Telegram Web Link
Tik tok account ነው የተለያዩ አርቶዶክስ ነክ ነገሮችን ያገኛሉ follow & copy Link እዳይረሳ እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባረክ
መሐርኒ ድንግል pinned «tiktok.com/@mehereni_dngl»
Channel photo updated
#ትሕትና 

በትክክል ትሑት የኾነ ሰው ማን እንደ ኾነ ማወቅ ትወድዳለህን? በእውነት ያለ ሐሰት ትሑት የነበረውን ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስን ተመልከት፡፡ መምህረ ዓለም፣ መንፈሳዊ አንደበተ ርቱዕ፣ ንዋይ ኅሩይ፣ ወጀብ የሌለበት ወደብ፣ የማይናወጽ ግንብ፣ በአካለ ሥጋ ትንሽ ሲኾን አክናፍ እንደ ተሰጡት ኾኖ ምድርን ኹሉ ያካለለውን ጳውሎስን ተመልከት፡፡ ያልተማረው ግን ደግሞ የተራቀቀውን፣ ድኻ ግን ደግሞ ባለጠጋ የኾነውን ይህን ቅዱስ ሰው ተመልከት፡፡ እልፍ ጊዜ መከራዎችን የተቀበለው፣ አእላፋት ጊዜ ዲያብሎስን ድል የነሣው፣ “ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም፤ ከኹላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ” ብሎ የተናገረው ተወዳጅ ጳውሎስን በእውነት ያለ ሐሰት ትሑት ነው ብዬ እጠራዋለሁ (1ኛ ቆሮ.15፡10)፡፡ ብዙ ጊዜ መታሰርን፣ ብዙ ጊዜ መገረፍን፣ ብዙ ጊዜ በድንጋይ መወገርን፣ [ከበረኻ አራዊት ጋር መጋደልን፣ በባሕር ውስጥ ለሦስት ቀናት ሲዋኝ ውሎ ሲዋኝ ማደርን፣ ቀንና ሌሊት ብዙ ጦምን፣ በብርድና በራቁትነት መኾንን] የታገሠ የተቀበለ፣ በመልእክታቱ ዓለምን በወንጌል መረብነት ያጠመደ፣ ከሰማያት በመጣ ሰማያዊ ቃል የተጠራው እርሱ ራሱን ዝቅ አድርጎ፡- “እኔ ከሐዋርያት ኹሉ የማንስ ነኝ” ያለውን ብፁዕ ጳውሎስ አማን በአማን ትሑት ነው ብዬ እጠራዋለሁ (2ኛ ቆሮ.11፡23-27)፡፡

እንግዲህ የቅዱስ ጳውሎስን የትሕትናው ታላቅነት ታያለህን? ራሱን ዝቅ አድርጎ ታናሽ ነኝ ሲል ትመለከታለህን? “እኔ” አለ ቅዱስ ጳውሎስ፥ “ከሐዋርያት ኹሉ የማንስ፤ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ ነኝ፡፡” በትክክል ትሕትና ማለት ይህ ነው - በኹሉም ረገድ ራስን ዝቅ ማድረግ! ራስን እንደ ታናሽ መቊጠር! እነዚህን ኃይላተ ቃላት የተናገራቸው ማን እንደ ኾነ በነቂሐ ልቡና በሰቂለ ሕሊና ኾነህ አድምጥ! የሰማይ ሰው የምድር መልአክ የሚኾን ጳውሎስ፣ የአብያተ ክርስቲያናት ዓምድ የሚኾን ጳውሎስ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስን እጅግ አብልጬ የምወደውም ለዚህ ነው፡፡ ምግባር ትሩፋት ሥጋ ለብሳ ሥግው ኾና ተውባ ተሞሻሽራ የማያት በእርሱ በብፁዕ ጳውሎስ ዘንድ ነውና፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ፊት በዓይነ ሕሊናዬ ተቀርፆ የሚሰጠኝን ተድላ ደስታ ያህል የብርሃን ጮራዋን የምትለግሰው ፀሐይ ለዓይኖቼ ደስታን አትሰጠኝም፡፡ ምክንያቱም ይህቺ ፀሐይ የሥጋ ዓይኖቼ በብርሃን እንዲያዩ ታደርጋቸዋለች፤ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ ግን ዓይነ ልቡናዬ አክናፍ ኑሮት ወደ ሰማየ ሰማያት እንድወጣ ያደርግልኛል፡፡ ነፍስን ከፀሕይ ይልቅ ጽድልት፣ ከጨረቃም ይልቅ ልዕልት እንድትኾን ያደርጋል፡፡ የምግባር የትሩፋት ኃይሏ ሥልጣኗ ይህን ያህል ነውና - ሰውን መልአክ ታደርገዋለች ፡፡ ነፍስ አክናፍ አውጥታ ወደ ሰማየ ሰማያት እንድትበር ታደርጋለች፡፡ ተወዳጅ ጳውሎስም የሚያስተምረን ይህንን ነው - ምግባርን ! ስለዚህ ነቅተን ተግተን በምግባሩ አብነት እናደርገው፤ እርሱን እንምሰል፡፡

(ከገብረ እግዚአብሔር ኪደ "#ንስሓና_ምጽዋት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው "  መጽሐፍ የተቀነጨበ)

የቴሌግራም ቻናላችን 👉 @mehereni_dngl
👉 @mehereni_dngl

የቲክቶክ ቻናችን follow እዳይረሳ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
tiktok.com/@mehereni_dngl
✝️✝️✝️✝️

ከዛሬ ጀምሮ !

ቅዱስ አባ ጳውሊ ሰይጣንን አስሮ የሰው ልጆችን እንዴት እንደሚያስት የተንኮል ስራውን ሁሉ ያናገረበት በሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞአ አንድነት ገዳም ተተርጉሞ የተዘጋጀው "ከሰይጣን ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ በተከታታይ ክፍሎች መቅረብ እንደሚጀምር እናሳውቃለን፡፡

መሐርኒ ድንግል

👉 @mehereni_dngl
ዛሬ ማታ 3:00 የአባ ጳውሊን ታሪክ ክፍል አንድን እናቀርባለን 👉 @mehereni_dngl
#አዲስ_ዜና

ውድ የቻናላች ተከታዮች Admin ስለሚያስፈልገን ስለኦርቶዶክስ አስተምሮ ለምሳሌ ፦ መዝሙር ፣ምስባክ ፣ ገድለ ቅዱሳን ፣ እና የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ለwallpaper እና ለprofile picture የሚሆን ፎቶግራፍ እና ሰዕል የሚሆኑ እና የተለያዩ ኦርቶዶክስ ነክ ነገሮችን የምታቀርቡ ከሆነ Admin እንሰጣለን

በውስጥ መስመር ያናግሩን
👇👇👇👇👇👇👇👇
@mehereni_dngl_bot
@mehereni_dngl_bot


ኦርቶዶክስ ትቀጥላለች #መሐርኒ_ድንገል
መሐርኒ ድንግል
ዛሬ ማታ 3:00 የአባ ጳውሊን ታሪክ ክፍል አንድን እናቀርባለን 👉 @mehereni_dngl
ውድ የቻናላችን ተከታዮች ትላንት ማታ 3:00 እንለቃለን ያልነውን ታሪክ የአባታችን የአባ ጳውሊ ክፍል አንድ ዛሬ 3:30 እንለቃለን
ቅዱስ አባ ጳውሊ ከሰይጣን ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ!

👉 @mehereni_dngl

መግቢያ

👉 @mehereni_dngl


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

ይህንን ዓለም ከአለመኖር ወደ መኖር በአመጣና ፍጥረታትን ሁሉ በፈጠረ የአዳምንም ልጆች ሁሉ ጠላት ሰይጣንን ድል በሚያደርግ በአካል ሦስት በመለኮት አንድ በሚሆን በእግዚአብሔር ስም ንጹሕና ጻድቅ ቅዱስ የሚሆን ተጋዳይ መነኩሴ ካህን አባ ጳውሊ በየጊዜው ሰውን ሁሉ ከሚዋጋ ይልቁንም ሴቶችና ወንዶች ለክፉ ኃጢአት ወደ ዳንስ ጭፈራ ቤት በአንድነት እንዲሄዱ ከሚያደርግ ከሰይጣን ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ይህ ነው፡፡ የአባ ጳውሊ ጸሎቱና በረከቱ የፈጣሪያችን የእግዚአብሔር የይቅርታውንና የፍቅሩ ጥበቃ ከሁላችን ከሕዝበ ክርስቲያን ጋር ይሁን አሜን፡፡
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ቀጣዪን ሁልም ሰው እንዲመለከት ቻናሉን #share አርጉ

👉 @mehereni_dngl
👉 @mehereni_dngl
ቅዱስ አባ ጳውሊ ከሰይጣን ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ!

👉 @mehereni_dngl

ክፍል-1(፩)

👉 @mehereni_dngl

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

ቅዱስ አባ ጳውሊ በጸሎቱ አስሮ ከሰይጣን ጋራ ያደረገው ቃለ ምልልስ እንዲህ ነው፡፡
ልዩ ስሟ ሰሉቅያ (አስቀሎና) በምትባል በሳምር ሀገር እንዲህ ሆነ፡፡ ሰዎቿ ከሄሮድስ ወገን የሚሆኑ ኃጢአተኞችና ክፉዎች ነበሩ፡፡ ሴቶችም ወንዶችም ተሰብስበው በየጊዜው በየወሩ ወደ ጭፈራ ቤት የመግባት ክፉ ልማድ ነበራቸው፡፡ መነኩሴ የሆነ ቀሲስ ቅዱስ አባ ጳውሊ እድሜው ፲፭ ዓመት የሆነው አንድ ዲያቆን መነኩሴ አስከትሎ ከዚያች ሀገር ደረሰ፡፡ ቀኑም ረቡዕ ነበር፡፡

በዚያን ጊዜ እንደ እርሱ ለገዳሙ ሥራ ተልከው ከወጡ ከመነኮሳት ወንድሞቹ ጋር በመንገድ ተገናኘ፡፡ ጥቂት እንደሄዱ ጊዜው መሸ በአንድ ቦታም አደሩ፡፡
በዚያ ቀን የዚያች ሀገር ሰዎች ሴቶቹም ወንዶችም ተሰብስበው ወደ አንዲት ጭፈራ ቤት ሲሄዱ ባየጊዜ ቅዱስ አባ ጳውሊ የእነዚህን ሰዎች የኃጢአት ሥራ ባደረበት ጸጋ እግዚአብሔር አውቆ ፈጽሞ አዘነ፡፡

ወደ ጭፈራ ቤት ከሚሄዱት አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለው፡፡ ሰማይና ምድርን ባሕርና የብስን ፀሀይና ጨረቃን ከዋክብትን የፈጠረ እግዚአብሔር እያለ እርሱን ትታችሁ ይህን ክፉ ሥራ ለምን ትሠራላችሁ ? ወደ ዳንስ ቤት ከሚስቶቻችሁና ከልጆቻችሁ ጋር ለምን ትገባላችሁ አለው፡፡
ያም ሰው እንዲህ አለው፡፡ በመኝታን ከሚስቶቻችን ጋር አንድ እንደምንሆን በዳንስ ቤትም ከሴቶች ጋር አንድ እንሆናለን አለው፡፡ አባ ጳውሊም ማንን እንደምታመልኩ እስቲ ንገረኝ አለው፡፡ እኛ ከሄሮድስ ወገን ነን፡፡ የምናመልከውም ከቀደሙ አባቶቻችን ያገኘነውን ጣዖት ነው አለው፡፡ ያም ሰው ወደ ወንድሞቹ ሄዶ ከዳንስ ቤት ገባ፡፡
✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#share

👉 @mehereni_dngl
👉 @mehereni_dngl
መሐርኒ ድንግል pinned «ቅዱስ አባ ጳውሊ ከሰይጣን ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ! 👉 @mehereni_dngl ክፍል-1(፩) 👉 @mehereni_dngl በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡ ቅዱስ አባ ጳውሊ በጸሎቱ አስሮ ከሰይጣን ጋራ ያደረገው ቃለ ምልልስ እንዲህ ነው፡፡ ልዩ ስሟ ሰሉቅያ (አስቀሎና) በምትባል በሳምር ሀገር እንዲህ ሆነ፡፡ ሰዎቿ ከሄሮድስ ወገን የሚሆኑ ኃጢአተኞችና ክፉዎች ነበሩ፡፡ ሴቶችም…»
"ሁለት ወይም ሶስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁ"
(የማቴዎስ ወንጌል 18:20)

የመሐርኒ ድንግል YouTube channel ነው Subscribe አርጉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@mehereni_dngl
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ፀሎት ሙሉን ስሙት
ከአባ ገብረ ኪዳን የተወሰደ ስብከት

Telegram channel
👇👇👇👇👇👇
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl

tik tok channel
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
tiktok.com/@mehereni_dngl
tiktok.com/@mehereni_dngl

YouTube channel
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@mehereni_dngl
https://www.youtube.com/@mehereni_dngl
መሐርኒ ድንግል pinned «"ሁለት ወይም ሶስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁ" (የማቴዎስ ወንጌል 18:20) የመሐርኒ ድንግል YouTube channel ነው Subscribe አርጉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://www.youtube.com/@mehereni_dngl»
ቅዱስ አባ ጳውሊ ከሰይጣን ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ!

👉 @mehereni_dngl

ክፍል-2(፪)

👉 @mehereni_dngl

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

ያ ሰው ወደ ባልንጀሮቹ ከሄደ በኋላ አባ ጳውሊ ከእርሱ ጋር ያለውን ዲያቆን እንዲህ አለው፡፡ ወንድሜ የዚህች ሀገር ሰዎች ኃጢአታቸው ታላቅ ነው አለው፡፡
ሌሊት በሆነ ጊዜ በመንገድ የተገናኛቸው መነኮሳቱና ዲያቆኑ ተኝተው ሳለ አባ ጳውሊ ቀስ ብሎ ተነስቶ እየጸለየ ወደዚያ ዳንስ ቤት ከበር ቆመ ፤ ራቁታቸውን ሆነው ባየ ጊዜ ፈጽሞ አዘነ ፤ ጽኑዕ ልቅሶም አለቀሰ፡፡ ባለ ዳንስ ቤቱም ከውጭ ቁሞ ባየው ጊዜ ከሰዎች ጋር ወደ ዳንስ ቤቱ ያልገባኸው ለምንድነው ብሎ ጠየቀው፡፡ እርሱም በሆነ ምክንያት እንዳልገባ ነገረው፡
ከዚህ በኋላ የዳንስ ቤቱ ባለቤት ወደ ውስጥ ገባ፡፡ በገባም ጊዜ የዳንስ ቤቱን በር ዘግቶ መብራቱን አጠፋ፡፡ ያን ጊዜ አባ ጳውሊ በልቦናው እያዘነና እየጸለየ በምድር ላይ ይሰግድ ጀመር፡፡ በዳንስ ቤቱ ውስጥ ያሉት ሰዎች በዱር እንዳሉ እንደጠገቡ ፈረሶች ሲጮኹ ሰማቸው፡፡

አቤቱ ድንቅ ተአምራትን የምታደርግ አንተ ነህ፡፡ ስለቀደሙ ሰዎች ኃጢአት የጥፋት ውሃን በምድር ላይ ያመጣህ አንተ ነህ (ዘፍ. ፯:፲፯)፡፡ ስለ ኃጢአታቸውም ክፋት በሰዶምና በገሞራ ላይ እሳትን ያዘነምክ አንተ ነህ፡፡ (ዘፍ.፲፱፥፳፬)፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ለሌሎች የኃጢአት አብነት እንዳይሆኑ ታጠፋቸው ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ መዓትህንም በላያቸው ላይ ፈጥነህ አድርግ ፣ አጥፊ የሆነውንም ሰይጣን በኃይልህ አጥፋው እያለ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡

እግዚአብሔርም ጸሎቱንና ልመናውን ሰማው፡፡ ጸሎቱንም ከጨረሰ በኋላ ሰይጣን ጥቁር ሰው መስሎ እንደ እሳት የሚንቦገቦግ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ራቁቱን ከዳንስ ቤት ሲወጣ ታየው፡፡
ያም ሰይጣን በማስፈራራት ከዳንስ ቤቱ በር ቆመ፡፡ አባ ጳውሊም አንተ ማነህ? ማንን ትፈልጋለህ? ሰይፍህ በእጅህ የተመዘዘው ለምንድን ነው? አለው፡፡
ሰይጣንም የምትሻውን ንገረኝ ጠይቀኝ እንጂ አንተ ማነህ አትበለኝ፡፡ ከፈጣሪህ ከጌታህ የለመንከውን አንተ ታውቃለህና አለው፡፡
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#share

👉 @mehereni_dngl
👉 @mehereni_dngl
2024/09/27 07:17:25
Back to Top
HTML Embed Code: