ ሠምራ (ደብረ ሊባኖስ የገባችበት)
3.ቅዱስ አድሊጦስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
4.አቡነ ሰላማ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (መምሕረ ትሩፋት)
2.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
3.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
4.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
6."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
7.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮዽያዊ)

=>✝️✝️ #ፍቅር ያስታግሳል:: ፍቅር ያስተዛዝናል:: ፍቅር አያቀናናም::ፍቅር አያስመካም:: ፍቅር አያስታብይም:: ብቻዬን ይድላኝ አያሰኝም:: አያበሳጭም:: ክፉ ነገርን አያሳስብም:: ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም:: ሁሉን ይታገሣል:: ሁሉን ያምናል:: ሁሉን ተስፋ ያደርጋል:: በሁሉ ይጸናል:: ✝️✝️ (1ቆሮ. 13:4)

(ወስብሐት ለእግዚአብሔር)

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
#​መስከረም(፳፭) 25/01/2013 ዓ.ም

✝️✝️✝️በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✝️✝️✝️

✝️ዘነግህ✝️
✝️#️ምስባክ✝️

መዝ ፺፫፥፲፫(93፥13)
ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠፅኮ እግዚኦ
ወዘመሀርኮ ሕገከ
ከመ ይትገሐሥ እመዋዕለ እኩያት


✝️#ወንጌል✝️

ወንጌል ዘማቴዎስ ፲፮፥፳፩-፳፬(16፥21-24)
ወእምአሜሃ እግዚእ ኢየሱስ…


✝️#ምንባባት_ዘቅዳሴ✝️


✝️#ዲያቆን✝️
✝️ኀበ ሰብአ ሮሜ ፪፥፩-፲፪(2፥1-12)
እጓለ እመሕያው በምንትኑ ዘትትዋሥኦ…



#️ንፍቅ_ዲያቆን✝️
✝️ጴጥሮስ ፪ ም ፫፥፩-፰(3፥1-8)
ወዛቲ ይእቲ አኃውየ…


✝️#ንፍቅ_ካህን✝️
✝️ግብረሐዋርያት ፳፥፱-፳፰(20፥9-28)
ወእንዘ ይነብር ፩ ወልድ…




✝️#ምስባክ_ዘቅዳሴ✝️

✝️ወአይቴ እጎይይ እምቅድመ ገጽከ
እመኒ ዐረጉ ውስተ ሰማይ ህየኒ አንተ
ወእመኒ ወረድኩ ውስተ ቀላይ ህየኒ ሀሎከ

✝️#ትርጉም✝️

✝️መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፴፱ ቊ. ፯- ፰✝️

✝️፯ ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?

✝️፰ ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ። ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ።




✝️#ወንጌል_ዘቅዳሴ✝️

✝️የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፪ ቊ. ፴፰ - ፵፫✝️

✝️፴፰ በዚያን ጊዜ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ መለሱና። መምህር ሆይ፥ ከአንተ ምልክት እንድናይ እንወዳለን አሉ።

፴፱ እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው። ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።

✝️፵ ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።

✝️፵፩ የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፥ እነሆም፥ ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።

✝️፵፪ ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።

✝️፵፫ ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ፥ ዕረፍት እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፥ አያገኝምም።


#ቅዳሴ ✝️ዘሐዋርያት (ዘበደኃሪ)✝️


@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
††† እንኳን ከዘመነ ክረምት ወደ ዘመነ መጸው አሸጋግሮ ለቅዱስ ዮናስ ነቢይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††


††† ስንዱ #እመቤት #ቤተ_ክርስቲያን (ሃገራችን) ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነውና ዓመቱን በዘመናት ከፍላ ትጠቀማለች:: እሊሕም ዘመናት #መጸው (ጽጌ): #ሐጋይ (በጋ): #ጸደይ (በልግ) ና ክረምት ናቸው:: ዘመናቱ ወቅቶችን ከመለየትና ማሳወቅ ባሻገር የእኛ ሕይወትም ምሳሌዎች ናቸውና ልብ ልንላቸው ይገባል::

#ዘመነ_መጸው / #ወርኀ_ጽጌ/ #ጥቢ እየተባለም ይጠራል:: በዚህ ወቅት ምድር በአበባ የምታጌጥበት: ክረምት የተለፋበት አዝመራ የሚደርስበት በመሆኑ ደስ ያሰኛል:: በጊዜውም:-
1.የእመቤታችን የቅድስት #ድንግል_ማርያም ስደቷ ይታሠባል:: እርሷ ስለ እኛ:-
*የሕይወት እንጀራን ተሸክማ መራቧን::
*የሕይወት መጠጥን ይዛ መጠማቷን::
*የሕይወት ልብስን አዝላ መራቆቷን::
*ሙቀተ መንፈስ ቅዱስን የሚያድለውን ተሸክማ ብርድ መመታቷን እናስባለን::
*ዘመኑ የበረከት ነው::

2.በሌላ በኩል ጊዜው ወርኀ ትፍሥሕት (የደስታ ወቅት) ነው:: በክረምት የደከመ ዋጋውን አግኝቶ: በልቶ: ጠጥቶ ደስ ይለዋልና:: ያልሠራው ግን ከማዘን በቀር ሌላ እድል የለውም:: ይኼውም ምሳሌ ነው::

ዘመነ ክረምት የዚህ ዓለም ምሳሌ: ዘመነ መጸው ደግሞ የመንግስተ ሰማያት:: በዚህ ዓለም ምግባር ትሩፋትን የሠራ በወዲያኛው ዓለም ተድላን ሲያደርግ ሰነፎች ኃጥአን ግን እድል ፈንታቸው: ጽዋ ተርታቸው ከግብዞች ጋር የመሆኑ ምሳሌ ነው::

በወርኀ ትፍስሕት እንደ ሊቃውንቱ እንዲህ ብለን ልንጸልይ ይገባል::
"ድኅረ ኀለፈ ክረምት ወገብአ ዝናም: ዘአስተርአይከ እግዚኦ ጽጌያተ ገዳም:
አፈወ ሃይማኖት ነአልድ ወፍሬ ምግባር ጥዑም:
አትግሃነ ለስብሐቲከ ከመ ትጋሆሙ አዳም:
ለጽብስት ንሕብ ወነአስ ቃሕም::"

††† የዘመናት ባለቤት ዘመነ መጸውን #ወርኀ_ትፍስሕት ያድርግልን::

✝️✝️#ቅዱስ_ዮናስ_ነቢይ✝️✝️

††† ዮናስ ማለት 'ርግብ: የዋህ' ማለት ሲሆን ከ12ቱ #ደቂቀ_ነቢያት አንዱ ነው:: በሰራፕታ ተወልዶ ያደገው ነቢዩ በልጅነቱ ታሞ ሙቶ ነበር:: ታላቁ ነቢይ #ኤልያስ ግን 7 ጊዜ ጸሎት አድርጐ ከሞት አስነስቶታል:: (1ነገ. 17:17) እናቱ የሰራፕታዋ መበለትም ደግ ሴት ነበረች::

ቅዱስ ዮናስ በእድሜው ከፍ ሲል የቅዱስ ኤልያስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: የነ ኤልሳዕና አብድዩም ባልንጀራ ነበረ:: ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስ ካረገ በሁዋላ: ቅ.ል.ክርስቶስ በ800 ዓመት አካባቢ የነነዌ ሰዎች ኃጢአት ከመሥፈርቱ በማለፉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ መጣ::

"ሒድና ለነነዌ ሰዎች ንስሃን ስበክላቸው" አለው:: ከነቢያት ወገን ከሙሴና ከዳዊት ቀጥሎ የዮናስን ያህል የዋህ (ገራገር) የለምና እንቢ አለ (ሰምቶ ዝም አለ):: #እግዚአብሔር እየደጋገመ ሲናገረው ግን "እንዲህ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል!" ብሎ ወደ #ተርሴስ ኮበለለ::

ወገኖቼ አንድ ነገርን ልብ እንበል:: እንኩዋን ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዮናስ እኛ ክፉዎችም ከጌታ ፊት መሸሸት እንደማይቻል ጠንቅቀን እናውቃለን:: ታዲያ ለምን ሸሸ ቢሉ:- ጥበበ እግዚአብሔር በውስጡ ስለ ነበረበት ነው::

ምክንያቱም ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ 3 ቀን እና ሌሊት ኖሮ: ሙስና (ጥፋት) ሳያገኘው መውጣቱ ለጌታ ትንሳኤ ጥላ (ምሳሌ) ነው:: ለዚህም ምስክሩ ራሱ ጌታችን ነው::
"ወበከመ ነበረ #ዮናስ ውስተ ከርሠ አንበሪ ሠሉሰ ዕለተ ወሠሉሰ ለያልየ: ከማሁ ይነብር ወልደ እጉዋለ እመ ሕያው ውስተ ልበ ምድር ሠሉሰ ዕለተ: ወሠሉሰ ለያልየ" እንዲል:: (ማቴ. 12:39)

ቅዱስ ዮናስ በገንዘቡ ዋጅቶ ወደ መርከብ በገባ ጊዜ ታላቅ ማዕበል ሆነ:: የእምነት ሰው ነውና እንዲያ እየተናወጡ እርሱ በእርጋታ ተኝቷል:: እነርሱ ግን ቀስቅሰው ቢጠይቁት (እጣ ወድቆበታልና) "የእኔ ጥፋት ስለ ሆነ ወደ ማዕበሉ ጣሉኝ" አላቸው::

እያዘኑ ቢጥሉት ታላቅ ጸጥታ ሆነ:: እነዚያ አሕዛብም እግዚአብሔርን በመስዋዕትና በስዕለት አከበሩ:: ዮናስ ግን በማዕበልና በአሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ለ3 ቀናት ጸለየ:: አሣ አንበሪው በ3ኛው ቀን ወደ ነነዌ ተፋው::

ቅዱሱም "እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ #ነነዌ ዐባይ ሃገር" እያለ ንስሃን ሰበከ:: የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸውን አምነው ቢጸጸቱ ከሰማይ ወርዶ ከደመና ደርሶ የነበረው የእሳት ማዕበል ተመልሶላቸዋል::

የነቢዩ ትንቢት ግን አልቀረምና ታላቋ ነነዌ ከ300 ዓመታት በሁዋላ ጠፍታለች:: ቅዱስ ዮናስ ግን በቀሪ ዘመኑ ፈጣሪውን እያገለገለ ኑሯል:: ጠቅላላ እድሜውም 170 ዓመት ነው::

††† አምላከ ቅዱስ ዮናስ እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሃ አይንሳን:: ከበረከቱም ይክፈለን::

††† መስከረም 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ጸአተ ክረምት (የክረምት መውጫ)
2.ቅዱስ ዮናስ ነቢይ
3.ቅዱስ እንጦንዮስ
4.ቅድስት በርባራ
5.ሐዋርያት ዼጥሮስ ወዻውሎስ
6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
7.ታላቁ አባ ቢጻርዮን ገዳማዊ

††† "ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል:: ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም:: ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ: እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል:: የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዱበታል:: በዮናስ ስብከት ንስሃ ገብተዋልና:: እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ::" †††
(ማቴ. 12:39)

(ወስብሐት ለእግዚአብሔር)

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
#መስከረም(፲፮) 26/01/2013 ዓ.ም

✝️✝️✝️በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✝️✝️✝️

✝️ዘነግህ✝️
✝️#ምስባክ ✝️
መዝ ፲፰፥፰(18፥8)
ትእዛዙ ለእግዚአብሔር ብሩህ ወያበርህ አዕይንተ
ፈሪሀ እግዚአብሔር ንጹሕ ወየሐዩ ለዓለም
ፍትሑ ለእግዚአብሔር ጽድቅ ወርትዕ ኅቡረ


✝️#ወንጌል✝️
ወንጌል ዘማቴዎስ ፮፥፳፪-፳፭(6፥22-25)
ማኅቶቱ ለሥጋከ ዐይንከ ውእቱ…


✝️#ምንባባት_ዘቅዳሴ✝️

✝️#ዲያቆን✝️
✝️ኀበ ሰብእ ዕብራውያን ፲፪፥፩-፲፩(12፥1-11)
ወበእንተ ዝንቱ ንሕነኒ…


✝️#ንፍቅ_ዲያቆን✝️
✝️ጴጥሮስ ፩ ም ፪፥፳-፳፭(2፥20-25)
ወምንትኑ ይእቲ አኰቴትክሙ…

✝️#ንፍቅ_ካህን✝️
✝️ግብረሐዋርያት ፲፥፩-፱(10፥1-9)
ወሀሎ ፩ዱ ብእሲ…


✝️#ምስባክ_ዘቅዳሴ✝️

በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ
ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ ወእገኒ ለስምከ

✝️#ትርጉም✝️

መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፴፰ ቊ. ፩ - ፪

፩ አቤቱ፥ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፥ የአፌን ነገር ሰምተኸኛልና፤ በመላእክት ፊት እዘምርልሃለሁ።

፪ ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።


✝️#ወንጌል_ዘቅዳሴ✝️

የሉቃስ ወንጌል ም. ፩ ቊ. ፩-፬ - ፳፫

፩-፬ የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው በዓይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን፥ በኛ ዘንድ ስለ ተፈጸመው ነገር ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ፥ እኔ ደግሞ ስለ ተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ በየተራው ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ።

፭ በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች፥ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ።

፮ ሁለቱም በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ።

፯ ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር።

፰ እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት ሲያገለግል፥

፱ እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት።

፲ በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይጸልዩ ነበር።

፲፩ የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው።

፲፪ ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፥ ፍርሃትም ወደቀበት።

፲፫ መልአኩም እንዲህ አለው። ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።

፲፬ ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።

፲፭ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤

፲፮ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል።

፲፯ እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።

፲፰ ዘካርያስም መልአኩን። እኔ ሽማግሌ ነኝ ምስቴም በዕድሜዋ አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ? አለው።

፲፱ መልአኩም መልሶ። እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፤

፳ እነሆም፥ በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ መናገርም አትችልም አለው።

፳፩ ሕዝቡም ዘካርያስን ይጠብቁት ነበር፤ በቤተ መቅደስም ውስጥ ስለ ዘገየ ይደነቁ ነበር።

፳፪ በወጣም ጊዜ ሊነግራቸው አልቻለም፥ በቤተ መቅደስም ራእይ እንዳየ አስተዋሉ፤ እርሱም ይጠቅሳቸው ነበር፤ ድዳም ሆኖ ኖረ።

፳፫ የማገልገሉም ወራት ሲፈጸም ወደ ቤቱ ሄደ።



#ቅዳሴ=>ዘኤጲፋንዮስ (ዐቢይ)


@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
✝️✝️✝️ እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✝️✝️✝️


✝️✝️✝️#ተአምረ_ማርያም✝️✝️✝️

✝️✝️✝️ተአምር ማለት "ድንቅ: ምልክት: ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ የሆነ ክዋኔ: በሰብአዊ አቅም ሊሠራ የማይችል ተግባር (ድርጊት)" ነው:: ተአምራት ከባለቤቱ ከጌታችን ሲሆኑ የባሕርዩ ናቸው:: ከቅዱሳኑ ሲሆኑ ደግሞ የጸጋ እንላቸዋለን:: ቅዱስ መጽሐፍ ላይ በእግዚአብሔር ወዳጆች የተሠሩ ተአምራት እጅግ ብዙ ናቸው:: ነገር ግን:-
*ተአምራት ከአጋንንትም ሊሆኑ እንደሚችሉ መረዳት::
*ሁሌ ምልክትን (ተአምርን) አለመፈለግ::
*መመርመርና ማስተዋል ከአንድ ክርስቲያን ይጠበቃል::
*ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በድርሳኑ እንደ ነገረን ተአምር መሥራት ከሲዖል እሳት አያድንም:: ጌታም በዚህ ነገር ተባብሮበታል:: (ማቴ. 7:22, 12:39)

ከጌታችን እግዚአብሔር ቀጥሎ የድንግል ማርያምን ያህል ተአምራትን የሠራ አይገኝም:: እንዲያው ሌላውን ትተን በእያንዳንዳችን ሕይወት ላይ እንኳ ብዙ ድንቅ ነገሮችን አድርጋለችና ምስክሮቹ እኛው ራሳችን ነን:: የእመቤታችን ተአምር የተጀመረው ገና ከፍጥረተ ዓለም ነው::

በእርግጥ ይህንን ለመረዳት ሠፊ አዕምሮና አስተዋይ ልቡናን ይጠይቃል:: ድንግል ማርያም ማለት የእግዚአብሔር የቸርነቱ ግምጃ ቤት: የጸጋው ደጅ ናት:: እርሱ ይህንን መርጦ ወዷልና:: እመ ብርሃን ተጸንሳ ከተወለደች በኋላ ደግሞ እጅግ ብዙ ኃይልን ታደርግ ነበር:: በዚህ ዕለት ከ2007 ዓመታት በፊት ያደረገችው ተአምር ደግሞ ድንቅ ነው::

አጐቷ /ጠባቂዋ/ አገልጋዩዋ አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ከቤተ መቅደስ ተቀብሎ ካመጣት በኋላ እርሱ እንጨትን ይጠርብ ነበር:: ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ (የችግር ዘመን) በመሆኑ ለሥራ ጉዳይ ወደ ሩቅ ሃገር ሒዶ የተመለሰው ከወራት በኋላ ነው::

ዮሐንስ የሚሉት ፈላስፋ ባልንጀራ ነበረውና ሽማግሌው ዮሴፍ ልብ ያላለውን ነገር ነገረው:: "ይህች ብላቴና ጸንሳለችና መርምራት" ብሎ ሔደ:: ቅዱስ ዮሴፍ ግን ደነገጠ:: "እኔ እንዲህ ያለ ነገር እንኳን በገቢር (በሥራ) በሃሳብም አላውቅባት" ብሎት ወደ ቤት ገባ::

ቀጥሎም እመቤታችንን "ልጄ ሆይ! ከማን ጸነስሽ" አላት:: "እመንፈስ ቅዱስ" አለችው:: ግራ ገባው: ምሥጢርም ተሠወረበት:: "እንዴት አንዲት ሴት ያለ ወንድ ዘር ልትጸንስ ትችላለች?" ብሎ ያወጣ: ያወርድ: ይጨነቅም ገባ:: የእኛ እመቤት ግን እንደ ጨነቀው ባወቀች ጊዜ ጠርታ ወደ ውጪ ይዛው ወጣች::

ከረዥም ጊዜ በፊት ጠርቦ የጣለውን እንጨት አንስታ ተከለችውና ጸለየችበት:: በደቂቃም የአረጋዊው ዐይን እያየ ያ ደረቅ እንጨት ለምልሞ: አብቦ አፈራ:: ቅዱስ ዮሴፍ በጣም ደነገጠ::

"አባቴ ተመልከት እስኪ! ይህንን ማን አደረገ?" አለችው:: "ልጄና እመቤቴ! እግዚአብሔር ነው" አላት:: እርሷም "በማሕጸኔ ያለውም ኢሳይያስ ትንቢትን የተናገረለት አምላክ ነውና ሁሉን ይችላል" አለችው:: አረጋዊውም ቅዱስ ኤራቅሊስ በሃይማኖተ አበው እንደ ነገረን "ሰገደ ላቲ" ወደ ምድር ወድቆ በፊቷ ሰገደ::

✝️✝️✝️#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ✝️✝️✝️

✝️✝️✝️ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር::

እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ ደግሞ 100 ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በኋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

✝️✝️✝️የእመቤታችን ልመናዋ: ክብሯ: የልጇ የወዳጇም ቸርነት በእውነት ከሁላችን ጋር ይሁን:: የመጥምቁንም በረከት ያብዛልን::

✝️✝️✝️መስከረም 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ድንግል ማርያም
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
3.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ (ጽንሰቱ)
4.ቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ
5.ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት (ፍልሠቱ)

✝️✝️✝️ ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

✝️✝️✝️ "ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ጽንሱ በማሕጸኗ ውስጥ ዘለለ:: በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት:: በታላቅ ድምጽም ጮኻ እንዲህ አለች:-
'አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ: የማሕጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው:: የጌታየ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? . . . ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብጽዕት ናት::" ✝️✝️✝️
(ሉቃ. ፩፥፵፩)

(ወስብሐት ለእግዚአብሔር)
መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ:

"በሌላ ሀገር ትንሽ ወንዝ ካለች መዝናኛ አድርገው ይዝናኑባታል፡፡ እኛ ሀገር ትንሽ ወንዝ ካለች የመለያያ ድንበር አድርገን እንጋጭባታለን፡፡"

(መጋቤ ሐዲስ እሸቱ)

ታላቁ ሊቅ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል …
‹ሰው እግዚአብሔር ሲለየው፤ ጠባዩ እንደ አራዊት፤ አመጋገቡ እንደ እንስሳ፣ ሆኖ መልኩ ብቻ የእግዚአብሔር ሆኖ ይቀራል›። በጣም ቀለል ባለ አገላለጽ ሲም ካርዱ የወጣ ሞባይል ማለት ነው። ጥሪ የማይቀበል….
...እኔ በዕውነቱ ከተማው ፈርሶ እየተሰራ ነው እየተባለ ዐይናማዎቹ ሲያወሩም ሲያስወሩም እሰማለው። ፈርሶ መሰራት ያለበት ግን የሰዉ አስተሳሰብ ነው።...
የሰዉ አስተሳሰብ ፈርሶ ካልተሰራ፤ የተሰራ ከተማ ይፈርሳል።
ጃፓንና ቻይና ሀገራቸውን ያለሙት መጀመሪያ አስተሳሰባቸውን አልምተው ነው። ቤታችሁ ገብታችሁ እንድታጤኑት ነው።
… እንደምታዩኝ እኔ ዐይነ ስውር ነኝ። ቀላል አይደለም.... እንክዋን ዘውትር ዓይን አጥቶ አንድ ቀን መብራት ሲሄድ ስንት እንደምታማርሩ ታውቅታላችሁ።
እኔ ግን ዓይኔ ባለማየቱ አንድ ቀን እንኳን አልቅሼ አላውቅም። ከሞት ወዲያ መብራት አለ። ከመቃብር በላይ መብራት አለ። ... ወደ መቃብር ሲወርድ ማንም ዓይነ ስውር ነው። ማንም ዐይኑ እያየ የተቀበረ የለም።
ተስፋችን ግን ምንድን ነው? ከሞት ወዲያ ሕይወት አለ። ከሞት ወዲያ ብርሃን አለ...
አንድ አንድ ጊዜ እመኛለሁ። የማይረባ ነገር ስናይ (ዓይናችንን) የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር... መልካም ነገር እስክናይ ድረስ ለጊዜው የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር።
…አሁን እንደው ጆሮ በካርድ የሚሰራ ቢሆን ሐሜት እንሰማ ነበር? የምንፈልገውን (ብቻ) አውርተን ስዊች ኦፍ እናደርገው ነበር።
ችግሩ ብዙ ነው፡፡ ስንት ዞማ ጸጉር ይዞ አስተሳሰቡ የከረደደ አለ።
... እባካችሁ ሰው እንሁን… የንጉሠ ነገሥቱ የክርስቶስ አልጋ ወራሾች ነን... የደስታችሁ ልኬት የደስታችሁ ሚዛን ምግብና መጠጥ አይሁን፤ መኪናና ቤት ዝናንም አታርጉ።
እኛ መለኪያችን ጽድቅ ነው። መከኪያችን መንግሥተ ሰማያት ነው። ያ የምንገባበት ቤት ደግም የተዋበ፣ የደመቀ፣ መብራት ውሀ የማይሄድበት፤ 24 ሰዓት ክርስቶስ የሚያበራበት፤ 24 ሰዓት የሕይወት ውሀ የሚጠጣበት፤ ሀብታም፤ ደሀ፣ ተራ ሰው የማይባልበት፣ እገሌ ግባ እገሌ ውጣ የማይባልበት
ቦታ ነው.....።

(ወስብሐት ለእግዚአብሔር)

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
#ፆመ_ፅጌ

እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የስደቷ መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ !

ድንግል ሆይ ረሀቡን ጥሙን፣ ችግርና ሀዘኑን፣ ከእርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ ድንግል ሆይ ከአይኖችሽ የፈሰሰውንና
በተወደደው ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ።

Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
#ጥቅምት (፫) 03/02/2014 ዓ.ም

✝️✝️✝️በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✝️✝️✝️

✝️ዘነግህ✝️
✝️#ምስባክ✝️
መዝ ፸፱፥፱(79፥9)
ተከልከ ሥርዊሃ ወመልዐት ምድረ
ወከደነ አድባረ ጽላሎታ
ወአእፁቂሃኒ ከመ አርዘ ሊባኖስ


✝️#ወንጌል✝️
ወንጌል ዘዮሐንስ ፲፭፥፩-፲፪(15፥1-12)
አነነ ውእቱ ሐረገ ወይን…


✝️#ምንባባት_ዘቅዳሴ✝️

✝️#ዲያቆን✝️
✝️ኀበ ቲቶ ፪፥፩-፱(2፥1-9)
ወአንተሰ ንግር ዘይደሉ…


✝️#ንፍቅ_ዲያቆን✝️
✝️ጴጥሮስ ፩ ም ፭፥፪-፭(5፥2-5)
ረዐዩ ዘሀሎ ኀቤክሙ…


✝️#ንፍቅ_ካህን✝️
✝️ግብረሐዋርያት ፳፥፳፰-፴፩(20-28-31)
ወይእዜኒ ዕቀቡ…


✝️#ምስባክ_ዘቅዳሴ✝️
አዋልደ ንግሥት ለክብርከ
ወትቀወወም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት


✝️#ትርጉም✝️
መዝሙረ ዳዊት ም. ፵፬ ቊ. ፱- ፲

፱ የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።

፲ ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤



✝️#ወንጌል_ዘቅዳሴ✝️
የሉቃስ ወንጌል ም. ፲ ቊ. ፴፰ - ፵፪

፴፰ ሲሄዱም እርሱ ወደ አንዲት መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤትዋ ተቀበለችው።

፴፱ ለእርስዋም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች።

፵ ማርታ ግን አገልግሎት ስለ በዛባት ባከነች፤ ቀርባም። ጌታ ሆይ፥ እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ አይገድህምን? እንኪያስ እንድታግዘኝ ንገራት አለችው።

፵፩ ኢየሱስም መልሶ። ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥

፵፪ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።


#ቅዳሴ ✝️ዘሰለስቱ ምዕት (ግሩም)

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
✝️✝️✝️ጥቅምት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት✝️✝️✝️

✝️✝️#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሐዲስ✝️✝️

✝️✝️✝️ሰማዕቱ የተወለደው በምድረ ግብጽ አሕዛብ (ተንባላት) በሰለጠኑበት የመጀመሪያው ዘመን ነበር:: በተለይ ተንባላቱ ግብፅና ሶርያን ከያዙ በኋላ ባልተጠበቀ ፍጥነት በኃይልም በሰውም ተደራጅተው ነበር:: ቅዱስ ጊዮርጊስ (ልብ በሉልኝ ሊቀ ሰማዕታት አይደለም) የተወለደው በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር::

✝️እናቱ የተመሠከረላት ክርስቲያን ብትሆንም እንዳለመታደል አባቱ ተንባላታዊ (አሕዛብ) ነበር:: ስሙንም መዛሕዝም ይሉታል:: ሕጻኑ እንደተወለደ ያወጡለት ስም አሕዛባዊ ከመሆኑ ባለፈ በሰዓቱ መጠመቅ አልቻለም:: የወቅቱ ሕግ ከወላጆቹ አንዱ አሕዛባዊ ከሆነና አጠምቃለሁ ቢባል የሚከተለው ሰይፍ ነበር:: በዚሕ ምክንያት ሳይጠመቅ 7 ዓመት ሞላው::

✝️እናቱ ግን ሕጻን ቢሆንም ፍቅረ ክርስትናን ታስተምረው ነበር:: ባይጠመቅም ጸበሉን: እመነቱን ትቀባው ነበር:: ደብቃ ቅዳሴ ታሰማውም ነበር:: አንድ ቀን ግን ሕጻናት ሲቆርቡ አይቶ ካልቆረብኩ ብሎ አለቀሰ:: ምን ታድርገው? ወደ ውጪ አውጥታ ከአውሎግያ (የሰንበት በረከት) አበላችው:: "ጌታየ! ልጄን እርዳው" አለች::

✝️ልክ በአፉ ሲቀምሳት መዓዛ መንፈስ ቅዱስ አደረበትና ፍጹም ተደሰተ:: ትንሽ ከፍ ሲል ለምን እንደማይጠመቅና እንደማይቆርብ እናቱን ጠየቃት:: "ልጄ ሆይ! ይገድሉሃል" አለችው::
ከዚህች ቀን ጀምሮ የሚጠመቅበትን ዘዴ ይፈልግ ጀመር::

✝️አስቀድሞ ትምሕርተ ክርስትናን ተማረ:: ለአካለ መጠን ሲደርስ አፈላልጐ ጠንካራ ክርስቲያን የሆነች ሴት አገባ:: ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ሚስቱን ስለ መጠመቅ አማከራት:: "ሌላ ሃገር ሒደህ ተጠመቅ" አለችው:: ከግብፅ ተነስቶ ሶርያ ገባ::
አባቶችን አፈላልጎ ተጠመቀ:: ቀጥሎም መንገዱን ወደ ልዳ አደረገ::

✝️ወደ ደብሩ ተጠግቶ አባቶችን "ስም አውጡልኝ" ቢላቸው መንፈስ ቅዱስ አናግሯቸው "ጊዮርጊስ" አሉት:: እሱም ደስ እያለው: ባጭር ታጥቆ የልዳውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያገለግለው ገባ:: ትንሽ ቆይቶ ሁከት መንፈሳዊ ተሰማው:: ማለትም ስለ ሃይማኖቱ ደሙን ማፍሰስ ፈለገና ወደ ግብፅ ተመለሰ::

+በዚያ ያሉ አሕዛብ በክርስትና ስም: ልብስና ሞገስ ሲመለከቱት ተበሳጩ:: ዕለቱኑ አሠሩት:: ሌሊት እናቱና ሚስቱ መጥተው አሉት:- "አደራ! ፍቅረ ዓለም እንዳያታልልህ:: ሰማዕት ብትሆን ላንተም ክብር: ለእኛም ሞገስ ነው" ብለውም አጽናኑት:: እንዲህ ያሉ እናትና ሚስት ማግኘትም ታላቅ እድል ነው::

✝️ሐዲስ ጊዮርጊስም ጸና:: ከዚያች ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ደበደቡት: አካሉን ቆራረጡት: ደሙንም መሬት ላይ አንጠፈጠፉት:: በየመንገዱ እየጎተቱ ተሳለቁበት:: እርሱ ግን ክርስቶስን ወዷልና ሁሉን ታገሰ:: ሌሊት በሆነ ጊዜም ጌታችን ተገልጦ "ከሰማዕታት ተቆጠርህ" አለው::

+በማግስቱ በአደባባይ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት:: ክፋታቸው የጸና ነውና ሥጋውን በእሳት አቃጠሉት:: ወደ ባሕርም ጣሉት:: እናቱ ከባሕር ስታወጣው ግን ምንም አላገኘውም ነበር:: በዚሕች ቀን እናቱና ሚስቱ በክብር ቀብረውታል::

✝️✝️#አባ_ስምዖን_ሊቀ_ዻዻሳስ✝️✝️

✝️በምድረ ግብጽ ተነስተው: በማርቆስ ወንጌላዊ መንበር ላይ ይቀመጡ ዘንድ ከተገባቸው ሊቃነ ዻዻሳት አንዱ እኒህ አባት ናቸው:: ከልጅነታቸው መንነው ብዙ ዘመናትን በተጋድሎ በማሳለፋቸው ሥጋዊ አካላቸው ደካማ ሆኖ ነበር::

✝️ከገዳማዊ አገልግሎታቸው ቀጥሎም ከእርሳቸው በፊት ለነበሩ ሁለት ፓትሪያርኮች ረዳት ሆነው አገልግለዋል:: በዚህ ጊዜም ለመንጋው የሚሆኑ ተግባራትን ከመፈጸማቸው ባሻገር በጾምና በጸሎት መጋደልን አልተዉም ነበር::

+ጊዜው ደርሶ በእግዚአብሔር ፈቃድ: በሕዝቡና ዻዻሳቱ ምርጫ: የእስክንድርያ 51ኛ ፓትርያርክ ሲሆኑ እርሳቸው እንደ ሌሎቹ አበው 'አልፈልግም' ብለው ነበር::

+ቀደም ሲል እንዳልነው አካላቸው በተጋድሎ የተቀጠቀጠ ነበርና በመንበራቸው ላይ ለብዙ ጊዜ መቆየት አልቻሉም::እግራቸውን በጠና በመታመማቸው ፈጣሪ ነፍሳቸውን እንዲቀበል ለመኑት: እርሱም ሰማቸው:: ሊቀ ዻዻሳት ሆነው በተሾሙ በ165ኛው ቀን (ማለትም በ5 ወር ከ15 ቀናቸው) በክብር ዐርፈው ተቀብረዋል::

✝️✝️✝️ቸሩ አምላክ ከሰማዕቱ ጽናትን: ትእግስትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን::

††† ጥቅምት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ (ሰማዕት)
2.አባ ስምዖን ሊቀ ዻዻሳት
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ
4.ቅድስት ታኦድራ ልዕልት
5.ቅድስት ታኦፊላ

✝️✝️✝️ " ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?... እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና:: "✝️✝️✝️ (1ቆሮ. 10:14-18)

(ወስብሐት ለእግዚአብሔር)

Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
Join @mehereni_dngl
​​#ምሥጢረ_ንስሐ

#ንስሐ ፦ መፀፀት ሲሆን ፤ ንስሐ ማለት በሠሩት ኃጢአት መፀፀት ፣ ማዘን ፣ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ መወሰን ማለት ነው። ንስሐ ከዘለዓለማዊ ፍርድ የሚያድን ፤ ዘማዊውን እንደ ድንግል ፤ ሌባውን መጽዋች የሚያደርግ በፊት ከተሠራው ኃጢአት ንጹህ አድርጎ ፤ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ የሚያደርግ ምሥጢር ነው ።

#ከንስሐ_በፊት

#መፀፀት
አንድ ክርስቲያን በድፍረትም ይሁን በስህተት “የሠራው በደል” መጻሕፍት በማንበብ ፣ ከመምህራን ተምሮ ፣ የስብከት ካሴት አዳምጦ ፤ ህሊናው ወቅሶት ፣ ወይም በሌላ በአንድ ምክንያት ስህተት መሆኑን ከተረዳ በኋላ ተፀፅቶ ከእግዚአብሔር ለመታረቅ (በደሉንለማስተስረይ)የሚያደርገው ጉዞ ንስሐ ይባላል።

በሠራው በደል ሳይፀፀት ፤ ለጊዜው ህሊናውን ስለረበሸው ብቻ ንስሐ የሚገባ ሰው ፤ ከንስሐው በኋላ ወደ ቀደመ ሕይወቱ ሊመለስ ይችላል ። ምክንያቱም ፡ ንስሐ የገባው ፡ በሠራው በደል ከልቡ ተፀፅቶ ሳይሆን ፤ በስሜት ተነሳስቶ ነውና ፤

#ኃጢአትን_መጥላት
በበደላችን ከተፀፅትን በኋላ የሰራነውን በደል መጥላትና ወደፊትም መሥራት እንደሌለብን ራሳችንን ማሳመንና ከኃጢዓት መንገድ መራቅ ማለት ነው ።

ከንስሐ በኋላ ስላለው ሕይወት መወሰን
አንድ ምዕመን ንስሐ ከመግባቱ በፊት ለወደፊቱ የሚኖረውን ሕይወት አስቀድሞ መመርመርና መወሰን ይገባዋል የእግዚአብሔን ቃል ስንሰማ ለጊዜው ልባችን ሊነካ ፣ ምን እናድርግ ልንል እንችላለን ። የሐ ሥ 2 ፥ 37።

ነገር ግን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ዓለሙን ወደመምሰል እንደማንመለስ አስቀድመን ራሳችንን መመርመር አለብን። ብዙዎቹ በስሜት ወደ ክርስትና ከገቡ በኋላ ፤ በጊዜያዊ ነገር ተታለው በድንገት ከሃይማኖት መንገድ ወጥተዋልና ።

#በንስሐ_ጊዜ

አንድ ምዕመን ካለፈ በደሉ በንስሐ ታጥቦ በአዲስ ሕይወት ራሱን ለማስተካከልና ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ከወሰነ በኋላ የንስሐ አባት ሊኖረው ይገባል።

ጌታችን “ካህናትን” ራሱን ወክለው መንጋውን እንዲጠብቁ “በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሁን” (ማቴ8 ፥ ዮሐ 21 ፥ 15 ። ማቴ 16 ፥ 19)በማለት መንጋውን እንዲጠብቁ ሾሟቸዋልና።

አንድ ክርስቲያን በሕይወት ሲኖር ፤ የእግዚአብሔርን መንገድ የሚመራው ፤ ሲሳሳት ንስሐውን ተቀብሎ ቀኖና በመስጠት ከእግዚአብሔር የሚያስታርቀው የንስሐ አባት የግድ ሊኖረው ይገባል።

✝️💙@mehereni_dngl💙✝️
✝️💛@mehereni_dngl💛✝️
✝️💜@mehereni_dngl💜✝️
የዮሐንስ ወንጌል ትርጓሜ /ክፍል 57/





እውነተኛ ስጦታ


“ከዮሐንስ ዘንድ ሰምተው ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበረ” /ዮሐ. 1፡41/።


መጥምቁ ዮሐንስ የክርስቶስን ታላቅነት ገለጠ። ክብሩ ከክርስቶስ ክብር እንደሚበልጥ የሚያስቡ ነበሩና እኔ የጫማውን ጠፈር እንኳ መፍታት አይቻለኝም አለ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቻ የሌለው በመሆኑ ከእርሱ ቀጠሎ የሚባልለት ተቀራራቢ የለበትም። የእግዚአብሔር ባሕርይ ብሑተ ሕላዌ ወይም ብቻውን ነዋሪ ነው /1ጢሞ. 1፡17፤ 6፡16፤ ሮሜ. 16፡27/። አንዳንድ ጊዜ ክርስቶስን አንደኛ የሚል ስያሜ ሲሰጠው እንሰማለን። አንደኛ ግን ተቀራራቢ ሁለተኛ አለበት። እርሱ ግን ብቻውን ኃይለኛ ነው። በእርሱ ታላቅነት ፊት ፍጥረት ሁሉ እንደ እንግጫ ዝቅ ዝቅ ይላል። እንደ ሕጉ ቢሆን ዮሐንስ በምድረ በዳ የሚጮህ ሳይሆን በመቅደስ የሚሠዋ ነበር። ብቻውንም የሚኖር ሳይሆን በካህናትና በሚራዱ ሌዋውያን ተከብቦ የሚኖር ነው። ክርስቶስን ግን ያገኘው በሞቀው መቅደስ ሳይሆን ጭው ባለው በረሃ ነው። ዮሐንስ በክህነት መንገዱ ቢሄድ ኖሮ ኃጢአትን የሚያዳፍኑ መሥዋዕቶችን ያቀርብ ነበር። አሁን ግን ኃጢአትን የሚያስወግደውን በግ ሰበከ። ዮሐንስ ወደ እርሱ የሚመጡትን ወደ ጌታችን ይመራ ነበር። ይህ እምነት ነው። ይስሐቅ ወደ አብርሃም መጣ፣ አብርሃምም ወደ እግዚአብሔር ሸኘው። መልሶ አገኘው። ሰዎች የእኛ ወይስ የክርስቶስ ወዳጅ ናቸው? የእኛ ወዳጆች የክርስቶስ ወዳጆች ላይሆኑ ይችላሉ። የክርስቶስ ወዳጆች ግን የእኛ ወዳጆች መሆናቸው አይቀርም። እርሱ የሚያስተምረው ፍቅርን ነውና።



ዮሐንስ በታላቅ ቅድስና የኖረ ነው። ነገር ግን በመጨረሻ አንገቱ ተቆረጠ። ትልቅ ደግነት ትልቅ መከራ ሊያመጣ ይችላል። እውነተኛ ደግነት በመከራ ውስጥም የሚቀጥል ደግነት ነው።


ዮሐንስ የእግዚአብሔር በግ በማለት ለአይሁድ፣ ለተነሣህያንና ለደቀ መዛሙርቱ ተናገረ። በብሉይ ኪዳን ብዙ ሺህ መሥዋዕቶች ቀርበዋል። ነገር ግን ምሕረት አልተገኘም። ሰሎሞን እንኳ በመቅደሱ ምርቃት ቀን በአንድ ቀን 22ሺህ በሬዎችንና 120 ሺህ በጎችን አቅርቧል /1ነገሥ. 8፡63/። በእነዚህ ሁሉ መሥዋዕቶች ግን የሰማይ ደጅ ሊከፈት አልቻለም። ወይ ከገንዘባቸው ወይም ከመልሱ አልሆኑም። በዚህ ሁሉ ድካማቸው ግን የሚያጽናናቸው ክርስቶስ እንደሚመጣ ማሰባቸው ነው። በዚህ ዓለም ላይ የብክነት በጀቶች ይኖራሉ፣ የምንረጋው ግን ክርስቶስን ስናገኝ ነው። ከብዙ ሙከራዎችና ትርምሶች የሚያድነው ክርስቶስ ነው። ትላንት እንደ ፈረሰኛ ወንዝ ይጋልብ የነበረው ኃጢአት በክርስቶስ ታገደ፣ ዛሬም እንደ ፈረሰኛ የሚጋልበውን መከራ ክርስቶስ በምጽአቱ ይገድበዋል። ዮሐንስ ይህን መልካም መፍትሔ፣ ይህን መልካም ገበያ፣ ይህን መልካም ማትረፊያ፣ ይህን መልካም ወዳጅ ለደቀ መዛሙርቱ አሳያቸው። የእጁን ቀስት ተመልክተው ጌታን ተከተሉት። ጌታም ምን ትፈልጋላችሁ? በማለት እርሱ በመፈለግ መከተል እንዳለባቸው ተናገረ። እርሱ ሁሉንም ያፈቅራል፣ ከወደደ መጥላት አይሻም። ግን ማንንም አያባብልም። ሰዎች ዋጋ ተምነው እንዲከተሉት ይፈልጋል። ዮሐንስ ከዚህ በኋላ ይጣላል ማለት አይደለም። የሚጮህ ሰው የሚጮህለት ነገር ሲደርስ ያርፋል። ዕረፍት ያገኛል። እግዚአብሔር ማንንም ተጠቅሞ አይጥልም።


አራቱም ወንጌላት ስለ ደቀ መዛሙርቱ ጥሪ በተለያየ መንገድ ዘግበዋል። ጌታን ወስነው ለመከተል የዮሐንስ መጥምቅ ትምህርት፣ ጌታ ያሳያው ተአምራት፣ የዮሐንስ ጥቆማ፣ የእንድርያስ ጥሪ አስተዋጽኦ አድርገዋል። “ሰዓቱ ሲደርስ አምባ ይፈርስ” እንዲሉ ሰዓቱ ደርሶአልና ድምፅ በዛባቸው። ተአምራት አዩ። ጌታን እሺ ብለው የተከተሉባት ያች ቀን ግን የተለወጡባት ቀን ናት። የጌታችን ደቀ መዛሙርት የተለያየ ስብጥር ነበራቸው። የነገድ ስብጥራቸው ከአሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ነበር። የመጀመሪያይቱ ማኅበር እስራኤል በአሥራ ሁለቱ ነገድ ተመሠረተች። አዲሲቱ ቤተሰብ ቤተ ክርስቲያንም በአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አእማድነት ተመሠረተች።


👉 @mehereni_dngl
👉 @mehereni_dngl
መሐርኒ ድንግል pinned «የዮሐንስ ወንጌል ትርጓሜ /ክፍል 57/ እውነተኛ ስጦታ “ከዮሐንስ ዘንድ ሰምተው ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበረ” /ዮሐ. 1፡41/። መጥምቁ ዮሐንስ የክርስቶስን ታላቅነት ገለጠ። ክብሩ ከክርስቶስ ክብር እንደሚበልጥ የሚያስቡ ነበሩና እኔ የጫማውን ጠፈር እንኳ መፍታት አይቻለኝም አለ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቻ የሌለው በመሆኑ ከእርሱ ቀጠሎ የሚባልለት…»
#ጥቅምት (፲፩) 11/02/2014 ዓ.ም

✝️✝️✝️በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✝️✝️✝️

✝️ዘነግህ✝️
✝️#ምስባክ✝️
መዝ ፻፲፰፥፹፮(118፥86)
በዐመፃ ሰደዱኒ ርድአኒ
ሕቀ ከመ ዘእምደምሰሱኒ ውስተ ምድር
ወአንሰ ኢኀደጉ ትእዛዘከ


✝️#ወንጌል✝️
ወንጌል ዘሉቃስ ፳፥፱-፲፯(20፥9-17)
ወአኀዘ ይመስል ሎሙ…


✝️#ምንባባት_ዘቅዳሴ✝️

✝️#ዲያቆን✝️
✝️ኀበ ጢሞቴዎስ ፩ ም ፬፥፱-፲፮(4፥9-16)
እሙን ነገሩ ወርቱዕ ይትወከፍዎ…


✝️#ንፍቅ_ዲያቆን✝️
✝️ያዕቆብ ፫፥፩-፭(3፥1-5)
ወኢይኩኑ እምውስቴትክሙ…


✝️#ንፍቅ_ካህን✝️
✝️ግብረሐዋርያት ፳፥፳፰-፴፩(20፥28-31)
ወይእዜኒ ዕቀቡ ርእሰክሙ…



✝️#ምስባክ_ዘቅዳሴ✝️
እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ
ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል
ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን


✝️#ትርጉም✝️
መዝሙረ ዳዊት ም. ፹፬ ቊ. ፮ - ፲፪

፮ በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወሰነው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና።

፯ ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ፤ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።


✝️#ወንጌል_ዘቅዳሴ✝️
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፭ ቊ. ፲፩ - ፲፯

፲፩ ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።

፲፪ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።

፲፫ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።

፲፬ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።

፲፭ መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።

፲፮ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።

፲፯ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።



#ቅዳሴ ✝️ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)✝️


✝️መሐርኒ ድንግል✝️
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
2024/11/15 18:00:18
Back to Top
HTML Embed Code: