Telegram Web Link
✞ እንኳን አደረሰን !

" ... ዓቢየ እግዚእ ነዓ ምስለ ገብርኤል መልአከ ዳኅና፤
ታብዕለኒ በንዋዮሙ ውዱሰ ነገር ወዜና፤
ለኢየሉጣ ሰማዕት ወቂርቆስ ሕጻና!"
                           (መልክዐ አቡነ ዓቢየ እግዚእ)

" ... ገብርኤል ውኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ፤
አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ፤
ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ!"
                            (መልክዐ ቅዱስ ገብርኤል)

" ሰላም ለክሙ ጥቡዓነ ልብ ወሕሊና፤
ሰማዕታተ ክርስቶስ ዘሃገረ እስና፤
ምስለ አብ ወእም ወምስለ ሕጻና፤
ዘቀተሉክሙ ወዓልተ መኮንን አርያና፤
እንበለ ያትርፉ አሐደ ለዜና!"
                             (አርኬ)

❖እኅተ መላእክት ፥ እመ ሰማዕታት ፥ ተስፋ መነኮሳት ፥ አክሊል ንጹሕ ለካህናት የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም በረድኤት አትለየን!

ከበረከታቸውም ይክፈለን!

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት

ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል)
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)
የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ጸሎት

አምላኬ ሆይ ክፉ የማያስብ ምኞቶችም የማይጠጉት ንፁህ እና ቅን ልብን ፍጠርልኝ። ንፁህ ልብ መጥፎ ጨዋታን የማያውቅ ባልንጀራውን የማይነቅፍ ነው። ንፁህ ልብ ሁል ጊዜ በፍቅር የተሞላ እና ለእያንዳንዱ ሰው ደህንነትን እና ሰላምን የሚፈልግ ነው። ንፁህ ልብ መጾምን፣ መጸለይን፣ ማረፍን፣ አካልን ማዋረድን፣ ሁልጊዜ መሥራትና መድከምን ይወዳል።
የማኅበረ ቅዱሳን የሰቆጣ ማእከል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማኅበር ሰቆጣ ቅርንጫፍ አባላትን በአካል በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈ፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን የሰቆጣ ማእከል ሰብሳቢ አቶ ፈንታ ዓለምሰገድ ዛሬ ላይ ከዚህ የተገናኘነው የሀገር ባለውለታ የነበሩ የመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማኅበር ሰቆጣ ቅርንጫፍ አባላትን እንኳን ለ2017 ዓ.ም የዘመን መለወጫ አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ በማለት ከአባቶች ምርቃትና ቡራኬ ለማገኘት ነው ብለዋል።

አቶ ፈንታ አክለውም በአሁኑ ሰዓት የዕድሜ ባለፀጋ የሆኑ አረጋውያን አባቶችና እናቶች ማየት ብርቅ በሆነበት ዘመን እንደናንተ ያሉ የዕድሜ ባለፀጋዎችን ማየት ለእኛ ደስታም በረከትም በመሆኑ ግንኙነታችን በቀጣይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

ሀገራችን ከዚህ የደረሰችው በእናንተ ጸሎትና ቡራኬ ነው ያሉት ሰብሳቢው የምንሰማውና የምናየው የፀጥታ መደፍረስ ችግር ተወግዶ ሀገራችን ሰላም እንድትሆን ጸሎታችሁ ዛሬም እንደትናንቱ እንዳይለየን በማለት አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ተመኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ ተገኝተው ትምህርተ ወንጌል የሰጡት የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ኀላፊ መጋቤ ሐዲስ ተመስገን መዘመር አረጋውያን አባቶቻችንና እናቶቻችን የምትንከባከቡ ወንድሞቼና እህቶች ዋጋችሁ ምድራዊ ሳይሆን ሠማያዊ መሆኑን ተገንዝባችሁ ከዚህ በተሻለ ሁኔታ መንከባከብ ይኖርባችኋል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ይህ ሁሉ ሰው የሚጎበኛችሁና የሚንከባከባችሁ ሰላም በመኖሩ ነው  ያሉት መጋቤ ሐዲስ ተመስገን በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለሁ እንዳለው ነብዬ ልዑል ዳዊት እናንተም ሥለ ራሳችሁ፣ ሥለ ወገኖችሁና ሥለ ሀገራችን አብዝታችሁ መጸለይና መማለድ ይኖርባችኋል ብለዋል።

የተራብነው በሥጋችን ሳይሆን በነፍሳችን ነውና ማኅበረ ቅዱሳን ዛሬ ላይ የጀመረውን መንፈሳዊ ትምህርት አጠናክሮ መቀጠል አለበት ያሉት የመቄዶንያ አረጋውያን  አዲሱ ዓመት ለሀገራችን ሰላም፣ አንድነትና ፍቅር ይሁን ሲሉ  ቡራኬ ሰጥተው መርሐ ግብሩን በጸሎት ዘግተዋል
✝️ከአንድ ቤተሰብ፣
#ለአንድ ተማሪ✝️
+++
ማኅበረ ቅዱሳን በተለያዩ ማኅበራዊ ቀውሶች ምክንያት ለተጎዱ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ፣ በገንዘብና በዓይነት ድጋፍ እያሰባሰሰበ ይገኛል።
ድጋፍ ለማድረግ፡-
  በገንዘብ
በማኅበረ ቅዱሳን #የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1.  በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
2.  በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
3.  በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
4.  በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5.   በአዋሽ ባንክ 01329817420400 
  በዓይነት
ደብተር፣ እስክርቢቶ፣ እርሳስና ቦርሳ                                                                                                                              
ለበለጠ መረጃ
•  09 84 18 15 44
•  09 20 27 42 98
               ማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 1ኛ ወለል
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ
የማኅበረቅዱሳን ወልድያ ወረዳ ማእከል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ከተፈናቃይ ወገኖች ጋር የዘመን መለወጫ በዓል አከበረ፡፡

ማእከሉ በወልድያ ከተማ በሦስት ካምፕ ከሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ጋር መስከረም 4 ቀን 2017 ዓ.ም የዘመን መለወጫን አክብሯል፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን የወልድያ ማእከል ተወካይ አቶ ገደፋው ሙላው የመጣነው የከተማው በጎ አድራጊ ምእመናንና ተቋማትን መልእክት ይዘን ነው ካሉ በኋላ ትንሽም ቢሆን ያለንን ይዘን በዓልን ከእናንተ ጋር ለመዋል በመቻላችን ደስተኞች ነን፤ በቀጣይም መሰል ድጋፎችን የምናደርግ ይሆናል ብለዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ተገኝተው ትምህርተ ወንጌል የሰጡት የወልድያ ከተማ አስተዳደር ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት አክሊለ ብርሃን ተመስገን በበኩላቸው የተመረጠች የእግዚአብሔር ዓመት እንዲሆንልን ሁላችንም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ ምንም እንኳን አሁን በችግር ውስጥ ብትሆኑም መንፈሰ ጠንካሮች መሆን አለባችሁ ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ሥራ እስኪያጁ አክለውም ማኅበረ ቅዱሳን የከተማውን ምእመናን አስተባብሮ ይህንን የመሰለ መርሐ ግብር ማዘጋጀቱ የሚያስመሰግን መንፈሳዊ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ተፈናቃይ ወገኖች በበኩላቸው እስካሁን የከተማው ሕዝብ ስለሚደግፈን ብዙ አልከፋንም፤ በዓላት ሲመጡም እንደቀደመው ጊዜ መጨነቅ አቁመናል ያሉ ሲሆን ችግሩ በዘላቂነት እንዲፈታላቸው የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዘመን መለወጫ የበዓል መርሐ ግብሩ ላይ ከ371 በላይ ተፈናቃዮች መገኘታቸው ታውቋል።
በማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል 30ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሔደ ይገኛል፡፡

ማእከሉ ከ1,500 በላይ አባላት፣ 26 ግቢ ጉባኤያት፣ 3 የንዋየ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ እና አንድ የዜማ መሣሪያዎች ማሠልጠኛ ተቋም፣ 2 ዘመናዊ ትምህርት ቤቶች እንዳሉት በዕለቱ በቀረበው ሪፖርት ተጠቅሷል፡፡

በዓመቱም 553 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን የአብነት ትምህርት በማስተማር 9 ዲያቆናት ክህነት እንዲቀበሉ ያደረገ ሲሆን 334 በደረጃ 1 እና 64 በደረጃ 2 አዳዲስ አመራሮችን ማሠልጠኑም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም 5 ተማሪዎችን ማስጠመቅ መቻሉን፣ ለ18 ሰንበት ትምህርት ቤቶችና 86 መምህራነ ወንጌል እንዲሁም በ4 አጥቢያዎች ለሚገኙ ካህናትና ለቅድመ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ሥልጠናዎች መሰጠታቸው ተነግሯል፡፡

በክልሉ ባለው ጦርነት ምክንያት በምእመናን እና ካህናት ላይ የደረሰውን ጥቃት መረጃ መሰብሰብ መቻሉንና በጦርነት ውስጥ የሚገኙ የወረዳ ማእከላት ሥራ አስፈጻሚዎችን ባሕር ዳር እንዲመጡ በማድረግ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች እንዲሰጣቸው ተደርጓልም ተብሏል፡፡

በሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍም ማእከሉ በደብረ ሰላም ወረዳ ማእከል በችግር ዉስጥ የሚገኙ የሀቢታት ነዋሪዎች ከ900,000 ብር በላይ፤ በጣና ወረዳ ማእከል ዝግባ የአረጋዉያንና የሕጻናት ማእከልና በጊዮን ወረዳ ማእከል ለጎልማሶች ማገገሚያ የትንሳኤ በዓልን ለማክበር ከ200,000 ብር በላይ ወጭ በማድረግ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

የዋና ማእከል የብሮድካስት አገልግሎትን የሚያግዝ የሚድያ ክፍል ግብዓት አሟልቶ ወደ ሥራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
በጉባኤው የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ መልአከ ብርሃን ቀሲስ ፍሥሐን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የልዩ ልዩ የክፍል ኀላፊዎች፣ የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ ጽ/ቤት ኀላፊ አቶ ንጉሤ መብራቱ ፤የማኅበረ ቅዱሳን ሰሜን ምእራብ ማእከላት ማስተባበሪያ ም/ሰብሳቢ ዶ/ር በሪሁን ተፈራና የጉባኤው ልዑክ ፤ የወረዳ ቤተ ክህነት ተወካዮች፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፤ የወረዳ ማእከላት ፣ የግቢ ጉባኤያት ተወካዮችና የማእከሉ አባላት ተገኝተዋል፡፡

ከ500 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤው ለ2 ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
የማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ማርቆስ ማእከል 29ኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤዉን ማካሄድ ጀመረ።

በጉባኤው የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ መ/ር አባ ኤልያስ ታደሰ፣ የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ኀላፊዎች ፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ መነኮሳትና መምህራን፣ የሰንበት ት/ቤትና የኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች ኅብረት አመራሮች፣አጋር አካላትና የክብር እንግዶች እንዲሁም የማኅበሩ አባላት በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን የደብረ ማርቆስ ማእከል ሰብሳቢ አቶ ድረስ እንዳላማው በእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸው ይህ ጉባኤ 5ኛው ዙር ሥልታዊ ዕቅድ 2016 ዓ.ም ሪፖርት የሚቀርብበትና የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ከመዋቅራዊ ለውጡ አንጻር የምንተገብርበት ነው ብለዋል፡፡
2024/11/16 13:03:23
Back to Top
HTML Embed Code: