ኦርቶዳካሳዊ እሳቤ በማጎልበት ዓላማ ያለው ሰው ማፍራት እንደሚገባ ተገለጸ
ሰኔ ፲፫/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን ደሴ ማእከል ለግቢ ጉባኤያት የደረጃ ሁለት ተተኪ አመራር ሥልጠና እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ሥልጠናው ለተከታታይ 7 ቀናት የሚቆይ እንደሆነም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የነበራት፣ ያላትና ሊኖራት የሚገባ የመሪነት ሚና ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየተሰጠ ያለው ሥልጠናው የሴኩላሪዝም ተጽእኖ ከኦርቶዳካሳዊነት እሳቤና ኑሮ አንጻር በሥልጠናው የተዳሰሰ እንደሆነም ተመላክቷል።
የማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት ፣ የአኃትና የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ተሞክሮ ኦርቶዶክሳዊ ሕይወትና ክህሎት በሥልጠናው ትኩረት የተደረገባቸው ርእሰ ጉዳዮች ሲሆኑ ኦርቶዶክሳዊ እሳቤን በማጎልበት ዓላማ ያለው ሰው ማፍራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም የቤተክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳዮች ፣ የቡድን መሪነት እንዲሁም ማኅበራዊ አገልግሎት በሥልጠናው ትኩረት የተደረገባቸው ጉዳዮች እንደሆነም ተገልጿል።

❤17
#የሰኔ ወር ሐመር #መጽሔት በሁሉም የማኅበረ ቅዱሳን ሱቆች በሥርጭት ላይ ትገኛለች ።!
#የሰኔ ወር ሐመር #መጽሔት ሥርጭት ላይ መሆኗን ያውቃሉ ?? #በውስጧ ምን ይዛለች ? ሙሉውን #ሐመሯን መጽሔቷ በቅርብ ባሉ ሱቆች ገዝተው ያንብቡ ያስነብቡ!
የሰኔ ወር ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን "#ሁሉም የክርስቶስን እውነት #በቋንቋቸው ይሰሙ ዘንድ እንትጋ ››
.#ዐውደ ስብከት ሥር” #የንስሓ አባትና ልጅ ግንኙነት ከየት ወደ የት?
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “#የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ክፍል _፪
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “# የቅዱሳን ኅብረት
"#ማኅበራዊ በክርስትና _#ኦርቶዶክሳውያን በማኅበረሰብ ውስጥ ቦታችን የት ነው _ክፍል _፪"
• #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#የደብረ ብርሃን ደብረ ገነት ቅዱስ ዑራኤልና አኔቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን _ክፍል ፪"
• #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር “ "ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን ህልውና #ምንጩን ማጥራትና መጠበቅ "
ክፍል _፪
#በኪነ ጥበብ ዐምድ #ከፍቅረኛህ ጋር ታረቅ " በሚል ታስነብባለች ።
• #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “#ቤዛና ቤዛነትን” በተመለከተ ክፍል _፪ ላይ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገን ምላሽ አዘጋጅተናል።
ሐመር መጽሔት #፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፮ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
Magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል

❤10
በደቡብ ማእከላት ማስተባበሪያ አዘጋጅነት በወላይታ ሀገረስብከት በሚገኘው ካህናት ማሠልጠኛ ለስድስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የደረጃ ሁለት ተተኪ አመራር ሥልጠና መጠናቀቁ ተገለጸ።
ሰኔ ፲፬/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን ደቡብ ማእከላት ማስተባበሪያ አዘጋጅነት ከተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ለተዉጣጡ ለግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ለስድስት ተከታታይ ቀናት እየተሰጠ የቆየው የደረጃ ሁለት ተተኪ አመራር ሥልጠናና ውይይት በዛሬው ዕለት ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ በተገኙበት የማጠቃለያ መርሐ ግብር በርእሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም መከናወኑ ተገልጿል ።
ሠልጣኞች ከአርባ ምንጭ ፣ ከወላይታ ፣ ከጂንካ ፣ከሆሳዕና ማእከላት የተወጣጡ ቁጥራቸው ከ50 በላይ እንደሆኑ ተጠቁሟል ።
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የመሪነት ሚና ትላንት፣ ዛሬና ነገ ፣ ኦርቶዶክሳዊነት ሕይወቱና ክህሎቱ ፣የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ተሞክሮ፣ ሴኩላሪዝም ከኦርቶዶክስ እሳቤና ኑሮ አንጻርና ሌሎች ሥልጠናዎች እንደሰጠም ተመላክቷል።
በዛሬው ዕለት በተካሄደው በማጠቃለያ መርሐግብር የወላይታ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ " የተካሄደው ሥልጠና እጅግ ጠቃሚ የሆነና ሊበረታታ የሚገባው መሆኑን ጠቅሰው " የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው በማለት ሠልጣኞች በተሰጠው ሥልጠና እግዚአብሔርን በመፍራት፣ ሕይወታቸውን በመምራት፣ መክሊታቸውን በማትረፍ በሚሄዱበት ሁሉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን፣ ወላጆቻቸውንና አገራቸውን እንዲያገለግሉ የአደራ መልእክትና አባታዊ ቡራኬ ሰጥተዋል።

❤9
የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ግቢ_ጉባኤ ያስተማራቸዉን ተማሪዎች ብፁዕ አቡነ እንጦንስ በተገኙበት አስመረቀ
ሰኔ ፲፮/፳፻፲፯ ዓ.ም
የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ለአራትና አምስት አመታት ያስተማራቸዉን 225 ተማሪዎችን የምዕራብ ሐረርጌ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ በተገኙበት አስመርቋል።
ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ቃለ እግዚአብሔርን መሰረት በማድረግ ፣ ህገ ቤተ ክርስቲያንን በመጠበቅ ቤተ ክርስቲያንንና ሀገርን ማገልገል ይጠበቅባችኋል በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።
አክለውም አገልግሎታችሁም ሁሉ በፍቅር መሆን አለበት ያሉ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚገኙ ወጣቶች ላይ ሥራ እየሠራ በመገኘቱም አመስግነዋል።
የጭሮ ማእከል ሰብሳቢ ዲ/ን ዳንኤል ሞገስ እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚገኙ ተማሪዎች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እደሚገኝ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ለተመራቂ ተማሪዎች የአደራ መስቀል የሰጡ ሲሆን ከተመራቂዎች መካከል ከፍተኛ ነጥብ በማምጣት በሜዳሊያ ለተመረቁ አራት ተማሪዎች ዕዉቅናና ሽልማት ተበርክቷል።

❤5