Telegram Web Link
ማኅበረ ቅዱሳን ከሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጋር በመተባበር ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ልዩ ሥልጠና አዘጋጅቷል።
ሰኔ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ የሚሰጠውን ሥልጠና ከሥር በተቀመጠው የቴሌግራም አድራሻ ላይ መከታተል ይችላሉ።
@MKFOR12TH
3👍3🕊1
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባሏት ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች ላይ አጋር አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ግንቦት ፴/፳፻፲፯ ዓ.ም

የቅድስተ ቤተ ክርስቲያን በርካታ አገልግሎት በሁለም ዘርፎች እንዲሰፋ፣እንዲጎለብት እና እንዲያድግ አቅም እና ገንዘብ ያላቸው ምእመናን  መሳተፍ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡ 

የተለያዩ ገዳማት እና አብያተ ክርስቲያናት ለሚያስፍልጋቸው ድጋፍ እገዛ በማድረግ እና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማስፋፋት ረገድ በግልም ሆነ በኮሚቴ አቅም እና ገንዘብ ካላቸው ባለሀብት ጋር አብረው እየሠሩ መሆናቸውን በግል የሥራ ዘርፍ የተሰማሩት ወ/ሮ ሜሮን ታደለ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በግለሰብ ደረጃ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመለሱ በማድረግ፣በክረምት ወቅት ለሕጻናት፣ለአዳጊዎች  እና ለወላጆች የተለያዩ መንፈሳዊ ሥልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም ከተቋማት ጋር በመተባበር  በሴቶች እና በሕጻናት ላይ ሥራችዎን እየሠሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

ወ/ሮ ሜሮን አክለውም ከባለሀብቶች በተጨማሪ ሌሎች ምእመናን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያላቸውን ጊዜ እና ገንዘብ እንዲያበረክቱ ከማድረግ በፊት ራሳቸውን እንዲሰጡ ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

አሁን ያለው የተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲሰፋ  የምእመናንን ጎዶሏቸውን ማገዝ እንዲሁም መሳተፍ የሚችሉበትን ዕድል እና ሁኔታ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ወ/ሮ ሜሮን አያይዘው አንስተዋል፡፡

ትንሽ በመስጠት ብዙ ለማትረፍ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባሏት ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች ላይ ባለሀብቶች በመሳተፍ ኀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባቸው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
6
ማኅበረ ቅዱሳን ለወጣቶች የሱስ ማገገሚያ ተቋም ለማቋቋም የሚያስችል ጥናታዊ የምክክር ጉባኤ አካሄደ

ግንቦት ፴/፳፻፲፯ ዓ.ም

"ማኅበራዊ ቀውስን በማከም ትውልድን እንታደግ"  በሚል መሪ ቃል ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደው ጉባኤ በማኅበረ ቅዱሳን ሙያ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት  ከባለድርሻዎች ጋር ሰፊ ጥናታዊ ሰነድን መነሻ ያደረገ ምክክር ተደርጓል።

በአሁኑ ወቅትም በአገራችን ኢትዮጵያ 46 ከመቶ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ለሱስ (በአልኮል፣ ጫት ወይም የሲጋራ) ተጠቂ ሁነዋል ተብሏል። በተመሳሳይ የንጥረ ነገርም ይሁን የባሕሪ ሱስ የተጋላጮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ስለመሆኑ ተነግሯል።

በዳሰሳ ጥናቱ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች በንጥረ ነገር ሱስ ከመጠቃታቸው ባሻገር ሲሶ የሚሆኑት የኢንተርኔት ሱስ ተጠቂ ናቸው ተብሏል። ይህም ብቻ ያይደለ በጥናቱ  የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎቹም ማኅበራዊ የመገናኛ አውታር መጠቀም የማይችሉበት አጋጣሚ ከተፈጠረ ጭንቀት እንደሚፈጥርባቸው አምነዋል ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጥናቱ 52 ከመቶ ገደማ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በተለያዩ የሱስ አምጭ ንጥረ ነገሮች አማካኝነት የሱስ ተጠቂ ሁነው መገኘታቸው የተገለጸ ሲሆን  ከቤተክርስቲያናችን ምእመናን ውስጥ 50 ከመቶ ገደማ የሚሆኑትም ለተለያዩ ሱሶች ተገዢ መሆናቸው ተጠቅሷል።

በማያያዝም ምእመናን በሱስ ምክንያት የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ለመፈጸም እንደሚቸገሩ ነው የተነሳ ሲሆን ቁጥር ልክ የሱሰኛ ወገኖቻችን ቁጥር መጨመሩ ለአገራችን እና ለቤተክርስቲያናችን እጅግ አሳሳቢ ነው ተብሏል።
14👍1
የንጥረ ነገርም ይሁን የባሕሪ ሱስ ተጠቂ የሆኑ ግለሰቦች የአካልና የአእምሮ ጤናቸው ከመታወኩ ባለፈ ሱሰኝነት በማኅበራዊ ሕይወት ፤ በሰላም እና ደህንነት ብሎም በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳርፈው ጠባሳም ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ተመላክቷል።

ታዲያ ለቤተክርስቲያናችን ብሎም በአገር ደረጃ አሳሳቢ ለሆነው ሱሰኝነት በጊዜ መፍትሔ ማስቀመጡ አግባብነት ያለው ተግባር መሆኑ ነው በምክክር መርሐ ግብሩ የተነገረው።

ማኅበረ ቅዱሳንም በሙያ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በኩል ለችግሩ መፍትሔ ብሎ ያስቀመጠው ቤተክርስቲያናችን ባሏት ገዳማትና አድባራት "የሱስ ማገገሚያ ማእከል" ማቋቋምን ሲሆን ለምክረ ሐሳቡ ተግባራዊነት ደግሞ ለእያንዳንዱ ሱስ የሚያስፈልገው የማገገሚያ ዓይነትና ተቋም የሚለያይ በመሆኑ ለሁሉም የሱስ ዓይነቶች ማገገሚያ ተቋም በአንድ ላይ እንዲሁም በተናጠል ማቋቋም በርከት ያለ ገንዘብ፣ ጊዜ፣ የሰው ኃይል ማሰናዳት ያስፈልጋል ተብሏል።


በቀጣይ ጊዜም ይህን ሥራ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ ለመቀየር የሚቻልበት ዝርዝር መፍትሔዎችን ወደ ተግባር የሚቀየር ግብረ  ኃይል በማቋቋም ጉባኤው ፍጻሜውን አግኝቷል ተብሏል።
22👍2
ማኅበረ ቅዱሳን ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሥነ ልቡና ዝግጅት ሥልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ተጠቆመ

ሰኔ ፪/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሥነ ልቡና ዝግጅት ሥልጠና እስካሁን በማእከላት ሲሰጡ የነበረ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በጅግጅጋ፣ በመቱ፣ በነቀምቴ፣ በጂንካ ማእከላትና በስማዳ ወረዳ ማእከል እንደሚገኙበት ተመላክቷል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ሰኔ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በቴሌግራም (@MKFOR12TH) የስነ ልቦና ሥልጠና እንደሚሰጥ የተጠቆመ ሲሆን በዚህም ማኅበረ ቅዱሳን ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሥልጠናው እንዲሳተፉ ጥሪውን ያቀርባል።
👍62
2025/07/08 20:41:34
Back to Top
HTML Embed Code: