የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት በሚያካሂደው የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ሥርጭት ላይ ይሳተፉ፡፡ ግቢ ጉባኤያትን ይደግፉ፡፡
• የመማሪያ መጻሕፍት ዝግጅትንና ኅትመት ወጪን በመደገፍ የቅድስት ቤተ ክርስተያንና ሃይማኖቱን የተረዳ፣ በሙያው፣ በገንዘቡ፣ በጉልበቱ የሚረዳ ትውልድን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ አሻራዎን ያሳርፉ፡፡
የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች፣
በግቢ ጉባኤያት ተምራችሁ ያለፋችሁ፣
የግቢ ጉባኤት ምሩቃን ኅብረት፣
የተማሪዎች ቤተሰቦች፣
በጎ አድራጊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች፣ … በገቢ ማሰባሰቡ ላይ ይሳተፉ፡፡

👍11❤1
የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነፃ የትምሕርት ዕድል መርሐ ግብር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ተባለ።
( ግንቦት 18/2017)
የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነፃ የትምሕርት ዕድል መርሐ ግብር አፈጻጸምና ቀጣይነቱ ላይ ትኩረት ያደረገ የዳሰሳ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ውይይቱ በማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገትና መንፈሳዊ ትምሕርት ቤቶች አገልግሎት አዘጋጅነት በራስ አምባ ሆቴል ባሳለፍነው ቅዳሜ ግንቦት 16/2017 ዓ/ም የተከናወነ ሲሆን ‘’የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነፃ የትምሕርት ዕድል መርሐ ግብር አፈጻጸምና ቀጣይነቱ’’ በሚል ርእስ የዳሰሳ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል ።
በማኅበረ ቅዱሳን የተጀመረው ነፃ የትምሕርት ዕድሉ በሦስት ዘርፎች ላይ ያተኮረ ሲሆን ከዘመናዊ ት/ት ወደ አብነት ት/ት፣ ከአብነት ወደዘመናዊ እና የአገልጋይ እጥረት ካለባቸው ጠረፋማ አከባቢዎች ወደ ነገረ መለኮት ዪኒቨርሲቲና ኮሌጆች ገብተው እንዲማሩ የሚያስችል መርሐ ግብር ሲሆን መርሐግብሩ ባለፉት አሥር ዓመታት ተስፋ ሰጪ አፈጻጸም እንደታየበት በውይይቱ ተገልጿል። በዚህም 93 በመቶ መርሐ ግብሩ ውጤታማ እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡

👍2
በበጀት እጥረት፣ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተማሪዎችን አለማግኘት እና በመሳሰሉት ችግሮች ቀሪዎቹን ሰባት በመቶ ማሳካት አልተቻለም ተብሏል። ከ180 በላይ አገልጋዮችን የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነፃ የትምሕርት ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም በቀረበው የዳሰሳ ጽሑፍ ተጠቅሷል።
የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነፃ የትምሕርት ዕድል መሰጠት በመቻሉ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የግእዝ መምህራንን ማፍራት ተችሏል፣ ደቀ መዛሙርት ወደየ ሀገረ ስብከታቸው ተመልሰው ቤተ ክርስቲያንን በብቃት እንዲያገለግሉም አስችሏል ተብሏል።
መርሐ ግብሩን የሚያስፈጽም አደረጃጀት ጠንካራ አለመሆን፣ የበጀት እጥረት እና ግልጽ የሥምሪት አቅጣጫ አለመቀመጥ መርሐ ግብሩን በታሰበለት ልክ ማከናወን እንዳይቻል ያደረጉ ተግዳሮቶች መሆናቸው የገተገለጸ ሲሆን በቀጣይ የፋይናንስ አቅምን በማጠናከር፣ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ፣ ፖሊሲ እና መመሪያ በማዘጋጀት የመርሐ ግብሩን ዓላማ በማሳካት ቀጣይነቱ ላይ መሥራት እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።
የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ መ/ር ዋሲሁን በላይን ጨምሮ የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር እና ፣ የሥራ አስፈጻሚ ተወካዮች፣ ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ተጋባዥ እንግዶች፣ በማኅበረ ቅዱሳን የቤተክርስቲየን ሁለንተናዊ እድገት እና መንፈሳዊ ት/ቤቶች አገልግሎት አገልጋዮች ፣ የጉባኤ ቤት መምህራን እና በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ የነበሩና መምህራን በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል።

👍14🙏2❤1
ማኅበረ ቅዱሳን ወርኅ ግንቦትን “ግንቦት ልደታን ለግቢ ጉባኤያችን” በሚል መሪ ቃል 33ኛውን የግቢ ጉባኤያት ምስረታ አስመልክቶ በልዩ ልዩ መርሐ ግብራት እያከበረ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሔደው የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ስርጭት መርሐ ግብር ዋነኛው ነው፡፡ እርስዎም በዕለቱ በሚኖረው የቀጥታ ስርጭት በመሳተፍ የድርሻዎን ይወጡ፡፡
❤11👍2
ማኅበረ ቅዱሳን እየተገበረ በሚገኘው ስልታዊ ዕቅድ ላይ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ ለማሳካት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አስታወቀ።
ግንቦት ፲፱/፳፻፲፯ ዓ.ም
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዐሥር ዓመት እተገብራቸዋለው ብላ የያዘቻቸው መንፈሳዊና ኢኮኖሚያዊ ዕቅዶች ለመተግበር ማኅበረ ቅዱሳን በስልታዊ ዕቅዱ ላይ አካቶ በሁሉም ማእከላት እንዲተገበሩ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል።
የማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ሥራ አስኪያጅ ዲ/ን ሲሳይ ብርሃኑ እንደገለጹት የማኅበረ ቅዱሳን ስልታዊ ዕቅድ የቤተ ክርስቲያኒቱን መሪ ዕቅድ ተከትሎ ለመደገፍ በሚያስችል ሁኔታ የተዘጋጀ በመሆኑ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ከ2016 ዓ.ም ወዲህ በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን ማኅበሩ ለዚህ መሪ ዕቅድ ተግባራዊነትና ውጤታማነት ሊሠራባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች ተደርገዋል ብለዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን በሀገር ውስጥና በውጭ በሚገኙ ማእከላቱ እንዲሁም የግንኙነት ጣቢያዎች ያሉትን አባላትና ባለሙያዎች በማሳተፍ ለመሪ ዕቅዱ መሳካት ከሀገረ ስብከቶቻቸው መመሪያ በመቀበል ድጋፍ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ማስቀመጡም ተጠቅሷል።
ማኅበረ ቅዱሳን በስልታዊ ዕቅዱ ውስጥ ከቤተ ክርስቲያን መሪ ዕቅድ ጋር የሚጣጣሙ በርካታ አገልግሎቶችን አካቶ እንዲተገበሩ እያደረገ ሲሆን እነዚህ ዕቅዶች ለቤተ ክርስቲያን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖራቸውም ተጠቁሟል።
የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ላይ ያሉ አካላት መሪ ዕቅዱ ትልቅ ጥቅም እንዳለው በማመን ለውጤታማነቱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ እንደሚገባ ም/ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

👍9❤8🕊2
ግቢ ጉባኤያትን በተሻለ ጥራት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ለማስተማር፣ መምህራንን ለማፍራትና አስፈላጊውን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ መሠረተ ልማቶችን ለማሟላት በገቢ ማሰባበስብ መርሐ ግብሩ ላይ ይሳተፉ፤ የድርሻዎንም ይወጡ፡፡
❤1
የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
ግንቦት ፳/፳፻፲፯ ዓ.ም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ አካሂዷል፡፡
የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና እድገት፣ ለሀገር ሰላምና መረጋጋት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋትና ለመንፈሳዊ ልዕልና ልዩ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. ለሰላምና ለአንድነት ቅድሚያ መስጠት፣ምትክ ለሌለው የሰው ልጅ ሕይወት ባለአደራ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ሰላም ያለማቋረጥ መጸለይ፣ ጸሎተ ምሕላ ማወጅ፣ የሰላምና የአንድነት ጥሪ ማስተላለፉ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሰላምና ለአንድነት ልዩ ትኩረት ሰጥተው ሁሉን አቀፍ ሥራ የሚሠሩ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን “የሀገራዊ ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ኮሚቴ” በማድረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
ኮሚቴውም ዘላቂ ሰላምንና አንድነትን ለማስፈን፣ የዜጎችን ሕይወት እየነጠቀ ያለው ግጭት እንዲቆም ጥረት እንዲያደርግ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ባካተተ መልኩ በየደረጃው የምክክርና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና፣ ውይይቶችንና የጥናት መድረኮችን እንዲያዘጋጅ፤ አፈጻጸሙንም በየሦስት ወሩ ለቋሚ ሲኖዶስ ሪፖርት እንዲያደርግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡