‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሺ፥ ተመለሺ››
(መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን ፯፥፩)
ክፍል ሁለት
ጽጌ ማለት አበባ ማለት ነው፡፡ አበባ የተባለችም ድንግል ማርያም ናት፡፡ የነገረ ማርያም ሊቃውንት እመቤታችን በአበባ፣ ልጇን በፍሬ፣ እርሷን በዕፅ፣ ልጇን በአበባ እየመሰሉ ማስተማር ልማዳቸው ነው፡፡ ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን የዜማ አባት ቅዱስ ያሬድም ‹‹በማዕከለ አስዋክ ዘጸገየት ጽጌ ሃይማኖት ዘበአማን፤ በእሾህ መካከል ያበበች በእውነት የሃይማኖት አበባ ናት›› በማለት ይገልጻታል፡፡ (ነገረ ማርያም) እሾህ በተባለ ጥንተ አብሶ አዳማዊና ሔዋናዊ ኃጢአት መካከል ያበበች የፍሬ ሕይወት ክርስቶስ መገኛ አማናዊት የሃይማኖት አበባ እመቤታችን በዚህ በአበባው ወቅት (በጽጌ ወራት) መራራው የጣፈጠበት፥ ፍሬ ሕይወት ልጇን እንዳይገሉባት መራራውን የስደት ሕይወት የተጋፈጠችበት መታሰቢያ ወቅት ነው፡፡
ምክንያተ ስደት፡- ጌታችን በተወለደ ጊዜ ቤተ ልሔም በእሳት ተቀጽራ አጋንንት ሊቀርቧት፣ ሊወጡባት ሊወርዱባት አልቻሉም፡፡ ለአለቃቸው ነግረውት እርሱም እንደ ጌታ እሆናለሁ ብሎ በኪሩቤል አምሳል አራት ጸወርተ መንበር አዘጋጅቶ በእነርሱ ላይ ሆኖ ቢወርድ መላእክት በሐጸ እሳት እየነደፉ አላስቀርብ አሉት፡፡ በዚህም ክርስቶስ እንደ ተወለደ አስቦ ለሄሮድስ “የእኔን ሥልጣን የአንተን መንግሥት የሚነጥቅ ንጉሥ ተወልዷልና ልብስ እቀዳለሁ/እሰጣለሁ፤ ቀለብ እሰፍራለሁ ብለህ ዓመት፣ ዓመት ከመንፈቅ፣ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ሕፃናት ሰብሰቡልኝ ብለህ ፍጃቸው፤ ከእነዚያ መካከል አንዱ ይሆናል” ብሎ ላከበት።

👍10
በዚህ ጊዜ መልአኩ ዮሴፍን ‹‹ንሣእ ሕፃነ ወእሞ ወጕየይ ውስተ ብሔረ ግብፅ›› ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ” ብሎት ወጥተው ሄደዋል፡፡ (ማቴ.፪፡፲፫) ሄሮድስም ዐዋጅ አስነግሮ ያላቸው ልጆቻቸውን፣ የሌላቸው ልጅ ተውሰው ልብስ ቀለብ ሊቀበሉ የተሰበሰቡ አንድ መቶ አርባ አራት ሺህ ሕፃናት አስፈጅቷል፡፡ (ማቴ.፪፡፲፮) እነዚህም ሕፃናት በዘመነ ሐዲስ በኩራት ሆነው ደማቸውን በማፍሰስ ሰማዕት የሆኑ ናቸው፡፡ (ራእየ ዮሐንስ የዓለም መጨረሻ እና ትርጓሜ ሠለስቱ ሐዲሳት) ከዚህ ሁሉ በኋላ ግን ወደ ግብፅ መሸሻቸውን ቢነግሩት “አራት ቤት ጭፍራ ሸልሞ ይዛችሁ ያመጣችሁልኝ እንደሆነ ሙሉ ሽልማት እሸልማችኋለሁ” ብሎ ልኳቸዋል፡፡ እነ እመቤታችንም ከጊጋር መስፍነ ሶርያ ቤት ሰንብተው ስደታቸውን ቀጥለዋል፡፡
የዮሴፍ ልጅ ዮሳ ታሞ ወደ ኋላ ቀርቶ ነበርና ጭፍራ እንደተከተላቸው የጊጋር ብላቴኖች ሲነጋገሩ ሰምቶ ወጥቶ እየሮጠ ሲሄድ ሰይጣን መንገድ ላይ ጠበቀና ‹‹ምንት ያረውጸከ ከመዝ›› ምን ያስሮጥሀል? አለው፡፡ ሄሮድስ “ዘመዶቸን ያዙ ብሎ ጭፍራ ሰደደ ቢሉኝ ይህን ልነግራቸው ብዩ ነው” አለው፡፡ ያዘነ መስሎ “እነርሱማ ቀድመውህ ሄደዋል እስከ አሁን ገድለዋቸው ይሆናልና አትድከም ተመለስ” አለው፡፡ከሞቱም እቀብራቸዋለሁ ካሉም እነግራቸዋለሁ ብሎ ትቶት ሮጠ፡፡ (መዝገበ ታሪክ ቁጥር አንድ)
እመቤታችንና ዮሴፍ ደክሟቸው ዐረፍ ብለው ሰሎሜ ጌታን ስታጥበው አግኝቷቸው “እናንተ ሄሮድስ ይዛችሁ አምጡልኝ ብሎ ጭፍራ ልኮ ከዚህ ተቀምጣችኋል?” አላቸው፡፡ እመቤታችን ደንግጣ ጌታን ከሰሎሜ ተቀብላ እንባዋ በፊቱ ላይ እስኪወርድ ድረስ አለቀሰች፡፡ ሊቁ አባ ሕርያቆስ ‹‹አዘክሪ ድንግል አንብዐ መሪረ ዘውኅዘ እምአዕይንትኪ ወወረደ ዲበ ገጸ ፍቁር ወልድኪ›› የሚለው ይህን ነው፡፡
ጌታም ዮሳን “አመጣጥህ መልካም ዋጋ የሚያሰጥ ነበር፤ ነገረ ግን እናቴን ስላስደነገጥካት በዳግም ምጽአቴ አስነሥቼ ዋጋህን እስክከፍልህ ድረስ ይህን ድንጋይ ተንተርሰህ ተኛ” ብሎት ከዚያው ድንጋይ ተንተርሶ ድንጋይ መስሎ ቀርቷል፡፡
ከዚህ በኋላ ተነሥተው ሲሄዱ የሄሮድስ ጭፍሮች ገስግሰው ደረሱባቸው፡፡ አንዲት የሾላ ዛፍ ተከፍታ ከነጓዛቸው ከእነ አህዮቻቸው ሰውራቸዋለች፡፡ እነዚያም አህዮች ከውስጥ ሆነው ሲያናፉ ድምፃቸውን እየሰሙ ነገር ግን ሊያገኟቸው ስላልቻሉ የሄሮድስ ጭፍሮች ተመልሰዋል፡ ፡ከዚያ ወጥተው መንገዳቸውን ሲጓዙ በደረሱባት ሀገር በአደባባዮቿ ሲሄዱም ግመሎች መጡ፡፡ በመንገድም አስቸገሯቸው፤ ጌታም አያቸውና ቁሙ አላቸው፡፡ አምስቱም እስከ አሁን ድንጋይ ሆነው አሉ፡፡ (ድርሳነ ማርያም)
እመቤታችንና ልጇ መንገዳቸውን በእግዚአብሔር መልአክ እየተመሩ፣ የሲናን በረሃ አቋርጠው ወደ ግብፅ ሀገር ሄዱ። በዚያን ሰዓት ውርጩ፣ ብርዱ፣ ረኃቡ፣ እንግልቱ በዝቶባቸው ነበር፤ ጉዞውም አስጨናቂ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር የደረሰባት እንግልት፣ ሥቃይ፣ ረኃብ፣ ጥምን ሁሉ በሰው አንደበት የማይገለጽ እጅግ መራራ እንደ ነበር ቅዱሳት መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡
አባታችን ቅዱስ አባ ሕርያቆስ ‹‹አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምአ ምንዳቤ ወኀዘነ ወኩሎ አጸባ ዘበጽሃኪ ምስሌሁ አንዘ ትጎይዪ ምስሌሁ እምሀገር ለሀገር በመዋዕለ ሄሮድስ ርጉም፤ ድንግል ሆይ፥ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከእርሱ ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስትሸሺ ረኃቡንና ጥሙን ችግሩንና ኀዘኑን ከእርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ›› በማለት ገልጾታል፡፡ (ቅዳሴ ማርያም)
ስደት መከራንና ሥቃይን መቀበል ነው፡፡ ነቢያት፣ በኋላም ሐዋርያት ቅዱሳን ተሰደዋል፤ ‹‹እውነተኞች ምንጊዜም ስደት አለባቸውና›› (፪ኛጢሞ.፫፥፲፪) የክርስቶስ የሆኑ ሁሉ ይሰደዳሉ፤ ከዓለም አይደሉምና ዓለም ያሳድዳቸዋል፡፡ እመቤታችንም የክርስቶስ ናትና እውነትና የእውነት መገኛ ራሷም እውነት ናትና ስደትን ተሰደደች፤ በስደቷም ብዙ መከራ አገኛት፡፡
ውድ የዚህ ጽሑፍ አንባብያን! የልጇ ፈቃድ ቢሆን የእርሷም ምልጃዋ ቢረዳን እመቤታችን ከኢየሩሳሌም ተነሥታ እስከ ምድረ ግብፅ ስትጓዝ የደረሱባት ዋና ዋና ችግሮችና የተደረጉ ተአምራትን በክፍል ሦስት ይዘንላችሁ እንቀርባለን፤ ቸር እንሰንብት፡፡
ይቆየን!

👍12👎3
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የተለያዩ መጽሐፍት የአእምሮ ንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ አገኘች
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ለአገልግሎት እና ለትምህርት የሚሆኑ የተለያዩ መጽሐፍት በማዘጋጀት ለምእመናን ስታደርስ ቆይታለች።
ሆኖም የተለያዩ ግለሰቦች እነኚህን መጽሐፍት በስማቸው በማዘጋጀት የባለቤትነት መብት ይገባኛል ብለው ሲጠይቁ ይስተዋላል።
ይህንን ችግር ለመፍታት ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የሚመራ ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ሥራ የገባች ሲሆን ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት ውጤትም ተገኝቷል።
ብፁእ አቡነ አብርሃም የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በዛሬው ዕለት ለአጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት እንዳሳወቁት ቤተ ክርስቲያን በመጽሐፍቱ ላይ የጠየቀችው የባለቤትነት መብት መልስ አግኝቶ የአእምሮ ንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ተቀብላለች።
ብፁእነታቸው ጨምረው እንደገለጹት አሁን በመጻሕፍቱ ላይ የተገኘው ውጤት ወደ ሌሎች የቤተ ክርስቲያን ንዋየተ ቅድሳትም እንዲሸጋገር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል

👍59
"የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከጠፋንበት አገኘችን" ትውልደ አሜሪካዊው ካህን
የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የሦስተኛ ቀን ውሎ የአኅጉረ ስብከቶችን ሪፖርት በማዳመጥ ላይ ይገኛል።
በዛሬው የሪፖርት ቀን ከሀገር ውስጥ አኅጉረ ስብከቶች በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ አኅጉረ ስብከቶች ሪፖርታቸውን ማቅረብ ጀምረዋል።
በጉባኤው ላይ ከቀረቡት ሪፖርቶች መካከል አንዱ የሆነው የኒዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሪፖርት ሲሆን ያቀረቡት ትውልደ አሜሪካዊው መልአከ ገነት ተስፋ ኢየሱስ ናቸው።
መልአከ ገነት ተስፋ ኢየሱስ በ1975 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ አማካኝነት በሀገረ አሜሪካ ተጠምቀው የቤተ ክርስቲያን ልጅነትን ያገኙ ሲሆን በ1988 ዓ.ም ደግሞ ቅስናን ተቀብለዋል።
ባላቸው የአገልግሎት ትጋት እና የቤተ ክርስቲያን ፍቅር አማካኝነት በብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መልአከ ገነት ተብለው በሀገረ አሜሪካ የደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ተሹመዋል።
በአሁኑ ወቅት በደብሩ ውስጥ በቅስና የሚያገለግሉት እርሳቸው ብቻ ሲሆኑ ሁለት ዲያቆናት አብረዋቸው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
በዛሬው የአጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ በመገኘት የሀገረ ስብከቱን ሪፖርት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ያቀረቡ ሲሆን በጉባኤው ላይ በመገኘታቸው ትልቅ ደስታን እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።
"እኛ ምዕራባውያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፈልጋ እስክታገኘን ድረስ ጠፍተን ነበር አሁን ግን ከጠፋንበት አግኝታናለች" በማለት ለቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ፍቅር እና አክብሮት ገልጸዋል።
ጉባኤውም ትልቅ አድናቆት እና ክብር ሰጥቷቸዋል።

👍26
የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የሦስተኛ ቀን ውሎ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት ተከናውኗል
የዛሬው መርሐ ግብር ቀሪ የአኅጉረ ስብከቶች ሪፖርት ቀረበበት ነው። የሀገር ውስጥ አኅጉረ ስብከቶች ሪፖርቶቻቸውን አቅርበው ያጠናቀቁ ሲሆን ይህንን ተከትሎ ጉባኤው የውጭ ሀገራት አኅጉረ ስብከቶች የአፈጻጸም ሪፖርትን ማዳመጥ ጀምሯል።
በዛሬው የአጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ውሎ ላይ የውጭ ሀገራት ዜግነት ያላቸው ከኒውዮርክ እና ከካሪቢያን ደሴቶች አኅጉረ ስብከቶች የመጡ አገልጋዮች በእንግሊዘኛ ቋንቋ ሪፖርታቸውን በማቅረባቸው በጉባኤው ዘንድ አድናቆትን ፈጥሯል።
በሦስተኛው ቀን የአጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ሪፖርታቸው ያቀረቡት አኅጉረ ስብከቶች የሚከተሉት ናቸው።

👍9
ምዕራብ ጎንደር ሀ/ስብከት፣ ዳውሮ ሀ/ስብከት፣ ጌዲኦ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች ሀ/ስብከት፣ ምዕራብ አርሲ ሀ/ስብከት፣ ቡኖ በደሌ ህ/ስብከት፣ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት፣ ዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀ/ስብከት፣ ደቡብ ካሊፎርኒያ እና አካባቢው ሀ/ስብከት፣ የሰሜን ካሊፎርኒያና አካባቢው ሀ/ስብከት፣ ዋሺንግተን ሲያትል እና አካባቢው ሀ/ስብከት፣ ቴክሳስ እና አካባቢው ሀ/ስብከት፣ ጆርጂያ እና አካባቢው ሀ/ስብከት፣ ኒውዮርክ እና አካባቢው ሀ/ስብከት፣ ኮሎራዶ እና አካባቢው ሀ/ስብከት፣ ኦሃዮና አካባቢው ሀ/ስብከት፣ ምዕራብ ካናዳና አካባቢው ሀ/ስብከት፣ ካሪቢያን ደሴቶች እና አካባቢው ሀ/ስብከት፣ እንግሊዝ እና አካባቢው ሀ/ስብከት፣ ጀርመን እና አካባቢው ሀ/ስብከት፣ ጣሊያን እና አካባቢው ሀ/ስበከት፣ ስዊድን ስካንዲኒቪያንና ግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት እና የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ናቸው።
ጉባኤው በቅዱስ ፓትርያርኩ ጸሎት ፍጻሜውን ያገኘ ሲሆን ቀሪ አኅጉረ ስብከቶች ሪፖርታቸውን በነገው ዕለት እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።

👍12
3 ቀናት ብቻ ቀሩት!
ጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም!
በሚሊኒየም አዳራሽ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ!
የቻለ ሁሉ የማይቀርበት ልዩ ጉባኤ!
ኑ! አንድ ሁነን ቅዱስ ያሬድን ዘክረን ከበረከቱ እንካፈል!
በዕለቱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የገዳሙ ማኅበረ መነኮሳት፣ መምህራነ ወንጌል፣ መዘምራን እና ተጋባዥ እንግዶች ይገኛሉ።
መግቢያ ዋጋ 100 ብር!
ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም
አካውንት.ቁጥሮች ንግድ ባንክ 1000560510091 አቢሲኒያ ባንክ 145735858 ዓባይ ባንክ 1461019959527013 አሐዱ ባንክ
0003488720301
አዋሽ ባንክ 013040800017700 ዳሽን 0088872166011
ወገን ፈንድ
https://www.wegenfund.com/causes/semeka-hheyaawe/

👍16
የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አራተኛ ቀን ውሎ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት በጸሎት ተከፍቶ ተጀምሯል።
ዛሬ ቀሪ የውጭ አገራት አኅጉረ ስብከቶች የ2015 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።
እኛም ከቦታው በቀጥታ የጉባኤውን ክንውን የምናስተላልፍላችሁ ይሆናል።

👍22