የማኅበረ ቅዱሳን 33ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በመከበር ላይ ይገኛል።
ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ሥር የሚገኝ አገልግሎት ማኅበር ነው።
ማኅበሩ እግዚአብሔር ያከበራቸው የሐዋርያት የነቢያት የጻድቃን የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከርበት በመሆኑ ይህን ስያሜውን አግኝቷል።
የ33ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉ በማኅበሩ ዋና ማእከል 3ኛ ወለል ላይ በመከበር ላ የሚገኝ ሲሆን መጋቤ ሐዲስ ምሥጢረ ሥላሴ ማንአየ "አሸናፊ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶምና ገሞራ በሆንን ነበር!" በሚል ኃይለ ቃል ስለ እመቤታችን ቅድስት ማርያምን ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪምየማኅበሩ መዘመራን ወረብ እና የበገና ዝማሬ አቅርበዋል፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የማኅበሩ መሥራች፣የአሁን እና የቀድሞ አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

❤19👍4🕊1
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል እና የማኅበረ ቅዱሳን ፴፫ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በአሜሪካ ማእከል የፖርትላድ ግንኙነት ጣቢያ አባላት በድምቀት አክብረዋል።
❤9🕊3