Telegram Web Link
ዝክረ ቅድስት እናት ኢሪን እና መንፈሳዊ የትርጉም ፊልም የምርቃት መርሐ ግብር ተከናወነ።

በማኅበረ ቅዱሳን መዝሙር እና ኪነ ጥበባት አገልግሎት ማስተባበሪያ አዘጋጅነት የዘመናችን የ21ኛው ክፍለ ዘመን ቅድስት እናት ኢሪንን የሚዘክር መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተካናውኗል። በመርሐ ግብሩ ላይ የቅድስቷን  የተጋድሎ ሕይወት እና ኦርቶዶክሳውያን ከሕይወቷ መማር የሚገባንን ትምህርት በተመለከተ መነሻ ጽሑፍ ቀርቧል።

በዕለቱ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የማኅበሩ አባላት እና ምእመናም የተገኙ ሲሆን በእናት ኢሪን ዙሪያ የተዘጋጀው መንፈሳዊ ትርጉም ፊልም የምርቃት ሥነ ሥርዓትም  ተከናውኗል።

መንፈሳዊ ፊልሙ  በዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን የዩቲዩብ ቻናል ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

https://youtube.com/@-zemawetibebzmk7905?si=2jTnKZXGAfEJWRi7
 
‹‹እባክህ አሁን አድነን!››
 
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹…ከእኔ ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና…››  በማለት  ትሕትናን በአንደበቱ ትምህርት ከማስተማሩ በተጓዳኝ በተግባር ሕይወቱም ተግብሮ ካሳየባቸው ዕለታት አንዱ በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ቤተ መቅደስ የገባበት ዕለት ነው፤ (ማቴ.፲፩፥፳፱) ይህ ግሩም አምላክ በትሕትና ከተገለጠባቸው ዕለታት አንዱ የሆነው ድንቅ ቀን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ‹‹ሆሣዕና›› በመባል ይታወቃል፡፡ ሆሣዕና መተርጉማነ አበው በአንድምታቸው ‹‹ ሆሣዕና በአርያም በሰማይ ያለ መድኃኒት››  ብለው ተርጉመውልናል(ማቴ.፳፩፥፱ ወንጌል አንድምታ)  አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ደግሞ በመዝገበ ቃላታቸው ሆሣዕና ማለት ‹‹…እባክህ አሁን አድነን፤…መድኃኒት፣ መድኃኒት መሆን …›› በማለት ገልጸውታል፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ ፫፻፸፫)
 
‹‹እባክህ አሁን አድነን››፡- ይህን የተማጽኖ ቃል የተናገሩት ጌታችን በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ በኢየሩሳሌም የነበሩ ሕዝብ ናቸው፡፡ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው፣ አንድም የወይራ ቅጠል እንዲሁም ልብሳቸውን ከምድር አንጥፈው ከልብ በመነጨ፣ ምስጋናቸው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያሉ ሆሣዕና በአርያም ‹‹…እባክህ አድነን…›› በማለት አመሰገኑት፡፡ የነቢየ እግዚአብሔር ንጉሥ ዳዊት ትንቢት ተፈጽሞ በእናታቸው ጀርባ ያሉ የሚጠቡ ሕፃናት አመሰገኑ፤ ‹‹…ከሕፃናት ከሚጠቡ ልጆች አፍም ምስጋናን አዘጋጀህ…›› እንዲል፡፡ (መዝ.፰፥፪) 
https://youtu.be/Q0WJSswrkTo?si=ajqfBbrGS6e31m5Y

ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም
ወደ አንቺ መጥቷልና አምላክ ዘለዓለም/፪/

ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ
ሕፃናት በኢየሩሳሌም

አንቺ ቤተልሔም የዳዊት ከተማ
የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/፪/
     አዝ
ሆሣዕና እያሉ አመሰገኑት
በኢየሩሳሌም አእሩግ ወሕፃናት/፪/
  አዝ
ኪሩቤል መንበሩን  የሚሸከሙት
መስቀል ተሸክሞ ሆነን መድኃኒት/፪/
  አዝ
የኢየሱስን ሕማም ደናግል አይተው
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/፪/
ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ለ582 ደቀመዛሙርት መዓርገ ክህነት ሰጡ።

ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ የምዕራብ አርሲ ፣ጉጂ፣ምዕራብ ጉጂ  ፣ቦረና  ሊበን  አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ለ582 ደቀመዛሙርት መዓርገ ክህነት በዛሬው ዕለት በሻሸመኔ ደብረ አስቦ አ/ተ/ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰጥተዋል።

ለዲቁና ለቅስና እና ለቁምስና ፈተና ሲፈተኑ የቆዩ አግልጋዮች 546 ዲቁና፤34 የቅስና እና 3 የቁምስና መዓርግ የተሰጣቸው ሲሆን  ከእነዚህ ውስጥ 171 ዲቁና እና 5 የቅስና መዓርግ በአጠቃላይ 176 የተሰጣቸው በማኅበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማእከል እና ሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት  ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ ጋር  በመተባበር ሲያስተምራችው የነበሩ ደቀመዛሙርት ናቸው።

ማኅበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማእከል ከሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት  ጋር በመተባበር በዚህ ዓመት ከዚህ ቀደም መዓርገ ክህነትን የተቀበሉ 61 ካህናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 237 መዓርገ ክህነት እዲቀበሉ አድርጓል።

በዛሬው ዕለት ክህነት የተቀበሉት አገልጋዮች በአካባቢው ያለውን የካህናት እጥረት ለመፍታት ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።
በማኅበረ ቅዱሳን የጀርመን ንዑስ ማእከል ለገዳማትና ጉባኤ ቤቶች ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አካሄደ።

ንዑስ ማዕከሉ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ጉባኤውን  በሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ያሬድ ምስጋናው፣ መምህራነ ወንጌል፣ ካህናት እና ምዕመናን በተገኙበት አከናውኗል። 

በዚህ መርሐ ግብር በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አህጉረ ስብከት ለሚገኙ ለአብነት ትምህርት ቤት መምህራን እና ተማሪዎች ድጋፍ የሚውል  የገቢ ማሰባሰብ ሥራ ተከናውኗል።

ማኅበረ ቅዱሳን በገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች የተገበራቸውን ፕሮጀክቶችና ልዩ ልዩ ድጋፎችን ገለጻ የተደረገ ሲሆን በዚህም ምእመናን እየተተገበሩ ስላሉ ሥራዎች ግንዛቤ አግኝተዋል። የሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ያሬድ ምእመናን የቤተ ክርስቲያን አእማድ የሆኑ ገዳማትና ጉባኤ ቤቶችን እንዲደግፋ ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት መሠረት ድጋፍ መሰብሰብ ተችሏል።

በተመሳሳይ ሚያዚያ 12ና 13 /2016 ዓ.ም በሩስልስሃይም ደ/ምጥማቅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ አብርሃም፣ የደብሩ ካህናትና ምእመናን በተገኙበት ዐውደ ርዕይ እና ለገዳማትና አብነት ት/ቤቶች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር የተከናወነ ሲሆን በወቅታዊ ጉዳይ ጉዳት ለደረሰባቸው ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ገንዘብ መሰብሰብ ተችሏል፡፡
የተሰበሰቡ ድጋፎች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች በማኅበሩ በኩል እንደሚውል ንዑስ ማእከሉ አስታውቋል።
2024/09/28 18:17:05
Back to Top
HTML Embed Code: