በማኅበረ ቅዱሳን ዲላ ማእከል በዲላ ማረሚያ ተቋም እና በዲላ ዋለሜ ደብረ ሰላም ቤተክርስቲያን የተለያዩ መርሐ ግብር የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ በተገኙበት ተካሄደ!!
በዲላ ማረሚያ ተቋም በዓለ ትንሣኤን ከታራሚዎች ጋር ማዕድን የማጋራትን ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሀገረ ስብከቱና የወረዳ ቤተ ክህነት ተወካዮች በተገኙበት ማዕዱን የተጋሩ ሲሆን ድጋፍ ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል።
በእለቱም ብእፁ አባታችን አቡነ ገሪማ ትምህርተ ወንጌል ያስተማሩ ሲሆን ያሬዳዊ ዝማሬ በግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ቀርቧል ።
በተመሳሳይ ብፁዕነታቸው በተገኙበት በዲላ ዋለሜ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ምግባረ ሰናይ ኮሚቴ ከግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ጋር በመተባበር የተቸገሩ ወገኖቻችን የማዕድ ማጋራትና የአልባሳት ስጦታ ተከናውኗል።
በተጨማሪም በሁሉም ግቢ ጉባኤያት መንፈሳዊ መርሐ ግብር ኮርስ በሚማሩበት አዳራሽ የተከናወነ ሲሆን በዲላ ዋለሜ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን በተዘጋጀው መርሐ ግብር በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ቃለምዕዳን ተደርጎ በጸሎት ተፈጽሟል።

👍33❤4
የኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የማኅበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈ።
ሚያዚያ ፲፮/ ፳፻፲፯ ዓ.ም
መምሪያው ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር በጻፈው ደብዳቤ ማኅበሩ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ ርቱዕ እምነትን ከሥነ ምግባር ጋር ይዞ የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያን ያሳዘነ፣ እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ለጠላት መሳለቂያ እንድትሆን ያደረገ፣ ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ጋር የሚቃረን እመቤታችን ቤዛ አይደለችም የሚል ጤናማ ያልሆነ ትምህርት ሚያዝያ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በማኅበሩ ሚዲያ ማስተላለፉን እንደተመለከተ ገልጾ የማኀበራት ምዝገባ ክትትል እና ቁጥጥር መምሪያው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ጸድቆ በተሰጠው ደንብ መሠረት በማኅበራት መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ዙሪያ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮች ሲፈጠሩ ተገቢውን ክትትልና አስፈላጊውን እርምት የመስጠት ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ በደብዳቤው ለተጠቀሱ አምስት ነጥቦችን በማኅበሩ በኩል አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥባቸው በጥብቅ አሳስቧል።
መምሪያው በጻፈው ደብዳቤ ላይም በዕለተ ስቅለት የተላለፈው ትምህርት ቪዲዩ በአስቸኳይ ከማኅበሩ ዩቲዩብ እንዲወርድ እንዲያደርግና በዕለቱ የተላለፈውን ትምህርት ሙሉ ቪዲዮ ቅጂ ለመምሪያው እንዲያቀርብ ጥብቅ መመሪያ ሰጥቷል።

👍72❤13🙏11