ከሰ/ት/ቤቶች ጋርም የመግባባትና አብሮ የመሥራት ለውጥ እየመጣ ሲሆን በተለይ የተወሰኑት በተግባር በሚታይ መንገድ ከሕትመት ጀምሮ መሳሪያ አጠቃቀምን ጭምር ለውጥ የታየባቸው ቢሆንም በቂ ነው ማለት ግን አይቻልም ስለዚህ ከዚህ በላይ አስቦ፣ ተናቦ፣ ተቀናጅቶ እንደ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዘርፍ የሚያገለግል የትኛውም አወቃቀር ጋር በጋራ መወያየት ያስፈልጋል በማለት የማእከሉ ም/ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ምሕረቴ አመላክተዋል።
በመጨረሻም አቶ ፍቃዱ ከሰ/ት/ቤቶችና ከሚመለከተው አካላት ጋር በጋራ በመሥራት፣ በመተጋገዝ፣ በመረዳዳት ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያለውን አገልግሎት ሰፊ ተደራሽነት እንዲኖረው ለማድረግ ሁሉም አካል የበኩሉን መወጣት ቢችል ለውጥ ማምጣት ይቻላል በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።

❤19🙏4
በማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማእከል የምእራብ ማስተባበሪያ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።
"በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው" መዝ ፬፥፮ በሚል መሪ ቃል በሳንፍራንሲስኮ ከተማ የተጀመረው ጉባኤ ለ፫ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የባለፈው ዓመት ክንውን የሚመጣው ዓመት እቅድ ጨምሮ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች እንደሚመክር ከአዘጋጅ ኮሚቴው ለዝግጅት ክፍላችን ያደረሰው መረጃ ያሳያል። አሜሪካ ማእከል በተቋማዊ ለውጡ በሦስት ማስተባበሪያዎች የተደራጀ ሲሆን የምእራብ ማስተባባሪያም አንዱ ነው። በሥሩም
አምስት ንዑሳን ማእከላት እና ሁለት ግንኙነት ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆኑ የጠቅላላ ጉባኤው ተሳታፊዎች ናቸው እነርሱም ሳን ሆዜ ን/ማእከል ፥ ላስ ቬጋስ ን/ማእከል ፥ ሎስ አንጀለስ ን/ማእከል ፥ ሲያትል ን/ማእከል ፥ ዴንቨር ን/ማእከል ፥ ፖርትላንድና አሪዞና ግጣቢያዎች ናቸው።
የምእራብ ማስተባበሪያ ማእከል ጠቅላላ ጉባኤ ለ፪ተኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን በአካል ግን የመጀመሪያ ነው:: የሳንሆዜ ንዑስ ማእከል ተረኛው አዘጋጅ ነው ።
ጉባኤው በተሳታፊዎች የእድሜ ደረጃ መሠረት በ፬ ደረጃዎች የተከፈለ ሲሆን ከዋናው ጉባኤ በተጨማሪ ለሕጻናትና ወጣቶች እንደ እድሜያቸው ዝግጅቶች መሰናዳታቸውን ለማወቅ ችለናል።
ዘገባው የአሜሪካ ማዕከል ሚዲያ ክፍል ነው።

❤13