Telegram Web Link
በማኅበረ ቅዱሳን ሎጊያ ማእከል ጠቅላላ ጉባኤውን አከናወነ፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን ሎጊያ ማእከል የ28ኛ ዓመት 25ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ከመስከረም 18 እስከ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ አከናውኗል።

 ጉባኤው ከአፋር ሀገረ ስብከት፤ ከአጥቢያ ቤተክርስቲያን ፤ ከሰንበት ት/ቤት፤  ከበጎ አድራጎት ማኅበራት የተወጣጡ ልዑካን በተገኙበት በጸሎተ ወንጌል ተከፍቷል፡፡ 

ማእከሉ 5 ወረዳ ማእከላት፤ 4 ግቢ ጉባኤያት፤ 3 ግንኙት ጣቢያዎች እና 1 የንዋየ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ እንዳሉት ሪፖርት በቀረበበት ወቅት ተመላክቷል፡፡

 በዓመቱ የማእከሉ ዕቅድ አፈጻጸም ላይ  ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት፤ ለማረሚያ ቤቶች፤ ለግቢ ጉባኤያት የወንጌል ትምህርት እንደተሰጠ፤ በግቢ ጉባኤያት ደረጃ-1 ተተኪ መምህራን ለ 45 ሠልጣኞች መስጠቱ፤ እንዲሁም በአዋሽ ወረዳ ማእከል አንድ ግቢ ጉባኤ ማቋቋም መቻሉ ተገልጧል፡፡  

በተጨማሪም ግቢ ጉባኤ ሊያስተምሩ የሚችሉ 14 መምህራንንም በ2016 ዓ.ም በተሠጠ ሥልጠና ማፍራት እንደተቻለም ተገልጿል፡፡

ማእከሉ የአገልጋይ  ፍልሰት እና እጥረት፣ ቋሚ ገቢ አለመኖር እና የአከባቢው የአየር ንብረት ሁኔታ ፈተና እንደሆኑበት በሪፖርቱ አስገንዝቧል።

በጉባኤው ላይ ከ58 በላይ ልዑካን ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
31👍14🕊3
አደራ አለብኝ!

ዓለም አቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ጉባኤ

የ2017 ዓ.ም 1 ኛ ዙር ቨርቹዋል ጉባኤ

ቀን፡ መስከረም 26/2017 ዓ.ም

ሰዓት፡ ምሽት 2፡00-3፡00

ሁሌም በየወሩ በግቢ ጉባኤያት ምሩቃን ዓለም አቀፍ ኅብረት የቴሌግራም ቻናል

https://www.tg-me.com/gibigubayat_mirukan_hibret
👍288🙏7🕊4
የጉባኤ ቦታ ለውጥ

በማኅበረ ቅዱሳን ትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ አዘጋጅነት በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ የሚከናወነው ወርኃዊ የስብከተ ወንጌል ጉባኤ ነገ መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም 5ኪሎ በሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 3ኛ ወለል ላይ ከ7:00 ሰዓት ጀምሮ የሚከናወን መሆኑን እንገልጻለን።
👍199
✝️ማኅበረ ቅዱሳን በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ለ303 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ግብዓቶችን ድጋፍ አደረገ፡፡ 
+++
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ፣ በሀገራችን እያጋጠሙ ያሉ መጠነ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውሶች በልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ የሚያስከትሉትን ችግር ለማቃለል ልዩ ልዩ የማኅበራዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና በመተግበር ማኅበራዊና ሰብአዊ ሚናውን እየተወጣ እንዳለ ይታወቃል።

ማስተባበሪያው ከሚያደርጋቸው ማኅበራዊ ድጋፎች መካከል በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን በተገቢ ሁኔታ ለመከታተል የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሕጻናትና ታዳጊዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ አንዱ ነው። በዚህ መሠረት በየዓመቱ እንደሚደረገው መስከረም 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከማኅበረ ቅዱሳን ጂንካ ማእከል ጋር በመተባበር፣ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በኦሞ ወንዝና በቱርካና ሐይቅ ውኃ ሙላት ምክንያት ከቦታቸው ተፈናቅለው በመርመርቴ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ተጠልለው ለሚማሩ እና በድርቁ ሰለባ ለሆኑ 303 ተማሪዎች ፣ 2,232 ደብተር እና 970 እስክርቢቶ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
👍132🕊2
በድጋፉ ርክክብ ወቅትም የማኅበረ ቅዱሳን የጂንካ ማዕከል ተወካዮች፣ የዳሰነች ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የት/ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን እና ተማሪዎች ተገኝተዋል። በሌሎች አካባቢዎችም ተመሳሳይ ድጋፎችን እየተሰራጩ ሲሆን፣ የነገ ሀገርና ቤተ ክርስቲያን ተስፋ ለማስቀጠል በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን፣ ማኅበራት፣ ልዩ ልዩ ተቋማትና በጎ አድራጊ ድርጅቶች የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ማስተባበሪያው ጥሪውን ያቀርባል።

ድጋፍ ለማድረግ፡-
#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400
6. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ
👍8🙏72
ሐመር መጽሔት በጥቅምት ወር እትሟ!

✍️".....በዚህ ዓመት  ምን ያህል ገንዘብ ፈሰስ አደረገ ከሚለው ይልቅ በዚህ ዓመት ስንት ነፍስ በንስሓ አተረፍን? ስንት የሥላሴ ልጆችን በጥምቀት አፈራን  ወይም ቅድስት  ቤተ ክርስቲያን ስንት ኢአማንያንን በጥምቀት ወለደች??  ...."✍️ #ሐመር #መጽሔት ዐቢይ ጉዳይ ጥቅምት  ፳፻፲፯ ዓ.ም  )
                      ༺ ༻ 
#የኅትመት ዘመን ፦#ጥቅምት ፳፻፲፯ ዓ.ም ቁ.፲ 
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል #በየወሩ የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
•  ገጽ ብዛት፦፳፰
   ዋጋ ፦፵ ብር 
•  ሐመር  መጽሔት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት  ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል  በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
👍125
2025/07/08 20:39:25
Back to Top
HTML Embed Code: