Telegram Web Link
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አጀንዳ
አርቃቂ ብፁዓን አባቶችን ሰየመ።
****


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የጥቅምት ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ምልአተ ጉባኤውን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የመክፈቻ መልዕክት ዛሬ ጠዋት መጀመሩ ይታወቃል።

ከቅዱስነታቸው የመክፈቻ መልእክት በኋላም የመወያያ አጀንዳ ቀርጸው የሚያቀርቡ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳትን ሰይሟል።

በዚህም መሠረት፦
፩ኛ ብፁዕ አቡነ ሔኖክ
፪ኛ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
፫ኛ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ
፬ኛ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ
፭ኛ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል
፮ኛ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
፯ኛ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በመሆን አጀንዳ የማርቀቅ ተግባራቸውን በማከናወን ላይ ይገኛሉ።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ የሚያቀርቡትን ረቂቅ አጀንዳ ከመረመረና ማስተካከያ ካደረገበት በኋላ የጸደቀውን አጀንዳ መሰረት በማድረግ በቅደም ተከተል እየተወያየ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

ምንጭ: የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
“ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ልከተለው እሄዳለሁ” (መጽሐፈ ስንክሳር)

ለመንግሥቱ ፍጻሜ ለባሕርዩ ኅልፈት ውላጤ የሌለበት ወይም የማይኖርበት እግዚአብሔር አብ፣ አዳምን ለማዳን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከነፍስዋ ነፍስ ነሥቶ ሥጋዋን ተዋሕዶ ሰው የሆነ እግዚአብሔር ወልድ፣ በባሕርዩ መጉደል ወይም መጨመር ሳይኖርበት በመንግሥቱ ከአብ ከወልድ ጋር አንድ የሚሆን በኀምሳኛው ቀን በደብረ ጽዮን የወረደ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይድረሳቸውና ለእኛ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ውስጥ ለምንኖር ምእመናን ብንቆጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ የሚበዙ ድንቅ ምስክሮችን ጻድቃንን በአማላጅነታቸው እንድንጠቀም አድለውናል፡፡ ከእነዚህ መካከል ጥቅምት ፲፬ ቀን በዓላቸውን የምናከብረው ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ እና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ይገኙበታል፡፡

አባታችን አቡነ አረጋዊ አስቀድሞ ራሱ ባለቤቱ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ የመሠረተውን ሥርዓተ ገዳምን ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያመጡ ታላቅ መናኝና ጻድቅ አባት ናቸው፡፡ አባታችን ከእንጦንስና ከመቃርስ፣ ከጳኵሚስም የምንኵስና ሐረግ ዐራተኛ ትውልድ ናቸው፡፡ ከሮም ነገሥታት መካከል ከሆኑት ከአባታቸው ከይስሐቅ ከእናታቸው ከእድና የተወለዱት አባታችን ወላጆቻቸው የታላላቅ ነገሥታት ወገን የምትሆን ሚስት ቢያጩላቸው እምቢ በማለት ከሮም ወደ ፅርዕ (ግሪክ) አገር በመሔድ ታላቁን የመንፈሳዊ ማኅበር ከመሠረተውና የመነኮሳት አባት ከሆነው ከቅዱስ ጳኵሚስ ዘንድ የምንኵስናን ልብስ የተቀበሉና ክርስቶስን ለመከተል ገና በልጅነታቸው የመረጡ አባት ናቸው፡፡ በሥጋዊ መጠነ ቁመታቸው ወይም በዕድሜ ታናሽ የሆኑት አባታችን በጥበብ ፣ በምክርና በዕውቀት ግን የልጅ ዐዋቂ በመሆናቸው ዘሚካኤል ከተባሉበት ስማቸው አረጋዊ ለመባል በቅተዋል፡፡
ጻድቁ አባታችን አምላክን በወለደች በእመቤታችን በድንግል ማርያምና ጌታችን ዐሥራት አድርጎ በሰጣት በኢትዮጵያ ፍቅር ልባቸው በመነደፉ ከሁለት ደቀ መዛሙርቶቻቸው ጋር ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ከእርሳቸው ጋር ዘጠኝ ለሆኑት ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ምክንያት የሆኑ አባት ናቸው፡፡ በጥቅምት ፲፬ ዕለትም እንደነ ሄኖክ ፣ ኤልያስና ዕዝራ ሞትን ሳያዩ ወደ ብሔረ ሕያዋን የተሰወሩበትን በዓል የምናከብራላቸው ክርስቶስን በእውነት የተከተሉ አባት ናቸው፡፡

የቅዱስ ገብረ ክርስቶስም ሕይወት እንደ ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ ክርስቶስን የመከተል ሕይወት ነው፡፡ የቊስጥንጥንያ ንጉሥ የሆነው አባቱ ቴዎዶስዮስ እና እናቱ መርኬዛ ከሮም ንጉሥ ልጅ ጋር ቢያጋቡትም ክርስቶስን ለመከተል ከሙሽራ ቤት የወጣ ታላቅ የትሕትና እና የትዕግሥት መምህር ነው፡፡ በጥቅምት ፲፬ ቀን የሚነበበው የስንክሳር መጽሐፋችን ስለ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ የሰርግ ምሽት እንዲህ ይላል ፡- “ከሌሊቱ እኩሌታም በሆነ ጊዜ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ ተነሥቶ ወደ ሙሽራዪቱ ገባ፤ እጅዋንም ይዞ ከእርስዋ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፡፡ ከዚያም የሃይማኖት ጸሎት “በአንድ አምላክ እናምናለን” የሚለውን እስከ መጨረሻ ጸለየ፤ የተሞሸረበትንም ልብስ ከላዩ አውልቆ የግምጃ ልብስን ለበሰ፤ ወደ ሙሽሪቱም ሒዶ ራስዋን ሳማት፤ እንዲህም እያለ ተሰናበታት፤ “እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይኑር፤ ከሰይጣን ሥራ ሁሉ ያድንሽ፡፡ እርሷም አልቅሳ “ጌታዬ ወዴት ትሔዳለህ? ለማንስ ትተወኛህ?” አለችው፤ እርሱም “በእግዚአብሔር ዘንድ እተውሻለሁ፤ እኔም ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ልከተለው እሔዳለሁ፤ የአባቴ መንግሥት አላፊ ነውና አንቺም መሐላሽን አስቢ” አላት፤ ያን ጊዜ መሐላዋን አስባ ዝም አለች፡፡ ቅዱስ ያሬድ ይህን የቅዱስ ገብረ ክርስቶስን የልዕልና ተግባር “ቦ ዘፈለሰ ኀዲጎ ብእሲቶ ኃዲጎ ብእሲቶ ቦ ዘፈለሰ ወቦ ገዳመ ዘተግሕሠ መኒኖ መንግሥቶ መንግሥቶ ገብረ ክርስቶስ፤ ሚስቱን ትቶ ተሰደደ ገብረ ክርስቶስ ንግሥናውን ንቆ ገዳም ገብቶ ተቀመጠ” በማለት ጠቅሶታል፡፡
ከዚህ በኋላ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በአርማንያ አገር በተሠራች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ደጅ የሚኖር ሆነ ፡፡ በዚህም ‹‹አብደርኩ እትገደፍ ውስተ ቤተ እግዚአብሔር፤እምንበር ውስተ ቤተ ኃጥአን፤ በኃጥአን ድንካኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ” የሚኖረውን የቅዱስ ዳዊትን ቃል ፈጸመ፡፡ (መዝ.፹፫፥፲)

ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ልከተለው እሔዳለሁ›› በማለት እውነተኛውን ፍቅር በመከተል ለክብር በቅቷል፡፡ እኛስ ምን እንከተል? ምንስ እንተው? ፍቅርን ትተን ጥላቻን በመከተላችን በእያንዳንዳችንም ሆነ በሀገር ደረጃ ትልቅ መከራ እያሳለፍን ነው፡፡ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ በእመቤታችን ስም በታነጸች ቤተክርስቲያን ደጅ መጣልን መርጧል፤ እኛስ ከየትኛው ደጅ ተጥለን እንገኝ? ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዕለት ዕለት ከምትሰብከው በኅብረት የመኖር ደጅ ወይስ በዘር የመለያየት ደጅ? አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም፣ በአባቶቻችን በአቡነ አረጋዊ እና በቅዱስ ገብረ ክርስቶስ አማላጅነት ጥላቻን ትተን፣ ንቀንና ፍቅርን ተከትለን በቤተ ክርስቲያን ኅብረት በአንድነት እንድንኖር ይርዳን፡፡

ምንጭ ፡- ስንክሳር ዘወርኀ ጥቅምት፣ ገድለ አቡነ አረጋዊ
✝️ማኅበረ ቅዱሳን አ/አ/ማእከል ጥቅምት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ የምክረ አበው መርሐ ግብር በማኅበረ ቅዱሳን ሕንፃ 3ተኛ ወለል ላይ አዘጋጅቷል፡፡ እኛም እንገኝ የመርሐ ግብሩ ተሳታፊ እንሁን!!!
👉👉
🌹መቅረት ያስቆጫል!!!🌹👈👈
‹‹ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ›› (መሓ.፯፥፩)
ክፍል ሦስት

ይህ ወቅት የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወቅት ነው፡፡ ‹‹ወቆመ ውእቱ አርዌ አንጻረ ይእቲ ብእሲት ከመ ሶበ ወለደት ይብላዕ ሕፃና ወወለደት ወልደ ተባዕተ ዘውእቱ ይርዕዮሙ ለኩሉ አሕዛብ በበትረ ኀጺን….ወጎየት ይእቲ ብሲት ውስተ ገዳም ወውስተ መካን ዘአስተዳለወ ላቲ እግዚአብሔር፤ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ፡፡ አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸውም ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ ወለደች፡፡……..ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሃ ሸሸች፡፡ (ራእ.፲፪፥፬-፮) የነገረ ማርያም ሊቃውንት ሴቲቱ የተባለች እመቤታችን፣ አሕዛብን በብረት በትር የሚገዛቸው ወንድ ልጅ የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብለው ተርጉመዋል፡፡ ‹‹ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል›› (ኢሳ.፱፥፮) እንዳለ ኢሳይያስ፡፡

ዘንዶ የተባለ ዲያብሎስ በጨካኙ ሄሮድስ ላይ አድሮ ያለ አባት በድንግልና የወለደችውን ልጇን ይገድልባት ዘንድ ተነሥቶባታልና፤ በረሃ ወደ ተባለ ግብጽ ተሰደደች፡፡ በዚያም ብዙ መከራን ተቀበለች፡፡ እስከ ምድረ ግብጽ ባደረገችው ስደት ለ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ያህል በረሃ ለበረሃ፣ ጫካ ለጫካ፣ እሾህ እየወጋት፥ እንቅፋት እየመታት፣ ረኃቡና ጥሙ እያሠቃያት ሽፍቶች እና ጨካኞች አራዊት ባገኟት ቁጥር በድንጋጤ፣ በጭንቀት ብዙ መከራ እየተቀበለች ተንከራታለች፡፡
ልጇ በስደቷ ወቅት ያደረጋቸውን ተአምራትና ስለደረሰባት መከራም ስትናገር ‹‹…ሁሉን ብነግርህ ኖሮ ወረቀት ባልቻለውም ነበር›› ትላለች፡፡ (ድርሳነ ማርያም ገጽ ፪፻፰) በስደቷ ወቅት ከደረሱባት መከራዎች ጥቂቶቹን እንኳን ስንናገራቸው ስናስባቸው እንዴት አስጨናቂ እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ ‹‹ኵሉ እኁዝ ውስተ እዴሁ›› የተባለ ልጇን ይዛ ግን ተሰደደች፤ በስደትም ትበላው ዘንድ ምግብ፣ ትጠጣው ዘንድ ውኃ አጥታ ፍለጋ ልመና ወደ ሰዎች ቤት ሄደች፤ ወደ መንደር ገብታ ስመ እግዚአብሔር ጠርታ ስትለምን ሰይጣን እየተከታተለ የሰዎችን ልብ ያስጨክንባት ነበርና አንድ ስንኳ የሚዘክራት ሰው አጣች፡፡ በዚህም እያዘነች ስትመለስ ሰብአ ሰገል ለልጇ ያመጡለትን የወርቅ ጫማ በሽፍታ ተወስዶ ጠበቃት፡፡ ‹‹ሄጄም ላላገኝ የልጀንም ጫማ አስወሰደኩት›› ብላ አምርራ አለቀሰች፡፡

እመቤታችን ራስዋ ይህንን ስትተርከው እንዲህ ትላለች፤ ‹‹ውኃ ፈለግሁ የሰጠኝ ግን አልነበረም፡፡ የልጄን ጫማ ከማጥፋት በቀር የተጠቀምኩት የለም፡፡ ይህን ብዬም አለቀስሁ፡፡ የተወደደው ልጄም እንባዬን ተመልክቶ በጣቶቹ ጠረገልኝ፡፡ ትንሽ ጣቱንም ወደ መሬት አወረደ፤ እንደ ማር የሚጣፍጥ እንደ ወተት የነጣ ውኃ አፈለቀ፡፡ ይህንንም ውኃ ከዚያች ሀገር ሰዎች በቀር ለሚጠጣው ለሚያልፈው ለሚያገድመው ሁሉ ፈውስ፣ ጤና ይሁን! ብሎ ባረከው፡፡›› (ድርሳነ ማርያም)

‹‹ሰሚዖ ሕፃን ለእሙ ገዓራ፤ ባረከ ኰኩሐ ወአንቅዐ ማየ እምታሕተ እግራ፤ ወእምኔሃ ለጽምኣ ትስተይ አመራ፤ ሕፃን ልጇ ክርስቶስ የእናቱን ጭንቀት ሰምቶ ዓለቱን ባረከው፤ ከእግሯ ሥርም ውኃን አፈለቀ፤ ከዚያችም ለጥሟ ትጠጣ ዘንድ አመለከታት›› እንዳለ ደራሲ ከዐለት ላይ ውኃ አፍልቆ፣ በእሳት ዓምድ መርቶ፣ በደመና መሶብ መና አዘግኖ እስራኤልን የመራ የስደተኞች ተስፋ፣ የራብተኞች ምግብ ልጇ ለእናቱ አዘነላት፡፡ (ሰቆቃወ ድንግል) እንባዋንም በእጆቹ ጠረገላት፤ ተጠምታለችና ውኃ ፍለጋ ሄዳ አንድም ሰው ስላላዘነላት አዝናለችና አዘነላት፤ እንደ መዓር ጣፋጭ እንደ ወተት ነጭ ለሚጠጡት ሁሉ ፈውስና ጤና የሚሆን ውኃ ከቆመችበት ምድር ከእግሯ ሥር አፈለቀላት፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ያ ምንጭ ‹‹የማርያም ምንጭ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ እመቤታችንም በዚያ ውኃ የልጇን ልብስ አጥባ በደፋችበት ቦታ ቅብዓ ሜሮን የሚዘጋጅበት ዕፅ በቅሎበታል፡፡

በዚህ ታሪክ ውስጥ አንድ የሚያሳዝን ነገር ተከስቷል፡፡ ከእናቱ አግር የፈለቀው ለሕሙማን ፈውስ የሆነው ውኃ ለሀገሩ ሰዎች ግን እንደ እሬት መራራ ሆኖባቸዋል፡፡ ለነጋድያን ለፈላስያን ግን እንደ ማር የሚጣፍጥ ፈውሰ ሥጋ የሚያሰጥ አድርጎታል፡፡ ‹‹ከሀገሩ ሰዎች አንዳቸው እንኳን አይዳን›› ብሎ ረግሞታል፡፡ ያሳዝናል! መራራውን የሚያጠፍጠውን፣ ለተጠሙት ሁሉ የሕይወት ውኃ የሚሰጠውን፣ ለሕሙማን ፈውስ፣ ለስዱዳን ሞገስ የሆነውን ክርስቶስን እና እናቱን አልተቀበሉምና ትንሽም አልራሩላቸውምና ርግማን ሆነባቸው፡፡

ያጋጠማቸውን መከራ፣ የተደረገውን ተአምራት ሁሉ መዘርዘር እመቤታችን እንዳለችው ምን ወረቀት ሊበቃ ይችላል? ጦጣና ዝንጀሮ ስለሆኑት እነ ትእማን ዘመዶች ወይስ መሬት ተክፍታ ስለዋጠቻቸው ትእማንና ኮቲባ ታሪክ እንተርክ? ተራሮችና ኮረብቶች የሰገዱለትን ወይስ ግመሎቹ ሐውልት የሆኑበትን ታሪክ እንጻፍ? የግብጽን ጣዖታት ስለመሰባበሩ ወይስ ዕረፍት እስኪያጣ ስለፈወሳቸው ሕሙማን እንተርክ? በዚያች መንገድ ለማለፉ ምልክት ትሆን ዘንድ ተክሎ ስላጸደቃት የዮሴፍ የወይራ በትር ወይስ የተጠለሉበትን ጨለማ ቤት እንዴት በብርሃን እንደሞላው እንናገር? የቱ ተነሥቶ የቱ ይቀራል? እንዲያው አድንቆ ማለፍ እንጂ፡፡

ውድ አንባብያን! አንድ ግን ሳንተርክላችሁ የማናልፈው ታሪክ አለና እርሱን ብቻ በጥቂቱ እንተርከው፡፡ ታሪኩም እንዲህ ነው፤ እመቤታችንን ካስጨነቁ ገጠመኞች መካከል የሁለቱ ሽፍቶች ነገር ዋነኛው ነው፡፡ አንድ ግብጻዊና አንድ ዕብራዊ ሽፍቶች በጋራ ነፍስ እየገደሉ፣ ቋንጃ እየቆረጡ፣ ሀብት ንብረት እየዘረፉ ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህ ሽፍቶች እመቤታቸንን በስደቷ ገጥመዋታል፡፡ ስለ እነዚህ ሽፍቶች እንዲህ ትላለች፤ ‹‹…ግብጽ እንደገባን ከበጋው ፀሐይ እናርፍ ዘንድ ከከተማው ውጭ ከዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጥን፤ ይህም ግንቦት ፳፬ ቀን ነው፡፡ ሁለት ሽፍቶችም በመንገድ አለፉ፤ አንዱ ግብጻዊ አንዱ ዕብራዊ ነው፡፡ ዕብራዊው ግብጻዊውን “የዚህችን ሴት ልብስ፣ የልጇንም ልብስ ልወስደው እሻለሁ፤ የነገሥታቱን ልብስ ይመስላልና” አለው፡፡ ግብጻዊውም ከተፈጠርኩ ጀምሮ እንደዚህ ያለ ሕፃን አላየሁምና ተው” አለው፡፡ ውኃ ፍለጋ ሄጄ ስመለስ የልጄን ጫማ ወስደውት አገኘሁ፡፡ እነ ዮሴፍንም ቀስቅሼ የልጄን ጫማ ወስደውታል፤ የልጄን ጫማ ከማጥፋት በቀር የተጠቀምኩት ነገር የለም ብዬ አለቀስኩ›› ትላለች፡፡

ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ከተማ፥ ከተማውን እንሂድ ሲል እመቤታችን ግን የሰውን ክፋት ተረድታለችና ልጄን ይገሉብኛል፤ ጫካ ጫካውን እንሂድ ትላለች፡፡ የሆነውንም እንዲህ ስትል ትቀጥላለች፡፡ ‹‹ፀሐይ ሲገባ ወደ ተራራው ሄድን፤ ስንጓዝም ለመንጋት ትንሽ ቀረው፡፡ በሌላኛይቱ ሀገር ቀደም ሲል ያየናቸው ሁለቱ ሽፍታዎች እስከዚህች ቦታ ድረስ ተከተሉን፡፡ በዚያ ቦታ በተመለከቱን ጊዜ ዕርቃናቸውን ወደ እኛ እየሮጡ መጡ፡፡ በእጆቻቸውም የተመዘዙ ሰይፎች ነበሩ፡፡ ስንከተላችሁ ብዙ ጊዜ ደከምን፤ ነገር ግን ከዛሬ በቀር የምንይዛችሁን ቀን አላገኘንም፤ አሁን ግን በእጃችን ወድቃችኋልና እንበቀላችኋለን አሉን›› (ድርሳነ ማርያም)፡፡

ከዚህ በኋላ ዘለው የተወደደ ልጇን ከእቅፏ ወሰዱባት፡፡ ልብሶቹንም ገፈፉት፤ የእርሷንም መጎናጸፊያ ከላይዋ ላየ ገፈፏት፤ አረጋዊ ዮሴፍም እንደ በግ ሆነላቸው፤ ልብሱንም ከላዩ ላይ ቀደዱት፤ ሰሎሜም ይህንን በተመለከተች ጊዜ በድንጋጤ መጎናጸፊዋን ጣለች፡፡ በዚህ አላበቁም፤ ልብሶቻቸውን ከወሰዱ በኋላ እርስ በርስ ቆመው ሲነጋገሩ እንዳልሄዱ ባየች ጊዜ ጽኑ ፍርሃትን ፈራች፤ ልጄን ሊገድሉብኝ ነው እንጅ ሌባ ቀማኛ ከቀማ በኋላ አዩኝ አላዩኝ ብሎ ይሄዳል ብላ እጅግ አለቀሰች፡፡ እንዲህም አለች፤ ‹‹ተወዳጅ ልጄ ሆይ፥ ወዮልኝ! በዚህች ሰዓት የት እሄዳለሁ? ወደየትስ እሸሻለሁ? እንዳይገድልህ ርጉም ሄሮድስን በመፍራት ከኢየሩሳሌም ሸሸሁ፤ ከሀገሬ ብቀመጥ ኖሮ ይህንን ሁሉ ድካም ባላወቅሁም ነበር፡፡ የዐይኖቼ ብርሃን ሆይ፥ ከዚህ ሀገር ማንን አውቃለሁ? ያለሁት በምድረ በዳ ነው፤ ዛሬ ከእኔ ጋር ያለቅሱ ዘንድ የሚያውቁኝ የት አሉ? ተወዳጅ ልጄ ሆይ፥ ከአንተ ጋር በመሸሽ አንድ ቀን እንኳ ባልደከምሁ ነበር፤ በዚህ ቦታ አንተን ሲገድሉህ ከማያቸው ቀድመው ቢገድሉኝ በተሻለኝ ነበር፤ ሄሮድስ ልጆቻቸውን የገደለባቸውን ሴቶች ባያቸው ኖሮ ከእኔ ጋር ያለቅሱ ዘንድ በወደድሁ ነበር….፡፡›› ይህንና የመሳሰለውን በዙ ነገር እየተናገረች ምርር ብላ አለቀሰች፡፡

እነዚያ ወንበዴዎች ግን ይጨቃጨቁ የነበረው ግብጻዊው ለዕብራዊው “እባክህ ልብሳቸውን እንመልስላቸው” እያለው ስለነበር ነው፡፡ ‹‹እለምንሃለሁ፤ በፊታቸው ከሰው ሁሉ ይልቅ ታላቅ ብርሃንን እመለከታለሁና፤ ሕፃኑም የንጉሥ ልጅ ይመስላል፤ የሚመስለውም አላየሁምና›› አለው፡፡ አይሁዳዊውም “አልሰማህም? የነገሥታት ልብሶች ናቸውና›› አለው፡፡ ግብጻዊውም ማሳመን እንዳልቻለ ባየ ጊዜ ከቤተ ልሔም ጀምሮ የዘረፉትን ብዙ ሀብት እንደሚለቅለት ለመነው፤ በዚህም ተስማምቷል፤ ያ ግብጻዊ አዝኖላቸው ልብሳቸውን መልሶላቸው ጌታንም በትከሻው ተሸክሞ ሸኛቸው፡፡
ጌታም ለተወዳጅ እናቱ እንዲህ አላት፤ ‹‹እነዚህን ሁለት ወንበዴዎች ታያለሽን? በኢየሩሳሌም አይሁድ አንዱን በቀኜ አንዱን በግራዬ አድርገው ይሰቅሏቸዋል፡፡ ይህ በልቡናው ቸርነት ያለውም የቸር አባቴ ነው፤ እርሱ በመስቀል እያለሁ ያምንብኛል፤ አዳምና ዘሮቹን ቀድሞም መንግሥተ ሰማያት ይገባል›› አላት፡፡ እነዚህ ሽፍቶች ጥጦስና ዳክርስ ናቸው፡፡ (ማቴ፳፯፥፴፰) ፈያታዊ ዘየማንና ፈያታዊ ዘጸጋም ተብለው በኋላ ከክርስቶስ ጋር በግራና በቀኝ የተሰቀሉት እነዚህ ሽፍቶች ናቸው፡፡

እንደ እውነቱ ቢሆን ከግብጻዊው ይልቅ ዕብራዊው ሊያዝንላቸው በተገባ ነበር፡፡ ነገር ግን ጨከነባቸው፤ ግብጻዊው ግን ቸርነት አሳይቷልና ቸርነት ተደረገለት፡፡ በመንግሥተ ሰማያትም አዳምን በመቅደም የገነት ጠባቂዋ ሱራፊን አስደመመው፡፡ ከባለ ተስፋው አዳም ቀድሞ ገነት ገብቷልና፡፡ ተወዳጆች ሆይ! መቼም የስደቷን ነገር ተናግሮ መጨረስ፣ ተመራምሮ መድረስ የሚቻለን ሆኖ አይደለም፤ እንዲያው ለመዘከር ያህል እንጂ፡፡ ለመሆኑ የስደቷ ዓላማ ምን ይሆን? እንመለስበታለን፤ ቸር እንሰንብት!
ይቆየን!
የ2016 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተጠናቀቀ።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት ዕለታዊ መግለጫ ጥቅምት 17 ቀን 2016 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አስተዳደራዊ ጉዳይን የያዘ የመሪ እቅድ ተጨማሪ ግብዓት ተጨምሮበት ለግንቦት ርክበ ካህናት እንዲቀርብ መወሰኑን ገለጹ፡፡ በጸደቁ አጀንዳዎች ላይ ላለፈው አንድ ሳምንት ሲወያይ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መንፈስ ቅዱስን አጋዥ በማድረግ መግባባት በሰፈነበት ሁኔታ ጉባኤውን ማጠናቀቁን የገለጹት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በማጠናቀቂያው በሕግ በመሪ እቅድ ትግበራ እና በልዩ ልዩ ጉዳዮች ጥናት ላቀረቡ እና ማብራሪያ ለሰጡ ባለሙያዎች በብፁዕ ወቅዱስ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ምስጋና ማቅረባቸውን ገልጸዋል። በአጠቃላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችንአስመልክቶ ቅዱስነታቸው ሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም መግለጫ እንደሚሰጡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት ዕለታዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ የኢኦተቤክ ቴቪ
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል 

" ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ። "

[ ዳን.፱፥፳፩ ]

ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ" [ዘፍ.፵፰፥፲፮]


ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል

- ከ፯ [ 7 ] ቱ ሊቃናት አንዱ::
- በራማ አርባብ በሚባሉ ፲ [10] ነገደ መላእክት ላይ የተሾመ::
- በመጀመሪያዋ የፍጥረት ቀን መላእክትን ያጸና::
- ቅዱሳንን ሁሉ የሚረዳ::
- ሠለስቱ ደቂቅን : ዳንኤልን : ሶስናን ከሞት የታደገ ታላቅ መልዐክ ነው::

ከምንም በላይ ግን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዱሱን መልዐክ "መጋቤ - ሐዲስ" ብላ ታከብረዋለች:: ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጉዋሜ "አምላክ ወሰብእ - እግዚእ ወገብር" ነውና ለሥነ ፍጥረት ሁሉ የሚሆን ሐዲስ ዜናን ወደ እመቤታችን ድንግል ማርያም አምጥቷል::


የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ፥ ያድናቸውማል። [መዝ.፴፬፥፯]

የቴሌግራም ገፃችን - https://www.tg-me.com/betel_et
የፌስቡክ ገጻችን - https://www.facebook.com/profile.php?id=61552723809417
ኑ! በድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን ሕይዎት እንታደግ!
+++
በሀገራችን እያጋጠሙ ባሉት ማኅበራዊ ውሶች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወገኖች አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ የሚፈልጉ ሆነዋል። በተለይ ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተከሰተው ድርቅ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ፣ ጠለምት፣ በየዳና ጃና አሞራ፣ እንዲሁም በዋግኸምራ ዞን ሰሃላና አካባቢው የሚገኙ ወገኖቻችን ለጽኑ ማኅበራዊ ችግር ተጋልጠዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን በእነዚህ አካባቢዎች የነፍስ አድን ሥራዎችን ለማከናወን የተለመደ ድጋፋችሁን በማድረግ ሰብአዊና ማኅበራዊ ኃላፊነትዎ ይወጡ ሲል ጥሪውን ያቀርባል።
ድጋፍ ለማድረግም፡-
በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
2. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
3. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
4. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
5. በአዋሽ ባንክ - 01329817420400 መጠቀም የምትሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ
• 09 43 00 04 03
• 09 1 1 38 27 53
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

እንኩዋን ለታላቁ ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር እና ለቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር

በቤተ ክርስቲያን ያሉ አበው ሊቃውንት እንደሚሉት ከቅዱሳን በቁመቱ የአባ አርሳኒን ያክል ረዥም አልነበረም:: እርሱ እንደ ዝግባ ቀጥ ያለ ነበር:: በዚያው ልክ ደግሞ የቅዱስ ዮሐንስን (ዛሬ የምናከብረውን) ያህል አጭር አልነበረም:: በዚህ ምክንያት ይሔው ለዘለዓለም "ዮሐንስ ሐጺር - አጭሩ አባ ዮሐንስ" ሲባል ይኖራል::

ሊቃውንትም ቁመቱንና ቅድስናውን በንጽጽር ሲገልጡ:-
"ሰላም ሰላም ዕብሎ በሕቁ:
ለዮሐንስ ሐጺር ዘነዊኅ ሒሩተ ጽድቁ
" ይላሉ:: "ቁመቱ እጅግ ያጠረ: ጽድቁ ግን ከሰማይ የደረሰ ቅዱስ ዮሐንስን ሰላም ሰላም እንለዋለን" እንደ ማለት ነው::

ቅዱሱ የተወለደው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ ነው:: ወላጆቹ ምንም ከሥጋዊ ሃብት ድሆች ቢሆኑም ባለ መልካም ክርስትና ነበሩና በጐውን ሕይወት አስተምረውታል:: ወደ ምናኔ የገባው ገና በ18 ዓመቱ ሲሆን የታላቁ አባ ባይሞይ ደቀ መዝሙር ሆኖ ተጋድሎንና ትሕርምትን ተምሯል::

ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር በወቅቱ ከነበሩ ቅዱሳን ከቁመቱ ባሻገር በትሕትናው: በትእግስቱና በመታዘዙ ይታወቅ ነበር:: አባ ባይሞይ ይጠራውና ያለ ምንም ምክንያት ደብድቦ ያባርረው ነበር:: እርሱ ግን "ምን አጠፋሁ?" ብሎ እንኩዋ ሳይጠይቅ "አባቴ ሆይ! ማረኝ?" እያለ ከእግሩ ሥር ይወድቅ ነበር::

ለብዙ ጊዜ በተመሳሳይ ሲደበድበው: እርሱም እርሱው ተደብድቦ: እርሱው ይቅርታን ሲጠይቅ ኖረ:: አንድ ቀን ግን እንደ ልማዱ ሊገርፈው ሲሔድ 7ቱ ሊቃነ መላእክት ከበውት አይቶ ደንግጦ ተመልሷል::

አባ ባይሞይ ይሕንን ሁሉ የሚያደርገው ጠልቶት ወይ ክፉ ሆኖ አይደለም:: አንድ ሰው የሌላኛውን ግፍ መቀበል ካልቻለ ሰይጣንን ድል አይነሳም የሚል ትምሕርት ስለ ነበረ ነው እንጂ::

አንድ ቀን ቅዱስ ዮሐንስ ወደ መምሕሩ ቀርቦ "አባቴ ጅብ ካገኘሁ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀው:: (የአካባቢው ጅብ መናጢ ነበር) አባ ባይሞይ ግን "ይዘህልኝ አምጣው" አለው:: ትዕዛዝ ነውና ቅዱሱ ወደ በርሃ ወርዶ: ጅብ አልምዶ ይዞለት መጥቷል::

ሌላ ቀን ደግሞ አባ ባይሞይ ቅዱስ ዮሐንስን ጠራውና ተፈልጦ የወደቀ ደረቅ እንጨት ሠጠው:: "ምን ላድርገው አባ?" አለው:: "ትከለውና እንዲያፈራ አድርገው:: ከዚያ አምጥተህ አብላኝ" ሲል መለሰለት:: ይህ ነገር ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ መሆኑን እያወቀ ቅዱስ ዮሐንስ "እሺ" ብሎ ወስዶ ተከለው::

ከዚያም ለ2 ዓመታት ሳይታክት ውሃ አጠጣው:: ውሃውን የሚያመጣበት ቦታ ደግሞ 10 ኪሎ ሜትር ያህል ከገዳሙ ይርቅ ነበር:: ቅዱሱ ላቡን እያፈሰሰ አሁንም ማጠጣቱን ቀጠለ::

በ3ኛው ዓመት ግን ለምልሞ አበበ: ደግሞም አፈራ:: ካፈራው በኩረ ሎሚም ወስዶ ለመምሕሩ "አባቴ! እንካ ብላ" ብሎ ሰጠው:: አባ ባይሞይ ግን ማመን አልቻለም:: እጅግ አደነቀ: አለቀሰም::

ወዲያው ያን ፍሬ ታቅፎ ወስዶ ለገዳሙ መነኮሳት አላቸው- "ንሱ ብሉ: በረከትንም አግኙ:: ይህ የዛፍ ሳይሆን የመታዘዝ ፍሬ ነው:: ቅዱስ ዮሐንስ አባ ባይሞይ ቢታመም ለ12 ዓመት አስታሞታል::

መምሕሩ ከማረፉ በፊትም መነኮሳቱን ሰብስቦ የቅዱስ ዮሐንስን እጅ አስጨበጣቸው:: "ይህ የያዛችሁት እጅ የሰው ሳይሆን የመልአክ እጅ ነው" ብሏቸው ዐርፏል:: ቅዱስ ዮሐንስም ከዓመታት ቆይታ በሁዋላ የገዳሙ አበ ምኔት ሆኖ አገልግሏል:: ብዙ ነፍሳትንም ለቅድስና ማርኩዋል::

መላእክት ንጽሕናው ደስ ስለሚያሰኛቸው አብረውት ይውሉ ነበር:: ሲተኛም በተራ በተራ ክንፋቸውን ያለብሱት ነበር:: ምጽዋትን በጣም ስለሚወድ ሰፌድ እየሰፋ ይሸጥና ገንዘቡን ለነዳያን ያን ያካፍል ነበር::

አንድ ቀን እንደ ልማዱ ወደ ገበያ ወጥቶ ሳለ ተደሞ (ተመስጦ) መጣበት:: ሰማያት ተከፍተው: ቅዱሳን ሊቃነ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል በግርማ በጌታ ፊት ቆመው ተመለከተ::

"እጹብ: እጹብ" እያለ ሲያደንቅ አንድ ገዢ መጥቶ "ባለ እንቅብ ዋጋው ስንት ነው?" ቢለው "እኁየ ሚካኤልኑ የዓቢ ወሚመ ገብርኤል - ከሚካኤልና ከገብርኤል ማን ይበልጣል?" ብሎታል:: ገዢውም ደንግጦ "እብድ መነኩሴ" ብሎት ሔዷል::

ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ወደ ባቢሎን (የአሁኗ ኢራቅ) ሒዶ ከተመለሰ በሁዋላ በበርበሮች ምክንያት ከአስቄጥስ ወደ ቁልዝም ተሰዷል:: በዚያም በአባ እንጦንስ በዓት ውስጥ ዐርፏል:: ለ400 ዓመታት በዚያው ቆይቷል::

825 ዓ/ም ግን በአባ ዮሐንስ ፓትርያርክ ዘመን ክቡር ሥጋው ወደ ገዳመ አስቄጥስ ተመልሷል:: ቅዱሱ ያረፈው ጥቅምት 20 ቀን ሲሆን ዛሬ ሥጋው የፈለሠበት ነው:: በዚህ ዕለትም የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና የታላቁ ቅዱስ መቃርስ ሥጋ በተገናኙ ጊዜ ግሩም ተአምር ተደርጉዋል:: ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ሲገባም ታላቅ የብርሃን ጐርፍ ሲፈስ ታይቷል::

ሰማያዊ መዓዛም አካባቢውን ሞልቶታል:: ከዻዻሳቱ አንዱ እባረካለሁ ብሎ የቅዱስ ዮሐንስን ሥጋ ቢገልጠው አካባቢው ተናወጠ:: መባርቅትም (መብረቆች) ተብለጨለጩ:: ደንግጠው ቶሎ ቢያለብሱት ጸጥታ ሆኗል:: በዚህ ሁሉ ደስ ያላቸው አበው ቅዱሱን በዝማሬ ሲያወድሱት ውለዋል::

ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ

- ከነቢያተ እሥራኤል አንዱ
- ከእርሻ ሥራ ቅዱስ ኤልያስን የተከተለ
- መናኔ ጥሪት የተባለ
- በድንግልና ሕይወት የኖረ
- የታላቁ ነቢይ ኤልያስ መንፈስ እጥፍ የሆነለት
- እጅግ ብዙ ተአምራትን ያደረገ
- አንዴ በሕይወቱ: አንዴ በአጽሙ ሙታንን - - ያስነሳ ታላቅ ነቢይና አባት ነው::

ቅዱስ ኤልሳዕ በጣም ረዥም: ራሱ ገባ ያለ (ራሰ በራ): ቀጠን ያለ: ፊቱ ቅጭም ያለ (የማይስቅ) ሽማግሌ ነበር::

አምላከ ቅዱሳን የሐጺር ቅዱስ ዮሐንስን መታዘዙን: ትሕትናውን: ትእግስቱንና ቅንነቱን ያድለን:: በበረከቱም ይባርከን::

#ጥቅምት_20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ
የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር
2.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ
3.አባ ባይሞይ

ወርኀዊ በዓላት
1..ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
2.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
3.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
4.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
5.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
6.ቅዱስ ወክቡር ማር ቴዎድሮስ ሰማዕት

" እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ 'የማንጠቅም ባሪያዎች ነን: ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል' በሉ:: " (ሉቃ. 17:10)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን":: የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: 

የቴሌግራም ገፃችን - https://www.tg-me.com/betel_et
የፌስቡክ ገጻችን - https://www.facebook.com/profile.php?id=61552723809417
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

#ጥቅምት_21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

እግዝእትነ ማርያም

እመቤታችን ድንግል ማርያም የወልደ እግዚአብሔር
እናቱ ናትና ሁሉን ትችላለች:: እርሱን ከሃሊ (ሁሉን ቻይ)
ካልን እርሷን "ከሃሊት" ልንላት ይገባል:: ልክ ልጇ ሁሉን
ማድረግ ሲችል በትእግስት ዝም እንደሚለው እመ
ብርሃንም ስንት ነገር እየተደረገ: በእርሷ ላይም አንዳንዶቹ
ስንት ነገርን ሲናገሩ እንደማትሰማ ዝም ትላለች::

እኛ ኃጥአን ንስሃ እስክንገባ ድረስም "ልጄ! የዛሬን
ታገሣቸው?" እያለች ትለምንልናለች:: ቸሩ ልጇም ሊምረን
እንጂ ሊያጠፋን አይሻምና "እሺ እናቴ!" እያለ ይኼው
በዚህ ሁሉ ክፋታችን እስከ ዛሬ ድረስ አላጠፋንም::
- ቸር ነው
- መሐሪ ነው
- ይቅር ባይ ነው
- ታጋሽ ነው
- ርሕሩሕ ነው
- ቂምም የለውም::

በንስሃ ካልተመለስን ግን አንድ ቀን
መፍረዱ አይቀርምና ወገኖቼ ንስሃ እንግባ: ወደ እርሱም እንቅረብ::

ይህቺ ዕለት ለእመቤታችን እሥረኞችን የምትፈታባት
ናት:: የሰው ልጅ በ3 ወገን እሥረኛ ሊሆን ይችላል::

በሥጋዊው :- አጥፍቶም ሆነ ሳያጠፋ ሊታሠር ይችላል::

በመንፈሳዊው - ግን ሰው በኃጢአት ማሠሪያ የሚታሠረው
በጥፋቱ ብቻ ነው::

ሌላኛው ማሠሪያ ደግሞ ማዕሠረ ደዌ (በደዌ ዳኝነት)
መታሠር ነው:: መታመም የኃጢአተኛነት መገለጫ
አይደለም:: ምክንያቱም ከቅዱሳን ወገን ከ80 %
(ፐርሰንቱ) በላይ ድውያን ነበሩና::

ታዲያ በዚህች ዕለት እመብርሃን 3ቱንም ማሠሪያዎች
እንደምትፈታ እናምናለን:: በእሥር ቤትም: በኃጢአትም
ሆነ በደዌ ማሠሪያ የታሠርን ሁላችን በዚሁ ዕለት
እንድትፈታን የአምላክ እናትን እንለምናት::

በ3ቱም ማሠሪያዎች የታሠሩ ወገኖቻችንንም እያሰብን
"ይባእ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሐን - የእሥረኞች ጩኸት
ወደ አንተ ይድረስ" እያልን (መዝ. 78:11) ልንጸልይ ይገባል::

እመ ብርሃንንም እንደ ሊቃውንቱ :-
"እማእሠረ ጌጋይ ፍትሕኒ ወላዲተ ክርስቶስ አምላክ:
እምነ ሙቃሔ ጽኑዕ ወእማዕሠር ድሩክ:
ከመ ፈታሕኪዮ ዮም ለማትያስ ላዕክ::" እንበላት::

ቅዱስ አልዓዛር ሐዋርያ

ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ
ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው
ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት
ማርያና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት
ቆጥሯቸዋል::

በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደነበር ተገልጧል::
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ
አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ
የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደነበር ሲነግረን ነው እንጂ::

ቅዱስ መጽሐፍ እንደነገረን ጌታችን በነአልዓዛር ቤት
በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: በመጨረሻዋ ምሴተ
ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ
ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው::

ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ
ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል::
(ዮሐ.11)

ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ4 ቀናት በኋላ ሊያስነሳው
ይመጣል::

ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው
ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ:: ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር
ተቀበለችው::

'አዳም ወዴት ነህ' ያለ (ዘፍ. 3) የአዳም ፈጣሪ
'አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት' አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ
ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ::

ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር አልዓዛር" ብሎ
አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ
ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት::
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ
እንዲህ ታስተምራለች:: (ዮሐ. 11:1-ፍጻሜው)

ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በኋላ በበዓለ ሃምሳ
መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ (ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት
ነውና): ለ40 ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ: በ74 ዓ/ም
አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል::

ፍልሠት

ይህቺ ዕለት ለቅዱሱ ሐዋርያ በዓለ ፍልሠቱ ስትሆን ይህ የተደረገውም በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ቅዱሱ
ያረፈው ቆዽሮስ ውስጥ ነው:: ግን ባልታወቀ ጊዜና
ምክንያት ወደ ኢየሩሳሌም ሒዷል::

አንድ ቀንም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ኢየሩሳሌም
ውስጥ ሲቆፍሩ አንድ አንድ ሳጥን አገኙ:: በላዩ ላይ
ደግሞ "ይህ የጌታ ወዳጅ የአልዓዛር ሥጋ ነው" የሚል
ጽሑፍ አግኝተው ደስ ተሰኝተዋል:: በታላቅ ዝማሬና
ፍስሐም ከኢየሩሳሌም ወደ ቁስጥንጥንያ አፍልሠውታል::
+የጌታችን ቸርነቱ: የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን::

አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም

እኒህ ጻድቅ ሰው ግብጻዊ ሲሆኑ በሰፊው የሚታወቁት
በኢትዮዽያና በኢየሩሳሌም ነበር:: ገና በወጣትነት
የጀመሩትን የተጋድሎ ሕይወት ገፍተው በበርሃ ሲኖሩ
የወቅቱ የግብጽ ሲኖዶስ ከበርሃ ጠርቶ የኢየሩሳሌም
ዻዻስ እንዳደረጋቸው ይነገራል::

በቅድስት ሃገርም በንጽሕናና በመንኖ ጥሪት ወንጌልን
እየሰበኩ ኑረዋል:: አባ ዮሐንስ የነበሩበት ዘመን 14ኛው
መቶ ክ/ዘመን ሲሆን የወቅቱ የኢትዮዽያ ንጉሥ ደጉ አፄ
ዳዊት ነበሩ::

ንጉሡ የግብጽ ክርስቲያኖችን ደም ለመበቀል (በወቅቱ
ከሊፋዎች ያሰቃዩዋቸው ነበር) እስከ ላይኛው ግብጽ
ወርደዋል::
በሃገር ውስጥ ያሉ ተንባላት አባሪዎቻቸውንም ቀጥተዋል::
በዚህ የተደናገጠው የግብጹ ሡልጣን 'አስታርቁኝ' ብሎ
ስለ ለመነ ለእርቅ የተመረጡ አባ ዮሐንስና አባ ሳዊሮስ
ዘምሥር ናቸው::

እነዚህ አባቶች በ1390ዎቹ አካባቢ ወደ ኢትዮዽያ
ከመጡ በኋላ አልተመለሱም:: ምክንያቱም ደጉ አፄ
ዳዊት እጅግ ስለ ወደዷቸው 'አትሔዱም' ብለው
ስላስቀሯቸው ነው:: እንዲያውም ለግማደ መስቀሉ
መምጣት ትልቁን አስተዋጽኦ ያደረጉት አባ ዮሐንስ
ሳይሆኑ አይቀሩም:: ዛሬ የጻድቁ ዕረፍታቸው ነው::

አምላከ ቅዱሳን ስለ ድንግል እናቱ ብሎ ከኃጢአት ሁሉ
ማሠሪያ ይፍታን:: የወዳጆቹን በረከትም አያርቅብን::

ጥቅምት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.እግዝእትነ ማርያም
2.ቅዱስ አልዓዛር ሐዋርያ
3.አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
4.ቅዱስ ኢዩኤል ነቢይ
5.ቅዱስ ማትያስ ረድእ

በ 21 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ
2.አበው ጎርጎርዮሳት
3.አቡነ ምዕመነ ድንግል
4.አቡነ አምደ ሥላሴ
5.አባ አሮን ሶርያዊ
6.አባ መርትያኖስ ጻድቅ

" ጌታ ኢየሱስም 'ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር
እንድታዪ አልነገርሁሽምን?' አላት... ይሕንም ብሎ በታላቅ
ድምጽ 'አልዓዛር ሆይ ወደ ውጭ ና' ብሎ ጮኸ::
የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ::
ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም
'ፍቱትና ይሂድ ተውት' አላቸው::" (ዮሐ. 11:40-44)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የቴሌግራም ገፃችን - https://www.tg-me.com/betel_et
የፌስቡክ ገጻችን - https://www.facebook.com/profile.php?id=61552723809417
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

#ጥቅምት_22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ

ቅዱስ ሉቃስ :-
- ሐዋርያ ነው
- ወንጌላዊ ነው
- ሰማዕት ነው
- ዓቃቤ ሥራይ (ዶክተር) ነው
- የጥበብ ሰው (ሰዓሊ) ነው

ዘጋቢ (የሐዋርያትን ዜና ሕይወት የጻፈ) ነው:: ይሕስ እንደምን ነው ቢሉ:-

በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን መነሻ አካባቢ: በተወደደች የጌታ ዓመት ከእሥራኤላውያን ወገኖቹ ቅዱስ ሉቃስ ተወልዷል:: ያደገውም መቄዶንያ አካባቢ ነው:: ጌታችን ተጠምቆ ማስተማር ሲጀምር ከተከተሉት የ5 ገበያ ሕዝብ መካከል 120ውን ለቤተሰብነት መምረጡ ይታወቃል::

ታዲያ እንዲጠቅም አውቆ ቅዱስ ሉቃስን ከ72ቱ አርድእት ደምሮታል:: ቅዱስ ሉቃስ ጌታን ከተከተለ በኋላ ለ3 ዓመት ከ3 ወር: ከዋለበት እየዋለ: ካደረበትም እያደረ የቃሉን ትምሕርት: የእጆቹን ተአምራት በጥሞና ይከታተል ነበር::

ጌታችን ለዓለም ድኅነት ተሰቅሎ: ሙቶ: ከተነሳ በኋላ ስለዚህ ቅዱስ የሚናገር አንድ የወንጌል ክፍል እናገኛለን:: በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ላይ ከምናያቸው የኤማሁስ መንገደኞች አንዱ ይህ ቅዱስ እንደ ሆነ አባቶች አስተምረውናል::

በእርግጥ 'ቀለዮዻ' የሚለው ስም በዘመኑ የብዙዎች መጠሪያ ቢሆንም እርሱም ጌታን ከመከተሉ በፊት በዚህ ስም ይጠራ እንደ ነበር ይታመናል:: በወቅቱ ታዲያ 2ቱ ደቀ መዛሙርት (ሉቃስና ኒቆዲሞስ) ወደ ኤማሁስ ሲሔዱ ጌታ መንገድ ላይ ተገልጦ እያጫወታቸው አብሮ ተጉዟል::

እነርሱም ማንነቱን አላወቁምና ስለ ራሱ ለራሱ እየሰበኩለት ተጉዘዋል:: ከሐዘናቸው ብዛት ማስተዋል ተስኗቸው: ቀቢጸ ተስፋም ወሯቸው ነበርና መድኃኒታችን ክርስቶስ የነቢያትን ትንቢት ተረጐመላቸው::

በዚህ ጊዜም ከነገሩ ማማር: ከምሥጢሩ መሥመር ጋር እየገረማቸው ልቦናቸው ይቃጠል (ይቀልጥባቸው) ነበር:: "አኮኑ ይነድደነ ልበነ" እንዲል:: ወደ ኤማሁስ ሲደርሱ ግን ደጐች ናቸውና "በቤት ካላደርክ: ራት ካልበላህ" ብለው ግድ አሉት::

በማዕድ ሰዓት ግን ቡራኬውን ሰጥቷቸው: ቸር አምላክነቱን ገልጦላቸው ተሰወራቸው:: እነርሱም በሐሴት ከኤማሁት ተመልሰው እየሮጡ ኢየሩሳሌም ደርሰው ትንሳኤውን ሰበኩ::

የመንገዱ ርዝመትም አልታወቃቸውም ነበር:: ከዚህ በኋላ ቅዱስ ሉቃስ እንደ ሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን ተምሮ: መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል::

ቅዱሱ ዶክተር

በትውፊት ትምሕርት እንደ ተማርነው ቅዱስ ሉቃስ ጌታን ከመከተሉ በፊት ሥራው ሐኪምነት (ዶክተር) ነበር:: በዚህም አበው "አቃቤ ሥራይ / ባለ መድኃኒት" ይሉታል:: በተሰጠው ሙያም ብዙዎችን አገልግሏል::

የጌታ ደቀ መዝሙር ከሆነ በኋላ ደግሞ "አቃቤ ሥራይ ዘነፍስ-የነፍስ ሐኪም" ተብሏል:: እንዲያውም አባቶቻችን ሐዋርያትን ያክማቸው ነበር ይባላል:: ምክንያቱም ቅዱሳን ሐዋርያት አብዛኞቹ በሽተኞች ነበርና ነው:: ከደግነታቸው የተነሳም እልፍ አእላፍ ድውያንን በተአምራት ሲፈውሱ እነርሱ ግን በስቃይ ይኖሩ ነበር::

ሕመማቸው ሲጠናባቸው ግን ቅዱሱ ዶክተር ሉቃስ ይራዳቸው ነበር:: ይሕንንም ቅዱስ ዻውሎስ በቆላስይስ መልእክቱ ላይ "የተወደደው ባለ መድኃኒቱ ሉቃስ: ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላቹሃል" ሲል ገልጾታል:: (ቆላ. 4:14)

ዘጋቢው ሐዋርያ

ቅዱስ ሉቃስ እንደ ዛሬው ነገሮች ምቹ ባልነበሩበት ዘመን እጅግ አድካሚ የሆነ ጉዞ አድርጐ የሐዋርያትን ዜና ሕይወት ዘግቦልናል:: ልክ ወንጌሉን ለታኦፊላ (ቴዎፍሎስ) ደቀ መዝሙሩ እንደ ጻፈለት ግብረ ሐዋርያትንም ለእርሱ በትረካ መልክ አቅርቦለታል::

ሲጽፍለትም "ሰማሁ" እያለ ሳይሆን: አብሮ እያለ ያየውንና የተሳተፈበትን ነው:: አተራረኩም በአንደኛና በ3ኛ መደብ አድርጐ እያቀያየረ ነው:: ማለትም አንዳንዴ "እኛ" እያለ ሌላ ጊዜ ደግሞ "እነርሱ" እያለ ነበር የሚተርክለት::

መጽሐፉም 28 ምዕራፎች ሲኖሩት በጌታ ዕርገት ጀምሮ በኢየሩሳሌምና በአሕዛብ የነበረውን ስብከተ ወንጌል ገልጦ: የቅዱስ ዻውሎስን ጉዞዎች በሰፊው ዳስሶ ይጠናቀቃል::

ወንጌላዊው ሐዋርያ

ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን እንዲጽፉ ከተመረጡ (ከተፈቀደላቸው) ሐዋርያት አንዱ ነው:: በቤተ ክርስቲያንም "ዘላሕም" እየተባለ ይጠራል:: ለዚህም ምክንያቱ:-

1.ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በበረት: በላምና በአህያ መካከል መወለዱን በመጻፉ
2.ጌታችንን "መግዝአ ላሕም-የሚታረድ ሜልገች (ላም)" ብሎ በመግለጹ እና
3.ከ4ቱ እንስሳ (ኪሩቤል) አንዱ (ገጸ ላሕም) ይራዳው: ይጠብቀውም ስለ ነበር ነው::

ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጻፈው ጌታ ባረገ በ22ኛው ዓመት ሲሆን ይኼውም በ56 ዓ/ም አካባቢ ማለት ነው:: ሲጽፍም ብቻውን አልነበረም:: ልክ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌሉን የጻፈው ከሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ጋር እንደ ሆነው ሁሉ: ቅዱስ ሉቃስም የጻፈው ከብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ጋር ነው:: ምክንያቱም ለረዥም ዓመታት አብረው ለስብከተ ወንጌል ተጉዘዋልና::

ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን ሲጽፍ በነ ዘካርያስ ቤተሰብ ጀምሮ: ብሥራተ ገብርኤልን: ክብረ ድንግል ማርያምን: የጌታን ልደት: እድገት: መጠመቅ: ማስተማር: መሰቀል: መሞት: መነሳትና ማረግ በቅደም ተከተል ይተርክልናል::

ጥበበኛው (ሰዓሊው) ሐዋርያ

ቅዱስ ሉቃስን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች ሌላኛው ደግሞ ጐበዝ ሰዓሊ የነበረ መሆኑ ነው:: በሐዲስ ኪዳንም የመጀመሪያውን የእመቤታችንን ስዕል (ምስለ ፍቁር ወልዳን) የሳለው እሱ ነው::

አንድ ቀን የአምላክ እናት ባለችበት ከጌታ አስፈቅዶ የሳላት ስዕለ አድኅኖ ሥጋን የለበሰች: ከፊቷ ወዝ የሚወጣ: የምታለቅስ: ስትወጋ የምትደማና ድውያንን የምትፈውስ ሆና ተገኝታለች:: ይህች ስዕል ዛሬ ሃገራችን ኢትዮዽያ ውስጥ አለች ይባላል።

ሰማዕቱ ሐዋርያ

ቅዱስ ሉቃስ እንዲህ ባለ ሕይወት ሲመላለስ በትጋት (ያለ ዕረፍት) ወንጌልን እየሰበከ ነበር:: በ66 እና በ67 ዓ/ም ብርሃናተ ዓለም ዼጥሮስ ወዻውሎስ በኔሮን ቄሣር እጅ ሲገደሉ የሮም ግዛት ክርስቲያኖች ኃላፊነት በእርሱ ላይ ነበረ::

ከወንጌሉና ግብረ ሐዋርያቱ ባለፈ በመልእክታት: አንድም እየዞረ ክርስቲያኖችን አጸና: አሕዛብንም አሳመነ:: ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ዝናውን የሰማው ኔሮን ሊገድለው ፈለገ:: በዚህ ጊዜ ቅዱስ ሉቃስ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ሲላስ የሚባለውን ሽማግሌ መርጦ መጽሐፎቹን ሁሉ አስረከበው::

በድፍረትም ወደ ኔሮን ቄሣር ቀርቦ ተናገረው:: ንጉሡም "ክርስቶስን አምልኩ የምትል ቀኝ እጅህ መቆረጥ አለባት" ብሎ እጁን ከትክሻው በሰይፍ ለይቶ መሬት ላይ ጣለው:: ሁሉ ሰው ሲደነግጥ ቅዱሱ ተጐንብሶ የወደቀች እጁን አነሳትና እንደ ነበረችው አደረጋት::

በዚያ የነበሩ አሕዛብም "ግሩም" አሉ:: መልሶ ግን "አሁን እጄ ሥራዋን ስለ ጨረሰች አልፈልጋትም" ብሎ እንደ ገና ለይቶ ጣላት::

"ከመ ያርኢ ኃይለ ቅድመ ኔሮን ወተዓይኑ:
አስተላጸቃ ወሌለያ ለምትርት የማኑ:
እስመ ላዕሌሁ ተሰውጠ ለክርስቶስ ስልጣኑ::" እንዲል::


የቴሌግራም ገፃችን - https://www.tg-me.com/betel_et
የፌስቡክ ገጻችን - https://www.facebook.com/profile.php?id=61552723809417
2024/10/01 04:59:08
Back to Top
HTML Embed Code: