Telegram Web Link
ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያላቸው አስተዋፅኦ

ክፍል አንድ


በሐዋርያት ትምህርት ላይ የተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዋናው ተልእኮዋ የምሥራች ቃልን ለዓለም ማዳረስ ነው። ይህን የምሥራቹን ቃል ለማዳረስም በተለያየ ዘመን ብዙ ፈተናዎች ገጥሟታል፡፡ ፈተናዋን በጸሎት እና በዘመኑ በነበሩ አበው ምእመናን ጥብዓት ተሻግራ አሁን ካለንበት ዘመን ደርሳለች። ከአባቶቻችን የተረከብናትን ቤተ ክርስቲያን ከእነ ሙሉ ክብሯ ለመጠበቅ ትምህርት ላይ መሥራት ለነገ የማይባል ሥራ መሆኑ የሚያጠራጥር ባይሆንም ነገር ግን አሁን ባለንበት ዘመን ያለውን የትምህርት አሰጣጥ ሁኔታ ስንገመግመው ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሐዋርያት የተቀበለችውን ትምህርት ለማስተማር ከምትጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ ልጆቿን በሰንበት ትምህርት ቤት መዋቅር ውስጥ እንዲታቀፉ በማድረግ አስፈላጊውን ትምህርት እንዲያገኙ በማስቻል ነው። በመሆኑም የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች መጠንከርም ሆነ መድከም ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ያለው ተጽዕኖ ቀላል ይሆናል ተብሎ አይታሰብም። በዚህ አጭር ጽሑፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያላቸውን አስተዋፅኦ ለማየት እንሞክራለን።

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት ምን ማለት ነው?

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ሥር ታቅፈው በበዓላት፣ በዕረፍት ቀናት (በሰንበታት) በመገኘት ትምህርተ ሃይማኖት የሚማሩ ተማሪዎች ስብስብ ማለት ነው።

የአገልግሎት ትርጕም

የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሲባል ገና ተጋድሎዋን ያልፈጸመችው እና የሚደርስባትን መከራ በጸጋ በመቀበል ክርስቶስን በመከራ ለመምሰል ሥርዓተ አምልኮዋን ዘወትር የምታከናውን ሲሆን ነው፡፡ “እግዚአብሔር የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ እንማልዳለን” ብላ በዐጸደ ነፍስ ካሉ ቅዱሳን እንዲሁም ዘወትር ያለማቋረጥ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት ጋር አንድ የሚያደርጋት አገልግሎት ተብሎ ሊገለጽ ይችላል።
ይቆየን!
በአዲስ አበባ የዘነበ ወርቅ ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ እና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ፈለገ ሰላም ሰንበት ት/ቤት ማኅበረ ቅዱሳን ለሚያከናውነው ሐዋርያዊ አገልግሎት ድጋፍ አደረገ::

ድጋፉም በደቡብ ቤንች ወረዳ ለምትገኘው እና ለአዳዲስ አማንያን መገልገያነት ለታነጸችው ለካቡል ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ነው::

ሰንበት ትምህር ቤቱ 62ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ መለገሱ የተገለጸ ሲሆን ለ24 ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ልብሰ ስብሐት እና 5 መጽሐፍ ቅዱስ አስረክቧል::

የሰንበት ተ/ቤት ተማሪዎች በሃይማኖታቸው እንዲበረቱ፣ ቁጥራቸው እንዲጨምር የማደረግ ጥቅም የሚኖረው ሲሆን ሌሎች ሰንበት ት/ቤቶችም በእንደዚህ አይነት አገልግሎት መሳተፍ እንዳለባቸው የትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ኃላፊ የሆኑት ዲ/ን ኃይሌ አርአያ በርክክቡ ወቅት ገልጸዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮች፣ በአካባቢው በቤንችኛ እና ሸክኛ ቋንቋዎች የሚያገለግሉት መጋቤ ኃይማኖት ቀሲስ ደመላሽ አማኑኤል ጨምሮ የፈለገ ሰላም ሰንበት ት/ቤት አገልጋዮች ተገኝተዋል::

ሰንበት ት/ቤቱ በዚሁ ዓመት በቤንች ወረዳዎች ለሐዋርያዊ ተልእኮ የሚሠማሩ 25 ሰባክያነ ወንጌልን ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመሆን አሰልጥኖ መላኩ ይታወሳል፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት አገር አቀፍ የደም ልገሳ መርሐ ግብር እየተከናወነ ይገኛል።

ማኅበረ ቅዱሳን ከኢትዮጵያ የደም ባንክ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የደም ልገሳ መርሐ ገብር በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ እየተከናወነ ይገኛል።

አዲስ አበባ በሚገኘው የማኅበሩ ዋና ማእከል ጽ/ቤት በተከናወነው የደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ በርካታ ምእመናን ተገኝተው በመለገስ ላይ ይገኛሉ።
‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ››

ክፍል ሰባት


ተወዳጆች! እንዴት ሰነበታችሁ? እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ!

በክፍል ስድስት “ክብረ ምንኩስና ትናንት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የነበረውን ክብርና ሞገስ ያስገኘውን የቅድስና ፍሬና ያሳረፈውን አሻራ” አንስተን ለመዳሰስ ሞክረናል፡፡

በዚህ በክፍል ሰባት ደግሞ ምንኩስና ዛሬ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እያጋጠመው ያለውን ተግዳሮት ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡ ቀደም ብለን እንደ ተመለከትነው ምንኩስና ከምድራዊው ይልቅ ሰማያዊውን፣ ከሰው ይልቅ የመላእክትን ግብር መምረጥ፣ ፍጹም ሆኖ ፍጹም የሆነችውን መንግሥት ለመውረስ ሁሉን ትቶ መመነን፣ ከሰው ከዓለም መለየት፣ በገዳም በአጽንዖ በአት፣ በግብረ ምንኩስና መወሰን መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጅ በዘመናችን ምንኩስና በዘርፈ ብዙ ተግዳሮት ውስጥ ይገኛል፤ የተወሰኑ ችግሮችን ለማሳየት ያህል፡-

፩. የምንኩስና ሥርዓትን ተከትሎ አለመመንኮስ፡-

በገዳም ሕግ አንድ መናኝ ሁሉንም ትቶ ወደ ገዳም ሲገባና “እመነኩሳለሁ” ሲል በገዳሙ ያለውን ሥርዓተ መነኮሳት መማርና መጠበቅ፣ የተቀመጠውን የአበው ሥርዓት ማክበር፣ በጉልበቱ እንጨት ሰብሮ፣ ውኃ ቀድቶ፣ ከብት ነድቶ፣ ቡኮ አብኩቶ፣ ዳቤ ጋግሮ በእርድና መነኮሳትን መርዳት ይገባዋል፡፡ ‹‹መነኮሳትን ሳይረዱ “እመነኩሳለሁ” ማለት ሳይበጡ መታገም ነው፡። ምክንያቱም ከሁሉም እርድና ይበልጣልና ከእርድና በኋላ ቢመነኩስ ይጠቅማል›› ይላል መጽሐፈ ምዕዳን፡፡ (ገጽ ፻፶) ይሁን እንጅ በአሁኑ ሰዓት የአመክሮ ጊዜ የሌላቸው ገዳማትን አበው መነኮሳትን በጉልበታቸው በእርድና ያላገለገሉ፣ የኋላ ታሪካቸውና የወደፊት ትልማቸው ያልተገመገመ፣ አንዳዶቹም የትና በማን እንደመነኮሱ የማይታወቁ፣ ተጠየቅ የሌለበት የምንኩስና ሥርዓት ቤተ ክርስቲያንን ፈትኗታል፡፡
፪. በቦታ ያለመርጋት (አጽንኦ በዓት) አለመኖር፡-

ትልቁ የአንድ መናኝ ፈተና አጽንኦ በዓት ማለትም በዓትን አጽንቶ ወዲያ ወዲህ ሳይሉ ከቦታ ቦታ ከመዘዋወር ተቆጥቦ በገዳም መኖር አለመቻል ነው፡፡ የምንኩስና ጀማሪው አባ ጳውሊ ይሁን እንጅ መልክና ቁመና የሰጠው አባ እንጦንስ እንደሆነ ይነገራል፡፡ አባ አንጦንስ ከ፪፻፶፩-፫፻፶፮ ዓ.ም ለ፻፭ ዓመት የኖረ አባት ሲሆን በአባ እንጦንስ እንደ መነኮሰ የሚነገርለት ቅዱስ አትናቴዎስ ጽፎታል ተብሎ የሚታመነው የአባ እንጦንስን ታሪክ አባ እንጦንስ በ፹፭ የምናኔ ዓመታት ከበአቱ የወጣው ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ይባላል፡፡ (ገድለ አባ እንጦንስ)

አንድ ጊዜ በመክስምያኖስ ስደት የደረሰባቸውን ክርስቲያኖች ለማጽናናት በ፫፻፲፩ ዓ.ም ሲሆን ሁለተኛው አርዮሳውያን በአትናቴዎስ ላይ በተነሱ ጊዜ በ፫፻፴፰ ዓ.ም ለተመሳሳይ ዓላማ ወጥቷል፡፡ በሕንጻ መነኮሳትም ‹‹በአቱን ትቶ ከቦታው ውጭ የሚያድር መነኩሴ አይኑር›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ (ክፍ. ፪ ቁጥ ፭) ሕንጻ መነኮሳት በዚህ ሳይወሰን መነኮሳትን የሚያረክሱ አምስት ነገሮች ብሎ ከሚዘረዝራቸው አንዱ ‹‹ከቦታ ቦታ ከሀገር ሀገር መዘዋወር›› ነው ይላል፡፡

‹‹በገዳም መኖር ማቅ መልበስ፣ በዝናር መታጠቅ ይገባል›› የሚል ሕግ ቢኖርም አሁን ያለው ችግር ከገዳም መውጣት ከገዳም ገዳም መዘዋወር አይደለም፤ እርሱስ ቢሆን በተሻለ ነበር፡፡(ፍት.መን. አንቀጽ ፲ ቁ ፫፻፶፯) ከገዳም ወደ ከተማ ከከተማም ወደሌላው ከተማ፣ ከሀገር ወደ ውጭ ሀገር ያለው የመነኮሳት ፍልሰትና እንቅስቃሴ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ‹‹ለመነኩሴ ከተማ መግባት፣ አደባባይ ተቀምጦ መፍረድ፣ ምስክርነት ዋስነት አይገባውም፡፡ ለምውት ይህ ሁሉ ሥራው አይደለምና›› ተብሎ ቢጻፍም አሁን ላይ ብዙ ገዳማት ባዶ ናቸው፤ ጥቂቶቹም ጥቂት መነኮሳት ብቻ ይኖሩባቸዋል፤ መናንያኑ ከተሞችን ሞልተውታል፤ ግብረ ምነኩስናን የሚፈጽሙበት፣ ለአገልግሎት ለትሩፋት የሚፋጠኑበት ጊዜ የላቸውም፤ በጣም ከዓለማዊው ሰው ባነሰና በሚያስደነግጥ በዓለማዊ ሐሳብና ግብር ላይ ተጠምደው ይታያሉ፤ ያሰቡትን የሚያሳካ ፍላጎታቸውን የሚያረካ ነገር ሳያገኙ ሲቀሩ ባልተገባ አኳኋን ባልተገባ ቦታ የሚገኙ ወንጀል የሚሰሩ በርካታ መነኮሳት የታዩበት ዘመን ነው፡፡ (መ-ምዕዳን ገጽ ፻፶፪)

፫. በዚህ ዓለም ሐሳብ መሸነፍ፡-

በገንዘብ ፍቅር መሸነፍ ሁሉን ትተው ፍጹም ይሆኑ ዘንድ የተከተሉ መነኮሳት ትተውት ከሄዱት ዓለም ተመልሰው ሀብትና ባለጸግነትን በመሻት ብዙዎች ወድቀዋል፡፡ አንድ መነኩሴ/መነኩሲት እንዲመንኑ የገፋቸው አምላካዊ ቃል ‹‹ሂደህ ገንዘብህን ሁሉ ሸጠህ ለነዳያን መጽውት፤ በሰማይም ድልብን ታከማቻለህ ና ተከተለኝ›› የሚለው ነው፡፡ (ማቴ.፲፱፥፳፩) አሁን ውሻ ወደ ትፋቱ እንዲመለስ ተፍተውት የሄዱትን ሀብት ፍለጋ ብዙዎች በገንዘብ ፍቅር ወድቀዋል፡፡ አርአያ ምንኩስናን ፈተና ላይ ጥለዋል፤ ስለሚነዱት መኪና ስለሚሰሩት ፎቅና ምድር፣ ስለሚያጌጡበት ወርቅና ብር የሚጨነቁ፣ ይህን ክፉ መሻታቸውን ለማሳካትም በየፍርድ ቤቱ በየመንግሥት ተቋማቱ ደጅ ተሰልፈው በክርክርና በንትርክ በአሕዛብ መድረክ ዳኝነት የሚፈልጉ ብዙ መነኮሳትን እንመለከታለን፡፡

በአንድ ወቅት የቦሌ ክ/ከተማ መሬት ማኔጅመንትን ያጨናነቁ መነኮሳትና የደብር አለቆች መሆናቸውን የሚገልጽ መረጃ ተሰራጭቶ ተመልክተናል፡፡ (መገናኛ ብዙኃናት) ይህ ብቻ ሳይሆን እነዚህ መነኮሳት በሕይወት ሲያልፉ የሚነሳው የወራሽነት መብት ጥያቄና ሙግት በራሱ የቤተ ክርስቲያኗን ክብር የሚያዋርድ፣ ምእመናንን አንገት የሚያስደፋ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ በተራ መነኮሳት ሳይወሰን በአንዳድ ጳጳሳትም ዘንድ ይስተዋላል፡፡

በሥልጣን ፍቅር መውደቅ፡- የአንድ መናኝ (መነኩሴ) ሥልጣንን ሹመትን መሻት አንዱ የፈተናው ምንጭ እንደሆነና እንዲጠነቀቅ መጽሐፍ ይመክራል፡፡ ፍትሐ ነገስሥት እንዲህ ይላል፤ ‹‹የሹመት ፍቅር ሰይጣናዊ በሽታ ነውና በዚህ በሽታ ላይ የወደቀ ሰው ካህናትና ሹማምንት ሊሆኑ በሚገባቸው ላይ ቀናተኛ ይሆናል፡፡ ሰው ጠቅሶ ያነሳሳባቸዋል፡፡ በእነርሱ ሹመት ይተካ ዘንድ ሞታቸውን ይወዳል፡፡ ሹመቱ ባልሆነለት ጊዜ በርሱና በነርሱ ችግር ይፈጠራል፡፡ ከዚህ መጥፎ ፈቃድ ይራቅ እንጅ፡፡›› (ፍ.መ አ.፫፣ ቁ. ፫፻፹፭) ብዙ መነኮሳት በዛሬዋ ቤተ ክርስቲያናችን ተፈትነው የወደቁበት ፈተና ነው፡፡

አለቃ ለመሆን፣ ጸሐፊ ለመሆን፣ የመምሪያ ኃላፊ ወይም ሌላ ሥልጣን በመሻት ቦታቸውን ለመንጠቅ፣ በተሾሙት ፋንታ ለመሾም፣ በተቀቡት ቦታ ለመቀመጥ አባቶቻቸውንና ወንድሞቻቸውን ለመወንጀል በዓለም ያሉ ተባባሪዎችን ለማግኘት የጠላት በር ሳይቀር ያንኳኳሉ፤ የተከበሩትን ያዋርዳሉ፤ በሐሰት ክስም ይከሷቸዋል ክፉዎችን ቀስቅሰው ያነሳሱባቸዋል፡፡ አሁን ደረጃውን ከፍ አድርጎ እስከ ጵጵስናም ደርሷል፡፡ መጽሐፍ ግን ‹‹ወኢያፍቅር ምንተኒ ዘዝንቱ ዓለም፤ የዚህን ዓለም ምንም ምን አይውደድ›› ነው የሚለው፡፡ (መጽሐፈ ምዕዳን ገጽ ፶፩)

በሥጋ ምቾት መጠመድ፡- ብዙ መነኮሳት በሥጋዊ ምቾት ውስጥ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን እንዳንበላ፣ እንዳንጠጣ፣ እንዳንለብስ፣ እንዳናጌጥና እንዳይመቸን አይደለም የፈጠረን፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሁሉ አላፊ ጠፊ መሆናቸውን ተገንዝበን ሁሉንም በመጠን በአግባቡ በሥርዓት ብናደርገው በሚያልፈው ዓለም ውስጥ የተውነው ምቾት በማያልፈው ዓለም ውስጥ ዋጋ እንደሚያሰጠን በተለይ ለመነኮሳት ሲሆን የበለጠ መሆኑን በቀኖና መጻሕፍት ተጽፎ እናነባለን፡፡ እንኳንስ መነኮሳት የዚህን ዓለም ውበቱን ድምቀቱን፣ መብሉን መጠጡን ትተው የመነኑትን፣ ራሳቸውን በፈቃዳቸው ከሙታን ዓለም የቆጠሩትን ቀርቶ ሕዝባውያንም በሚበላ በሚጠጣ በሚለበስ ነገር ሁሉ በመጠን እንዲኖሩ ታዟል፡፡ ይሁንና አሁን ላይ ብዙዎች በሥጋ ምቾት በመብል መጠጥ ተጠልፈው ፈተና ብዝቶባቸው ለምእመናንም ለቤተ ክርስቲያንም ኃፍረት ሲሆኑ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ሕንጻ መነኮሳት ‹‹መነኩሴን ከሚያረክሱ ነገሮች አንዱ ከመጠን በላይ መብላትና መጠጣት ነው››ይላል፡፡

መጽሐፈ ምዕዳን ደግሞ ‹‹መነኩሴ የእንጦንስን የመቃርስን የቅዱሳንን ገድል ይመልከት፤ እንዲጸና ምግብ ይክፈል፡፡ አይምረጥ፤ የመጠጥንም ነገር የጽም ያህል ይጠጣ፡፡ ሥጋ አይብላ፤ ወይን ጠጅ አይጠጣ፡፡ ለመነኩሴ ምሳ የለውም፡፡ ዓመት እስከ ዓመት ጾም ነው እንጅ መነኩሴ ምሳውን ከበላ ሴት ከወንድ ጋራ አድራ በማኅፀኗ ልጅ እንዲፀነስ በሰውነቱ ሦስት ነገሮች ይፀነስበታል፡፡ ትዕቢት፣ ምንዝርነት፣ ቁጣ ይመጣበታል፤ ከዚህ በኋላ ሰይጣን ይሰለጥንበታል፤ ቆቡን ከመቅደድ፣ ዲቃላ ከመውለድ ያደርሰዋል፤ የንጽሕና መሣሪያ ከመብል መከልከል ነው›› ይላል፡። (ገጽ ፻፶፩) አሁን ሁሉም ነገር እየሆነ ነው፡፡ ብዙዎች በሆዳቸው ተገምግመዋል፤ በትዕቢትም፣ በቁጣም፣ በምንዝርነትም እየተፈተኑ ያሉበት ዘመን ነው፡፡

ይቆየን!
የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻ ጸሎት መርሐ ግብር በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል።

ምንጭ: የኢኦቴቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
2024/11/16 09:09:15
Back to Top
HTML Embed Code: