Telegram Web Link
ቅዱስ አባ አበስኪሮን

ዳግመኛም በዚህች ቀን ቀሊን ከምትባል አገር ቅዱስና ቡሩክ ድል አድራጊም የሆነው አባ አበስኪሮን በሰማዕትነት ሞተ።

➯ይህም ቅዱስ ከእንዴናው ገዥ ከአርያኖስ ጭፍራ ውስጥ ነበር የከሀዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ስለ አምልኮ ጣዖት የሆነች ትእዛዙ በደረሰች ጊዜ። ወዲያውኑ ይህ ቅዱስ በሕዝብ መካከል ተነሥቶ ንጉሡን ረገመው ጣዖታቱንም ሰደበ ወታደር ስለ ሆነም ያሠቃየው ዘንድ ማንም አልደፈረም ነገር ግን በንጉሥ አዳራሽ ውስጥ አሠሩት።

➯መኰንኑም ወደ ሀገረ አስዩጥ በሔደ ጊዜ ወደ ንጉሥ ላከው ከእርሱም ጋራ ሌሎች ወልፍዮስ፣ አርማንዮስ፣ አርኪያስ፣ ጴጥሮስ፣ ቀራንዮስ የተባሉ ነበሩ እሊህም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደማቸውን ሊአፈሱ ከአባ አበስኪሮን ጋራ ተስማሙ።

➯በንጉሡም ፊት በቆሙ ጊዜ በጌታችን ታመኑ ንጉሡም ትጥቃቸውን ይቆርጡ ዘንድ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዘም አደረጉባቸው። ከእኒህ ከአምስቱ ግን ራሶቻቸውን የቆረጡአቸው አሉ የሰቀሉአቸውም አሉ እንዲህም ገድላቸውን ፈጽመው የሕይወት አክሊልን ተቀበሉ።

➯የከበረ አበስኪሮስን ግን ታላቅ ግርፋትን እንዲገርፉት አዘዘ ከዚያም በኋላ ከራሱ እስከ አንገቱ ቆዳውን እንዲገፉ በፈረስ ጅራትም አሥረው በከተማው ውስጥ እንዲጐትቱት አዘዘ ይህንም ሁሉ አደረጉበት።

➯ከዚህም በኋላ በብረት ምጣድ ውስጥ አድርገው በላዩ አፉን ዘግተው ተሸክመው ወስደው በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ጨመሩት በሥቃዩም ውስጥ ሁሉ የእግዚአብሔር መልአክ ወደርሱ ይመጣና ያጽናናው ነበር ያስታግሠውም ነበር ያለ ምንም ጉዳት አድኖ በደኅና ያስነሣው ነበር።

➯ከማሠቃየቱም በደከመ ጊዜ ከሥራየኞች ሁሉ የሚበልጥ በሥራዩም ወደ አየር ወጥቶ ከአጋንንት ጋራ የሚነጋገር ሥራየኛ አመጣለት። እርሱም የውሽባ ቤቱን ዘግተው ሽንት እንዲረጩበት አዘዘ እንዲሁም አደረጉ። እባብንም ይዞ በላዩ አሾከሾከና ለሁለት ክፍልም ሁኖ ተሠነጠቀ መርዙንና ሆድ ዕቃውን ወስዶ በብረት ወጭት አድርጎ አበሰላቸው በውሽባ ቤቱ ውስጥ ወደ አባ አበስኪሮን አቅርቦ ያንን መርዝ ይበላ ዘንድ ሰጠው ቅዱሱም በላ ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም።

➯ያም መሠርይ የመኳንንተ ጽልመት አለቃቸው ሆይ በዚህ ክርስቲያናዊ ላይ ኃይልህን አድርግ ብሎ ጮኸ ምንም ምን ጥፋት ባልደረሰበት ጊዜ መሠርዩ አደነቀ።

➯ቅዱስ አበስኪሮንም መሠርዩን የሚራዳህ ሰይጣንህስ በክብር ባለቤት በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃያል አንተን ይቀጣሃል አለው። ወዲያውኑ ጥሎ የሚያንከባልለው ክፉ ሰይጣን ተጫነበት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ታመነ ድረስ አሠቃየው። መኰንኑም የመሠርዩን ራስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና በሰማዕትነት ሞተ።

➯በቅዱስ አበስኪሮን ላይ ግን ቁጣና ብስጭትን በመጨመር ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው አባለ ዘሩንም እንዲቆርጡ አዘዘ እርሱ ግን በመከራው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር። ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡት የድል አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

➯ከቅዱስ አበስኪሮን ተአምራትም አንዱን አንነግራችኋለን በግብጽ ደቡብ በስሙ የታነፀች ቤተ ክርስቲያን ነበረች ካህናቷም ከፉ ሥራ የሚሠሩ ክፉዎች ነበሩ ቅዱስ አበስኪሮንም ከክፋታቸው ተመልሰው ንስሓ ቢገቡ ብሎ ጠበቃቸው። ባልተመለሱ ጊዜ ግን የንዳድ በሽታ አምጥቶ ሁሉም በአንዲት ጊዜ ሞቱ።

➯ከዚህም በኋላ ቅዱስ አበስኪሮን ተቀምጦ የላዕላይ ግብጽ የሆነች ብያሁ ወደምትባል አገር ደረሰ የአገር ሰዎችም በደጃቸው ተቀምጠው ሳይተኙ በጨረቃ ብርሃን እርስ በርሳቸው ያወሩ ነበር። የከበረ አበስኪሮንም ከፊታቸው ደርሶ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው በአዩትም ጊዜ የሰላምታውን አጸፋ እየመለሱ ተነሥተው ተቀበሉት ሁለተኛም ያቺን የሚሻትን ምድር እያመለከታቸው ከምድራችሁ ጥቂት እንድትሰጡኝ እሻለሁ አላቸው እነርሱም ጌታችን እንደወደድክ ይሁንልህ አሉት መቶ የወርቅ ዲናርም ሰጥቷቸው ተሠወራችው።

➯እነርሱም ከዚህ ራእይ የተነሣ አደነቁ። ከተኙ በኋላም ቤተ ክርስቲያኒቱን አፍልሶ ከግብጽ ደቡብ ወደ ላዕላይ ግብጽ ብያሁ ወደምትባል አገር በመቶ የወርቅ ዲናር ወደ ገዛት ምድር ከንዋየ ቅድሳቷ ሁሉና ከዐፀዷ ጋር አምጥቶ በዚያ አቆማት።

➯የሀገር ሰዎች በጠዋት ነቅተው ወደ ውጪ በወጡ ጊዜ ቤተክርስቲያኒቱን በደጃቸው አገኙዋት እጅግ ፈጽሞም አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ከዚያች ጊዜ ጀምሮ ድንቅ ተአምር የሚደረግባት ሆነ።


➯ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

#ስንክሳር ሰኔ 7
ቄርሎስ ዐቢይ ዘሰመይዎ ዓምደ ሃይማኖት፤
ታኦዶኮስ ይቤላ ለማርያም ቅድስት፤
ወክልስቲያኖስ ክቡር ዘሮሜ ሊቀ ጳጳሳት፤
ሉቅያስ ወምኒልክ ቀዳማይ እምነገሥት!

እንኳን አደረሰን !
✞ እንኳን አደረሰን !

" ... ዓቢየ እግዚእ ነዓ ምስለ ገብርኤል መልአከ ዳኅና፤
ታብዕለኒ በንዋዮሙ ውዱሰ ነገር ወዜና፤
ለኢየሉጣ ሰማዕት ወቂርቆስ ሕጻና!"
                           (መልክዐ አቡነ ዓቢየ እግዚእ)

" ... ገብርኤል ውኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ፤
አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ፤
ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ!"
                            (መልክዐ ቅዱስ ገብርኤል)

" ሰላም ለክሙ ጥቡዓነ ልብ ወሕሊና፤
ሰማዕታተ ክርስቶስ ዘሃገረ እስና፤
ምስለ አብ ወእም ወምስለ ሕጻና፤
ዘቀተሉክሙ ወዓልተ መኮንን አርያና፤
እንበለ ያትርፉ አሐደ ለዜና!"
                             (አርኬ)

❖እኅተ መላእክት ፥ እመ ሰማዕታት ፥ ተስፋ መነኮሳት ፥ አክሊል ንጹሕ ለካህናት የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም በረድኤት አትለየን!

ከበረከታቸውም ይክፈለን!

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት

ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል)
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)
የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ጸሎት

አምላኬ ሆይ ክፉ የማያስብ ምኞቶችም የማይጠጉት ንፁህ እና ቅን ልብን ፍጠርልኝ። ንፁህ ልብ መጥፎ ጨዋታን የማያውቅ ባልንጀራውን የማይነቅፍ ነው። ንፁህ ልብ ሁል ጊዜ በፍቅር የተሞላ እና ለእያንዳንዱ ሰው ደህንነትን እና ሰላምን የሚፈልግ ነው። ንፁህ ልብ መጾምን፣ መጸለይን፣ ማረፍን፣ አካልን ማዋረድን፣ ሁልጊዜ መሥራትና መድከምን ይወዳል።
የማኅበረ ቅዱሳን የሰቆጣ ማእከል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማኅበር ሰቆጣ ቅርንጫፍ አባላትን በአካል በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈ፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን የሰቆጣ ማእከል ሰብሳቢ አቶ ፈንታ ዓለምሰገድ ዛሬ ላይ ከዚህ የተገናኘነው የሀገር ባለውለታ የነበሩ የመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማኅበር ሰቆጣ ቅርንጫፍ አባላትን እንኳን ለ2017 ዓ.ም የዘመን መለወጫ አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ በማለት ከአባቶች ምርቃትና ቡራኬ ለማገኘት ነው ብለዋል።

አቶ ፈንታ አክለውም በአሁኑ ሰዓት የዕድሜ ባለፀጋ የሆኑ አረጋውያን አባቶችና እናቶች ማየት ብርቅ በሆነበት ዘመን እንደናንተ ያሉ የዕድሜ ባለፀጋዎችን ማየት ለእኛ ደስታም በረከትም በመሆኑ ግንኙነታችን በቀጣይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

ሀገራችን ከዚህ የደረሰችው በእናንተ ጸሎትና ቡራኬ ነው ያሉት ሰብሳቢው የምንሰማውና የምናየው የፀጥታ መደፍረስ ችግር ተወግዶ ሀገራችን ሰላም እንድትሆን ጸሎታችሁ ዛሬም እንደትናንቱ እንዳይለየን በማለት አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ተመኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ ተገኝተው ትምህርተ ወንጌል የሰጡት የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ኀላፊ መጋቤ ሐዲስ ተመስገን መዘመር አረጋውያን አባቶቻችንና እናቶቻችን የምትንከባከቡ ወንድሞቼና እህቶች ዋጋችሁ ምድራዊ ሳይሆን ሠማያዊ መሆኑን ተገንዝባችሁ ከዚህ በተሻለ ሁኔታ መንከባከብ ይኖርባችኋል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ይህ ሁሉ ሰው የሚጎበኛችሁና የሚንከባከባችሁ ሰላም በመኖሩ ነው  ያሉት መጋቤ ሐዲስ ተመስገን በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለሁ እንዳለው ነብዬ ልዑል ዳዊት እናንተም ሥለ ራሳችሁ፣ ሥለ ወገኖችሁና ሥለ ሀገራችን አብዝታችሁ መጸለይና መማለድ ይኖርባችኋል ብለዋል።

የተራብነው በሥጋችን ሳይሆን በነፍሳችን ነውና ማኅበረ ቅዱሳን ዛሬ ላይ የጀመረውን መንፈሳዊ ትምህርት አጠናክሮ መቀጠል አለበት ያሉት የመቄዶንያ አረጋውያን  አዲሱ ዓመት ለሀገራችን ሰላም፣ አንድነትና ፍቅር ይሁን ሲሉ  ቡራኬ ሰጥተው መርሐ ግብሩን በጸሎት ዘግተዋል
✝️ከአንድ ቤተሰብ፣
#ለአንድ ተማሪ✝️
+++
ማኅበረ ቅዱሳን በተለያዩ ማኅበራዊ ቀውሶች ምክንያት ለተጎዱ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ፣ በገንዘብና በዓይነት ድጋፍ እያሰባሰሰበ ይገኛል።
ድጋፍ ለማድረግ፡-
  በገንዘብ
በማኅበረ ቅዱሳን #የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1.  በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
2.  በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
3.  በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
4.  በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5.   በአዋሽ ባንክ 01329817420400 
  በዓይነት
ደብተር፣ እስክርቢቶ፣ እርሳስና ቦርሳ                                                                                                                              
ለበለጠ መረጃ
•  09 84 18 15 44
•  09 20 27 42 98
               ማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 1ኛ ወለል
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ
የማኅበረቅዱሳን ወልድያ ወረዳ ማእከል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ከተፈናቃይ ወገኖች ጋር የዘመን መለወጫ በዓል አከበረ፡፡

ማእከሉ በወልድያ ከተማ በሦስት ካምፕ ከሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ጋር መስከረም 4 ቀን 2017 ዓ.ም የዘመን መለወጫን አክብሯል፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን የወልድያ ማእከል ተወካይ አቶ ገደፋው ሙላው የመጣነው የከተማው በጎ አድራጊ ምእመናንና ተቋማትን መልእክት ይዘን ነው ካሉ በኋላ ትንሽም ቢሆን ያለንን ይዘን በዓልን ከእናንተ ጋር ለመዋል በመቻላችን ደስተኞች ነን፤ በቀጣይም መሰል ድጋፎችን የምናደርግ ይሆናል ብለዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ተገኝተው ትምህርተ ወንጌል የሰጡት የወልድያ ከተማ አስተዳደር ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት አክሊለ ብርሃን ተመስገን በበኩላቸው የተመረጠች የእግዚአብሔር ዓመት እንዲሆንልን ሁላችንም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ ምንም እንኳን አሁን በችግር ውስጥ ብትሆኑም መንፈሰ ጠንካሮች መሆን አለባችሁ ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ሥራ እስኪያጁ አክለውም ማኅበረ ቅዱሳን የከተማውን ምእመናን አስተባብሮ ይህንን የመሰለ መርሐ ግብር ማዘጋጀቱ የሚያስመሰግን መንፈሳዊ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ተፈናቃይ ወገኖች በበኩላቸው እስካሁን የከተማው ሕዝብ ስለሚደግፈን ብዙ አልከፋንም፤ በዓላት ሲመጡም እንደቀደመው ጊዜ መጨነቅ አቁመናል ያሉ ሲሆን ችግሩ በዘላቂነት እንዲፈታላቸው የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዘመን መለወጫ የበዓል መርሐ ግብሩ ላይ ከ371 በላይ ተፈናቃዮች መገኘታቸው ታውቋል።
በማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል 30ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሔደ ይገኛል፡፡

ማእከሉ ከ1,500 በላይ አባላት፣ 26 ግቢ ጉባኤያት፣ 3 የንዋየ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ እና አንድ የዜማ መሣሪያዎች ማሠልጠኛ ተቋም፣ 2 ዘመናዊ ትምህርት ቤቶች እንዳሉት በዕለቱ በቀረበው ሪፖርት ተጠቅሷል፡፡

በዓመቱም 553 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን የአብነት ትምህርት በማስተማር 9 ዲያቆናት ክህነት እንዲቀበሉ ያደረገ ሲሆን 334 በደረጃ 1 እና 64 በደረጃ 2 አዳዲስ አመራሮችን ማሠልጠኑም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም 5 ተማሪዎችን ማስጠመቅ መቻሉን፣ ለ18 ሰንበት ትምህርት ቤቶችና 86 መምህራነ ወንጌል እንዲሁም በ4 አጥቢያዎች ለሚገኙ ካህናትና ለቅድመ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ሥልጠናዎች መሰጠታቸው ተነግሯል፡፡

በክልሉ ባለው ጦርነት ምክንያት በምእመናን እና ካህናት ላይ የደረሰውን ጥቃት መረጃ መሰብሰብ መቻሉንና በጦርነት ውስጥ የሚገኙ የወረዳ ማእከላት ሥራ አስፈጻሚዎችን ባሕር ዳር እንዲመጡ በማድረግ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች እንዲሰጣቸው ተደርጓልም ተብሏል፡፡

በሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍም ማእከሉ በደብረ ሰላም ወረዳ ማእከል በችግር ዉስጥ የሚገኙ የሀቢታት ነዋሪዎች ከ900,000 ብር በላይ፤ በጣና ወረዳ ማእከል ዝግባ የአረጋዉያንና የሕጻናት ማእከልና በጊዮን ወረዳ ማእከል ለጎልማሶች ማገገሚያ የትንሳኤ በዓልን ለማክበር ከ200,000 ብር በላይ ወጭ በማድረግ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

የዋና ማእከል የብሮድካስት አገልግሎትን የሚያግዝ የሚድያ ክፍል ግብዓት አሟልቶ ወደ ሥራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
በጉባኤው የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ መልአከ ብርሃን ቀሲስ ፍሥሐን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የልዩ ልዩ የክፍል ኀላፊዎች፣ የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ ጽ/ቤት ኀላፊ አቶ ንጉሤ መብራቱ ፤የማኅበረ ቅዱሳን ሰሜን ምእራብ ማእከላት ማስተባበሪያ ም/ሰብሳቢ ዶ/ር በሪሁን ተፈራና የጉባኤው ልዑክ ፤ የወረዳ ቤተ ክህነት ተወካዮች፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፤ የወረዳ ማእከላት ፣ የግቢ ጉባኤያት ተወካዮችና የማእከሉ አባላት ተገኝተዋል፡፡

ከ500 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤው ለ2 ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
የማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ማርቆስ ማእከል 29ኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤዉን ማካሄድ ጀመረ።

በጉባኤው የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ መ/ር አባ ኤልያስ ታደሰ፣ የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ኀላፊዎች ፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ መነኮሳትና መምህራን፣ የሰንበት ት/ቤትና የኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች ኅብረት አመራሮች፣አጋር አካላትና የክብር እንግዶች እንዲሁም የማኅበሩ አባላት በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን የደብረ ማርቆስ ማእከል ሰብሳቢ አቶ ድረስ እንዳላማው በእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸው ይህ ጉባኤ 5ኛው ዙር ሥልታዊ ዕቅድ 2016 ዓ.ም ሪፖርት የሚቀርብበትና የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ከመዋቅራዊ ለውጡ አንጻር የምንተገብርበት ነው ብለዋል፡፡
2024/09/28 06:14:38
Back to Top
HTML Embed Code: