Telegram Web Link
በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር አዘጋጅነት ለአንድ ሳምንት ሲከናወን የቆየው የመጽሐፍ ቅዱስ ሳምንት እና የቅዱሳት መጽሐፍት ዐውደ ርእይ ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተከናወነ።

በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበረ አዘጋጅነት ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በስካይ ላይት ሆቴል " መጽሐፍ ቅዱሳዊ እሴቶችን በሕዝባችን ሕይወት እናስርጽ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የመጽሐፍ ቅዱስ ሳምንት እና የቅዱሳት መጽሐፍት ዐውደ ርእይ የማጠቃለያ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።

መርሐ ግብሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ  ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ   ቤተ  ክህነት  ዋና  ሥራ  አስኪያጅ    እና  የባሕር  ዳር ሀገረ  ስብከት  ሊቀ  ጳጳስ ፤ ብፁዓን አበው ሊቀነ ጳጳሳት ፣ የቤተ እምነት መሪዎች ፤ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተከናውኗል።

የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሊቀ ኅሩያን ይልማ ጌታሁን በመርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎች ሐሳብ ሳይጨመርበት ለምእመናን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ከመተርጎም ጀምሮ የማሰራጨት ተግባርን ላለፉት 98 ዓመታት ሲያከናውን እንደነበር ገልጸው ይህንን ሥራ በቀጣይ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ዋና ጸሐፊው በተጨማሪም ለመርሐ ግብሩ መሳካት በአገር ውስጥ እና በውጭ አገራት የሚገኙ ደጋፊ አካላት ላደረጉት ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም በተመለከተ ሦስት ጽሑፎች ለታዳሚው ቀርቧል።
መፃጒዕ

አራተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹መፃጒዕ› ይባላል፡፡ ስያሜው በዮሐንስ ወንጌል ፭፥፩ ላይ ከሚገኘው ኃይለ ቃል ያለ ነው፡፡ መፃጒዕ ደዌ የጸናበት በሽተኛ፣ ሕመምተኛ ማለት ነው፡፡ መፃጒዕ ለ፴፰ ዓመት በአልጋው ላይ ሆኖ ምሕረትን ሲጠባበቅ የኖረ ሰው ነው። ስፍራዋም “ቤተ ሳይዳ” ትባላለች።ቤተ ሣህል (የምሕረት ቤት) ማለት ነው፤ መጠመቂያዋም በሰሎሞን ቤተ መቅደስ አጠገብ የምትገኝ ናት፡፡ (ዘሌ.፱፥፪) “ቤተ ሳይዳ” ዘይሁዳና “ቤተ ሳይዳ” ዘገሊላ የሚባሉ እንዳሉ በግልጽ በቅዱሳት መጻሕፍት ተገልጿል። “ወቦ ውስተ ኢየሩሳሌም ምጥማቃት ዘጵሩጳጥቄ ቅልንብትራ ዘውእቱ ቀላየ አባግዕ ብሂል ወይቤልዋ ስማ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ወባቲ ኃምስቱ ሕዋራት” …በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት” ብሎ ሲገልጽ ነው። (ዮሐ.፭፥፪)

ቤተ ሳይዳ ዘኢየሩሳሌም ባለ አምስት በር፣ እርከን (መመላለሻ)፣ አምስት ዓይነት ድውያን ፈውስን ለማግኘት ጥምቀቱን ሲጠባበቁ የሚኖሩባት ናት። ውኃው የቤተ አይሁድ ምሳሌ፣ አምስት መመላለሻ የሕግጋተ ኦሪት እና የአምስቱ መጻሕፍተ ሙሴ ምሳሌ በእነዚያ ተጠብቀው ለመኖራቸው ምሳሌ ነው። ቀድሞ የገባባት አንዱ እንዲድን፣ እነርሱም አንድነት ቤተ እስራኤል ተሰኝተው ለመኖራቸው ምሳሌ ነው። አንድም አምስቱ እርከን (መመላለሻ) የአምስቱ አዕማደ ምሥጢር በዚያ ሊያምኑ ያሉ ተስፈኞችና ያመኑባትም ልጅነትን ያገኙባታልና። አምስቱ ዓይነት ድውያንም የአምስቱ ጾታ ምእመናን ከእነ ፈተናቸው ምሳሌ ነው፡፡ እነርሱም አእሩግ በፍቅረ ነዋይ፣ ወራዙት በዝሙት፣ አንስት በትውዝፍት (በምንዝር ጌጥ)፣ ካህናት በትዕቢት አእምሯችን ረቂቅ መዓረጋችን ምጡቅ እያሉ፣ መነኮሳት በስስት ምግብን በፈለጉት ጊዜ ባያገኙት ይልቁንም በአት እየፈቱ በከንቱ የመፈተናቸው ምሳሌ ሆኖ ይነገራል።

መልአከ እግዚአብሔር ወርዶ ውኃውን ሲያናውጥ ቀድሞ የገባ የሚነጻባት፣ ነገር ግን በዕለቱ ከአንድ ሕመምተኛ በቀር ለሌላው ፈውስ የማይደገምባት ቦታ ናት። ሐተታው የመጠመቂያ ውኀው የማየ ጥምቀት ምሳሌ ሲሆን ውኃውን ያናውጥ (ይባርክ) የነበረው መልአክ የቀሳውስት (ካህናት) “ለቀድሶተ ማየ ጥምቀት” የመውረዳቸው ምሳሌ ነው፤ ፈውሱም የሚከናወነው በዕለተ ቀዳሚት ሲሆን የሚፈወሰው አንድ ሰው ብቻ ነበር፡፡ የሚድነው አንድ ታማሚ ብቻ መሆኑ የአባቶቻቸው ምሕረት አለመቅረቱን ሲያሳይ፣ አለመደገሙ ደግሞ ፍጹም ድኅነት እንዳልነበረ ያሳያል፡፡

ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ያህል በደዌ ዳኛ፣ በአልጋ ቁራኛ ተይዞ የኖረ መፃጉዕን በአልጋው ተኝቶ ሳለ ደዌው እንደጠናበት ፈውስ እንደዘገየበት አይቶ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀርቦ ያንን በሽተኛ “ትፈቅድኑ ትሕየው? … ባድንህ ፈቃድህ ነውን?” አለው። ማእምረ ኅቡዓት ክርስቶስ፣” አዎን፥ እንዲለው እያወቀ”፤ ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልእክቱ “የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም” ብሎ የመሰከረለት ጌታችን ፈውስን በመጠባበቅ ከመዳን ውጪ ሌላ ዓላማ ያልነበረውን ይህን ሰው አይቶ ፈቃዱን እያወቀ ግን ፍቀድልኝና ላድንህ አለው። (ዕብ.፬፥፲፪) “ሰው በከንቱ ወራቱ ቍጥርና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማነው?“ እንዲል፤ (መክ.፮፥፲፪) የሚያስፈልገንን ሳንነግረው የሚያውቅ የሚሰጠንም ከእርሱ ከፈጣሪው ውጪ በእውነት ማን አለ?

መፃጉዕ በኋላ የሚክድ ነውና “ሳልፈቅድለት ነው ያዳነኝና አልጋ ያሸከመኝ” እንዳይል፣ በዕለተ ዓርብ የሚከስበትን ሲያሳጣውና ለኋላ ጥፋቱ የገዛ ኅሊናው እንዲቀጣው ፈቃዱን ጠየቀው። “ሰው የሌለኝ ሆኖ እንጂ ያንንማ ማን ይጠላል” በሚል ጉጉቱን ከወዳጅ አልባነቱ ጋር ድኅነትን ፈቅዶ ገለጠ። እስከ ውኃው መናወጥ ሳያቆየው “ተንሥእ ንሣእ ዓራተከ ወሑር …፤ ተነሥና አልጋህን አንሥተህ ሂድ” አለው፤ ወዲያው አፈፍ ብሎ በፍጥነት ያን ሁሉ ዘመን የተሸከመች አልጋ ተሸክሟት ሄደ።

ጌታችን መፃጉዕን ‹‹ተነሥተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ›› ያለው፦

• አንደኛው ቅዱስ ኤስድሮስ እንዳለው አልጋው ጠንካራ የብረት አልጋ ነበረና ጽንዓ ተአምራቱን ለማሳየት ነው፡፡

• ሁለተኛው ‹‹ታዲያ ቢያድነኝ በከንቱ መች ሆነና የገዛ አልጋዬን ትቼለት የመጣሁ ለመዳኔ ዋጋ የከፈልኩበት አይደለምን?›› እንዳይል “አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” ብሎታል።

ያለ ተረፈ ደዌ አንሥቶት “ያለህን ይዘህ ሂድ፤ እኔ ከአንተ አንዳች አልሻም” ባሰኘ ቃል ሸኝቶታል። ታዲያ ይህ ምስኪን መፃጒዕ “ሰው የለኝም” ብሎ የደረሰለትን ረሳ፤ ማን እንደሆነ እንኳን አላወቀውም። ወንጌላዊውም “ዘሐይወ ኢያእመረ ዘአሕየዎ …፤የዳነው ያዳነውን አላወቀውም” ይለዋል። ( ዮሐ.፭፥፲፫) ይህን ሁሉ ያደረገው አምላክ ተዘነጋ። ዛሬም ከደዌው፣ ከማጣቱ፣ ከችግሩ፣ ከሥጋ ኑሮ ጉድለቱ እንደ መፃጒዕ አምላኩን ያልረሳ ማነው? ተአምራቱን አይቶ፣ ቃሉን ሰምቶ አምላኩን ያስታወሰስ ማነው? ቃሉን ያይና ይሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ምክር የቆመ ማን ነውና? ቃሉንስ ያደመጠስ ማን ነው?” (ኤር. ፳፫፥፲፰)። እኛም ብንሆን ከአዳም በደል ነጻ ያደረገንን አምላክ ውለታ ዘንግተን የምናፌዝ ሁላችንንም ወደ ልባችን እንድንመለስ ነቢዩ እንዲህ ሲል ይመክረናል “እስራት እንዳይጸናባችሁ አታፊዙ፡፡” (ኢሳ.፳፰፥፳፪ )

መፃጉዕ ያዳነው ማን እንደሆነ ሲጠየቅ እንኳን አላወቀም። ወንጌላዊውም “የዳነው ያዳነውን አላወቀውም” ብሎ ገልጾታል። (ዮሐ.፭፥፲፫) በምኩራብ አግኝቶት ያዳነውን እንዳወቀውም ሄዶ ለአይሁድ “ያዳነኝ እርሱ ጌታ ኢየሱስ ነው” ብሎ ነገራቸው፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በቤተ መቅደስ ሳለ ያን ያዳነውን ሰው አገኘውና “ዑቅ ኢትአብስ ዳግመ እንከ ከመ ዘየአኪ ኢይርከብከ፤ ከዚህ የከፋ “ስለ ደዌ ሥጋ ፈንታ ደዌ ነፍስ” እንዳያገኝህ ሁለተኛ እንዳትበድል” (ቁ.፲፬) ያለውን ዘንግቶ ደዌ ዘኃጢአትን ጠርቶ ተወዳጃት፤ በዕለተ ዓርብ የጌታውን ጉንጮች የጸፉች እጁም ደርቃ ሰላ ቀርታለች።

ዛሬም ቢሆን እንደ መፃጉዕ ሰዎች በኃጢአት ብዛት ልባቸው የደረቀና ያበጠ፣ ሰውነታቸው የሰለለ፣ ዓይነ ሕሊናቸው የታወረ፣ እግረ ልቡናቸው የተሰበረ ብዙዎች ሕሙማን በጠበል ቦታ፣ በገዳማት እና በአድባራት አሁንም አሉ፡፡ ፈውስን ይሻሉ፤ ድኅነትን ይፈልጋሉ፡፡ እንደ መፃጕዕ ቦታቸውን ሳይለቁ እግዚአብሔርን በተስፋ ቢጠብቁት አንድ ቀን ይፈወሳሉ።

ስለዚህ ይህ ሳምንት ጌታችን ድውያንን ስለመፈወሱ የሚነገርበትና እኛም ባለን ዓቅም በነፍስ በሥጋ የተቸገሩትን ሁሉ መርዳትና ማገዝ እንዳለብን የምንማርበት ሳምንት ነው፡፡ ሕሙማንን መጠየቅ፣ የታሰሩትን መጎብኘትና ማስፈታት፣ የተራቡትን ማብላት፣ የተጠሙትን ማጠጣት፣ የታረዙትን ማልበስ፣ ያዘኑትን ማረጋጋት ከጌታችን የተማርናቸው ክርስቲያናዊ ምግባራት ናቸው፡፡

በዚህ ዕለት የእግዚአብሔር አምላካችን ፈዋሽነትና አዳኝነት እንዲሁም ታዳጊነትና የወደቁትን የማይረሳ እውነተኛ መድኃኒት መሆኑ የሚዘከርበትና ምስጋና የሚቀርብበት ነው። ቅዱስ ዳዊትም "እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ፣ ወይመይጥ ሎቱ ኩሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ፣ አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ፤ እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውንም ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል፣ እኔም አቤቱ ማረኝ እልሃለሁ” በማለት የእግዚአብሔርን አዳኝነት በዝማሬው አረጋግጧል።

ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ “ችግረኛውን ከቀማኛው እጅ፣ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና” ሲል ሲቀኝ፣ (መዝ.፸፪፥፲፪) ጻድቁ ኢዮብም እንዲሁ “ረዳት (ኃይል) የሌለውን ምንኛ ረዳኸው” በማለት የእግዚአብሔርን አዳኝነት መስክሯል፡፡ (ኢዮ.፳፮፥፪) ስለዚህ ገንዘብ፣ ሥልጣን፣ ወገን፣ ረዳት የለኝም በማለት ተስፋ የቆረጥን ሰዎች እግዚአብሔር ከሰውም፣ ከሥልጣንም፣ ከገንዘብም በላይ ነውና እርሱን ተስፋ አድርገን ሁል ጊዜ በስሙ መጽናናት እና የሚያስጨንቀንን ሁሉ በእርሱ ላይ መጣል እንደሚገባን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “አቤቱ የሚፈልጉህ ሁሉ በአንተ ደስ ይበላቸው፤ሐሤትም ያድርጉ፡፡ ሁል ጊዜ ማዳንህን የሚወዱ ዘወትር እግዚአብሔር ታላቅ ይሁን ይበሉ” እንዳለው ሁል ጊዜም በአምላካችን እግዚአብሔር ደስተኞች
እንሁን። (መዝ.፵፥፲፮)

በኃጢአት ከሚመጣ ደዌ ተጠብቀን በአባታዊ ምሕረቱ የሚጠብቀንን ቸሩ አምላካችንን እያመሰገንን በቤቱ እንድንጸና መፃጒዕን “ተነሣ” እንዳለው እኛንም ከወደቅንበት ኃጢአት በንስሓ እንዲያነሣንና ዳግም ከመበደልም እንዲጠብቀን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን። የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከት አይለየን፤ አሜን!

በመልእክታቱ የሚነበቡት
(ገላ.፭፥፩ እና ያዕ.፭፥፲፬) ስለ ድውያን መፈወስ የሚያወሱ ናቸው፡፡
ከሐዋርያት ሥራ የሚነበውም እንዲሁ (ሐዋ.፫፥፩)

የዕለቱ ምስባክ፦ “እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ፤ ወይመይጥ ሎቱ ኵሉ ምስካቢሁ እምደዌሁ፤ አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ፤ በደዌው አልጋ ላይ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውንም ሁሉ ከበሽታው የተነሣ ይለውጥለታል፡፡ እኔስ “አቤቱ ይቅር በለኝ፤ አንተን በድያለሁና ለነፍሴ አስተስርይላት” አልሁ፡፡” ይላል (መዝ.፵፥፫)
“ችግሮች ቢኖሩም ራሳቸውን ለቤተ ክርስቲያን አሳልፈው የሚሰጡ ልጀች እንዳሉ አይተናል፤ ቤተ ክርስቲያን መሻገሯ አይቀርም”

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባሕር ዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

የማኅበረ ቅዱሳን የ2016 ዓ.ም የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ በመጨረሻ ቀን ውሎው ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባሕር ዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተው ቃለ ምእዳን ሰጥተዋል።

የማኅበሩ ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም ለብፁዕነታቸው ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በዚህ የሥራ አመራር ጉባኤ በሀገር ውስጥ ካሉን 55 ማእከላት ውስጥ ጦርነት ውስጥ ካሉ አካባቢዎች ሳይቀር ከ48 ማእከላት ሰብሳቢዎች እና ተወካዮች እንዲሁም ከውጭ 9 ማእከላት ተሳትፈዋል ብለዋል።

ሰብሳቢው አክለውም ጉባኤው በሁለት ቀን ውሎው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሁናዊ ችግሮችና መፍትሔዎች እንዲሁም የማኅበረ ቅዳሳን የአገልግሎት ድርሻ ላይ መወያየታቸውን አስታውቀዋል።

“ጽና፤ እጅግም በርታ” በሚል ኃይለ ቃል ቃለ ምእዳን የሰጡት
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባሕር ዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

“የኛ የሆነውን አሳልፎ ላለመስጠትና በክብር የተቀበልነውን በክብር ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ጥንካሬ ያስፈልጋል፤ እናንተም ጽናት ባይኖራችሁ በዚህ ሁሉ መከራ መሀል አትገኙም።ችግሮች ቢኖሩም ራሳቸውን ለቤተ ክርስቲያን አሳልፈው የሚሰጡ ልጀች እንዳሉ አይተናል” ብለዋል።

ትውልዱ ጽናት ያለው የሚመስል ነገር ግን በጉዞ መሐል የሚንቀጠቀጥ የሚንገዳገድ ትውልድ መሆን የለበትም ሲሉም አብራርተዋል ።
“ከምእመን እስከአባቶች ከበረታን ቤተ ክርስቲያን ከእነሙሉ ክብሯ ትተላለፋለች፤ መሻገሯም አይቀርም” ያሉት ብፁዕ አቡነ አብርሃም “ ሌላ ጉልበት የለንም ጉልበታችንም ጽናታችንም እግዚአብሔር ነው፤ አቅጣጫ የሚሰጠንም ቃሉ ነው፤ እግዚአብሔር ሁሉን እንደሚያስተካክል እናምናለን የእኛ ድርሻ ግን እንወጣ ” ብለዋል።

ብፁዕነታቸው ማኅበሩ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጋር የበለጠ በመናበብና ግብዓት በመስጠት በፍቃደ እግዚአብሔርና በጥበብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እናሻገር ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ከውጭ ሀገራት የተሳተፉ አባላትን መነሻ በማድረግም “ጽኑ፤ በምትሠሩት መንፈሳዊ አገልግሎትም ቤተ ክርስቲያንን ድምጽ ስለሆናችሁ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ስም አመሰግናለሁ” ብለዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የ2016 ዓ.ም የ6 ወር የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤውን አጠናቀቀ::

ትናንት መጋቢት 21/2016 ዓ.ም በመጀመሪያ ቀን ውሎው የሥራ አመራር የ6ወር ቃለ ጉባኤ ፣ የሥራ አመራር ጉባኤ ጽ/ቤት ፣ የሥራ አሰፈጻሚ ጉባኤ ፣ የኤድቶሪያል አገልግሎት ማስተባበሪያ እና የኦዲት አገልግሎት ሪፖርቶች ቀርበው ተወያይቷል ፡፡

በዛሬው ሁለተኛ ቀን ውሎውም በወቅታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጉዳዮችና የማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ድርሻ ላይ በሰፊው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል::

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተውም ለተሳታፊዎቹ አባታዊ ቡራኬና ቃለ ምእዳን አስተላልፈዋል::

የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም በማጠቃለያ መልዕክታቸው ’’በፈተና ውስጥ ሁነንም ቢሆን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንትጋ፤ የማኅበረ ቅዱሳንን እሴቶችና መርሆዎችንም እንጠብቅ፤ በጸሎትና በመንፈሳዊ ሕይወታችንም እንበርታ’’ ብለዋል::

የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ በበኩላቸው የማኅበሩ አባላት የማኅበረ ቅዱሳንን መዋቅር በመጠበቅ የአገልግሎት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ካለፈው ጊዜ በላይ እንዲተጉ መልእክት አስተላልፈዋል::
The Impotent Man

There was once an impotent man during the apostasy age, embedded for 38 years at Bethsaida pool, in Jerusalem nearby the temple. His luck was so unfortunate that disabled him to enter the pool for cure whilst the Angel of God stirred it up once a while, that is on the first Sabbath. (John 5:4)

The Bethsaida had five porticoes and steps for the aliment to enter the pool and be baptized for their cure. The resemblance of the water is the Jews, the five porticoes resembles Torah and the five books of Mosses in which they were fenced by. The way one entered first to the pool and be cured, is the resemblances of the unity of theirs named “House of Israeli.” The other resemblance of the five porticoes is the “Five Sacrament of the Church.” Those who hope and in faith of them, are endowed Childhood of Holy Trinity. The five types of aliment are the resemblances of the five gender laity alongside their tribulations.
Those are elderly by love of money, youngsters by fornication, women by jewelries, Priests by conceit and monks by greed)

The Angel of God come down from the heavens and stirring up the water and only one who entered the pool was cured. The meaning of the water is baptism and the Angel who stirred it is the resemblance of priests who comes down to sanctify the water and on the sixth day; Sabbath, only one person was being cured which signifies the mercy of our fathers that is not seized and the truth about erratic of it, shows its un-absoluteness.

Lord and Savior Jesus Christ saw the impotent lying there, and knew that he already had been in that condition a long time, He said to him, “Do you want to be made well?” The sick man answered Him, “Sir, I have no man to put me into the pool when the water is stirred up; but while I am coming, another steps down before me.” Lord Jesus said to him, “Rise, take up your bed and walk.” And immediately the man was made well, took up his bed, and walked. And that day was the Sabbath. (John 5:6-9)

Lord Jesus whom Saint Paul witnessed for in his epistle to the Hebrews saying, “For the word of God is living and powerful, and sharper than any two-edged sword, piercing even to the division of soul and spirit, and of joints and marrow, and is a discerner of the thoughts and intents of the heart” asked the impotent man if he wished to be healed. (Hebrew 4:12) As it is stated, “For who knows what is good for man in life, all the days of his vain life which he passes like a shadow? Who can tell a man what will happen after him under the sun?” who can know and give us what we seek without us asking Him, but our God. (Ecclesiastes 6:12)

However, he was going to betray Him later on and for him not accuse the Lord saying, “He cure me without my permission, telling to carry my bed,” he asked his own permission, also for his conscience to castigate him.

The reason our Lord told the impotent man to “Rise, take up your bed and walk”: -
• is as Saint Esdros said, which the Lord will to reveal His miraculous as the bed was made up of strong metal
• the second is for the impotent man not to say “I have also payed sacrificed for my healing as I left my bed for Him.” and thus he told Him to “take up your bed and walk.”

Unfortunate though! The impotent man who was embedded for 38 years and had no one to take care, forgot His healer. He did not even know Who He was. The Evangelist John said, “But the one who was healed did not know who it was.” (John 5:13) The Lord Who has done all this was forgotten. Just as today, who has not forgotten God Who healed us from our aliments, tribulations and scarcity like the impotent man? And who has remembered Him listening to His words and seeing His miraculous? Is there anyone who stood up with the counsel of God to listen and witness His words? Any person who listen to His words?

Prophet Jeremiah said, “For who has stood in the counsel of the Lord, and has perceived and heard His word? Who has marked His word and heard it? (Jeremiah 23:18) We have also forgotten The Lord’s sacrifice who has freed us from the Adam’s infirmity and mock are told to look into our heart by Prophet Isaiah as, “Now therefore, do not be mockers.” (Isaiah 28:22)

The impotent was unaware of Who cured him. when he found Him in the synagogue, he went and told the Jews it was Lord Jesus who cured him. “Afterward Jesus found him in the temple, and said to him, “See, you have been made well. Sin no more, lest a worse thing come upon you.” (no. 14) But forgetting his healer, the impotent man slapped his Lord and therefore his hands dried and slimmed.

Now a days as well, alike the impotent man, many of our hearts has dried, personhood slimmed, consciously blinded, broken heart, seeking cure surrounding the baptism site, churches, parishes and monasteries. We seek healing and salvation. We can be healed if we hold on to the hope of God just like the impotent man.
The Ethiopian Orthodox Incarnation Church has named the fourth week of “The Great Lent” with the healed person in Bethsaida “The Impotent Man,” accordingly and commemorates it by the cured ailments of Lord and by helping out the poor. We shall then visit the sick, free the prisoners, feed the hungered, water the thirst, clothe the deprived and sympathize the depressed as we learned from our Lord.

On the Sabbath, it is the day we commemorate and glorify God’s healing and redemption. Prophet David sings as, “for He will deliver the needy when he cries, the poor also, and him who has no helper.” (Psalm 72:12) Righteous Job has witnessed saying, “How have you helped him who is without power? How have you saved the arm that has no strength?” (Job 26:2)

Prophet David’s words “Let all those who seek You rejoice and be glad in You; Let such as love Your salvation say continually, “The Lord be magnified!”, we shall also be happy about God. (Psalm 40:16)
Readings: -(Galatians 5:1 and James 5:14)
(Acts 3:1)
“Mesebak” Prophets David’s words in rhyme: - “The Lord will strengthen him on his bed of illness; You will sustain him on his sickbed. I said, “Lord, be merciful to me; Heal my soul, for I have sinned against You.” (Psalm 41:3-4)
May God’s mercy, benevolence and blessing be with us, Amen!
2024/09/29 22:29:55
Back to Top
HTML Embed Code: