የጀርመንና አካባቢው እና የምሥራቅ ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የዳግም ትንሣኤን በዓል ከችግረኞች ጋር አከበሩ።
ብፁዕነታቸው ግንቦት 04/2016 ዓ.ም በተካሄደ መርሐ ግብር "የአብነት ተማሪዎችን እና ችግረኞችን መርዳት ማገዝ የቅድስት ቤተከርስቲያን ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
ለአብነት ተማሪዎችና በችግር ያሉ ወገኖችን በዕለቱ የምሳ ግብዣ ያደረጉት የደ/ማርቆስ ከተማ ወ/ቤተ ክህነት ምግባረ ሰናይ ክፍል
፣በአድባራት የሰ/ት/ቤት ወጣቶች ኅብረት፣ በኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ኅብረት፣ በማኅበረ ቅዱሳን የደ/ማርቆስ ወረዳ ማእከል
በጋራ በመሆንና ምዕመናን በማስተባበር ነው።
ከምዕመናን የተሰበሰበውን የልብስ ስጦታ በብፁዕ አባታችን የተሰጠ ሲሆን ይህ በጎ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል የተሳተፋትንም አመስግነው በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችንም በእግዚአብሔር ቃል አጽናንተዋል።
ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ደ/ማርቆስ ማእከል ሚዲያ ክፍል ነው

"..የሥጋ ስሜትን በመንፈሳዊው አገልግሎት ቀላቅሎ የሚወራጭ ቢኖር እሱ የያሬድ ልጅ አይደለም ።መንፈሳዊ ተመስጦ እንጂ እስክስታ የሚያስመታ ዝማሬ ቅዱስ ያሬድ አልደረሰም"ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ
ሐመር መጽሔት ፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፭
የኅትመት ዘመን ፦ ግንቦት ፳፻፲፮ ዓ.ም
አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
• ገጽ ብዛት፦፳፰
ዋጋ ፦፵ ብር
• ሐመር መጽሔት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
• ሐመር መጽሔት ፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፭ ግንቦት ፳፻፲፮ ዓ.ም በመልዕክት ዐምድ "#ቅዱስ አባት ሆይ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ በስምህ ጠብቃቸው " በማለት ሁሉም አበው የክርስቶስ ማደሪያ ሆነው ከተገኙና መድኃዓለም ክርስቶስ በመካከላቸው ከሆነ የአንድነት ጠላት የሆነው ሰይጣን ፣መግቢያ ቀዳዳ ሊያገኝ ስለማይችል ፍጹም አንድነት እንደሚፈጠር ያሳያል፡፡ አባቶቻችን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአገልግሎት ሂደት የተፈጠረና የሚፈጠር ማንኛውንም አይነት ልዩነት በውይይትና በምክክር መፍታት እንደሚገባና እንደሚቻል ከራሳለው አልፈው ለዓለም ተግባራዊ ትምህርት ካልሰጡ ማን ሊሰጥ ይችላል? ቤተ ክርስቲያንን ከፈተና ለመታደግ የብጹዓን አባቶች እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል ። አጠቃላይ የሆነ የይቅርታና የዕርቅ መርሐ ግብር አዘጋጅቶ ሰላምን መመስረትና ፍቅርን ማጽናት ቀዳሚው የወቅቱ ጉዳይ እንደሆነ ይጠቁማል።
.#ዐውደ ስብከት ሥር” #እግዚአብሔር አይዘገይም " በሚል ርእስ በብላቴናው ያሬድ አእምሮ ዕውቀትን ከማሳደር የዘገየ ሊመስላቸው እንደሚችል ያሳያል ።አንድን ነገር ሁል ጊዜ እኛ በምናየው በኩል ብቻ ያለውን ገጽ በመመልከት ነገር እናበላሻለን። ዛሬ ከእኛ በታች የሆኑ ሁሉ ጊዜ ከእኛ በታች ሊሆን እንደሚችል ማሰብ እንደማይገባ ፣ከምድራዊ ጉባኤ ቤት የተሰናበተው ደቀ መዝሙር ያሬድ በሰማዩ ጉባኤ ቤት ተካፋይ እንደሆነ ያትታል ።
ቅዱስ ያሬድ ለቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያዘጋጀ ሊቅ ነው። የሥጋ ስሜትን በመንፈሳዊው አገልግሎት ቀላቅሎ የሚወራጭ ቢኖር እሱ የያሬድ ልጅ አይደለም ።መንፈሳዊ ተመስጦ እንጂ እስክስታ የሚያስመታ ዝማሬ ቅዱስ ያሬድ አልደረሰምና በምንዘምርበት ጊዜ ከመንፈሳዊ ተመስጦ እንዳንወጣ ራሳችንን መግዛት ይኖርብናል ።
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “#ጰራቅሊጦስ የእውነት መንፈስ "በሚል ዐቢይ ርእስ ጌታችን በኅምሳኛው መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት ቋንቋ እንደገለጸላቸው በበቂ ማስረጃ የተደገፈ ትምህርት ይዛለች።በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ ሲባል እንዴት ነው?የሚለውን ጥያቄ መልስ ትሰጣለች ።በዓለ ጰራቅሊጦስ፣ቋንቋና ቤተ ክርስቲያን ያለውን ሁኔታ ያሳያል።መንፈስ ቅዱስ ለሰው የሚጠቅም ለአገልግሎት የሚውል ቋንቋን እንጂ አረፋ የሚያስደፍቅ ትርጉም አልባ አጋንንታዊ ጬኸትን አይገልጥም ።በዓለ ጰራቅሊጦስን ስናስብ ከእኛ ምን እንደሚጠበቅ በዝርዝር ያሳያል ።
• ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “#የቅዱስ ሲኖዶስ ኃይል ክብርና ሥልጣን “ በሚል ርእስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ከሌሎች ቤተ እምነቶች የምትለይበት አንዱ ኦርቶዶክሳዊነት መገለጫ የቤተ ክርስቲያያኒቱ ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤትና የክርስቶስ እንደራሴ ቅዱስ ሲኖዶስ መሆኑን ያሳያል ። የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ነቀፋ የሌለባቸው ሲሆኑ መንጋው ይከተላቸዋል።ድምፃቸው ይሰማል።ልጆች በአባቶቻቸው መኩራት እንጂ ማፈር አይፈልጉም ።ልጆች በአባቶቻቸው መጽናናት እንጂ መሰቀቅ አይፈልጉም ።
በሐመር መጽሔት በዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል በሐሳብ መለያየት የሚመጣው የሆነ ወገን የመንፈስ ቅዱስን ፈቃድ ሳይሆን የራሱን ምኞት መከተል ሲጀምር ነው ትላለች። ቅዱስ ሲኖዶስን ራሱን ያስገኘው ምሥጢረ ክህነት እንደሆነ ያስተምራል። ከዱቁና እስከ ጵጵስና በሚሰጡ የክህነት መዓርጋት ለዚሁ የሚገቡ ሰዎችን የምንለይበት ሥርዓት በየጊዜው መጤን እንዳለበት ይጠቁማል ። ጳጳሳት ክህነት የሰጧቸውን ልጆቻቸውን ለመምከር ለመገሠጽ መሰቀቅ እንደማይገባቸው ያስገነዝባል።
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ኘቀፋ የሌለባቸው ሲሆኑ መንጋው እንደሚከተላቸው ድምጻቸው እንደሚሰማ ያሳያል።
• ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ " ትዳር _ክፍል ፩ “በማለት ባልና ሚስት በትዳራቸው ደስተኛና ውጤታማ እንዲሆን ከሚረዷቸው ነገሮች መካከል አንዱ የመንፈስ አንድነት ነው፡፡ ትዳር ለዕድሜ ለኢኮኖሚ ለቤተሰብ ጭቅጭቅ ለልጅ ፍቅር መልስ መስጫ አይደለም፡፡ ትዳር የራሱ ምንነትና መገለጫዎች አሉት።ትዳር እንደ ዕድር ወይም እንደ ዕቁብ ለመተጋገዝ ሲሉ ሰዎች የመሠረቱት ተቋም አይደለም፡፡ እነዚህ ማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ተቋማት እስከ ወደድህ አብረህ እስካለህ ብቻ በአባልነት የምትኖርባቸው ናቸው፡፡ የመኖርያ ቦታ ስትቀይር፡ ከአባላቱ ጋር መግባባት ካልቻልህ ወይም ደግሞ እንዲሁ ካልፈቀድህ አባልነትህን መተው ትችላለህ፡፡
ትዳር ግን የሰውን ባሕርይ፡ በባሕርይውም ያለውን ድካም፡ ለድካሙም የሚያስፈልገውን መፍትሄ ከሚያውቅ ከልዑል እግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡
• በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#በእንተ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ክፍል _፩ " በሚል ርእስ ስለቅዱስ ኤጲፋንዮስ ልደትና ዕድገት በስፋት ይዳስሳል ።
• በነገዋ ቤተ ክርስቲያን ዐምድ ሥር “ነገን ዛሬ እንሥራ _ክፍል ፪ “ በሚል ሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ ምንኩስናን በተመለከተ ፤በሥርዓተ ምንኩስና ውስጥ የሚነሱ ጉዳዮች ይዳስሳል ።ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክብሯ ተጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ ትተላለፍ ዘንድ ክህነት እና ምንኩስናን መጠበቅ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ ይታወቃል ።
#በኪነ ጥበብ ዐምድ "# ሎሚ ክፍል _፩ " በሚል ያስነብባል።
• የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “#ክርስትናና ዘመናዊነት ክፍል ፩- " በሚል ርእስ ከመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው ጋር የተደረገ ወቅታዊ ምላሽ ይዛለች ።
ሐመር መጽሔት ፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፭ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
magazine @eotcmk.org ሐመር መጽሔት ዝግጅት ክፍል

በህንድ ሀገር ማኅበረ ቅዱሳን ያስተማራቸው የማርዋዲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ተመረቁ።
በማኅበረ ቅዱሳን ሩቅ ምሥራቅ ማእከል አስተባባሪነት ላለፉት አራት ዓመታት ተከታታይ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሲማሩ የነበሩ አሥራ ዘጠኝ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ/ም ተመረቁ።
በዚህ የተማሪዎች ምርቃት መርሐ ግብር ላይ የግቢ ጉባኤው አባላትና ተመራቂ ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን የሩቅ ምሥራቅ ማእከል ጸሐፊ እና የግቢ ጉባኤ ማስተባበሪያ ክፍል አባላት መርሐ ግብሩን በዙም (Zoom) ተከታትለዋል።
የሩቅ ምሥራቅ ማእከል የተተኪ ትዉልድ እና ግቢ ጉባኤ ማስተባበሪያ ክፍል ተጠሪ ዶ/ር ሲራክ ተከተል ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
በመልእክታቸውም "ተመርቃችሁ ከወጣችሁ በኋላ በየአካባቢያችሁ በሚገኙ ማእከላት ሥር በመታቀፍ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የድርሻችሁን እንድትወጡ ማኅበራችሁ ማኅበረ ቅዱሳን ያሳስባችኋል" ብለዋል። በተጨማሪም ለግቢ ጉባኤዉ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ መምህራንና አስተባባሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።
በዕለቱም በዲ/ን ፋንታሁን የሩቅ ምሥራቅ ማእከል ጸሐፊ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል። ተመራቂዎችመእ መዝሙር ያቀረቡ ሲሆን ለተመራቂዎች የመስቀል ስጦታ በግቢ ግባኤው ሰብሳቢ መምህር ዋሲሁን አገሩ አማካኝነት ተበርክቷል።
በተመሳሳይ በህንድ ሀገር በኬአይአይቲ (KIIT) ግቢ ጉባኤ ስር ሆነዉ ላለፉት 3 ተካታታይ ዓመታት ሲማሩ የነበሩ 5 የግቢ ጉባኤዉ አባላት ተመርቀዋል።
ዘገባውን የማኅበረ ቅዱሳን ሩቅ ምሥራቅ ማእከል ሚዲያ ክፍል አድርሶናል።

በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች የሽኝት መርሐ ግብር ተከናወነ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አቡዳቢ ልዩ ግንኙነት ጣቢያ ከሊባኖስ፣የተባበሩት ዐረብ ኢምሬትስ እና የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገረ ስብከት ጋር በመተባበር ለትምህርት ወደ ተባበሩት ዐረብ ኤሜሬትስ በመሄድ ሲማሩ ለቆዩ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች የሽኝት መርሐ ግብር አከናወነ።
የመጀመሪያ ዓመት ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ አገር ቤት ለሚመለሱ ተማሪዎች ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በተከናወነው የሽኝት መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ በሊባኖስና የተባበሩት አረብ ኢምሬትና የመካከለኛው ምስራቅ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፤ የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ቀሲስ ደረጀ ጂማ፣ መላከ ሰላም መምህር ለይኩን ብርሃኑ፣ መምህር ኪሩቤል ይገዙ፣ ሊቃውንተ ቤተክርቲያናት እንዲሁም የልዩ ግንኙነት ጣቢያው አባላትና ተባባሪ አካላት ተገኝተዋል።
ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎችን ከመቀበል ጀምሮ፣ በግቢ ቆይታቸው መንፈሳዊ ሕይወታቸውንም አጠንክረው እንዲወጡ የተለያዩ ትምህርቶችን በመስጠት እና እንዲያገለግሉ በማድረግ ከፍተኛ ሥራ እየሠራ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን በኢማራት ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ሲያስተምራቸው የነበሩት እነዚህ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችም በመርሐ ግብሩ ላይ ወረብ እና መዝሙር፤ በኢማራት ላይ የአንድ አመት ቆይታቸውን በተመለከተ ውይይት ፤ እንዲሁም የአብነት ትምህርት ሁለንተናዊ ሕይወትንም የሚያስገነዝብ ትእይንትም አቅርበዋል።