Telegram Web Link
በህንድ ሀገር ማኅበረ ቅዱሳን ያስተማራቸው የማርዋዲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ተመረቁ።

በማኅበረ ቅዱሳን ሩቅ ምሥራቅ ማእከል አስተባባሪነት ላለፉት አራት ዓመታት ተከታታይ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሲማሩ የነበሩ አሥራ ዘጠኝ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ/ም ተመረቁ።

በዚህ የተማሪዎች ምርቃት መርሐ ግብር ላይ የግቢ ጉባኤው አባላትና ተመራቂ ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን የሩቅ ምሥራቅ ማእከል ጸሐፊ  እና የግቢ ጉባኤ ማስተባበሪያ ክፍል አባላት መርሐ ግብሩን በዙም (Zoom) ተከታትለዋል።

የሩቅ ምሥራቅ ማእከል የተተኪ ትዉልድ እና ግቢ ጉባኤ ማስተባበሪያ ክፍል ተጠሪ ዶ/ር ሲራክ ተከተል ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በመልእክታቸውም "ተመርቃችሁ ከወጣችሁ በኋላ በየአካባቢያችሁ በሚገኙ ማእከላት ሥር በመታቀፍ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የድርሻችሁን እንድትወጡ ማኅበራችሁ ማኅበረ ቅዱሳን ያሳስባችኋል" ብለዋል። በተጨማሪም ለግቢ ጉባኤዉ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ መምህራንና አስተባባሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።

በዕለቱም በዲ/ን ፋንታሁን የሩቅ ምሥራቅ ማእከል ጸሐፊ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል። ተመራቂዎችመ‍እ መዝሙር ያቀረቡ ሲሆን ለተመራቂዎች የመስቀል ስጦታ በግቢ ግባኤው ሰብሳቢ መምህር ዋሲሁን አገሩ አማካኝነት ተበርክቷል።

በተመሳሳይ በህንድ ሀገር በኬአይአይቲ (KIIT) ግቢ ጉባኤ ስር ሆነዉ ላለፉት 3 ተካታታይ ዓመታት  ሲማሩ የነበሩ 5 የግቢ ጉባኤዉ አባላት ተመርቀዋል።

ዘገባውን የማኅበረ ቅዱሳን ሩቅ ምሥራቅ ማእከል ሚዲያ ክፍል አድርሶናል።
በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች የሽኝት መርሐ ግብር ተከናወነ።
 
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን  አቡዳቢ ልዩ ግንኙነት ጣቢያ ከሊባኖስ፣የተባበሩት ዐረብ ኢምሬትስ እና የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገረ ስብከት ጋር በመተባበር ለትምህርት ወደ ተባበሩት ዐረብ ኤሜሬትስ በመሄድ ሲማሩ ለቆዩ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች የሽኝት መርሐ ግብር አከናወነ።

የመጀመሪያ ዓመት ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ አገር ቤት ለሚመለሱ ተማሪዎች ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በተከናወነው የሽኝት መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ በሊባኖስና የተባበሩት አረብ ኢምሬትና የመካከለኛው ምስራቅ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፤ የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ቀሲስ ደረጀ ጂማ፣ መላከ ሰላም መምህር ለይኩን ብርሃኑ፣ መምህር ኪሩቤል ይገዙ፣ ሊቃውንተ ቤተክርቲያናት እንዲሁም የልዩ ግንኙነት ጣቢያው አባላትና ተባባሪ አካላት ተገኝተዋል።

ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎችን ከመቀበል ጀምሮ፣ በግቢ ቆይታቸው መንፈሳዊ ሕይወታቸውንም አጠንክረው እንዲወጡ የተለያዩ ትምህርቶችን በመስጠት እና እንዲያገለግሉ በማድረግ ከፍተኛ ሥራ እየሠራ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን በኢማራት ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ሲያስተምራቸው የነበሩት እነዚህ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችም በመርሐ ግብሩ ላይ ወረብ እና መዝሙር፤  በኢማራት ላይ የአንድ አመት ቆይታቸውን በተመለከተ ውይይት ፤ እንዲሁም የአብነት ትምህርት ሁለንተናዊ ሕይወትንም የሚያስገነዝብ ትእይንትም አቅርበዋል።

2024/09/29 06:33:49
Back to Top
HTML Embed Code: