Telegram Web Link
የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በፎቶ
በዛሬው ዕለት እየተከበረ በሚገኘው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ የማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን "ሰላምህን ስጠን" በሚል ርእስ የተዘጋጀ ዝማሬ አቅርበዋል።
በማኅበረ ቅዱሳን የከሚሴ ወረዳ ማእከል የ2017 ዓ.ም በዓለ መስቀል ከከሚሴ ማረሚያ ቤት ታራሚዎች ጋር አከበረ።

የከሚሴ ወረዳ ማእከል ሰብሳቢ የሆኑት ዲ/ን ወርቁ ጌቶ ለታራሚዎች ባስተላለፉት መልእክት ተስፋንና ጽናት ተጎናጽፈው ሊኖሩ እንደሚገባና ወረዳ ማእከሉም የጸሎትና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

ወረዳ ማእከሉ በዓሉን ከታራሚዎች ጋር ያሳለፈው ለ7ኛ ጊዜ ሲሆን በየዓመቱ ከሌሎች መንፈሳዊ ማኅበራት፤ሰንበት ትምህርት ቤቶ ችና አጋር አካላት ጋር በመተባበር የመስቀል ፤ የልደት፤ የትንሳኤና የጥምቀት በዓልን አብሮ ያከብራል።

ታራሚዎች ወረዳ ማእከሉ በዓሉን ከነርሱ ጋር በማሳለፉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በየክብረ በዓሉ ብትጎበኙንና መዝሙርም ብታስጠኑን ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

በዕለቱ የማእከሉ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የወረዳ ማእከሉ ዘማሪዎችና መምህራነ ወንጌል ተገኝተዋል።
በማኅበረ ቅዱሳን ሎጊያ ማእከል ጠቅላላ ጉባኤውን አከናወነ፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን ሎጊያ ማእከል የ28ኛ ዓመት 25ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ከመስከረም 18 እስከ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ አከናውኗል።

 ጉባኤው ከአፋር ሀገረ ስብከት፤ ከአጥቢያ ቤተክርስቲያን ፤ ከሰንበት ት/ቤት፤  ከበጎ አድራጎት ማኅበራት የተወጣጡ ልዑካን በተገኙበት በጸሎተ ወንጌል ተከፍቷል፡፡ 

ማእከሉ 5 ወረዳ ማእከላት፤ 4 ግቢ ጉባኤያት፤ 3 ግንኙት ጣቢያዎች እና 1 የንዋየ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ እንዳሉት ሪፖርት በቀረበበት ወቅት ተመላክቷል፡፡

 በዓመቱ የማእከሉ ዕቅድ አፈጻጸም ላይ  ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት፤ ለማረሚያ ቤቶች፤ ለግቢ ጉባኤያት የወንጌል ትምህርት እንደተሰጠ፤ በግቢ ጉባኤያት ደረጃ-1 ተተኪ መምህራን ለ 45 ሠልጣኞች መስጠቱ፤ እንዲሁም በአዋሽ ወረዳ ማእከል አንድ ግቢ ጉባኤ ማቋቋም መቻሉ ተገልጧል፡፡  

በተጨማሪም ግቢ ጉባኤ ሊያስተምሩ የሚችሉ 14 መምህራንንም በ2016 ዓ.ም በተሠጠ ሥልጠና ማፍራት እንደተቻለም ተገልጿል፡፡

ማእከሉ የአገልጋይ  ፍልሰት እና እጥረት፣ ቋሚ ገቢ አለመኖር እና የአከባቢው የአየር ንብረት ሁኔታ ፈተና እንደሆኑበት በሪፖርቱ አስገንዝቧል።

በጉባኤው ላይ ከ58 በላይ ልዑካን ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
2024/09/30 00:38:27
Back to Top
HTML Embed Code: