በዲሲና ሜሪላንድ የሚገኙ አባላት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል እና የማኅበረ ቅዱሳን ፴፫ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በማእከሉ ጽ/ቤት በመገኘት በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል።
❤5👍2
ማኅበረ ቅዱሳን በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት የገነባው አዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት ተመረቀ፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት በነቀምት ምስካበ ቅዱሳን ዑራኤል ወሳሙኤል አንድነት ገዳም ያስገነባው አዳሪ አብነት ትምህርት ቤት ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጋምቤላ ክልልና የደቡብ ሱዳን ፣የቤንሻንጉል ጉሙዝ አሶሳ፣የቄለም ወለጋ፣የምዕራብ ወለጋ፣የምሥራቅ ወለጋ፣የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተመርቋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን አብነት ት/ት ቤት ባልተስፋፋባቸው እና የአገልጋይ እጥረት ባለባቸው የአገሪቱ አከባቢ ከሚተገብራቸው መካከል አንዱ ይህ አዳሪ አብነት ት/ቤት ነው፡ የአዳሪ አብነት ትምሕርት ቤቱ በተመላላሽ የሚማሩትን ጨምሮ 60 ደቀ መዛሙርትን ተቀብሎ የሚያስተናግድ ሲሆን የ2 መምህራን እና የ32 ተማሪዎች ማደሪያ ከሙሉ ግብዓቱ፣ የመማሪያ ጉባኤ ቤት፣ መመገቢያ አዳራሽ፣ ማብሰያ ቤት፣ የልብስ ማጠቢያ ገንዳዎችና እና መጸዳጃ ቤቶችን ያካተተ ነው፡፡
በምረቃው መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሩፋኤል አዳሪ አብነት ት/ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ ተማሪ ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡ ብፁዕነታቸው አክለው እንደገለጹት ከአራቱም ወለጋዎች ተማሪዎች ገብተው እንዲማሩ እንደሚሠሩ እና ከቅዱስ ሲኖዶስ በጀት እንደሚያስፈቅዱ ተናግረዋል፡፡
ታኅሣሥ ወር 2016 ዓ.ም ተጀምሮ በአንድ ዓመት የተጠናቀቀው የትምህርት ቤቱ ግንባታ ፕሮጀክት 8,870,407.125 (ስምንት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰባ ሺህ አራት መቶ ሰባት ብር ከ3/100 ሳንቲም) ብር ወጪ የወጣበት ሲሆን በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የሚገኙ በበጎ አድራጊ ምዕመናን ድጋፍ አድርገዋል፡፡

❤15👍2
ይህ የአዳሪ አብነት ትምህርት ቤት በሀገረ ስብከቱ እና አጎራባች አህጉረ ስብከት የሚታየውን የአገልጋይ አጥረት ችግር እንደሚፈታ ታምኖበት የተተገበረ ፕሮጀክት ነው፡፡
👍10
በሲያትል የሚገኙ የማኀበሩ አባላት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል እና የማኅበረ ቅዱሳን ፴፫ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል።
👍5❤4🕊2
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ ያስተላለፉት መልእክት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
* ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳር እና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
* ብፁዕ አቡነ ሄኖክ
የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
*ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!!
እንደዚሁም በዚህ ቀኖናዊና ዓመታዊ የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ የተገኛችሁ በሙሉ፤ ጸጋንና ሐዋርያነትን ያጐናጸፈን ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ትንሣኤውን በሰላም አክብረን ይህንን ዓመታዊውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ለማካሄድ ስለ ሰበሰበን ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን፤ የጉባኤው አባላት የሆናችሁ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትም እንኳን ለርክበ ካህናት ጉባኤ አደረሳችሁ! እንኳንም በሰላም መጣችሁ!
“ረከብነ ጸጋ ወተሰየምነ ሓዋርያተ ከመ ናስምዖሙ ለኣሕዛብ ወይእመኑ በስሙ፡- ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን” (ሮሜ.፩÷፭)፤ይህ ሐዋርያዊ አስተምህሮ የኛን ተልእኮና ተልእኮው ያስፈለገበትን ምክንያት አጉልቶ ያሳያል፤ የተቀበልነው ስጦታም ምን ያህል ታላቅ እንደ ሆነ ምንባቡ ያስረዳል፤ ሐዋርያው በዚህ መልእክት የቅዱስ ወንጌል አስተምህሮ ዋና ግብ ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ማድረግ ነው በማለት ያስተምረናል፤ እውነት ነው ድሮውኑም ቢሆን ለእግዚአብሔር መታዘዝ አቅቶን ነው የወደቅነው፤ ዛሬም የምንነሣው ከእምነት የተነሣ መታዘዝን ገንዘብ ስናደርግ ነው፤ ከሁሉ በፊት እምነት ይቀድማል፤ ከሱ በኋላ ደግሞ ለእምነቱ በሙሉ ልብ መታዘዝ ይከተላል፤ ይህ ሲሆን መዳንና ትንሣኤ ይገኛል፤

👍7